አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

የ2019 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት ይተኮሳል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ነገ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ/ም የሚከበረውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ፦
- በሸራተን አዲስ ሆቴል፣
- በሞናርክ ሆቴል
- በበ#ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ በዋዜማው ከሌሊቱ 6:00 - 6:15 ለ15 ደቂቃ ያህል ርችት እንደሚተኮስ ገልጿል፡፡

" ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው " ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍6🤪6
🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼
🍬🎉HAPPY NEW YEAR 🎉🍬
ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ❤️🙏

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17❤7
Academic Calendar for HEIs (2019 E) FINAL.pdf
1.8 MB
የ 2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር!

👉Exit Exam --ሰኔ 3--13/2019

👉Grade 12 Exam -- ሰኔ 28--ሐምሌ 9/2019

የትምህርት  ሚንስትር  አጠቃላይ  የአመት ካላንደር ከላይ ተያይዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍5❤4🤣1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ስራ እንዳይቀማ በማለት ሮቦቶች ተቃውሞ አሰሙ

​ሰዎች በቴክኖሎጂ ምክንያት ስራ አጥ እንዳይሆኑ እና የስራ ዋስትናቸው እንዲጠበቅ ለማስጠንቀቅ 30 የሚጠጉ ሮቦቶች በፖላንድ ዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስቴር ቢሮ ፊት ለፊት ተቃውሞ አሰሙ።

​ሰልፉን ያዘጋጁት አክቲቪስቶች፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ማሽኖች የሰውን ስራ ሊወስዱ የሚችሉበትን አደጋ በመቃወም መንግስት ጥብቅ የቁጥጥር ህጎችን እንዲያወጣ ጥሪ አቅርበዋል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪25❤12🤔10🤣7👍4😱2
#በፌዴራል_መንግስት እና #በትግራይ ክልል መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የተመሰረተዉ #ጥምረት«ወደ ኋላ የማይመለስ» መሆኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገለፁ

አዲስ አበባ — በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ያለው ውጥረት እና አዲስ ግጭት በበረታበት ወቅት፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ከሌሎች የፖለቲካ እና የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የተመሰረተው ጥምረት መዋቅራዊ እና «ወደ ኋላ የማይመለስ» መሆኑን የራሱ አመራር፣ ዕቅድ እና የተፈረመ ስምምነት እንዳለዉ መናገራቸውን ወይን ሚዲያ ዘግቧል።

ከወይን ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሕወሓት ሊቀመንበር እና የትግራይ ፕሬዚዳንት የሆኑት ደብረጽዮን እንደገለጹት፣ ጥምረቱ ከመደበኛ ያልሆነ ትብብር አልፎ በተዘረጋ መዋቅር ሥር እየሰራ እንደሚገኝ እና ተጨማሪ ኃይሎች ይቀላቀሉታል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት ይፋ እንደሚደረጉ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍8🤣7🕊1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፑቲን ከብሪክስ ጉባኤ ጎንዮሽ  እንደሚገናኙ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቭላድሚር ፑቲን በህንድ ከሚካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ነገ መስከረም 2 ውይይት እንደሚያካሂዱ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ህንድ መግባታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኒው ዴልሂ ሲደርሱ በከፍተኛ የህንድ ባለሥልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪14👍10❤5🤔1🕊1
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም ለመልሶ ቅበላ ብቁ የሆናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን 👇
ሰኞ መስከረም 11/2019 ዓ.ም

የትምህርት ክፍል ምርጫ 👇
መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም (የ1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች)

የምዝገባ ቀናት 👇
መስከረም 12 እና 13/2019 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀምርበት ቀን 👇
ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም.

በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሳችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል በመገኘት የምዝገባ ሂደታችሁን እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍5
በአሶሳ ከተማ ታግቶ የነበረው ህፃን ከአጋቹ እጅ ነፃ ወጣ

መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም
በአሶሳ ከተማ ተጠልፎ የተወሰደውን የ5 ዓመት ህፃን ልጅ ይዞ ሲያሸሽ የነበረ ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ አክመል ሸምሲ መሃመድ የተባለው ተጠርጣሪ መርሲሞይ ደረጀ የተባለውን ህፃን ከቤተሰቦቹ እይታ ውጭ በማድረግ ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማሸሽ ሲንቀሳቀስ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።

ድርጊቱ ወዲያውኑ ለፀጥታ አካላት በጥቆማ በመድረሱ በተደረገው የተቀናጀና ጥብቅ የክትትል ስራ ህፃኑን በሰላም ማዳን የተቻለ ሲሆን ተጠርጣሪውም በፖሊስ እጅ ወድቋል።

የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ሀሩን ሄረላም እንደገለጹት፤ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተቀናጀ የጋራ ጥረት ወንጀሉን ማክሸፍ ቢቻልም፣ ህፃናት ለእንዲህ አይነት ጥቃቶችና አደጋዎች እንዳይጋለጡ ወላጆችና አሳዳጊዎች ዘወትር የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮማንደሩ አክለውም ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር ለማዋል ላቀረቡት ፈጣን ጥቆማና ላደረጉት ከፍተኛ አጋርነት ህብረተሰቡን አመስግነው፤ መሰል ህገ-ወጥ እና ወንጀል አድራጊ አካላትን አጋልጦ በመስጠት በኩል ህዝቡ የሚያደርገውን አወንታዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

Via የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኒውዮርክ መንትያ ህንፃዎች በ 2,977 ድሮኖች ሰማይ ላይ ዳግም ተፈጠሩ

​የመስከረም 1 (ሴፕቴምበር 11) አሰቃቂ የሽብር ጥቃት 25ኛ ዓመት የምስረታ መዘከሪያን በማስመልከት፣ ትናንት በኒውዮርክ የባህር ወሽመጥ ላይ 2,977 በራሪ ድሮኖችን በመጠቀም አስደናቂ ትርኢት ተቀርቧል።

"2,977 Lights Over New York Harbor" በተሰኘው በዚህ ዝግጅት፣ እያንዳንዱ ድሮን በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን የሚወክል ሲሆን፣ የዓለም የንግድ ማዕከል የነበሩትን መንትያ ህንፃዎች ትክክለኛ ቅርፅ እና መጠን በምሽቱ ሰማይ ላይ መልሰው አሳይተዋል።

​በስካይ ኤሌመንትስ ኩባንያ የቀረበው ይህ ጥበባዊ ስራ ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ከአደጋ ጊዜ ደራሽ ሰራተኞች ጋር በመተባበር የተከናወነ ነው።

በተጨማሪም በግራውንድ ዚሮ በተካሄደው የስም ጥሪ ስነ-ስርዓት ላይ በጥቃቱ ምክንያት በደረሰ የጤና እክል ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መታሰቢያ የሚሆን ሰባተኛው የህሊና ጸሎት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22🤪8👍4🥰1🤔1😱1😢1
ፈሶትን አያዙ: የተከማቸ ፈስ በአፍ ሊወጣ ይችላል

​አንድ ሰው የሆድ አየርን (ፈስን) ከልክ በላይ ይዞ ለመቆየት ሲሞክር አየሩ በጨጓራና አንጀት ውስጥ ታፍኖ አይቀርም።

በሰውነት ውስጣዊ መዋቅር ምክንያት አየሩ ወደ ደም ዝውውር ስርአት ውስጥ እንደገና በመመጠቅ በመጨረሻም በአፍ በሚወጣው ትንፋሽ በኩል ሊወጣ እንደሚችል የህክምና ጥናቶች ያሳያሉ።

​ይህ ሂደት የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ የታቀበው ጋዝ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ወደ አንጀት ግድግዳ የደም ስሮች በመግባት ነው።

