የድሮን ጥቃት‼
አዳሩን በሕንጣሎ ወረዳ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
በትግራይ ክልል ሕንጣሎ ወረዳ ጣብያ ፍረወይኒ «ማይ ሽመት» ልዩ ቦታ ላይ ሌሊት 8:30 ሰዓት ተደጋጋሚ የድሮን ደብደባ መፈፀሙ ታውቋል።
የድሮን ጥቃቱ ኢላማ የህውሃት የጦር መሳሪያ ክምችት ላይ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ህውሃት በበኩሉ በጥቃቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎች (የአራት ዓመት ሕፃንን ጨምሮ) ሲሞቱ፣ የሟቾች እናት ደግሞ በጽኑ መቁሰላቸውንና በንብረት ላይም ከባድ ውድመት መድረሱ አሳውቋል።
ህውሃት መኖሪያ መንደሮችን አስታኮ የጦር መሳሪያ ስለሚያከማች በንፅሃን ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለው ክምችቱ በድሮን ሲመታ የሚወድመው ጦር መሳሪያ ፍንዳታ ነው ሲሉ ገለልተኛ ወገኖች እየገለፁ ነው።
@Addis_Reporter

❤14😢10👍6
ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የፍልሰት ጉዳዮች ለማስተናገድ፤ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ሊጀምር ነው።
በቢሮው ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ ገልጿል።
መቀመጫውን በአዲስ አበባ የሚያደርገው አዲሱ ቢሮ ለቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔ የሚሰጥ እንዳልሆነ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
ሆኖም ቢሮው ኢትዮጵያውያን ለፍልሰት ማመልከቻዎቻቸው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራን የሚያከናውን መሆኑን አገልግሎቱ አስገንዝቧል።
የተጠረጠሩ የሰነድ “ማጭበርበሮችን” የሚመረምሩት እና የቤተሰቦችን ዝምድና ለማረጋገጥ የዘረ-መል (DNA) ናሙናዎችን የሚሰበስቡት በአዲስ አበባ የሚከፈተው የአገልግሎቱ ቢሮ ሰራተኞች ይሆናሉ።
እነዚህ ስራዎች ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የነበረው፤ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እንደነበር ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።
የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት “ወሳኝ የስራ ኃላፊነቶች” ያላቸውን እነዚህን ተግባራት፤ አዲሱ ቢሮ “በቀጥታ ለማከናወን የሚያስችለውን ልዩ ውክልና ይሰጠዋል” ተብሏል።

👍6❤4
ለአዲስ ዓመት በዓል የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተሰርቷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር እንዳሉት፤ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስና ድንገተኛ ችግሮች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተሰርቷል፡፡
በበዓሉ ዋዜማና በበዓሉ ዕለት ሊከሰቱ የሚችሉ የኃይል መቆራረጦችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የተቋሙ መዋቅሮች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በቅንጅት የተደራጀ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ 24 ሰዓት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክ ቡድን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መግባቱንም ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም በሁሉም የአገልግሎቱ ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አጣዳፊ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ የጥገና ቡድኖች መደራጀታቸውን አመልክተዋል።
በበዓሉ ወቅት የሚፈጠረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ለማመጣጠን ደንበኞች ኃይል ቆጣቢ ቁሳቁሶችን እንዲጠቀሙና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶቻቸው ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

🤣10❤7👍7
📣[ታላቅ ቅናሽ]
መጪዉን አዲስ አመት በማስመልከት
🌼 ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ ?
🌻የምንሠጣቸዉ አገልግሎቶች
🌻 የድርጅት ማስታወቂያ
🌻 የተለያዮ አልባሳት
🌻 የ መድሀኒቶችን ማስታወቂያ
🌻 የክፍት ስራ ቦታ ማስታወቂያ
🌻 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
🌻 የስልክ እና የlaptop
🌻የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
🌻 የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
🌻ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች
🌻የትምህርት ተቋማት…...
🌻 የህክምና ማዕከላት
🌻የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች……
⚡️ ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
🌻 ህጋዊነት ያለውን ማንኛውም ማስታወቂያ እዚህ ቻናላችን ላይ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ
👇
@Addis_reporter_bot

