አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የዋጋ ግሽበቱ 15.1 በመቶ ሆኗል

የነሐሴ 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ። ከባለፈው ዓመት ነሐሴ 2017 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ1.5 በመቶ ጭማሪ ቢኖረውም፣ ከሐምሌ 2018 ዓ.ም የ15.3 በመቶ ጋር ሲታይ ግን መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።

በወቅቱ የተመዘገበው የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ግሽበት 14.9 በመቶ ደርሷል። በምግብ ምድብ ውስጥ ስኳር፣ ማር እና ቸኮሌት (38.3 በመቶ)፣ ስጋ (22.6 በመቶ)፣ እንዲሁም ፍራፍሬ (19.1 በመቶ) ከፍተኛውን ጭማሪ አሳይተዋል።

ምግብ ነክ ባልሆኑ ዘርፎች ደግሞ አጠቃላይ ግሽበቱ 15.4 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ምድብ ውስጥ የትምህርት አገልግሎቶች (25.3 በመቶ)፣ ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች (19.3 በመቶ)፣ እንዲሁም የአልኮል መጠጦችና ትምባሆ (16.0 በመቶ) ዋጋ መጨመር ለአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ ማሻቀብ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን አገልግሎቱን አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8💔8👍5🤔1😢1👀1
የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ከቀረበው አቅርቦት በ5 ሚሊዮን ዶላር ማነሱ ተነገረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው 28ተኛ ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ያልተጠበቀ የገበያ ለውጥ አሳይቷል። ማዕከላዊ ባንኩ ረቡዕ ባካሄደው በዚህ ጨረታዉ ያቀረበው የገንዘብ መጠን ከባንኮች የቀረበውን የጥያቄ መጠን ብልጫ ማሳየቱ ካፒታል ተመልክቷል።

በዕለቱ የጨረታ መርሃ ግብር ብሔራዊ ባንክ ለገበያ ያቀረበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 125 ሚሊዮን ዶላር ነበር። ይሁን እንጂ በሂደቱ ተሳታፊ የነበሩ የንግድ ባንኮች ያስገቡት አጠቃላይ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት 120 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ሆኗል፣ ይህ አቅርቦቱ ከፍላጎቱ በ5 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ማሳየቱ ነዉ ለመረዳት የተቻለው።

ይህ ከቀደምት መደበኛ ጨረታዎች አዝማሚያ በተለየ መልኩ በገበያ የቀረበው አቅርቦት ከፍላጎቱ የሰፋበት ሁኔታ መስተዋሉን የውጤቱ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በጨረታው ላይ የተሳተፉት 20ቱ የባንክ ተቋማትም ያቀረቡትን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ማግኘት ችለዋል።

በዕለቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 160 ብር ከ53 ሳንቲም ሲሆን፣ ይህም በ27ተኛ ዙር ከነበረዉ አማካይ ዋጋዉ 160.20 ሳንቲም አንፃር በተወሰነ ደረጃ የብር የመግዛት አቅም መቀዛቀዙን የሚያሳይ ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍1
በኤራትራ በወጣ አዲስ መመሪያ ግለሰቦች ከ25 ሺህ፣ ተቋማት ከ150 ሺሕ ናቅፋ በላይ ጥሬ ገንዘብ በእጅ እንዳይዙ ታዘዘ።

የኤርትራ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ከባንክ ሥርዓት ውጭ ለተወሰነ ጊዜ መያዝ የሚችሉትን የጥሬ ገንዘብ መጠን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ማውጣቷን የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

በአገሪቱ መንግሥታዊ የሕግ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ይፋ በተደረገው መመሪያ፣ ማንኛውም ዓይነት የኤርትራ ገንዘብ፣ ናቅፋ ዝውውር በባንኮች እና በገንዘብ ተቋማት ብቻ መሆን እንዳለበት ያዛል።

መመሪያው ግለሰቦች ከ25 ሺህ ናቅፋ በላይ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ከ15 ቀናት በላይ በእጃቸው ማቆየት እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል።

እንዲሁም በተለያዩ ሦስት ደረጃዎች የተመደቡ የንግድ ተቋማትም በ50 ሺህ፣ በ100 ሺህ እና በ150 ሺህ ናቅፋ መጠን የተገደበ ጥሬ ገንዘብ ለሁለት ሳምንታት ብቻ መያዝ እንዲችሉ ተፈቅዷል።

ከተፈቀደላቸው የጥሬ ገንዘብ መጠን እና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ተቀባይነት ካለው ምክንያት ውጭ ይዘው የተገኙ ተቋማትና ግለሰቦች #ሕጋዊ_እርምጃ" እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል።