ደም ወደ ሳንባ በሚሰራጭበት ወቅት እነዚህ ጋዞች ከደም ወጥተው ወደ ሳንባ አየር ከረጢቶች ስለሚሸጋገሩ፣ ግለሰቡ በሚተነፍስበት ጊዜ አየሩ በአፍ በኩል ይወጣል።

​ምንም እንኳን ይህ አጋጣሚ ለብዙዎች እንግዳና የሚያስቅ ቢመስልም፣ በተፈጥሮ የሚፈጠርን የሰውነት ጋዝ አፍኖ መያዝ የሆድ እብጠት፣ ህመም እና የአንጀት ምቾት ማጣት ስለሚያስከትል ተፈጥሯዊ ሂደቶችን አለመግታት ይመረጣል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙉19❤8🤪7🤣4👍3🤔1👌1🤡1👀1
የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ‼

በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ምንም አይነት ወንጀል ስላልፈጸሙ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲፈቱ የቀረበላቸውን ሀሳብ አለመቀበላቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ወይም ሲፒጄ አስታውቋል።

ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ ሲሆኑ በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2023 የተያዙ ናቸው። ከዚያም በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰው የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ እንደገለጹት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች ታሳሪዎች በመለየትና በማስፈራራት መንግስት ያዘጋጀውን የይቅርታ ወረቀት ፈርመው ከእስር እንዲወጡ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ስራቸውን እንዲተዉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር። 

ነገር ግን ጋዜጠኞቹ ምንም ያጠፉት ጥፋት በሌለበት ሁኔታ ራሳቸውን እንደ ወንጀለኛ አድርገው መቁጠርና ማመንን ባለመቀበል የቀረበላቸውን ጥያቄ ፈፅመው ውድቅ አድርገውታል ብለዋል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞቹን ለረጅም ጊዜ ካሰሩ በኋላ በፍርድ ቤት ማረጋገጥ ያልቻሉትን ወንጀል በግዴታ አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ የሚያደርጉትን አካሄድ ኮንነዋል።

አስተባባሪዋ አክለውም በጋዜጠኞቹ ላይ የሚፈጸመው ያልተገባ ጫና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የተመሰረተባቸው ክስ ተነስቶ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንዲሁም ሙያቸውን በነጻነት ማከናወን እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤32👍4🤔1🤣1
የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የልደት ቀናቸውን ብሔራዊ የሕዝብ በዓል አድርገው ሰየሙ

የዚምባብዌ መንግሥት የፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የልደት ቀን የሆነውን መስከረም 15 (ሴፕቴምበር 15) በየዓመቱ የሚከበር ብሔራዊ የሕዝብ በዓል አድርጎ ማወጁ ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ አስነሳ። “ሙንሁሙታፓ ቀን” በሚል የተሰየመው ይህ በዓል በሕግ ማዕቀፍ የወጣ ቢሆንም፣ ተቃዋሚዎች ግን እርምጃውን የፕሬዚዳንቱን ግላዊ ስልጣንና ዝና ለማገንነን የተደረገ ውሳኔ ነው ብለውታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣30❤7👍3😢2🙉2👀1🤪1🙊1
የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት መስከረም 2/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡10 በራያ_ኮረም ከተማ ዝናቡ ማልዴይ በሚባል ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
ጥቃቱ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ባህርዛፍ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ መድፎች እና ዙ-23 መሳሪያዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20👍8👌3🕊3🤪3🏆2😢1🎉1🌚1🤝1
እየተዘጋጀን ነው-የህወሓት ጄኔራል‼️
የፌዴራል መንግሥቱ እያደረገ ያለውን የጦርነት ትንኮሳና የድሮን ድብደባ በትግስት ይዘን ስራችን እያከናውን የምንገኘው ሲሉ የህወሓት ወታደራዊ መሪ የሆኑት ጄ/ ፍስሃ ማንጁስ ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂ/ድሮን/ጦርነት አያስቆምም ብለዋል።
ለህልውናችን ብለን የምናካሄደውን ትግል ደግሞ አሸንፈን ለመውጣት ሁሉንም ነገር በማስተካከል እየተዘጋጀን ነው ያለነው ብለዋል።

