#Ethiopia
ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እስከ 2 በመቶ ሊቆረጥ ነው።
የክልል መንግስታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከዜሮ ነጥብ 5 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበት አሠራር መዘርጋታቸውን ተሰምቷል።
ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ግን ቀሪ መደረጉ ይታወሳል።
ክልሎች ለመሰብሰብ የወሰኑት መዋጮ ተመሳሳይ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ መጠን ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።
በተያያዘ ዘገባ፦ ዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በማሳደግ ላይ ያሉ አገራት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ ጫና ሳያደርጉ ገቢያቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን የፖሊሲ ጥናት ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።
ባንኩ የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንጻር ያለው ድርሻ በታሪክ እጅግ ዝቅተኛው 7.5 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ አፈጻጸም፣ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 13 በመቶ አማካይ አጠቃላይ ገቢና በተለይም እንደ፦
-ኬንያ፣
-ሩዋንዳ እና
-ኡጋንዳ ካሉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ባንኩ ጠቅሷል።
ለሀገሪቱ የታክስ ገቢ ማነስ፣ ሕገወጥ ንግድ፣ የታክስ ነጻ መብቶች መብዛትና በግብር አሰባሰብ መዋቅር ላይ ያሉ ድክመቶች ዋና ምክንያት ናቸው ተብሏል። ባንኩ፣ በሀገራት የመዋቅራዊ አቅም ምድብ፣ ኢትዮጵያን 'በቅድሚያ መሰረታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ሒደት' ምድብ ውስጥ እንደምትገኝ ገልጿል።
@Addis_Reporter

😢31❤16😡15👍2
የአሜሪካ መንግስት የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆ ባይደን የተፈረመውን EXECUTIVE ORDER 14646 ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረው የጦር መሳሪያ ሽያጭ እቀባ ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ አንስቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤17👍11👌1🕊1
በአፋር ድንበር አካባቢ አዲስ ውጊያ‼️
የህወሓት ሀይል በአፋር አዋሳኝ በኩራን፣ ጎጎ እና አራዱ የድንበር አካባቢዎች ከአፋር ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል ጋር ውጊያ ጀምሯል።
ታጣቂዎቹ ትላንት ምሽት በሁለት ዶዘር መንገድ የማጽዳት ሥራ ሲያከናውኑ ነበር።

❤19🤯6👍2😈1👀1
አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ አነሳች
ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ መከላከያ ኃይልና በሌሎች የኤርትራ ተቋማት፣ አካላትና ባለሥልጣናት ላይ ጥላዉ የነበረዉን ማዕቀብ ዛሬ ማንሳቷን አስታወቀች።
በኤርትራ መከላከያ ሚንስቴርና በሌሎች የኤርትራ ተቋማት፣ አካላትና ባለሥልጣናት ላይ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2021 ማዕቀቡን የጣለዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የጆ ባይደን አስተዳደር ነበር።
የባይደን አስተዳደር በኤርትራ ገዢ ፓርቲ፣ በጦር ኃይሉና በሌሎች ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የጣለዉ ኤርትራ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን ሆና መዋጋቷን በመቃወም ነበር።
የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ዛሬ በአምደ መረቡ ባሰራጨዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ግን የባይደን አስተዳደር ጥሎት የነበረዉ ማዕቀብ ተነስቷል።
ሮይተርስ ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ማዕቀቡን ማንሳቱ የዋሽግተንና የአሥመራን ግንኙነት ለማሻሻል ይረዳል።

👍12❤5🤣5🤔2
በሳውዲ አረቢያ የስራ ቅጥር ታገደ‼️
📌የኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ባደረገው ውሳኔ መሰረት ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚደረጉ የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አግዷል።
📌ይህ ውሳኔ በሙሳኔድ(Musaned) ለቤት ሠራተኞች ቅጥር የሚደረጉ ክፍያዎች ግልጽነትን ለማረጋገጥ፣ ማጭበርበርን ለመከላከልና ክፍያዎች በኤሌክትሮኒክ መንገድ መፈፀም እንዳለባቸው ይደነግጋል።
📌ማንኛውንም የውል ሂደት ከመጀመሩ በፊት የቅጥር ቢሮዎች በሙሳኔድ ፈቃድ ያላቸው እና በይፋ የተመዘገቡ መሆናቸውን መረጋገጥ እንዳለባቸው አፅንዖት ተሰጥቷል።
📌የቤት ሠራተኞችን ቅጥር የሚመለከቱ ውሎች የሁሉም ወገኖች ህጋዊ እና የገንዘብ መብቶችን ለመጠበቅ በሙሳኔድ በኩል በኤሌክትሮኒክ መንገድ መገምገም እና መጽደቅ አለባቸው።
ይህ ጉዳይ እስከሚስተካከል ድረስ በሳውዲ አረቢያ የሚደረጉ የሰራተኞች ቅጥር በኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥያቄ እንዲቆም መጠየቁን musaned አሳውቋል።

👍12❤5
የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወረዳ ደረጃ ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ ጭማሪ ተደርጓል።
አዲስ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት እና ዲጂታል መታወቂያ በወቅቱ ለማደስ 300 ብር፣የእድሳት ጊዜ ያለፈበት መታወቂያ ለማደስ እና በተለያየ ምክንያት የተበላሸ ዲጂታል መታወቂያ ለመቀየር 600 ብር፣ያላገባ አገልግሎት 400 ብር፣ለትውልደ ኢትዮጵያን ያላገባ አገልግሎት ለማግኘት 800 ብር ይከፍላሉ።

❤13😢10😡9🥱3👍2👌1
ኦነሠ-የጽምዶ አባል «አይደለሁም» አለ
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” በተመሠረተዉ “ፅምዶ” በተባለዉ ህብረት ውስጥ ምንም ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታውቋል፡፡በትጥቅ ትግልና በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያ መንግስትን ለመውጋት ተቋቋመ የተባለው ጽምዶ የውጪ ኃላትንም ጭምር ያሳተፈ ነው በሚል በኢትዮጵያ መንግስት ጭምር መገለጹ ይታወሳል፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ዛሬ በ X ገጹ ባወጣው መግለጫ እንዳብራራው ግን “የኦነሠ እና ጽምዶን ግንኙነት አስመልክቶ የሚወራው ከእውነት የራቄ ነው” ብሏል፡፡
“ኦነሠ ጽምዶ በተባለ ትብብር ውስጥ የለም፤ ጉዳዩንም በቅርበት አይከታተል” ያለው መግለጫ፣ ነገር ግን “ከአገሪቱ ሰሜን አስከ ደቡብ እንዲሁም ከምስራቅ እና ምዕራብ ጫፍ ተቃዋሚዎችን ያቀፈ ትብብር ቅርጽ እየያዘ ነው” በማለት በሌላ ትብብር ውስጥ መሆኑን አሳውቋል፡፡
ታጣቂ ቡድኑ “ቅርጽ ይዟል” ስላለው አዲስ ትብብር ግን ማብራሪያ አልሰጠም፡፡
ኦነሠ ከፋኖ ኃይሎች፣ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትገግራይ (ህወሓት) እና ከኤርትራ መንግስት ጋር መሰረተ በተባለው “ጽምዶ” በተባለ ጥምረት ውስጥ እንዳለበት በሰፊው ሲነገር ቆይቶ ነበር፡፡
ኦነሠ በመግለጫው “ወለጋ ዉስጥ በመንቀሳቀስ ሲቪሎችን ኢላማ ያደርጋሉ” በማለት የወቀሳቸው “የፋኖ ታጣቂዎች” እንቅስቃሴን በመቃወም፤ የፋኖ ቡድን በአከባቢው ለመኖሩ በዋናነት መንግስትን ተወቃሽ አድርጎታል፡፡
የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሥዩም ጌቱ ኦነሠ ሥላሰራጨዉ መግለጫ የቡድኑ ዋና አዛዥ አማካሪ አቶ ጅሬኛ ጉደታን ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ቢደዉልም አቶ ጅሬኛ ሥልካቸዉን አላነሱም።
ዶቸቬሌ ነው የዘገበው

❤16🙉5👍4🥱4🤪4🤣1
#ደቡብ_ሱዳን #በፉላ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ለማልማት ያላትን ቁርጠኝነት አደሰች፤ #የግብፅን ተቃውሞም ውድቅ አደረገች‼️
ደቡብ ሱዳን በኒሙሌ አቅራቢያ በነጭ አባይ ተፋሰስ ላይ ለረጅም ጊዜ ስታቅደው የቆየችውን የፉላ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን ለማልማት በመዘጋጀት ላይ መሆኗን አስታወቀች።
"ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም" ያሉት ሚኒስቴሩ "ግድቦቻችንን ለመገንባት ዝግጁ ነን" ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም በመንግሥት ዝግጅት ላይ ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ገለፃ ማድረጋቸውን እና ኢንቨስተሮች እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ተወካዮች ሚኒስቴሩን ማነጋገር ጀመረዋል ያሉ ሲሆን መንግሥት ይፋ ለማድረግ ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ ተጨማሪ ዝርዝሮች ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

👍16❤12
ከባድ የድሮን ጥቃት‼️
ዛሬ መስከረም 9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:20-5:50 አካባቢ በራያ ማይጨው ከተማ ሶስት ጊዜ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
ጥቃቱ የህወሓት ታጣቂዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ያነጣጠረ ነበር። በዚህም:-ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የህወሓት ታጣቂዎች ተገድለዋል፤ቆስለዋል።
በተጨማሪም፦
➡️ የጦር መሣሪያ የጫነ ተሽከርካሪ
➡️ አንድ ታንክ
➡️ አንድ ዙ-23
➡️ አንድ የሎጂስቲክስ ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

👍24❤8😢4🕊2👀1
በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምሪት ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች "መሠረተ ቢስ ናቸው" አለ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር‼️
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ስላለው የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሂደት ዙሪያ የሚሰራጩ መረጃዎች መሠረተ ቢስ እና ከእውነት የራቁ ናቸው ሲል አስተባበለ።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በጉዳዩ ላይ በሰጠው ማብራሪያ፤ “አንድም ሰው ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሄድ አልቻለም”፣ “የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ (E-LMIS) ተዘግቷል” እና “ለኤጀንሲዎች በበቂ ሁኔታ መረጃ አልተሰጣቸውም” በሚል የሚሰራጩ ዘገባዎች የህዝብ ብዥታ የሚፈጥሩ አሉባልታዎች መሆናቸውን ገልጻል።
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፣ የሀገሪቱ የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሥርዓት የተዘረጋው ሕጋዊ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ክብር ያለው የሥራ ዕድል ለዜጎች ለማረጋገጥ ነው። በዚህ ሂደትም ሳዑዲ አረቢያ ቁልፍ አጋር ሀገር ሆና የምትቀጥል ሲሆን፣ ፈቃድ ያላቸው የቅጥር ኤጀንሲዎችም የምህዳሩ የማይነጠል አካል ሆነው እየሰሩ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
በሂደቱ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመቀናጀት የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሚገኝ የጠቆመው መግለጫው፤ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ (E-LMIS) ሳይቋረጥ ሕጋዊ የሥራ ስምሪቱን እያቀላጠፈ እንደሚገኝ አረጋግጧል።
በመጨረሻም ሚኒስቴሩ ህዝቡ በእንደዚህ አይነት ከእውነት የራቁ መረጃዎች እንዳይደናገር እያሳሰበ፣ አሳሳች መረጃዎችን በሚያሰራጩ አካላት ላይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ዜጎችና ባለድርሻ አካላት መረጃዎችን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ የመረጃ መረቦች ብቻ እንዲከታተሉም ጥሪ አቅርቧል።

❤13👍6
ዜና፦ የተከሳሾች ጠበቃ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው እና ጋዜጠኞች ‘ሕገ-ወጥ’ የይቅርታ ቅድመ-ሁኔታዎችን ባለመቀበላቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ
የተከሳሾች ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ #ለአዲስ_ስታንዳርድ እንደተናገሩት፣ ተከሳሾቹ ሕገ-ወጥ በሆነ የይቅርታ ሂደት አማካይነት የቀረቡላቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ባለስልጣናቱ ይቅርታን እና ክስ ማንሳትን ሕጋዊ ልዩነታቸውን በመካድ አንድ ላይ አደባልቀውታል ሲሉ ተችተዋል።
ከ600 በላይ ተከሳሾች በጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም “በምህረት እና በይቅርታ” ከእስር ከተፈቱት ውስጥ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለ፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባል ካሳ ተሻገር (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራር ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) ይገኙበታል።
እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ ሰነዱ ተከሳሾቹ በአማራ ክልል ለደረሰው ውድመት፣ ለሰዎች ሞት፣ አካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት ኃላፊነት እንዲወስዱ፣ እንዲሁም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖችን «አክራሪ» ብለው እንዲያወግዙ የሚጠይቅ ነበር።