❤3👍2🥰1👌1
መንታ ሆና የተወለደች እናት አምስት (5) ህፃናት በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏን ባለሙያዎች ገለጹ።
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አበርገለ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ ሲሆኑ በየጭላ መባእታዊ ሆስፒታል አምስት ህፃናትን ወልደዋል።
የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ እናቲቱ ራሷ መንታ ሆና የተወለደች መሆኗን የሚያሳይ የህክምና ታሪክ አላት።
ከአምስቱ ህፃናት መካከል አራቱ የእድገት ሂደታቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀው የተወለዱ ሲሆን፣ አምስተኛው ህፃን ግን ከአምስተኛው ወር በኋላ የእድገት ሂደቱ በመስተጓጎሉ የተነሳ የእድሜውን እድገት ሳያጠናቅቅ መወለዱን ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።
አዋላጅ የጤና ባለሙያዎች እንዳስረዱት፣ እናቲቱም ሆነች አምስቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፣ ተገቢውን የጤና ክትትልም እያገኙ ነው።
ባለሙያዎቹ አክለውም፣ እናቲቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የወለደች መሆኗን ጠቁመው፣ አምስቱን ህፃናት በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያስችል የተመቻቸ ኑሮና በቂ ገቢ ስለሌላት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

❤18👍6🙈6🥰1
#SalaleUniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች (2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ) የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን አሳውቋል።
ምዝገባ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ እንደሚከናወን የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ገልጿል።

❤11👍3
አዲስ አበባ‼️
አለም አቀፉ የጂኦ ስፓሻል ኤአይ ተቋም አልፋ ጂኦ የአለማችንን 72 ከተሞች ባጠናበት አዲሱ የምርምር ውጤት አዲስ አበባ የአየር ንብረት አደጋዎችን በመቋቋም ከአለም ሁለተኛን ደረጃ መያዟን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

🤪29❤24👍4🤯2🤔1👌1🤣1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርካታ ተሽከርካሪዎች ተቃጠሉ‼️
በኦሮሚያ ክልል በጊምቢ እና ቢላ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም ጀምም ነዳጅ የጫኑ ብዛት ያላቸው ተሽከርካሪዎች በታጠቁ ሀይሎች ተቃጥለዋል 14 አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል።

😡26😢12👍7❤1🕊1👀1
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለልማት ተነሺዎች ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉን ገለጸ
የየካ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት ምክንያት ከመኖሪያ ቦታቸው ለተነሱ የልማት ተነሺዎች ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ መክፈሉን አስታወቀ።
የካሳ ክፍያ፦ ክፍያው የዜጎችን መብት በማክበርና ተገቢውን ምትክ በመስጠት መፈጸሙን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ቢሆነኝ አበጋዝ ገልጸዋል።
የመልሶ ማልማት ፋይዳ፦ የተከናወኑት ሥራዎች ከተማዋን ጽዱ፣ አረንጓዴና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ለማስፋፋት ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተጠቁሟል።
የካርታ ዝግጅትና የገቢ አሰባሰብ፦ በበጀት ዓመቱ ለ781 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከሊዝና ከይዞታ አገልግሎቶች ከ674 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገልጿል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፦ የተገኘው ውጤት በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የታገዘ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንደሚሰራ ተመላክቷል።