አሁን የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ያወጣው በግለሰቦች እና በተቋማት ይዞታ ስር ሊቀመጥ የሚችልን የገንዘብ መጠንን የሚገድበው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ነው።

የመዋዕለ ነዋይ ዘርፍ በመንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር በሚገኘባት ኤርትራ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ዋነኛው እና በስፋት ጥቅም የሚውል ነው። የባንክ አገልግሎቶች በመላዋ አገሪቱ የተስፋፋ አይደለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍3😢2
የጥሬ ወተት ጉዳይ‼️
በተለይ በከተሞች ለገበያ የሚቀርብ ወተት ለአፍላቶክሲን እና ለተለያየ እክል የተጋለጠ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡

በአዲስ አበባ የሚቀርበው ወተት ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን የህግ ማዕቀፍ እየተሰናዳ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ከከብቶች ማደሪያ ፣ ከመኖ እና ሌሎች ሂደቶች ላይ መሟላት ያለባቸው ደረጃዎች በህጉ መደንገጋቸውን ሰምተናል፡፡

ጥራትን የማረጋገጡ ስራ ከወተት በተጨማሪ ሌሎችም የግብርና ምርቶችን የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡

ወተት በተለይ ለህፃናት በሰፊው የሚቀርብ እንደመሆኑ ተዘጋጅቶ ለገበያ እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ ለብክለት የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ፀጋለማ በቀለ ተናግረዋል፡፡

የህግ ማዕቀፉ አሁን ለሚያፀድቀው አካል መላኩን እና ተግባራዊ ሲሆን ሂደቱን የማይከተሉት ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ምክትል ኮሚሽነሩ ፀጋለማ በቀለ አክለዋል፡፡

በተለይ ወተትን በተመለከተ የሚወጣው የህግ ማዕቀፍ ተግባራዊ ሲሆን በከተማዋ በከብቶች እርባታ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ህጉ የሚጠይቀውን ሁሉ ለማሟላት ይገደዳሉ ተብሏል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን በአዲስ አበባ ጥሬ ወተት መሸጥ ሊከለከል እንደሚችል ሃላፊው አስረድተዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤25👍4🤔1😢1
ኢትዮጵያዊያን በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ🌼🌼🌼🌼
ይችን ቀን ለማክበር/ለማየት/ያልታደሉ ብዙ ናቸውና አሜን በሉ።
ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለኢትዮጵያ🕊🕊
አዲሱ አመት ህልማችሁን የምትኖሩበት፣ያቀዳችሁት የሚሳካበት፣ነጋዴው የሚያተርፍበት፣ገበሬው ጎተራው የሚሞላበት፣የኑሮ ውድነት የሚቀንስበት፣ሰው በሰላም ወጥቶ ውሎ የሚገባበት፣ ሰርቶ የሚለወጥበት፣የጦርነት ዜና የማንሰማበት ዘመን ያድርግልን።
ከሁሉ በላይ የሰው ልጆች ሁሉ የሚፈቃቀሩበት፣የሚተሳሰቡበት ዘመን እንዲሆንልን እንመኛለን።
በዚህ አጋጣሚ ያስቀየምናችሁ ካላችሁ ይቅርታ ለማለት እንወዳለን 'ይቅርታ ከሚጠይቁ ይልቅ ይቅርታን የሚቀበሉ ታላቅ ናቸው'።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤31🙏8👍3
“ችግሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው በውይይትና በይቅርታ መፍትሔ ሊበጅላቸው እንደሚገባ ” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ
 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የ2019 አዲስ ዓመት የቃለ በረከት መልእክት አስተላለፉ
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ አዲሱን የ2019 ዘመነ ሉቃስ በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
ቅዱስነታቸው በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ፣ በየጠረፉ ለቆሙ የሀገር ጠባቂዎች፣ በሕመም ላይ ላሉና በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ዜጎች የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ፓትርያርኩ በመልእክታቸው፤ ዓለማችን በራስ ወዳድነትና በክፋት ማዕበል ተውጣ የመጽናናት ዘመንን እንደምትሻ ገልጸው፤ እግዚአብሔር የመታደስ ዘመንን ይሰጠን ዘንድ ከእኛ የሚጠበቀው ከልብ የመነጨ ንስሐና ከስሕተት መመለስ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
 
