ከሰል እና እንጨት የሚጠቀሙ ሆቴል እና ሬስቶራንቶች ማብሰያቸውን በኤሌክትሪክ እንዲቀይሩ ሊደረግ እንደሆነ ተገለጸ
ከሰል እና እንጨት የሚጠቀሙ ሆቴል እና ሬስቶራንቶች ማብሰያቸውን በኤሌክትሪክ እንዲቀይሩ ሊደረግ እንደሆነ ተገለጸ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን የጤና ጉዳት ለመቀነስ ለደንበኞቻቸው የሚያቀርቡትን ምግብ በእንጨት እና በከሰል በሚሰራ ማብሰያ የሚያዘጋጁ ሆቴል እና ሬስቶራንቶች ኩሽናቸውን በኤሌክትሪክ ማብሰያ እንዲቀይሩ ሊገደዱ እንደሆነ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ገልጿል።
የባለሥልጣኑ የአየር ንብረት ለውጥ እና አማራጭ የኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ሰይድ አብደላ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፣ በቤት ውስጥ እና በንግድ ተቋማት የሚደረግ የከሰልና የእንጨት አጠቃቀም ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚያጋልጥ በካይ ጋዝ ይፈጥራል።
@Addis_Reporter

❤13👍4😡3🤔1
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን 24 ለሚጠጉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ የሰጠው የ12 ወራት የዕፎይታ ጊዜ መጠናቀቁን አስታወቀ
ከትምህርት ጥራት ማሻሻያ (ሪፎርም) በፊት ከነበሩት 375 የግል ተቋማት ውስጥ 290ዎቹ ለድጋሚ ምዝገባ ያመለከቱ ሲሆን፣ 85ቱ ራሳቸውን አግልለዋል። እስካሁንም ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሙሉ እውቅና (Accreditation) ማግኘት የቻሉት ሦስት ተቋማት፣ ሦስት ካምፓሶች እና 17 የትምህርት ፕሮግራሞች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በሚገኙ የግል ተቋማት ውስጥ 340,038 (አጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች 41 በመቶ) ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ።
የተቋማቱ ባለቤቶች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሆስፒታል መገንባትና የፒኤችዲ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ማሟላት አዳጋች መሆኑን በማንሳት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም፤ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አቢተው በትምህርት ጥራት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማይደረግ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

