አዲስ ሪፖርተር - NEWS
37K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአበሽጌ 13 ሰዎች ተገደሉ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና ልዩ ስሙ "ዋልጋ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፣ ትላንት መስከረም 4/2019 ዓ.ም ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች በከፈቱት አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 13 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ታጣቂዎቹ ንጹሃኑን ከመግደል ባለፈ 16 ያህል ሴቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ አፍነው ወስደዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንዳሉ እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ አልተቻለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢19💔11❤8👍4🕊4🤔1
ፍርድ ቤት በኖህ ሪልስቴት ላይ የ24 አፓርታማዎችን ሽያጭ የሚያግድ ትዕዛዝ አስተላለፈ

​የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ ኖህ ሪልስቴት በአዲስ አበባ "ቪክትሪ ሳይት" የሚገኙ የ32 ቤት ገዢዎችን 24 አፓርታማዎች እንዳይሸጥ ወይም ለሦስተኛ ወገን እንዳያስተላልፍ እግድ ጣለ።

​ቀደም ሲል ተሰጥቶ የነበረው ጊዜያዊ እግድ፣ መደበኛ ክሱ መቅረቡን ተከተሎ ፍርድ ቤቱ ክርክሩ የመጨረሻ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ፀንቶ እንዲቆይ ወስኗል።

​የከሳሾች ጠበቃ አበበ ገብሩ እንደገለጹት፣ ድርጅቱ በውሉ መሰረት ቤቶቹን ባለማስረከቡ እና ውል ሰርዞ ለሌላ ወገን ለማስተላለፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጣቱ ምክንያት ቅድመ ክስ እና እግድ ለማቅረብ ተገድደዋል።

​ችግሩን በድርድር ለመፍታት ለድርጅቱ የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ኖህ ሪልስቴት በቂ ምላሽ ባለመስጠቱ መደበኛ ክስ ለመመስረት መገደዳቸውን ጠበቃው አስረድተዋል። ጉዳዩን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ለሪልስቴት ድርጅቱ መጥሪያ የላከ ሲሆን፣ መደበኛ የፍርድ ቤት ክርክሩ ፍርድ ቤቶች ከእረፍት ሲመለሱ በጥቅምት ወር እንደሚቀጥል ታውቋል።

ምንጭ: ቲክቫህ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍4👀2
የጣሊያን ባንኮች የኮይሻ ግድብን ለማጠናቀቅ የሚያስችል 400 ሚሊዮን ዩሮ #ለኢትዮጵያ ሊያበድሩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ፦ #ኢትዮጵያ 1 ሺህ 800 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የሚገመተውን የኮይሻ ግድብን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የ400 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለማግኘት ከሦስት የጣሊያን ባንኮች ጋር ድርድር ላይ መሆኗን ብሉምበርግ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደገለጹት፣ ተቋማቸው 3 ቢልዮን ዩሮ የሚያወጣውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 100 ሚልዮን ዩሮ የሚያክል ገንዘብ ከአገር ውስጥ ምንጮች ማሰባሰብ ይችላል" ያሉ ሲሆን "የብድር ስምምነቱ በቀጣይ ጥቅምት ወር ይፈረማል ብለን እንጠብቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።

በጊቤ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው የዚህ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ በኢትዮጵያ የእዳ ሽግሽግ ምክንያት ከተያዘለት ጊዜ በሦስት ዓመታት ወደ ኋላ የቀረ ሲሆን አገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2023 የዩሮቦንድ የዋጋ ወለድ ክፍያ መፈጸም ባለመቻሏ የ4.5 ቢልዮን ዶላር ብድር እንደገና የማደራጀት ሂደት ላይ ትገኛለች።

ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በገዛ ሀብቷ የገነባችውን 4.8 ቢልዮን ዶላር ወጪ የተደረገበትን ግድብ እንዳስመረቀች የሚታወስ ነው። 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአገሪቱን የኃይል ማመንጨት አቅም በእጥፍ በማሳደግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመጀመሪያውን ዓመታዊ ትርፍ እንዲያስመዘግብ ረድቶታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19🤪13👍2😢2
አንድ ኪሎ ግራም ቡና በ2,376 ዶላር ተሸጠ!