ሁሉም ነገር አንዳለቀ ደግሞ ያኔ የሚሆነው ይሆናል።
አንደምናሸንፍም ኧርግጠኞች ነን ሲሉ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤24🤣21👍8🫡3🤪2🤷‍♂1🕊1
ሚስት የባለቤቷን ብልት በጥርሷ
ነክሳ ከባድ ጉዳት አደረሰች!

በዚምባብዌ ሃራሬ ከተማ ከባለቤቷ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የተናደደችው የ29 ዓመቷ ሻርሊን ሩቴንዶ ሙኔንጋ፣ የ33 ዓመቱን ባለቤቷን ብልት በመንከስ ከባድ ጉዳት ማድረሷን የዚምባብዌው "The Herald" ጋዜጣ ዘገበ።

የጋዜጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ይህ አሰቃቂ ድርጊት የተፈጸመው ባለቤቷ ከጋብቻ ውጭ ግንኙነት አለው በሚል ጥርጣሬ በተነሳ ከፍተኛ ጭቅጭቅና ግብግብ ወቅት ነው።

በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰደው ባለቤቱ አሁን ላይ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል። ጥፋተኛዋ ባለቤት በሃራሬ ማጂስትሬት ፍርድ ቤት ቀርባ በከባድ የአካል ጉዳት ወንጀል ክስ የተመሰረተባት ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ  በእስር እንድትቆይ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣45🙉14❤7👍4😎3🙈2😢1😈1👀1🤪1
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው «የኢትዮጵያው ገዢ የብልጽግና ፓርቲ የአፍሪካ ቀንድን አለመረጋጋት ውስጥ ለመዝፈቅ በንቃት እየሰራ ነው» ሲል ከሷል።

«ኢትዮጵያ በማያቋርጥ ሁኔታ በኤርትራ ላይ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመች ነው» ያለው መግለጫው ኤርትራ ግን በስትራተጂያዊ ትዕግስቷ ጸንታለች» ብሏል።በተጨማሪም ኢትዮጵያ «ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በመጣስ በኤርትራ ላይ ግልጽ የሆነ የሥርዓት ለውጥ አጀንዳ የያዙ ቅጥረኛ ቡድኖችን በማስተናገድ፣ በማሰልጠንና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ተጠምዳለች» ሲልም አክሏል መግለጫው።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ስለኤርትራው ክስ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤23🤪8👍7😎3🤷‍♂2🤣2🤡1
በፍኖተ ሰላም በ80 ሺህ ብር በተገዛ በሬ ውስጥ 13.7 ግራም ወርቅ ተገኘ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ 03 ቀበሌ ለአዲስ ዓመት በዓል ማጠቃለያ በተደረገ የከብት እርድ ወቅት፡ በበሬው ሆድ ውስጥ የወርቅ ቁራጭ መገኘቱ ተገለጸ።

አቶ አንዱአምላክ , አቶ ውለታው እና አቶ በፍትህ ከተባሉ አባላት ጋር በመሆን ለበዓል በ80,000 ብር የተገዛው በሬ ታርዶ በውስጡ የተገኘው ወርቅ በመጀመሪያው የወርቅ ሚዛን የመዘኑት ሰዎች 14 ግራም መሆኑን የገለጹ ሲሆን፡ ለሁለተኛ ጊዜ በሌላ ወርቅ ቤት ሲመዘን ደግሞ 13.7 ግራም ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ያልተጠበቀ ክስተት በከተማው ነዋሪዎችና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ እና ትኩረት ሳቢ አጋጣሚ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤪6👍3🙉3🤷‍♂2👀1
የአፍሪካ ሰማይን ያስደመመችው ኢትዮጵያ!