👍10❤8
AI የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል‼️
ከፍተኛ አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (#AI) ከሰው ልጅ አቅም በላይ ከደረሰና በቂ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጅ ህልውና ከባድ አደጋ ሊሆን እንደሚችል የAI ተመራማሪዎችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው።
#በአሜሪካዊው የAI ኩባንያ Anthropic የሚሰሩ ተመራማሪዎች ኃይለኛ AI በዚህ አስር ዓመት ውስጥ ለሰው ልጅ ህልውና አደጋ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።
ከኩባንያው የለቀቀው ጃኮብ ኮክሰን የተባለ ተመራማሪ፣ AI እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ/ሊገድል የሚችልበት #እድል እንዳለ ሲገልጽ፣ አንድ የአሁኑ የAnthropic ተመራማሪም የዚህ አደጋ ዕድል ከ10 በመቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል።
እንደ የAI ተመራማሪዎቹ ገለጻ፣ እጅግ የላቀ AI ከሰው ልጅ ጥቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲሰራ የሚያረጋግጥ በቂ #የደህንነት ዕቅድ አሁን የለም።
ይህ ስጋት #በብሪታንያ ፓርላማም ተነስቷል። የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዝ ብራውን እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ስቱዋርት ራሰል፣ እጅግ የላቀ AI ከኑክሌር መሣሪያዎች ጋር ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ የሚበልጥ ለሰው ልጅ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ሆኖም ሁሉም ባለሙያዎች በዚህ ላይ አይስማሙም። የAI እና ማኅበረሰብ ባለሙያ ፕሮፌሰር ኬት ዴቭሊን እንደሚሉት፣ " AI የሰው ልጅን #ሊያጠፋ ይችላል " የሚለው ትንበያ የተረጋገጠ እውነታ ሳይሆን የአደጋ ግምት ነው።
በአሁኑ ወቅት እጅግ የላቀ " ሱፐር ኢንተሊጀንት " AI እንደሌለን እና መቼ እንደሚኖርም በትክክል መተንበይ እንደማይቻል ገልጸዋል።
ባለሙያዎች ግን AI የሚያስከትለው አደጋ የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ መጥፋት #ብቻ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።
#የAI ስርዓቶች ለጎጂ ዓላማዎች መጠቀም፣ ሳይበር ጥቃት ማድረስ ወይም በሰው ስህተት አደገኛ ስርዓቶችን መቆጣጠር ከሚጠቀሱት አደጋዎች መካከል ናቸው።
በተጨማሪም የሐሰት መረጃ መስፋፋት፣ ሰው የሚሰራባቸውን ቦታዎች መተካት ፣ የግል መረጃ ደህንነት ስጋት እና AI ለማስኬድ የሚያስፈልገው ከፍተኛ ኃይል አሁኑ ወቅት እየታዩ ያሉ ችግሮችና ስጋቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
አሁን ላይ " AI የሰው ልጅን ያጠፋል ወይ ? " ከሚለው ጥያቄ ባሻገር፣ እጅግ ኃይለኛ AI ከተፈጠረ በኋላ በሰው ልጅ ጥቅም ላይ እንዲውል ምን ዓይነት ቁጥጥር፣ ሕግና የደህንነት ሥርዓት መዘርጋት አለበት ? የሚለው አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
ዘጋርዲያን

❤11👍5🤯2
"ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሠረተ-ቢስ ናቸው" - አቶ ክርስቲያን ታደለ
በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከእስር የተፈቱት አቶ ክርስቲያን ታደሰ በእስር ቆይታቸው ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ለቆሙ ግለሰቦችና ተቋማት ምስጋና አቀረቡ።
አቶ ክርስቲያን በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰራጩት የምስጋና መልዕክት፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ለቆሙ ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪ አሁን ላይ የጤናቸውን ሁኔታ እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸው " ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች መሠረተ-ቢስ " መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የጤናቸው ሁኔታ ሲሻሻል በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን እውነታ በዝርዝር ለሕዝብ እንደሚያሳውቁ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገልጸዋል።

❤23👍6😢1
ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት‼️
በራያ ኮረም ትናንት መስከረም 2/2019 ዓ.ም ከተፈፀመው የድሮን ጥቃት በተጨማሪ ዛሬም ሁለት ጊዜ ተፈፅሟል።
ጥቃቱ ዛሬ ረፋድ ላይ በራያ ኮረም በበሬ ገበያ አከባቢ #መስኮተ_ብርሀን ትምህርት ቤት ላይ የተፈፀመ ሲሆን የህወሓት አንድ ዙ-23 የጫነች #ፓትሮል እና የተለያዩ ተተኳሽ የጫነች አንድ FSR መኪና በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

👍9❤7🤔2👌2🤪2🍾1
ቶጎ አፍሪካ የኢትዮጵያን የቀን መቆጠሪያ መጠቀም እንዳለባት አሳስባለች።
ቶጎ የአፍሪካ ሀገራት የአውሮፓውያንን የቀኝ ግዛት ዘመን የቀን መቆጠሪያ በማስወገድ የራሳቸውን አህጉራዊ ማንነት የሚያንፀባርቁበት አዲስ ዓመት እና በዓላት ሊኖሯቸው እንደሚገባ ጥሪ አቀረበች።
የምዕራባውያንን የቀኝ ግዛት ዘመን የቀን መቆጠሪያዎችን በማስወገድ አፍሪካውያን የራሳቸውን አህጉራዊ ማንነትና ታሪክ የሚያንፀባርቅ የጊዜ አቆጣጠር ሊኖራቸው እንደሚገባ ቶጎ ጥሪ አቅርባለች። ቶጎ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር አህጉራዊ አንድነትን የሚያጎለብት አዲስ ዓመት እንዲታወጅ የጠየቀች ሲሆን፣ ለዚህም መፍትሔው መላው አፍሪካውያን የራሳቸውን ማንነት ለመመለስ የኢትዮጵያን የቀን መቆጠሪያ (ካላንደር) መጠቀም እንደሆነ አሳስባለች።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ካላንደር የነፃነት፣ የራሷን የቻለች ሀገር እና የጥንታዊ ሥልጣኔ ምልክት ተደርጎ ትልቅ አድናቆትና ክብር እየተቸረው ይገኛል። ሆኖም ግን ይህ የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን የጊዜ አቆጣጠር እንደ አህጉራዊ ኩራትና መፍትሔ አድርገው በሚመለከቱበት በአሁኑ ወቅት፣ በሀገር ውስጥ የካላንደር ለውጥ እንዲደረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ፍላጎቶች በብዙዎች ዘንድ አላስፈላጊና የሀገርን ታሪካዊ ቅርስ የሚሸረሽር ተደርጎ በመወሰዱ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።

❤98👍17🤝6👀4
የዳኞች ኮሚቴ ዩናይትድን ይቅርታ ጠየቀ !
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዳኞች ኮሚቴ ኤርሊንግ ሀላንድ ያስቆጠረው ግብ ከጨዋታ ውጪ እንደነበር ገለፀ።
ኮሚቴው ቫር ስህተት መስራቱን እና ጎሉ መሻር እንደነበረበት በይፋ አስታውቋል።
የዳኞች ኮሚቴው ለተፈጠረው ስህተት ማንችስተር ዩናይትድ የይቅርታ ደብዳቤ መላኩን አያይዞ ገልጿል።
የኤርሊንግ ሀላንድ ግብ ከጨዋታ ውጪ መሆኑን የሜዳ ላይ ዳኞች ቢገልፁም ቫር ውሳኔውን ሽሮ ማፅደቁ አይዘነጋም።

🤣50😢8❤5🤔4👍2🥱1
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በታዋቂው "ታይም" መጽሔት የፊት ገጽ ላይ ሽፋን አገኘ
የዓለማችን ግዙፍና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የሕትመት ውጤቶች አንዱ የሆነው «ታይም» መጽሔት፣ የመስከረም 2026 ዕትሙን የፊት ገጽ ሙሉ በሙሉ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሰጥቷል።
መጽሔቱ በሽፋን ገጹ ላይ «አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል» (The Power to Unite Africa) የሚል ታላቅ ዋና ርዕስ በመስጠት፣ ግድቡ በአህጉሪቱ ላይ እያሳደረ ያለውን መልካም ተፅዕኖ በስፋት ዳስሷል።
«ታይም» መጽሔት ባወጣው ሰፊ ዘገባ፣ የሕዳሴው ግድብ ለአህጉራዊ ትስስርና ለምስራቅ አፍሪካ አዲሱ የኢኮኖሚ ውህደት ምዕራፍ እየተጫወተ ያለውን ከፍተኛ ሚና በምሳሌነት ጠቅሷል።
ግድቡ የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ፣ ለአጠቃላይ የአፍሪካ አህጉር የቀጣናው ትስስርና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዋነኛ መሠረት መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
በተጨማሪም፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በምስራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የኃይልና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ በማጠናከር፣ በአህጉሪቱ አዲስ የትብብር፣ የልማትና የእድገት ምዕራፍ መክፈቱን መጽሔቱ በዕትሙ በዝርዝር አስፍሯል።
ግድቡ በአፍሪካውያን የራሳቸው ካፒታልና ጽናት የተገነባ መሆኑ አህጉሪቱ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን አቅም እንዳላት ያሳየበት ትልቅ ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።

👍18❤13🤝2
"ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣ "ግዙፍ እና እያደገ ያለ ኢኮኖሚ እንደመሆናችን መጠን፣ አስተማማኝ እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ተደራሽነት ያስፈልገናል" ብለዋል

❤24🤣11👍3🤪3🥱2😢1
ውሃ
ውሃ ለሕይወት አስፈላጊ ነው። በርካታ ዓለም አቀፍ መመሪያዎች አንድ ሴት በቀን ሁለት ሊትር፣ ወንድ ደግሞ 2.5 ሊትር ውሃ ቢጠጣ ለጤና መልካም መሆኑን ይመክራሉ።
ብዙዎቻችን ፕሮቲን፣ ቫይታሚን፣ ካርቦሃይድሬት እና ፋይበር ላይ እናተኩራለን። ውሃን በሕይወታችን ውስጥ እንደ ጠቃሚ ንጥረ ነገር አድርገን አናስብም።
ውሃ በሁሉም የሰውነታችን ተግባራት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የሃርቫርድ የሕክምና ትምህርት ቤት የውሃን አንዳንድ ቁልፍ ሚናዎች እንደሚከተለው ዘርዝሯል።
በሰውነታችን ውስጥ የውሃ ወሳኝ ሚና፤
• ንጥረ-ነገሮችን እና ኦክስጂንን ወደ ሴሎች ማጓጓዝ
• ከሽንት ከረጢት ውስጥ ባክቴሪያዎችን ማስወገድ
• የምግብ መፈጨትን መርዳት
• የሆድ ድርቀትን መከላከል
• የደም ግፊትን መደበኛ ማድረግ
• መገጣጠሚያዎችን ማለስለስ
• የአካል ብልቶችን እና ጡንቻዎችን መከላከል
• የሰውነት ሙቀትን መቆጣጠር
• የኤሌክትሮላይት (ሶዲየም) ሚዛንን መጠበቅ

👍19❤12
የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)
2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)
በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ
1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%)
4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ሆኗል።

❤12👍4
ስልክና እና ኢንተርኔት ለማቋረጥ‼️
ህወሓት በመላው ትግራይ ክልል የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የኢትዮ ቴሌኮም ትራንስፈርመሮችን ማንሳት ተጀምሯል ።
እስካሁን ድረስ በኤዳጋ ሃሙስ፣ አቢ አዲ፣ ሀገረ ሰላም፣ ራማ እና ዛጊር ጀምረዋል።
በራማ የሚገኙ የቴሌ ጠባቂዎች ትራንስፎርመሩን ለማስወገድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በቁጥጥር ስር ለማዋል የታጠቁ ሰዎችን እንዳሰማሩ ታውቋል።

😡27❤16🤔7👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሪዎቹ ወደ ስብሰባው በአንድ መኪና!
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ በህንድ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ በአንድ መኪና ሲጓዙ ታይተዋል።
መኪናው የፕሬዝዳንት ፑቲን ሲሆን፣ ፑቲን ወደ ውጭ ሀገራት በሚያደርጉት ጉዞ የራሳቸውን የፕሬዝዳንት መኪና ይዘው መጓዛቸው የተለመደ ነው።
በተለምዶም የፑቲን መኪና እጅግ ጥብቅ የደህንነት ፕሮቶኮል ያለው በመሆኑ፣ ሌላ መሪ አብሯቸው ሲጓዝ ማየት ብዙ ጊዜ የሚታይ ነገር አይደለም።
በዚህ ጊዜ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፑቲን ጋር በአንድ መኪና ወደ ስብሰባው ሲጓዙ መታየታቸው ትኩረት የሚስብ ነው።
ይህን እንደ ተራ የትራንስፖርት ሁኔታ ብቻ ማየት አይገባም፤ በዲፕሎማሲ ዓለም እንዲህ ያሉ ምስሎች ብዙ ጊዜ የመሪዎችን ቅርበት፣ የግንኙነት ደረጃ እና የጋራ ፖለቲካዊ መልዕክት የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ።
ፑቲን የሚጠቀሙት የፕሬዝዳንት መኪና Aurus Senat የተባለ በሩሲያ የተሰራ የቅንጦትና ከፍተኛ ጥበቃ ያለው ሊሙዚን ነው። የፕሬዝዳንቱ ልዩ ስሪት የታጠቀ (armored) ሲሆን፣ የሩሲያ ፕሬዝዳንታዊ ኮንቮይ ዋና አካል ነው። ፑቲንም በአንዳንድ የውጭ ሀገር ጉዞዎቻቸው ይህንን መኪና ይጠቀማሉ።
በዚህ ጊዜ ግን ዐቢይ አህመድ ከፑቲን ጋር በዚሁ መኪና ውስጥ አብረው ሲጓዙ መታየታቸው ትኩረት ስቧል። በተለይ የፕሬዝዳንታዊ መኪናውን ጥብቅ የደህንነት አሠራር ስንመለከት፣ ሁለቱ መሪዎች በአንድ መኪና መጓዛቸው በራሱ የሚያስተውል ነው።

🤣44❤22👍14🥱1😎1
የኤርትራ ክስ‼️
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአፍሪካ “የወደብ ኢምፔሪያሊዝም” እያካሄደች ነው - ኤርትራ‼️
ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር አካባቢ ስትራቴጂካዊ ወደቦች እና የጦር ኃይል ተፅዕኖን ለመጫን በሚደረገው ፉክክር መካከል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአፍሪካ “የወደብ ኢምፔሪያሊዝም” አካሄድን እየተከተለች ነው ስትል ከሳለች።
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኦስማን ሳሊህ ከሚድል ኢስት አይ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ ኤምሬትስ በቀጣናው ባሉ ወደቦች ላይ የምታደርገውን እየሰፋ የመጣ የባለቤትነት እና አስተዳደር እንቅስቃሴ ጥያቄ ውስጥ በማስገባት፣ የአፍሪካ ሀገራት አቡ ዳቢ በተለያዩ አካባቢዎች ለምን የወደብ መሠረተ-ልማቶችን እንደምትይዝ መጠየቅ አለባቸው ብለዋል።
ሚኒስትር ኦስማን ሳሊህ ለ MEE በሰጡት አስተያየት፣ “የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቀጣናው በሁሉም ቦታ የወደብ መሠረተ-ልማቶች አሏት፤ የአፍሪካ ሀገራት ግን ‘ለምን?’ ብለው መጠየቅ አለባቸው” ያሉ ሲሆን፤ “ግቡ ኢኮኖሚያዊ ብቻ ነውን? አይደለም” ሲሉ አብራርተዋል።
እንደ ሚኒስትር ኦስማን ገለጻ፤ ኤርትራ እ.ኤ.አ በ2016 ገደማ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዳህላክ ደሴቶች ላይ የጦር ሠፈር ለመሥራት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች።
የኤርትራ ባለሥልጣናት በተለይም ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊላንድ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ ቀንድ እየታየ ነው ያሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የእስራኤል ግንኙነት መጠናከር አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል።

❤21👍8🤷♂1🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Update‼️
በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለመዛወር የሚፈልጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እየተመዘገቡ መሆኑን አዩዘሀበሻ መዘገቡ ይታወሳል።
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ተገኝተው ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ነጋ ጋር ውይይት ተደርጓል።
ተማሪዎቹ ምዝገባ አካሂደው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚመደቡ ፕሮፌሰሩ ገልፃ አድርገውላቸዋል።