የቴስቲ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ፈይሰል አብዶሽ ያቀረቡት የጉጂ ስፔሻሊቲ ቡና በአንድ ኪሎ ግራም 2,376.50 ዶላር (ከ380 ሺህ ብር በላይ) በመሸጥ አዲስ ታሪካዊ ሪከርድ አስመዝገቧል። 

ከዚህ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም በጉጂ ዞን ለሚገነባው የጤና ጣቢያ ማጠናቀቂያ ይውላል።

እንግሊዝና አሜሪካ በሚገኙት የM-Cultivo የኦንላይን ጨረታ መድረክ ላይ የተካሄደው ይህ ሽያጭ፣ የኢትዮጵያ ቡና ጥራትና ተሰሚነት በዓለም ገበያ ላይ እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። 

ከዚህ ግዙፍ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም በጉጂ ዞን ሻኪሶ ወረዳ ለሚገነባው የጤና ጣቢያ ማጠናቀቂያ እንደሚውል ተገልጿል።

ቴስቲ ኮፊ ከዚህ ቀደምም በይርጋ ጨፌ፣ ሲዳማ እና ሻኪሶ 5 ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ከፍተኛ ማህበራዊ ኃላፊነት የተወጣ ኩባንያ ሲሆን፣ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ 67 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ውስጥ አስገኝቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21👍3🫡1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇨🇳ቻይና ለውሃ ውስጥ ቅኝትና ክትትል አገልግሎት የሚውል ራሱን በራሱ የሚመራ አዲስ የሮቦት ዓሣ አስተዋወቀች። ይህ ቴክኖሎጂ የሰዎች ቀጥተኛ ቁጥጥር ሳያስፈልገው በውሃ ውስጥ በነፃነት ተዘዋውሮ መረጃዎችን የመሰብሰብ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍19👀3❤2
«ኢትዮጵያ  የሱዳንን ግዛትመቆጣጠር  ትፈልጋለች»

የሱዳን ጦር ኤታ ማጆር ሹም ጄኔራል ያሰር አል-አታ፣ ኢትዮጵያ በሱዳን ያለውን ጦርነት በመጠቀም የሱዳንን ግዛት ለመቆጣጠር እና በቀይ ባህር ዙሪያ ስልታዊ ቦታዎችን ለማግኘት እየጣረች ነው ሲሉ ከሰዋል። አል-አታ በአል-ሾሩክ ጋዜጣ ላይ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣  አዲስ አበባ አል-ፋሻጋን፣ ቄይሳንን እና ኩርሙክን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ለመቆጣጠር እቅድ እንዳላት ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሁለቱ አገሮች ድንበር አቅራቢያ የሚደረገው ውጊያ ተባብሷል። የሱዳን ሠራዊት ድሮኖች ከኢትዮጵያ በኩል ተነስተው ጥቃት ሰንዝረዋል ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ይህንን ውንጀላ አስተባብላለች። ኢትዮጵያ  በበኩሏ፣ ሱዳን የኢትዮጵያ ታጣቂ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ትደግፋለች ስትል ትከሳለች።

ይህ የድንበር ውዝግብ የቆየ ሲሆን፣ በተለይ አል-ፋሻጋ በሚባለው ለም መሬት ላይ ያተኮረ ነው። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ሀገራቸው የቀይ ባህር መውጫ ለማግኘት እንደምትፈልግ ቢገልጹም፣ ይህንን ግብ ከወታደራዊ እርምጃ ይልቅ በውይይት ማሳካት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍2🤔2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአዲሱ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መበሰርን ተከትሎ ለመላው የሀገሪቱ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላፈዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው እንደገለጹት፤ ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያ ትልቁ ሀብት በመሆኑ እያንዳንዱ ተማሪ አዲሱን የትምህርት ዘመን በትጋትና በጽናት በመከታተል የሀገሪቱን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች ሊገነባ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
 በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የነገውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የታላቋን ኢትዮጵያ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የተማሪዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑንም አብራርተዋል።
 