❤16👍5🤪2🤣1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኢትዮጵያ የድሮን ምርት‼️
ኤኤፍፒ ‹‹ኢትዮጵያ አማፅያንን ለመዋጋት የድሮን ምርቷን አሳድጋለች›› ሲል ዘገበ፡፡ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የሆነው ኤኤፍፒ ዛሬ ባቀረበው ዘገባ ኢትዮጵያ ድሮን የማምረት አቅሟን ማሳደጓን ገልጿል፡፡ እንደዘገባው ካለፈው አመት አንስቶ በሁለት ፋብሪካዎች ውስጥ ድሮኖችን እያመረተች ሲሆን አሁን በሺህ የሚቆጠሩ ድሮኖች አሏት፡፡ እ.ኤ.አ ከ2020 እስከ 2022 በነበረው አውዳሚ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን የገለፀው ዘገባው የፌዴራል መንግስቱ ከአዲስ አበባ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የደረሱትን የትግራይ ክልል አማፅያን ጉዞ ለመግታት እንደተጠቀመባቸው አስረድቷል፡፡ 130 ሚሊዮን ህዝብ ባለባት አገር ወታደራዊ ድሮኖች ያሉት የፌዴራል መንግስቱ ብቻ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ አማፅያን ላይ እነዚህን ድሮኖች በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ ገልፆም አሁን በአገር ውስጥ ድሮኖችን የማምረት አቅሙን ማሳደጉን አስረድቷል፡፡ ባለፈው አመት መጋቢት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስካይዊን ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪ ፋብሪካን በመረቁበት ወቅት ፋብሪካው ለሲቪልም ሆነ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ድሮኖችን እንደሚያመርት መናገራቸውን አውስቷል፡፡ ፋብሪካውን ‹‹በራሳችን ወጣት ባለሙያዎች የተነደፉና የተገነቡ ናቸው›› በማለት መናገራቸውን ጨምሮ ያወሳው ዘገባው አላማው ግጭትን ማቀጣጠል ሳይሆን መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ መግለፃቸውን ጠቅሷል፡፡
ዘገባው በመቀጠል አብዛኛው የኢትዮጵያ ድሮን የማምረት አቅም ሚስጥራዊ እንደሆነና የውጭ ሚዲያዎች ፋብሪካውን እንዳይጎበኙ መከልከላቸውን አስታውቋል፡፡ በስቶኮልም አለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ፒተር ዌዜማን ለዜና ምንጩ ሲናገሩ ‹‹አብለጭልጨው የምናያቸው ድሮኖች ስለእውነተኛው የምርት አቅምና ቴክኖሎጂው ወይንም ወሳኝ አካላቱ ከየት እንደሚመጡ ብዙም አይነግሩንም›› ካሉ በኋላ በእሳቸው ግምት አብዛኛው የድሮኖቹ አካላት ከውጭ የሚገቡ እንደሚመስላቸው ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የቱርክን ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው አካንቺ ድሮኖችና መሰረታዊ የሆኑትን ባይራክታር ቲቢ 2 ሞዴሎችን መግዛቷን ያወሳው ዘገባው እንዲሁም ርካሽ የሆኑትን የቻይናውን ዊንግ ሉንግና የኢራንን ሞሀጅር 6 ድሮኖችን ገዝታ እንደነበር ጠቅሷል፡፡ የጄንስ መከላከያና የደህንነት ተቋም ባለሙያው ጄረሚ ቢኒ እንደገለፁት በስካይ ዊን ምርቃት ላይ የታየውና ‹‹ኤስደብሊው01›› የሚል ምልክት የተፃፈበት ድሮን በገበያ ላይ ካሉት የቻይና ምርቶች ጋር ይመሳሰላል፡፡ እነዚህን ድሮኖች በብዛት ማምረት በጦርነት ላይ ከመድፍ በሁለትና በ3 እጥፍ የበለጠ ውጤታማነትን ሊያመጣ እንደሚችል ገልፀው ምናልባትም እነዚህ ድሮኖች አነስተኛ ቦምቦችን እንዲይዙ ተደርገው ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ሁለተኛው የድሮን ፋብሪካ ኤሮአባይ ባለፈው አመት መገባደጃ የተመረቀ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው እያንዳንዳቸው ከ5000 እስከ 10000 ዶላር የሚያወጡ በሺህ የሚቆጠሩ ድሮኖችን ማምረቱን አስታውቋል፡፡ ግጭቶችን የሚከታተለው አክሊድ በአማራ ክልልና በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሱ አማፅያን ላይ 102 የድሮን ጥቃት መከናወኑን መጥቀሱን ያስታወቀው ዘገባው በዚህም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አስረድቷል፡፡

❤21🤪13👍3🕊2🤣2😈1
"መንግስት ከፋኖ እግር ስር ወድቆም ቢሆን እርቅ ያውርድ!" — ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ
በአገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ ከተፈለገ መንግስት እስከ መጨረሻው ዝቅ ብሎ ''ከፋኖ እግር ስር ወድቆም'' ቢሆን አስቸኳይ እርቅ ሊፈፅም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሌላው ነገር ሁሉ ቀላልና ሁለተኛ ደረጃ ነው ሲሉ የቀድሞው ጀኔራል ካሳዬ ጨመዳ ተናግረዋል።
በሻዕብያ እና በህወሓት መካከል የሚታየው ጊዜያዊ የፖለቲካ ፍቅር 15 ቀን እንኳ የሚዘልቅ አይደለም።
መሰረታዊውን የፋኖን ጥያቄና ሀይል ወደ ጎን ብሎ የሚደረግ ማንኛውም አይነት ስምምነትም ሆነ ህብረት የትም ሊደርስ አይችልም ብለዋል።''
ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ጥይት ስትተኩሱ ክርስቲያኖች በስመአም፣ መስሊሞች ቢስሚላህ እያላቸው ተኩሱ በሚለው ምክራቸው ይታወሳሉ።

❤46🤣15👍12💯2🥰1👌1🤝1😡1
"እርቅ ተፈጸመ ሲባል በማግስቱ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች ይገደላሉ" - የክልሉ ምክር ቤት አባል
በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት በሚደርስበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጥቃቱ ባለመቆሙ ሰሞኑንም ንጹሐን መገደላቸውን፣ ንብረት መዘረፉን አንድ የዞኑ አመራርና የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
አመራሩ በሰጡን ቃል፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ጋላናና ሱሮባርጉዳ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ መሆናቸውን አስረድተዋል።
መላኩ ማዝሬ የተባሉ ግለሰብ ከብቶች በማሰማራት ላይ በነበሩበት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።
ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከጋላና ወረዳ ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ዘልቀው በገቡ የጉጂ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ግለሰቡ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ማረጋገጣቸውንም አስረድተዋል።
ሌላኛው የቀበሌው ነዋሪ፣ የግድያ ጥቃት በታጣቂዎቹ ከብቶች መነዳታቸውን ገልጸው፣ "ከብቶቹ የተዘረፉት ከምዕራብ ጉጂ ጋላና ወረዳ ጋላና መጣሬ ልዩ ስሙ ቡልቶ ዳልጀሳ መንደር በሚኖሩ ታጣቂዎች ነው" ብለዋል።
"ታጣቂዎች አንድ ሰው ገድለው የአንድ በረት ከብቶችን ዘርፈዋል። በነሐሴ ወር እንዲሁም ሐምሌ 30/2018 የኬሌ ቀበሌ አስተዳደር ነዋሪ የሆነው ከድር አብዱ በጎርካ ወረዳ ጋሙሌ ቀበሌ መንገድ ላይ ተገድሏል" ተብሏል።
እንዲሁም፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከከጋላና ወረዳ ሻሞሌ ሽዳ ወደ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጋሙሌ ዘልቀው በገቡ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነሐሴ 22/2018 ዓ/ም፣ መሐመድ ደረሱ የተባሉ የዶርባዴ ቀበሌ ነዋሪ መገደላቸውም ተመልክቷል።
በዞኑ ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ በሚፈጸሙ ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ይገለፃል።

❤11👍2😢2
አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 300 የፖለቲካ እስረኞች የተሀድሶ ስልጠና አጠናቀው ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ከእስር እንደሚፈቱ ተሰምቷል።
በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤቶች ተይዘው የሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከመንግስት የቀረበላቸውን የይቅርታ ሰነድ እንዲፈርሙና እንዲፈቱ መንግሥት አማራጭ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