❤7👍3🤔1
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ የማዕድን ኩባንያዎችን አስጠነቀቀ
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) በኦሮሚያ የማዕድን ዘርፍ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች የአካባቢው ማህበረሰቦች በማዕድን ፕሮጀክቶች ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንዳለባቸው አስጠንቅቋል።
በቅርቡ በቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ላይ የደረሰው የሰው ሕይወት የጠፋበት አደጋ ያቀረባቸውን መስፈርቶች አለመቀበል የሚያስከትለው ውጤት ማሳያ እንደሆነም ጠቁሟል።
በኦሮሚያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች በላከው “የአስቸኳይ ጊዜ መስፈርት ማስታወቂያ”፣ በክልሉ ውስጥ ለመስራት የሚፈልጉ ኩባንያዎች ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር ቀጥታ ተሳትፏቸው እና ተጠቃሚነታቸው በሚረጋገጥበት ሁኔታ ላይ “ጥልቅ እና ግልጽ ውይይቶችን” ማድረግ እንዳለባቸው ኦነሰ ገልጿል።
ቡድኑ እንደነዚህ ያሉ አሰራሮች ሳይዘረጉ እና ስምምነት ሳይደረግባቸው ምንም አይነት የማዕድን ማውጣት እንቅስቃሴ መቀጠል የለበትም ብሏል።
በተጨማሪም ኩባንያዎች በሥራ ሂደታቸው በሙሉ ተረጋግጠው የሚፈጸሙ የአካባቢ ጥበቃ መስፈርቶችን እንዲተገብሩና አስከብረው እንዲቀጥሉ የጠየቀ ሲሆን፣ መመዘኛዎቹን ማክበር “ድርድር የማይደረግበት” እንደሆነ ገልጿል።

🤣22❤18👍7🤪2🤔1🤯1😢1😎1😡1
በማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግር ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በሐዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አቶ አንሺሶ ካጢሶ ሐሰተኛ የፌስቡክ ገጽ በመጠቀም በግል ተበዳዮች ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ጉዳት ማድረሱ ተረጋግጧል።
ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1181/2012 አንቀጽ 4፣ 5 እና 7 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት ተደራራቢ 13 የወንጀል ክሶችን መስርቶ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የሆሳዕና ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ በመሆኑ በከባድ ወንጀል መድቦታል።
ተከሳሹ በተከሰሰባቸው 13 ተደራራቢ የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።እያንዳንዱ ክስ እስከ 1 ዓመት ከ6 ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየትን መርምሯል።
ተከሳሹ ካቀረባቸው 7 የቅጣት ማቅለያ ምክኒያቶች ከዚህ ቀደም በወንጀል ተከሶ አለመቀጣቱ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የሦስት ልጆች አባት መሆኑ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ ይሳተፍ እንደነበር በማስረጃ በመረጋገጡ ሶስቱን ማቅለያዎች ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን ያርማል፣ ሌሎችንም ያስተምራል በሚል ባሳለፈው ውሳኔ ተከሳሹ በአምስት ዓመት ቀላል እስራት እና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

❤17👍11🤣10🤯2😢2
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ!
በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት እንዲመደቡ ተወስኗል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)።
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው መፍትሔ ከጠየቁ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ÷ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቅባቸው ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ መወሰኑን ገልጸዋል።
ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ማተኮር ያለባቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ መሆኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ሀገራቸውን የሚረከቡ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።
ሀገር ማጽናት የሚቻለው የዛሬው ትውልድ ለነገው ትውልድ ማሰብ ሲጀምር ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ያለውን ሁኔታ በመሸሽ ከትግራይ ክልል የወጡ ተማሪዎች በሰላም የመኖርና የመማር መብት እንዳላቸው አስገንዝበዋል።
በመሆኑም እነዚህን የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች በተለያየ መንገድ ማስተናገድና ትምህርታቸውን ያለመስተጓጎል እንዲቀጥሉ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ስለሆነም ተማሪዎች ለምዝገባ በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የበየነ መረብ (ኦንላይን) መተግበሪያ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
በምዝገባው ወቅትም ተማሪዎች ከዚህ በፊት ይማሩበት የነበረውን ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት ዘመናቸውን ና የሚማሩበትን የትምህርት መርሐ ግብር በመግለጽ ባሉበት ቦታ ሆነው የዝውውር ፎርሙን በአጭር ግዜ እንዲሞሉ ማሳሰባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

❤6👍3🤔2🤣1