በተጨማሪም ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ የመገንባት ጥረት ዋና ምሰሶ መምህራን መሆናቸውን በመጠቆም፤ ተማሪዎችን በማነቃቃትና የነገ ተፎካካሪ የሚያደርጋቸውን ዕውቀትና እሴት የማስታጠቅ አደራቸውን እንዲቀጥሉበት ጥሪ አቅርበዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪29❤13👍2🎉1
የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ያዘ‼️

የአቪዬሽን መረጃ ተንታኙ OAG ባወጣው የሴፕቴምበር 2026 መረጃ መሠረት፣ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በታቀደ የመንገደኞች ወንበር አቅም (Scheduled Seat Capacity) ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ይዟል።

ኤርፖርቱ በዚህ ወር 1.19 ሚሊዮን የሚጠጉ የመንገደኞች ወንበሮችን ያስተናግዳል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፣ ይህም ከአለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ6.5% ዕድገት አሳይቷል።

ደረጃውም:-

1ኛ. ካይሮ (ግብፅ) — ~1.79 ሚሊዮን ወንበሮች

2ኛ. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) — ~1.19 ሚሊዮን ወንበሮች

3ኛ. ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) — ~1.16 ሚሊዮን ወንበሮች

ይህ ስኬት አዲስ አበባ አፍሪካን ከሌላው ዓለም ጋር በማገናኘት ረገድ ያላትን ቁልፍ ሚና የሚያሳይ ሲሆን፣ ለዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰፊ የበረራ መስመር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

ማስታወሻ፦ ይህ ደረጃ የተሰላው ኤርፖርቱ ባስተናገደው የእውነተኛ መንገደኞች ቁጥር ሳይሆን አየር መንገዶች ለበረራ ባዘጋጁት የወንበር ቁጥር መጠን (Scheduled Seat Capacity) ላይ ተመስርቶ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍4
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
መካ ቀይ መስመር ነው-ሳውዲ‼️
ሳዑዲ አረቢያ የሁቲ ታጣቂዎች ወደ መካ የተኮሱትን ድሮን ማክሸፏን ገለጸች❗
ሳዑዲ አረቢያ ማክሰኞ ሌሊት በኢራን የሚደገፉት የሁቲ ታጣቂዎች መካን ለማጥቃት መሞከራቸውን በመግለጽ ድርጊቱን አወገዘች።
ሳዑዲ አረቢያ በመግለጫዋ መካ ላይ የሚፈጸም ጥቃት “ቀይ መስመር” መሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቃለች።
የሁቲ ባለሥልጣናት ወደ መካ ድሮኖች አለመተኮሳቸውን በመግለጽ በድርጊቱ እጃችን የለበትም ብለዋል።
መካ ከየመን ድንበር 1 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች።
መካ የነብዩ ሙሐመድ የትውልድ ቦታ እና ቅዱስ ቁርዓን የተቀበሉበት ሥፍራም ነው።
በሳዑዲ የሚመራው ጥምረት የአገሪቱ አየር ኃይል በሁቲዎች ወደ መካ የተተኮሰን ድሮን ማክሸፋቸውን እና ማውደማቸውን ያስታወቀው ረበዕ ዕለት ማለዳ ነበር።
የጥምረቱ ቃል አቀባይ ቱርኪ አል ማልኪ ድሮኑ የተተኮሰው ሌሊት መሆኑን አስታውቀው ወደ ተከለከለ ክልል ከመግባቱ በፊት ተመትቶ ስብርባሪው በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ወድቋል ብለዋል።
አል ማልኪ ሁቲዎች መካን ዒላማ ያደረጉት ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ባሌስቲክ ሚሳዔል መተኮሳቸውን አስታውሰዋል።
ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ከተማ በሆነችው መካ ላይ የሚፈጸም ጥቃት “ቀይ መስመር” ነው በማለት ጥምረቱ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም እርምጃ ይወስዳል ብለዋል።
ሁቲዎች በበኩላቸው ሳዑዲ ድሮን ተኩሰዋል ስትል ያቀረበችውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍7🤣7😡3
የራያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ‼️
መነሻቸውን ከኤርትራ ያደረጉ 24 ኦራል፣ 3 መድፍ፣ 3 ዙ-23 የታጠቁ ተሽከርካሪዎች፣ትጥቅ እና ስንቅን ጨምሮ በዓዲ-ዃላ አድርጎ ራማን፣ ዓድዋን እና ሓውዜንን አቋርጠው መቐለ ከገቡ በኋላ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6:00 አካባቢ በቀጥታ ወደ ራያ መግባቱ ታውቋል።
የፌደራል መንግስቱም ወደ ራያ አካባቢ ከባባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
በአካባቢው ውጊያ ሊጀመር እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍19❤7🕊3👀3😢2✍1
የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ‼️

ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።

ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።

ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን  ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍4
ከ46 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ተጠርጣሪ በኢንተርፖል ትብብር በቁጥጥር ሥር ዋለ

ከ46 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 12 የBYD Seagull ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በውክልና ለመሸጥ ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ከግል ተበዳይ አቶ ዮናስ ገብረመስቀል ጋር በነበረው የውክልና ስምምነት ተሽከርካሪዎቹን ከተረከበ በኋላ፣ የተገኘውን ገንዘብ ይዞ ከሀገር በመውጣት በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስ እና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ሲዘዋወር ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር ባደረገው የቅርብ ትብብር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት አድርጓል።

በዚህም መሠረት ተጠርጣሪው መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፤ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ነው የተገለጸው።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍8🤣3😢2😎1
ኡጋንዳ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድጋፏን እንደምትቀጥል  አረጋገጠች

የኡጋንዳዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ በምታደርገው የማስፋፋት ሥራ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ድጋፉ የተገለጸው የቤተክርስቲያኗ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከምክትል ፕሬዝዳንቷ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው። በስብሰባው ወቅት የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች የኡጋንዳ መንግሥት ለስደተኞች፣ ለሃይማኖት ነፃነትና ለቤተክርስቲያኗ እድገት ላደረገው እገዛ ምስጋና በማቅረብ የተጀመረው አጋርነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቷ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ለሀገርና ለሕዝብ ሰላም ያላቸውን ሚና አጉልተው አሳይተዋል። የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ምንም ዓይነት እንቅፋት ሳይገጥማቸው እንዲከናወኑና የቤተክርስቲያኗ የማስፋፋት ሥራዎች እንዲሳኩ መንግሥታቸው አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤72🤣12🙏5👍3👀1
በኢትዮጵያ በቀን 600 ሰዎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህይወታቸው ያልፋል ተባለ።

በአለምአቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፏ መምጣታቸው ተጠቁሟል።

ይህ የተባለው በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ  የሕሙማን ደህንነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።የጤና ሚኒስቴር ከአለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የሕሙማንን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ መድረኩን ያዘጋጀ ሲሆን እለቱም‹‹ ደህንነቱ የተጠበቀ ክብካቤ ለጤናማ ህይወት በሚል መሪ ቃል ›› በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ግርማ አሰፋ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ አራት ህይወታቸው ከሚያልፉ ሰዎች ሶስቱ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የተነሳ ህይወታቸውን ያጣሉ። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም ጎልቶ እንደሚታይ ተናግረው በቀን 600 የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ ህይወታቸው ያልፋል ነው ያሉት።ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የህክምና አገልግሎት ማዕቀፉ ተደራሽነትን ለማሳደግ ብዙ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ዶክተር ግርማ መረጃዎችን ጠቅሰው እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በደማቸው ውስጥ የደም ግፊት አለባቸው ተብለው የሚጠበቁ አዋቂዎች ከ11 እስከ 12 ሚሊዮን ይገመታሉ።እንደ የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የልብ፣ የደም ቧምባ በሽታ እና የካንሰር ህመም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል በዋነኛነት ተጠቃሽ ሲሆኑ የሚፈለገውን የጤና ግብ ለማሳካት የታካሚ ደህንነት እና እንክብካቤ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል።
በመሆኑም በዘንድሮው የህሙማን ደህንነት ቀን ለጉዳዮ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ ለመስራት ያግዛል ተብሏል።

@Addis_Reporter
❤14😢5👍2
«የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ የተገኙ ናቸው» እጅ የሰጡ ታጣቂዎች‼️
👉ምሽቱን ተጨማሪ 43 ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል።
ዛሬ በወልቃይት እጃቸውን የሰጡት የህወሓት ታጣቂዎች ለፀጥታ ኃይሎች መረጃ እየሰጡ ነው።

«ጠመንጃን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ የተገኙ ናቸው» ሲሉ ዛሬ እጃቸውን የሰጡት የህወሓት ታጣቂዎች ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በውጊያ የተያዙ ወይም የተማረኩ ሳይሆን፣ በራሳቸው ፈቃድ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እንደሰጡ ተረጋግጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16❤9🤪5
እጅ የሰጡት የእኛ አይደሉም-ህወሓት‼️
ሕወሓት በወልቃይት-ተከዜ መስመር እጃቸውን የሰጡትን ከ260 በላይ ታጣቂዎቹን «የእኛ አይደሉም» ሲል ካደ።

በወልቃይት፣ ተከዜ፣ አዲጎሹ እና ደደቢት መስመሮች በከባድ መሣሪያ የታገዘ ትንኮሳ ሲፈጽሙ የነበሩ ከ260 በላይ የሕወሓት አርሚ 17 አባላትና የመስመር አመራሮች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ሰጥተዋል። ይህን ተከትሎ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ እጃቸውን የሰጡት ተዋጊዎች የድርጅቱ አባላት አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ከአካባቢው የተገኙ የመረጃ ምንጮች እንደሚጠቅሙት፣ የታጣቂ ቡድኑ አባላት በከባድ መሣሪያ በመታገዝ በወልቃይት እና ተከዜ ኮሪደር አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ አድርገው ነበር። ሆኖም የመከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው ፈጣንና የተቀናጀ የመልስ ምት እንቅስቃሴው በቅጽበት ሊከሽፍ ችሏል። በዚህም የክፍለ-ጦሩ አዛዦች፣ የታችኛው ዕዝ አመራሮችና ከ260 በላይ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለመስጠት ሲገደዱ፣ የተቀሩት ደግሞ አቅጣጫ አጥተው መበታተናቸው ተረጋገጧል።

በግንባር የተመዘገበውን ወታደራዊ ሽንፈትና የዕዝ መበታተን ተከትሎ፣ አቶ አማኑኤል አሰፋ በሰጡት መግለጫ «በምዕራብ ትግራይ እጃቸውን የሰጡት ታጣቂዎች የእኛ አባል አይደሉም» ሲሉ አስተባብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍7🤔5🤣5
በትግራይ ክልል ለተመደባችሁ በሙሉ‼️
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ና ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የትምህርት ሂደታችሁ እንዳይስተጓጎልና ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል፣ በጠየቃችሁት መሰርት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እየገለጽን በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሚገለፅላቹህ ሲሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ባሉት ዩኒቨርስቲዎች መቀጠል የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍4