አዲስ ሪፖርተር - NEWS
37K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በትግራይ ክልል ለተመደባችሁ በሙሉ‼️
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ና ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የትምህርት ሂደታችሁ እንዳይስተጓጎልና ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል፣ በጠየቃችሁት መሰርት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እየገለጽን በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሚገለፅላቹህ ሲሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ባሉት ዩኒቨርስቲዎች መቀጠል የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍4
ፀሊሞይ‼️
ዛሬ መስከረም 7/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:00 አከባቢ ጀምሮ በወልቃይት በኩል በተከዜ ዋናው ድልድይ፣ከደደቢት-በፀሊሞይ አቅጣጫ ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ለተወሰነ ደቂቃ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ የህወሓት አርሚ 17 ተዋጊዎች ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍7🤪3
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ጦርነት መግባት አትፈልግም❗️
ሲሉ የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ምክትል ኃላፊ ጄነራል ማሊክ አጋር አስታወቁ

🇸🇩የሱዳን የሉዓላዊነት ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ጄነራል ማሊክ አጋር ከኢትዮጵያ ጋር ውጥረት ቢኖርም ሀገራቸው ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር ወደ ወታደራዊ ግጭት የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ገለጹ።

🇸🇩ጄነራል ማሊክ አጋር በካርቱም በተካሄደ የጋዜጠኞች ፎረም ላይ እንደተናገሩት “ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ጦርነት መግባት አንፈልግም” ብለዋል።

🇸🇩የምክር ቤቱ ምክትል ኃላፊ ይህንን ያሉት በሱዳንና ኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ ውጥረት እየጨመረ በመጣበት እና የሱዳን ጦር ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይል  እና አጋሮቹ ከግዛቷ ድሮኖችን እንዲያሰማሩ ፈቅዳለች ሲሉ በከሰሱበት ወቅት ነው።

🇪🇹ኢትዮጵያ በበኩሏ በድሮን ጥቃቶች ላይ እጄ አለበት በሚል ከሱዳን የሚሰነዘሩብኝን ክሶች “መሰረተ ቢስ” ስትል ቀደም ሲል ውድቅ ማድረጓን ሬዲዮ ታማዙዥ በዘገባው አስታውሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍10❤8🥰2🕊2
«የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ የተገኙ ናቸው» እጅ የሰጡ ታጣቂዎች‼️
👉ምሽቱን ተጨማሪ 43 ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል።
ዛሬ በወልቃይት እጃቸውን የሰጡት የህወሓት ታጣቂዎች ለፀጥታ ኃይሎች መረጃ እየሰጡ ነው።

«ጠመንጃን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ የተገኙ ናቸው» ሲሉ ዛሬ እጃቸውን የሰጡት የህወሓት ታጣቂዎች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በውጊያ የተያዙ ወይም የተማረኩ ሳይሆን፣ በራሳቸው ፈቃድ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እንደሰጡ ተረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8🤪6❤2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች የማኅበር ቤት ግንባታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ አለ❗❗

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራት የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች መነሻ የግንባታ ዋጋ በካሬ ሜትር ከነበረበት 35 ሺህ ብር ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ እንዲል አድርጓል። የዋጋ ጭማሪውን መሸከም ባለመቻላቸው ከማኅበሩ ለመውጣትና የተከፈለውን ገንዘብ ለመመለስ የጠየቁ መምህራን ደግሞ "ገንዘቡ አይመለስላችሁም" መባላቸው ቅሬታን ፈጥሯል።

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶ/ር መኮንን ጥበቡ ቸኮል ለኅብረት ሥራ ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ መሠረት፣ በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም በካሬ ሜትር 35 ሺህ ብር የነበረው የመነሻ ግንባታ ዋጋ በመስከረም ወር 2018 ዓ.ም በተደረገ ክለሳ ወደ 50 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ተወሰኗል። በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተጠናው ወቅታዊ ጥናት መሠረት ደግሞ አንዳንዶቹ የግንባታ ተመኖች በካሬ ሜትር እስከ 82 ሺህ ብር ይደርሳሉ።

አስተዳደሩ ለመምህራን እና ለጤና ባለሙያዎች መሬት በነፃ በማቅረብ 25 በመቶ ቅድመ ክፍያ በሠራተኞች እንዲሸፈን እና ቀሪው 75 በመቶ በባንክ ብድር እንዲመቻች ባደረገው መርሃ-ግብር፣ 6 ሺህ 194 መምህራን በ57 ማኅበራት ተደራጅተው መሬት ተረክበው ነበር።

ሆኖም መምህራኑ የመጀመሪያውን የ25 በመቶ ቅድመ ክፍያ የከፈሉት ከወርሃዊ ደመወዛቸው በተጨማሪ በብድር እና በቤተሰብ ድጋፍ እንደነበር ገልጸው፣ አዲሱ ጭማሪ ከገቢያቸው አንጻር ሊሸከሙት የማይችሉት መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም ምክንያት ጭማሪውን መክፈል ባለመቻላቸው "ገንዘባችን ተመልሶልን ከማኅበሩ እንውጣ" ብለው የጠየቁ አባላት "ገንዘቡ አይመለስላችሁም" የሚል ምላሽ ስለተሰጣቸው ለከፍተኛ ስጋትና ቅሬታ ተዳርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12😢8👍3🤩2
ሁለት ተበዳዮችን በአንድ ለሊት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!