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን እና እጅግ ዘመናዊ የሆነውን "A350-1000" ሞዴል አውሮፕላን በማንቀሳቀስ ብቸኛዋ ሀገር በመሆን  ታሪክ ሰርታለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን ይህን ግዙፍ አውሮፕላን በህዳር 2024 የተረከበ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት እያንዳንዳቸው እስከ 395 ተሳፋሪዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው አራት A350-1000 አውሮፕላኖችን በስራ ላይ አውሏል።

እጅግ ለረጅም ርቀት በረራዎች የተነደፈው እና ወደ 15,557 ኪሎ ሜትር የመብረር አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን፣ ከቀድሞዎቹ ሞዴሎች ጋር ሲነጻጸር የላቀ ነዳጅ ቆጣቢነት አለው። ለኢትዮጵያ፣ ይህ ስኬት ሀገሪቱ በአፍሪካ ለረጅም ርቀት የአየር ትራንስፖርት ዋና ማዕከል ያላትን ቦታ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም አህጉሪቱን ከመላው ዓለም መዳረሻዎች ጋር በማገናኘት ላይ እንደሚገኝ አፍሪካ ግሎባል ኒውስ ዘግቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤41👍12
የሁቲ ግስጋሴና ቀይ ባህር

ሁቲ የየመንን የቀይ ባህር ዳርቻ ሙሉ በሙሉ በእጁ አስገብቷል።

የመንግስት ኃይሎች ጋር እየተፋለመ የሚገኘው ሁቲ ወሳኝ ደሴቶችን በመያዝ የበብ ኤል-መንደብን መተላለፊያም ዘግቷል።

በሳውዲ ዐረቢያ የሚደገፈው የኤደኑ መንግስት፤ በኢራን መሳሪያ የሚቀርብለትን ኃይል ለመቋቋም ጥረት ላይ ነው ተብሏል።

ጥቃቱና የተፈጠረው ቀውስ ፤ በቀይ ባህር ዳርቻ የሚገኙ ሀገራት ሁቲዎችን መቆጣጠር ሊያዳግታቸው እንደሚችል ማሳያም ሆኗል።

የቀይ ባህር ፖለቲካ እና ወታደራዊ አሰላለፍ አዲስ ቅርፅ እየያዘ ካልመጣ ከህንድ ውቅያኖስ ኤደን ባህረ ሰላጤ -በብ ኤል -መንደብ ሰርጥ እስከ ሰሜናዊ ቀይ ባህር ጫፍ የግብፁ -ስዊዝ ቦይ ድረስ የኢኮኖሚ ደህንነት ስጋት ውስጥ ይገባል።

እንደ ሳውዲ ዐረቢያ ያሉ ሀገራት ችግሩ ከአሁኑ የጀመራቸው ሲሆን፤ ከያንቡ ወደብ በበብ ኤል-መንደብ በኩል ነዳጇን ማሳለፍ አልቻለችም።

በተለይም የሳውዲው ኢስት-ዌስት የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ከኢራቅ በተነሳ ሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱን ተከትሎ ለቅድመ ጥንቃቄ በሚል መዝጋቷ በዓለም የነዳጅ ፖለቲካና ዋጋ ላይ አደጋ ይዞ ይመጣል።

ሁቲዎች ፕሪም ደሴትን መያዛቸውን ተከትሎ በቀይ ባህር አካባቢ የራሳቸውን የደህንነት ኃይል ያቋቋሙ ሀገራት አቅምም እየተፈተነ ነው።

ይህም በራሳቸው ትዕዛዝ ስር ሆኖ መንቀሳቀስን ይጠይቃልና አካባቢው ላይ አዲስ አሰላለፍ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቋሚ ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞች።

አልጀዚራ 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18👍5😢2👀1