ያለፈው ዓመት የሰው ደም የፈሰሰበት፣ አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ እገታና የኑሮ ውድነት የጎላበት ከባድ ጊዜ እንደነበር ያሳሰቡት አቡነ ማትያስ፤ እነዚህ ሁሉ ችግሮች ሰው ሰራሽ በመሆናቸው በሰው ልጅ መልካም ፈቃድ ሊቀሩ እንደሚችሉ አስረድተዋል።
 
በመሆኑም አዲሱን ዓመት ስንቀበል ያለፉ ስሕተቶችን ዳግመኛ ላለመደገም መወሰን እንዳለብን ገልጸዋል።
 
በመጨረሻም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን እንደ ጋራ ሀብት በመመልከት፣ ልዩነቶችን በውይይት፣ በመግባባትና በይቅርታ መንፈስ እንዲፈቱ አባታዊ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤39👍9🥰1
ቀይ ባህር❗
#በኢራን የሚደገፉት #የሁቲ ኃይሎች #የየመንን #ሞካ ወደብ መቆጣጠራቸው እና ወደ ባብ አል-መንደብ እየተቃረቡ መሆናቸው ተዘገበ።

አዲስ አበባ — በኢራን የሚደገፉት የሁቲ ኃይሎች በምዕራብ የመን የምትገኘውን ስትራቴጂያዊ የቀይ ባሕር ወደብ ከተማ ሞካን መቆጣጠራቸውን እና ወደ ባብ አል-መንደብ ሰርጥ እየተቃረቡ መሆናቸውን ሮይተርስ የየመን መንግሥት ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

አዲስ ወታደራዊ ክስተት ሁቲዎች በየመን የቀይ ባሕር ወደብ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማስፋፋታቸውን የሚያሳይ ሲሆን፣ ቡድኑን ለዓለም አቀፍ የባሕር ትራንስፖርት እጅግ ወሳኝ ወደሆነው የባሕር መስመር ይበልጥ እንዲቀርብ ያደርገዋል ተብሏል።

የሁቲ ኃይሎችን የሚቃወሙ ሦስት የየመን መንግሥት ምንጮች እንደገለጹት፣ ለመንግሥት ታማኝ የሆኑ ኃይሎች ሐሙስ ጧት ከከተማዋ ለቀው መውጣታቸውን ተከተሎ ሁቲዎች የቀይ ባሕር ወደብ ከተማዋን እንዲቆጣጠሩ ረድቷቸዋል።

አል-መካ (al-Makha) በሚል ስም የምትታወቀው የሞካ ከተማ በታኢዝ ግዛት ውስጥ ከባብ አል-መንደብ ሰርጥ በስተሰሜን በኩል በግምት 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

በጣረቅ ሳሊህ የሚመራው የብሔራዊ ተቃውሞ ኃይል (National Resistance Forces) ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በሁቲዎች እጅ ወደቀች መባሉን አስተባብሎ፣ ኃይሎቹ ወደ አካባቢው የገቡት የመከላከል አቅምን ዳግም ለማደራጀት እና ለማጠናከር በተደረገ እንቅስቃሴ ምክንያት ነው ብሏል።

ወደቧን መቆጣጠራቸው ሁቲዎች ቀደም ሲል የሁደይዳ ወደብን እና አካባቢውን ከተቆጣጠሩበት ሁኔታ ጋር ተደራርቦ በሁዳይዳና በጠቅላላው የቀይ ባሕር ሰርጥ ላይ ጠንካራ መደላደል እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።

ባብ አል-መንደብ ቀይ ባሕርን ከአደን ባሕረ ሰላጤ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን፣ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ፣ በአውሮፓ እና በአሲያ መካከል ለሚጓጓዙ የነዳጅ፣ የዘይት እና የሌሎች በርካታ ምርቶች መተላለፊያ ዋና የባሕር መስመር ነው።

ሮይተርስ አክሎ እንደዘገበው፣ ሁቲዎች በየመን የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር ለማስፋፋት በሚያደርጉት ጥረት ወደ ዳባብ (Dhubab) የባሕር ዳርቻ ከተማም እየተቃረቡ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍6
የ2018 የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ተቆረጠ፡ 20 ሚሊዮን ብሩን ያሸነፈው ዕጣ ቁጥር ታወቀ!

​የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ ልዩ ሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ምሽት ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ፊት በድምቀት ማካሄዱን አሳውቋል።

​በዚሁ መሠረት ከፍተኛውን የ20 ሚሊዮን ብር አንደኛ ዕጣ ያሸነፈው 2302203 የሆነው የዕጣ ቁጥር ነው።

​ዋና ዋና የዕጣ ቁጥሮች እና የሚያስገኙት የገንዘብ መጠን፦

​1ኛ ዕጣ (20,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 2302203

​2ኛ ዕጣ (10,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 1057413

​3ኛ ዕጣ (5,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 0829516

​4ኛ ዕጣ (2,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 2161591

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26👍9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

የ2019 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት ይተኮሳል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ነገ መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ/ም የሚከበረውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ፦
- በሸራተን አዲስ ሆቴል፣
- በሞናርክ ሆቴል
- በበ#ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ፤ ዛሬ በዋዜማው ከሌሊቱ 6:00 - 6:15 ለ15 ደቂቃ ያህል ርችት እንደሚተኮስ ገልጿል፡፡

" ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው " ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍6🤪6
🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼
🍬🎉HAPPY NEW YEAR 🎉🍬
ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ❤️🙏

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17❤7
Academic Calendar for HEIs (2019 E) FINAL.pdf
1.8 MB
የ 2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር!

👉Exit Exam --ሰኔ 3--13/2019

👉Grade 12 Exam -- ሰኔ 28--ሐምሌ 9/2019

የትምህርት  ሚንስትር  አጠቃላይ  የአመት ካላንደር ከላይ ተያይዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍5❤4🤣1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ስራ እንዳይቀማ በማለት ሮቦቶች ተቃውሞ አሰሙ

​ሰዎች በቴክኖሎጂ ምክንያት ስራ አጥ እንዳይሆኑ እና የስራ ዋስትናቸው እንዲጠበቅ ለማስጠንቀቅ 30 የሚጠጉ ሮቦቶች በፖላንድ ዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስቴር ቢሮ ፊት ለፊት ተቃውሞ አሰሙ።

​ሰልፉን ያዘጋጁት አክቲቪስቶች፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ማሽኖች የሰውን ስራ ሊወስዱ የሚችሉበትን አደጋ በመቃወም መንግስት ጥብቅ የቁጥጥር ህጎችን እንዲያወጣ ጥሪ አቅርበዋል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪25❤12🤔10🤣7👍4😱2
#በፌዴራል_መንግስት እና #በትግራይ ክልል መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የተመሰረተዉ #ጥምረት«ወደ ኋላ የማይመለስ» መሆኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገለፁ

አዲስ አበባ — በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ያለው ውጥረት እና አዲስ ግጭት በበረታበት ወቅት፣ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ከሌሎች የፖለቲካ እና የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የተመሰረተው ጥምረት መዋቅራዊ እና «ወደ ኋላ የማይመለስ» መሆኑን የራሱ አመራር፣ ዕቅድ እና የተፈረመ ስምምነት እንዳለዉ መናገራቸውን ወይን ሚዲያ ዘግቧል።

ከወይን ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሕወሓት ሊቀመንበር እና የትግራይ ፕሬዚዳንት የሆኑት ደብረጽዮን እንደገለጹት፣ ጥምረቱ ከመደበኛ ያልሆነ ትብብር አልፎ በተዘረጋ መዋቅር ሥር እየሰራ እንደሚገኝ እና ተጨማሪ ኃይሎች ይቀላቀሉታል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት ይፋ እንደሚደረጉ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍8🤣7🕊1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፑቲን ከብሪክስ ጉባኤ ጎንዮሽ  እንደሚገናኙ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቭላድሚር ፑቲን በህንድ ከሚካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ነገ መስከረም 2 ውይይት እንደሚያካሂዱ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ህንድ መግባታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኒው ዴልሂ ሲደርሱ በከፍተኛ የህንድ ባለሥልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪14👍10❤5🤔1🕊1
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ትምህርት ዘመን ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም ለመልሶ ቅበላ ብቁ የሆናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን 👇
ሰኞ መስከረም 11/2019 ዓ.ም

የትምህርት ክፍል ምርጫ 👇
መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም (የ1ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች)

የምዝገባ ቀናት 👇
መስከረም 12 እና 13/2019 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀምርበት ቀን 👇
ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም.

በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሳችሁ በሚገኙ የሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል በመገኘት የምዝገባ ሂደታችሁን እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍5
በአሶሳ ከተማ ታግቶ የነበረው ህፃን ከአጋቹ እጅ ነፃ ወጣ

መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም
በአሶሳ ከተማ ተጠልፎ የተወሰደውን የ5 ዓመት ህፃን ልጅ ይዞ ሲያሸሽ የነበረ ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ አክመል ሸምሲ መሃመድ የተባለው ተጠርጣሪ መርሲሞይ ደረጀ የተባለውን ህፃን ከቤተሰቦቹ እይታ ውጭ በማድረግ ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማሸሽ ሲንቀሳቀስ ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።

ድርጊቱ ወዲያውኑ ለፀጥታ አካላት በጥቆማ በመድረሱ በተደረገው የተቀናጀና ጥብቅ የክትትል ስራ ህፃኑን በሰላም ማዳን የተቻለ ሲሆን ተጠርጣሪውም በፖሊስ እጅ ወድቋል።

የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ሀሩን ሄረላም እንደገለጹት፤ የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተቀናጀ የጋራ ጥረት ወንጀሉን ማክሸፍ ቢቻልም፣ ህፃናት ለእንዲህ አይነት ጥቃቶችና አደጋዎች እንዳይጋለጡ ወላጆችና አሳዳጊዎች ዘወትር የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮማንደሩ አክለውም ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር ለማዋል ላቀረቡት ፈጣን ጥቆማና ላደረጉት ከፍተኛ አጋርነት ህብረተሰቡን አመስግነው፤ መሰል ህገ-ወጥ እና ወንጀል አድራጊ አካላትን አጋልጦ በመስጠት በኩል ህዝቡ የሚያደርገውን አወንታዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

Via የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26👍11
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኒውዮርክ መንትያ ህንፃዎች በ 2,977 ድሮኖች ሰማይ ላይ ዳግም ተፈጠሩ

​የመስከረም 1 (ሴፕቴምበር 11) አሰቃቂ የሽብር ጥቃት 25ኛ ዓመት የምስረታ መዘከሪያን በማስመልከት፣ ትናንት በኒውዮርክ የባህር ወሽመጥ ላይ 2,977 በራሪ ድሮኖችን በመጠቀም አስደናቂ ትርኢት ተቀርቧል።

"2,977 Lights Over New York Harbor" በተሰኘው በዚህ ዝግጅት፣ እያንዳንዱ ድሮን በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን የሚወክል ሲሆን፣ የዓለም የንግድ ማዕከል የነበሩትን መንትያ ህንፃዎች ትክክለኛ ቅርፅ እና መጠን በምሽቱ ሰማይ ላይ መልሰው አሳይተዋል።

​በስካይ ኤሌመንትስ ኩባንያ የቀረበው ይህ ጥበባዊ ስራ ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ከአደጋ ጊዜ ደራሽ ሰራተኞች ጋር በመተባበር የተከናወነ ነው።

በተጨማሪም በግራውንድ ዚሮ በተካሄደው የስም ጥሪ ስነ-ስርዓት ላይ በጥቃቱ ምክንያት በደረሰ የጤና እክል ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መታሰቢያ የሚሆን ሰባተኛው የህሊና ጸሎት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22🤪8👍4🥰1🤔1😱1😢1
ፈሶትን አያዙ: የተከማቸ ፈስ በአፍ ሊወጣ ይችላል

​አንድ ሰው የሆድ አየርን (ፈስን) ከልክ በላይ ይዞ ለመቆየት ሲሞክር አየሩ በጨጓራና አንጀት ውስጥ ታፍኖ አይቀርም።

በሰውነት ውስጣዊ መዋቅር ምክንያት አየሩ ወደ ደም ዝውውር ስርአት ውስጥ እንደገና በመመጠቅ በመጨረሻም በአፍ በሚወጣው ትንፋሽ በኩል ሊወጣ እንደሚችል የህክምና ጥናቶች ያሳያሉ።

​ይህ ሂደት የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ የታቀበው ጋዝ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ወደ አንጀት ግድግዳ የደም ስሮች በመግባት ነው።

ደም ወደ ሳንባ በሚሰራጭበት ወቅት እነዚህ ጋዞች ከደም ወጥተው ወደ ሳንባ አየር ከረጢቶች ስለሚሸጋገሩ፣ ግለሰቡ በሚተነፍስበት ጊዜ አየሩ በአፍ በኩል ይወጣል።

​ምንም እንኳን ይህ አጋጣሚ ለብዙዎች እንግዳና የሚያስቅ ቢመስልም፣ በተፈጥሮ የሚፈጠርን የሰውነት ጋዝ አፍኖ መያዝ የሆድ እብጠት፣ ህመም እና የአንጀት ምቾት ማጣት ስለሚያስከትል ተፈጥሯዊ ሂደቶችን አለመግታት ይመረጣል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙉19❤8🤪7🤣4👍3🤔1👌1🤡1👀1