የ39 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሽ ሰጣርጌ ግሩም በምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ ወረዳ ወይራ ጉሬዛም ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን፣ በወቅቱ ለሥራ ከተመደበበት ዲማ ቀበሌ ከሥራ ቦታ በመሰወር እተበዳይ ቤት መሄዱን ፖሊስ ገልጿል።

ተከሳሹ የሕግ አካል እንደሆነ በመግለጽ በቤቱ ውስጥ ሌባ ተደብቋል በማለት በሩን አስከፍቶ ወደ ቤቱ እንደገባ ተመላክቷል።

ተከሳሹ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የቤቱን በር በመዝጋትና በጦር መሣሪያ በማስፈራራት በቤቱ የነበሩ ሦስት ሰዎች እንዲተኙ ካስገደደ በኋላ_የተባለች የ18 ዓመት ወጣት እና_ የተባለች  የ20 ዓመት እድሜ ያላት (የመጀመርያዋ ተደፋሪ አክስትን)  ሁለቱን ግለሠቦች እስከ ንጋቱ 11፡00 ሰዓት ድረስ አስገድዶ መድፈሩን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

የእነማይ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ሹሜ ላቀው እንደገለጹት በማግስቱ መርማሪ ፖሊሶች በቦታው በመድረስ አስፈላጊውን የማጣራት ሥራ ካከናወኑ በኋላ ተጠርጣሪውንና ተጎጂዎችን ወደ ሆስፒታል በመውሰድ የሕክምና ምርመራ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በምርመራውም በተጎጂዎቹ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙ መረጋገጡን ኃላፊው ገልጸዋል።

ተከሳሹ ከዚህ በፊት በግድያ ወንጀል የ16 ዓመት እስራት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ ከዚያ ውስጥ አምስት ዓመት ከታሰረ በኋላ በ2015 ዓ.ም በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ ከማረሚያ ቤት አምልጦ ሕገ-ወጥ ታጣቂ ቡድንን ተቀላቅሎ ሲዋጋ ቆይቷል ተብሏል።

በኋላም መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀብሎ በመግባት በወረዳው የሰላም ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርቶ ሲሠራ እንደነበር ተመላክቷል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በፍጥነት በማጣራት ለእነማይ ወረዳ አቃቤ ሕግ ከላከ በኋላ በተከሳሹ ላይ ክስ ተመስርቶ ጉዳዩ ሲታይ ቆይቷል።

የእነማይ ወረዳ ፍርድ ቤትም መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቀረቡለትን ማስረጃዎችና የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ሁኔታዎችን መርምሮ ተከሳሹ ሰጣርጌ ግሩም በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

የእነማይ ወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ የፍርድ ውሳኔው በተመሳሳይ ወንጀል ሊሳተፉ ለሚችሉ ግለሰቦች ትምህርት የሚሰጥና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያሳይ ነው።

የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ፅህፈት ቤት ነው!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤27💔21😢6😡3👍2
በሚቀጥሉት ወራት "ወቅቱን ያልጠበቀ" ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት የ 2019 የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያውን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ጠንካራ የኤልኒኖ ክስተት ወይም የውቅያኖስ ሙቀት እንደሚኖር አስታውቋል።

በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚኖር የተተነበየ ሲሆን፤ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደግሞ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ብስራት ሬድዮ ሰምቷል ።

በተጨማሪም በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የቀን የሙቀት መጠን ከመደበኛ በላይ እንደሚሆንና ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች የሌሊት የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሊወርድ እንደሚችል ተነግሯል።

በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ተከታታይነት ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የቅፅበታዊ ጎርፍ፣ የወንዞች መሙላት እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል።

በተለይም በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ አካባቢዎች በሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ምክንያት በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል፣ አርሶ አደሮች ሰብላቸውን በፍጥነት እንዲሰበስቡ፤ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት የጎርፍ መውረጃ ቦዮችን በማጽዳት እና ማህበረሰቡን በማንቃት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተቋሙ አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍5
#Ethiopia

ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እስከ 2 በመቶ ሊቆረጥ ነው።

የክልል መንግስታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከዜሮ ነጥብ 5 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበት አሠራር መዘርጋታቸውን ተሰምቷል።

ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ግን ቀሪ መደረጉ ይታወሳል።

ክልሎች ለመሰብሰብ የወሰኑት መዋጮ ተመሳሳይ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ መጠን ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።

በተያያዘ ዘገባ፦ ዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በማሳደግ ላይ ያሉ አገራት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ ጫና ሳያደርጉ ገቢያቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን የፖሊሲ ጥናት ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።

ባንኩ የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንጻር ያለው ድርሻ በታሪክ እጅግ ዝቅተኛው 7.5 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ አፈጻጸም፣ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 13 በመቶ አማካይ አጠቃላይ ገቢና በተለይም እንደ፦
-ኬንያ፣
-ሩዋንዳ እና
-ኡጋንዳ ካሉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ባንኩ ጠቅሷል።

ለሀገሪቱ የታክስ ገቢ ማነስ፣ ሕገወጥ ንግድ፣ የታክስ ነጻ መብቶች መብዛትና በግብር አሰባሰብ መዋቅር ላይ ያሉ ድክመቶች ዋና ምክንያት ናቸው ተብሏል። ባንኩ፣ በሀገራት የመዋቅራዊ አቅም ምድብ፣ ኢትዮጵያን 'በቅድሚያ መሰረታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ሒደት' ምድብ ውስጥ እንደምትገኝ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢31❤16😡15👍2
የአሜሪካ መንግስት የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆ ባይደን የተፈረመውን EXECUTIVE ORDER 14646 ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረው የጦር መሳሪያ ሽያጭ እቀባ ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ አንስቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤17👍11👌1🕊1
በአፋር ድንበር አካባቢ አዲስ ውጊያ‼️ 
የህወሓት ሀይል በአፋር አዋሳኝ በኩራን፣ ጎጎ እና አራዱ የድንበር አካባቢዎች ከአፋር ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል ጋር ውጊያ ጀምሯል።
ታጣቂዎቹ ትላንት ምሽት በሁለት ዶዘር መንገድ የማጽዳት ሥራ ሲያከናውኑ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤯6👍2😈1👀1
አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ አነሳች

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ መከላከያ ኃይልና በሌሎች የኤርትራ ተቋማት፣ አካላትና ባለሥልጣናት ላይ ጥላዉ የነበረዉን ማዕቀብ ዛሬ ማንሳቷን አስታወቀች።

በኤርትራ መከላከያ ሚንስቴርና በሌሎች የኤርትራ ተቋማት፣ አካላትና ባለሥልጣናት ላይ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2021 ማዕቀቡን የጣለዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የጆ ባይደን አስተዳደር ነበር።

የባይደን አስተዳደር በኤርትራ ገዢ ፓርቲ፣ በጦር ኃይሉና በሌሎች ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ የጣለዉ ኤርትራ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን ሆና መዋጋቷን በመቃወም ነበር። 

የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ዛሬ በአምደ መረቡ ባሰራጨዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ግን የባይደን አስተዳደር ጥሎት የነበረዉ ማዕቀብ ተነስቷል።

ሮይተርስ ዜና አገልግሎት እንደዘገበዉ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ማዕቀቡን ማንሳቱ  የዋሽግተንና የአሥመራን ግንኙነት ለማሻሻል ይረዳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12❤5🤣5🤔2
በሳውዲ አረቢያ የስራ ቅጥር ታገደ‼️
📌የኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ባደረገው ውሳኔ መሰረት ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚደረጉ የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አግዷል።
📌ይህ ውሳኔ በሙሳኔድ(Musaned) ለቤት ሠራተኞች ቅጥር የሚደረጉ ክፍያዎች ግልጽነትን ለማረጋገጥ፣ ማጭበርበርን ለመከላከልና ክፍያዎች በኤሌክትሮኒክ መንገድ መፈፀም እንዳለባቸው ይደነግጋል።
📌ማንኛውንም የውል ሂደት ከመጀመሩ በፊት የቅጥር ቢሮዎች በሙሳኔድ ፈቃድ ያላቸው እና በይፋ የተመዘገቡ መሆናቸውን መረጋገጥ እንዳለባቸው አፅንዖት ተሰጥቷል።
📌የቤት ሠራተኞችን ቅጥር የሚመለከቱ ውሎች የሁሉም ወገኖች ህጋዊ እና የገንዘብ መብቶችን ለመጠበቅ በሙሳኔድ በኩል በኤሌክትሮኒክ መንገድ መገምገም እና መጽደቅ አለባቸው።
ይህ ጉዳይ እስከሚስተካከል ድረስ በሳውዲ አረቢያ የሚደረጉ የሰራተኞች ቅጥር በኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጥያቄ እንዲቆም መጠየቁን musaned አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12❤5
የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወረዳ ደረጃ ለነዋሪዎች አገልግሎት የሚጠይቀው የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ ጭማሪ ተደርጓል።
አዲስ ዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት እና ዲጂታል መታወቂያ በወቅቱ ለማደስ 300 ብር፣የእድሳት ጊዜ ያለፈበት መታወቂያ ለማደስ እና በተለያየ ምክንያት የተበላሸ ዲጂታል መታወቂያ ለመቀየር 600 ብር፣ያላገባ አገልግሎት 400 ብር፣ለትውልደ ኢትዮጵያን ያላገባ አገልግሎት ለማግኘት 800 ብር ይከፍላሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13😢10😡9🥱3👍2👌1
ኦነሠ-የጽምዶ አባል «አይደለሁም» አለ