❤11🌚3👍2😢2🤪2
የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ 2% ሊቆርጡ ነው።
የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከ0.5 እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበትን አሠራር መዘርጋታቸው ተሰማ። ይህ ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ቀሪ መደረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ክልሎች ተመሳሳይ የመዋጮ መጠን ለመሰብሰብ የወሰኑ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።

😢19❤13👍6
የስዌዲ ጣቢያው ጥቃት‼️
ትናንት መስከረም 9, 2019 ዓ.ም በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን በሚገኙ በርካታ ከተሞች መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ የኤርትራ ሰራዊት በስፋት እንዲገባ ተደርጓል።
ይህንን ተከትሎ ዛሬ ረፋድ በአዲ ነብሪ ኢድ እና አዲ ዳኤሮ መካከል ባለው #ስዌዲ ጣቢያ ላይ ተከታታይ የድሮን ጥቃቶች ተካሂደዋል።
ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
እህል የጫነ አንዳ ተሳቢ ተመቷል፣ ህወሓት የእርዳታ እህል ነው ያለ ቢሆንም እህሉ ለታጣቂዎቹ ከኤርትራ የተላከ መሆኑን የአካባቢው ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

👍9❤1🕊1
የወላጅነት ድካም ከመከሰቱ በፊት ራስን የማዳኛ 5 ወሳኝ መንገዶች
ወላጅነት በደስታ እና በፍቅር የተሞላ ታላቅ ኃላፊነት ቢሆንም፣ በሒደት ግን አእምሮአዊና አካላዊ ኃይልን የሚያሰጥም ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል።
የኃይል ምንጫችን ቀስ በቀስ ሲደፈቅ እና ሲደርቅ ወላጆች ለአእምሮአዊና አካላዊ ድካም ይጋለጣሉ። ይህ ደግሞ በድንገት ሳይሆን በቀስ በቀስ የሚከሰት በመሆኑ፣ የመጀመሪያዎቹን ማስጠንቀቂያዎች ቀድሞ መረዳትና አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ወላጅነትን በደስታ ለመምራት ይረዳል።
እነሆ የወላጅነት ድካምን ለመከላከልና አእምሮአዊ ብርታትን ለመመለስ የሚረዱ 5 መፍትሔዎች፦
የብስጭትና የውጥረት ስሜትን በፍጥነት ማንሳት፦
አጣዳፊ መፍትሔ፦ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የጡንቻ ውጥረትን ማስወገድ። ለምሳሌ፡ እጅና እግርን በኃይል ማናወጥ ወይም ስፖርታዊ ዝላይዎችን (መስራት ውጥረትን ወዲያውኑ ይቀንሳል።
ዘላቂ መፍትሔ፦ በጭንቀት ጊዜ ነገሮችን እንደተለመደው ዝም ብሎ ከመግፋት ይልቅ፣ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ለይቶ ማወቅና ከቤተሰብ ጋር በግልጽ መነጋገር።
የነርቭ ሥርዓትን ማረጋጋትና የእንቅልፍ ዕረፍት ማግኘት፦
አጣዳፊ መፍትሔ፦ የሳንባን የአተነፋፈስ ሥርዓት የሚያስተካክሉ ልምምዶችን ፣ የጡንቻ ማዝናኛዎችን ልምምዶችን ማድረግ።
ዘላቂ መፍትሔ፦ ውጤታማነት ላይ ብቻ ሳያተኩሩ ለራስ የሚያስደስቱና ዘና የሚያስኙ እንደ የእግር ጉዞ ወይም ፈጠራ ነክ ሥራዎች ላይ መሳተፍ።
ከራስና ከልጆች ጋር ያለውን ስሜታዊ ግንኙነት ማደስ፦
አጣዳፊ መፍትሔ፦ የስሜት ሕዋሳትን ማነቃቃት፤ ለምሳሌ ፊትን በቅዝቃዛ ውኃ መታጠብ፣ ገላን በጣፋጭ ጠረን ባለው ክሬም ማሸት ወይም አካልን ቀስ አድርጎ በመታሸት ወደ አሁኑ ጊዜ መመለስ።
ዘላቂ መፍትሔ፦ ከልጆች ጋር ጥራት ያለው ጊዜ ማሳለፍ፤ አብሮ ጨዋታዎችን መጫወት፣ ሽርሽር መውጣት ወይም የልጅነት ትዝታዎችን አብሮ ማሳለፍ።
የአእምሮ ጫናን መቀነስ፦
አጣዳፊ መፍትሔ፦ የሚሰሩ ሥራዎችንና የሚጨነቁባቸውን ነገሮች ወዲያውኑ በወረቀት ወይም በስልክ ላይ መጻፍ አእምሮ ዕረፍት እንዲያገኝ ይረዳል።
ዘላቂ መፍትሔ፦ በወላጆች መካከል የሥራ ክፍፍል ማድረግ፣ ግልጽ ዕቅዶችን ማውጣትና በዕቅዱ ውስጥ የግል የእረፍት ጊዜያትን ማካተት።
የበደለኛነት ስሜትንና አላስፈላጊ ጭንቀትን ማስወገድ፦
አጣዳፊ መፍትሔ፦ "ቅርብ ጓደኞት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ምን ይመክሩት ነበር?" ብሎ ራስን መጠየቅና ለራስ ሩህሩህ መሆን።
ዘላቂ መፍትሔ፦ ወላጅነት ማለት ልጆችን ከማንኛውም ችግር መሸፈን ሳይሆን፣ መምራትና ማሳደግ መሆኑን ተረድቶ የኅብረተሰቡን አላስፈላጊ ግፊት አለመቀበል።
ምንጭ: ብሊክ ጋዜጣ