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” በተመሠረተዉ “ፅምዶ” በተባለዉ ህብረት ውስጥ ምንም ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታውቋል፡፡በትጥቅ ትግልና በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያ መንግስትን ለመውጋት ተቋቋመ የተባለው ጽምዶ የውጪ ኃላትንም ጭምር ያሳተፈ ነው በሚል በኢትዮጵያ መንግስት ጭምር መገለጹ ይታወሳል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ዛሬ በ X ገጹ ባወጣው መግለጫ እንዳብራራው ግን “የኦነሠ እና ጽምዶን ግንኙነት አስመልክቶ የሚወራው ከእውነት የራቄ ነው” ብሏል፡፡

“ኦነሠ ጽምዶ በተባለ ትብብር ውስጥ የለም፤ ጉዳዩንም በቅርበት አይከታተል” ያለው መግለጫ፣ ነገር ግን “ከአገሪቱ ሰሜን አስከ ደቡብ እንዲሁም ከምስራቅ እና ምዕራብ ጫፍ ተቃዋሚዎችን ያቀፈ ትብብር ቅርጽ እየያዘ ነው” በማለት በሌላ ትብብር ውስጥ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ “ቅርጽ ይዟል” ስላለው አዲስ ትብብር ግን ማብራሪያ አልሰጠም፡፡

ኦነሠ ከፋኖ ኃይሎች፣ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትገግራይ (ህወሓት) እና ከኤርትራ መንግስት ጋር መሰረተ በተባለው “ጽምዶ” በተባለ ጥምረት ውስጥ እንዳለበት በሰፊው ሲነገር ቆይቶ ነበር፡፡

ኦነሠ በመግለጫው “ወለጋ ዉስጥ በመንቀሳቀስ ሲቪሎችን ኢላማ ያደርጋሉ” በማለት የወቀሳቸው “የፋኖ ታጣቂዎች” እንቅስቃሴን በመቃወም፤ የፋኖ ቡድን በአከባቢው ለመኖሩ በዋናነት መንግስትን ተወቃሽ አድርጎታል፡፡

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሥዩም ጌቱ ኦነሠ ሥላሰራጨዉ መግለጫ የቡድኑ ዋና አዛዥ አማካሪ አቶ ጅሬኛ ጉደታን ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ቢደዉልም አቶ ጅሬኛ ሥልካቸዉን አላነሱም።
ዶቸቬሌ ነው የዘገበው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16🙉5👍4🥱4🤪4🤣1
#ደቡብ_ሱዳን #በፉላ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ለማልማት ያላትን ቁርጠኝነት አደሰች፤ #የግብፅን ተቃውሞም ውድቅ አደረገች‼️

ደቡብ ሱዳን በኒሙሌ አቅራቢያ በነጭ አባይ ተፋሰስ ላይ ለረጅም ጊዜ ስታቅደው የቆየችውን የፉላ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክትን ለማልማት በመዘጋጀት ላይ መሆኗን አስታወቀች።
 
"ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም" ያሉት ሚኒስቴሩ "ግድቦቻችንን ለመገንባት ዝግጁ ነን" ሲሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም በመንግሥት ዝግጅት ላይ ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ገለፃ ማድረጋቸውን እና ኢንቨስተሮች እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ተወካዮች ሚኒስቴሩን ማነጋገር ጀመረዋል ያሉ ሲሆን መንግሥት ይፋ ለማድረግ ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ ተጨማሪ ዝርዝሮች ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤12
ከባድ የድሮን ጥቃት‼️
ዛሬ መስከረም 9/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:20-5:50 አካባቢ በራያ ማይጨው ከተማ ሶስት ጊዜ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል።
ጥቃቱ የህወሓት ታጣቂዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ያነጣጠረ ነበር። በዚህም:-ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የህወሓት ታጣቂዎች ተገድለዋል፤ቆስለዋል።
በተጨማሪም፦
➡️ የጦር መሣሪያ የጫነ ተሽከርካሪ
➡️ አንድ ታንክ
➡️ አንድ ዙ-23
➡️ አንድ የሎጂስቲክስ ተሽከርካሪ ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍24❤8😢4🕊2👀1