❤15👍3😢1
የአሜሪካ አስቸኳይ መግለጫ❗️
👉የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ሪያድ፣ አቡ ዳቢ፣ ዶሃ፣ እየሩሳሌም እና ሌሎችም ከትናንት ጀምሮ ያወጡት የተቀናጀ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
በየመኑ ሁቲዎች እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭትና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃቶች ማሻቀባቸው ግጭቱ በፍጥነት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊስፋፋ እንደሚችል ተስጋቷል።
👉 የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ የሲቪል አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።
በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ከዚያ ውጭ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን እና ዜጎችን ኢላማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ኤምባሲዎቹ አሳስበዋል።
👉በአካባቢው የሚገኙ የአየር ክልሎች በድንገት ሊዘጋጉ ስለሚችሉ፣ የበረራ ስረዛዎች እና ከፍተኛ የመንገድ መስተጓጎሎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
👉 በዱባይ፣ ዶሃ፣ አቡ ዳቢ፣ ሪያድ እና ጅዳ አየር ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የበረራ ሁኔታቸውን ከአየር መንገዶቻቸው ጋር በቀጥታ እንዲያረጋግጡ ታዟል።
👉 በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የሌሉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ አካባቢውም ሆነ በአካባቢው አየር ክልል አቋርጠው የሚያደርጉትን ጉዞ "በድጋሚ እንዲያጤኑት" ምክር ተሰጥቷል።

❤18👍4🤔3💯1
በኢትዮጵያ “አካታች የሽግግር መንግስት” ለመመስረት ያለመ የሰባት አማጽያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ትብብር መመስረቱ ይፋ ተደረገ። “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን ትብብር ከመሰረቱት ውስጥ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው ዛሬ እሁድ መስከረም 10፤ 2019 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዜና ማሰራጫዎች በኩል በተላለፈ መግለጫ ነው። መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው አፋብንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው።
አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውም በቪዲዮ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ተመልክቷል። የእዚሁ ትብብር ሌሎች መስራች አባላት የኦጋዴን ህዝብ ነጻነት ግንባር፣ የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር፣ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ እና የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እንደሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

❤41👍13🤣5🤔2🥱2🫡2🤯1👀1🤪1
ሰባት የታጠቁ እና የፖለቲካ ኃይሎች አዲስ ጥምረት መመሥረታቸውን አስታወቁ
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰባት የታጠቁ እና የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን አዲስ ጥምረት መሥረታቸውን የሚገልጽ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
ቡድኖቹ አዲሱን ጥምረት «የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትብብር ለህልውና» ወይም በአጭሩ «ትብብር ለህልውና» በሚል መጠሪያ እንደሚጠሩት ገልጸዋል።
በጥምረቱ የተካተቱት አካላት፦
በተሰራጨው መግለጫ መሠረት በጥምረቱ ውስጥ፦
• የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
• የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (OLA)
• ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)
• የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ONLF)
• የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር
• የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ
• የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ
እንደተካተቱ ተጠቅሷል።
መንግሥት የታጠቁ ኃይሎችን እንቅስቃሴ የሀገርን ሰላምና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት አደጋ ላይ የሚጥል አድርጎ እንደሚመለከተው ይታወቃል።

❤56👍12🤣8😢3🕊2😡2🥰1🤔1👀1🙈1