❤23👍6🤪2🥰1👌1
በቡርኪናፋሶ የተረጂዎችን ክብር ለመጠበቅ ሲባል ከሚሰጣቸው ዕርዳታ ጋር በፎቶ ማሳየት የሚከለክል አዲስ ህግ ፀደቀ‼️
“ለምን ሰውን ረድተህ ያንን ሰው ከሰጠኸው ምግብ፣ ልብስ ወይም ቁሳቁስ ጎን አቁመህ ለካሜራ ታሳየዋለህ?” ይህ ጥያቄ በቡርኪና ፋሶ አዲስ የመንግሥት አቅጣጫ መሠረት ላይ ተቀምጧል።
የኢብራሂም ትራኦሬ መንግሥት በጁላይ 2፣ 2026 በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የተጋላጭ የእርዳታ ተቀባዮችን ከሚሰጣቸው ዕርዳታ ጋር አብሮ በፎቶ ወይም በምስል ማሳየትን የሚገድብ አዲስ አቅጣጫ አጽድቋል።
በተለይ ሕፃናት፣ ተፈናቃዮች፣ የችግር ሰለባዎችና ሌሎች ተጋላጭ ዜጎች ምግብ ወይም ቁሳቁስ ሲቀበሉ ከዕርዳታው ጎን አቁሞ ፎቶ በመነሳት፣ ቪዲዮ በመቅረጽና ምስሉን በማሰራጨት የግለሰቡን የችግር ሁኔታ ለገበያ ወይም ለገንዘብ ማሰባሰቢያ መጠቀም በመሠረቱ እየተቃወመ ያለው ነገር ይህ ነው።
አንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ እርዳታ ሲሰጥ፣ ተረጂውን ከሰጠው ዕቃ ጎን አቁሞ፣ የፎቶ ወይም የቪዲዮ ምስሉን በማሰራጨት “እኛ እየረዳን ነው” ለማለት የተረጂውን ስቃይ እንደ ማስታወቂያ መጠቀም ነው።
እርዳታ መስጠት በራሱ በጎ ተግባር ነው።
ግን የሚረዳውን ሰው ክብር ማስከፈል የለበትም።
ቡርኪና ፋሶ በራሷ የእርዳታ ሥርዓት ላይም ትልቅ አቅም እያሳየች ነው። ለምሳሌ “Dɛmɛ Sira” በተባለው የአገር ውስጥ የአጋርነት ዘመቻ እስከ መጋቢት 2026 ድረስ ከ1.13 ቢሊዮን CFA ፍራንክ በላይ ማሰባሰቡን መንግሥቱ ገልጿል።
በ2025 ደግሞ የቡርኪና ፋሶ መንግሥት ከ22,000 ቶን በላይ ምግብና ከ290 ቶን በላይ መድኃኒት ወደ የጸጥታ ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች መላኩን፣ ወደ 59,000 የሚጠጉ የተፈናቃይ ቤተሰቦችም የቤት ዕቃዎችን ማግኘታቸውን አስታውቋል።

❤79🫡14👍12💯5🙏3🏆2👌1🤝1
የዋጋ ግሽበቱ 15.1 በመቶ ሆኗል
የነሐሴ 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 15.1 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ። ከባለፈው ዓመት ነሐሴ 2017 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ1.5 በመቶ ጭማሪ ቢኖረውም፣ ከሐምሌ 2018 ዓ.ም የ15.3 በመቶ ጋር ሲታይ ግን መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል።
በወቅቱ የተመዘገበው የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ግሽበት 14.9 በመቶ ደርሷል። በምግብ ምድብ ውስጥ ስኳር፣ ማር እና ቸኮሌት (38.3 በመቶ)፣ ስጋ (22.6 በመቶ)፣ እንዲሁም ፍራፍሬ (19.1 በመቶ) ከፍተኛውን ጭማሪ አሳይተዋል።
ምግብ ነክ ባልሆኑ ዘርፎች ደግሞ አጠቃላይ ግሽበቱ 15.4 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በዚህ ምድብ ውስጥ የትምህርት አገልግሎቶች (25.3 በመቶ)፣ ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች (19.3 በመቶ)፣ እንዲሁም የአልኮል መጠጦችና ትምባሆ (16.0 በመቶ) ዋጋ መጨመር ለአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ ማሻቀብ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን አገልግሎቱን አመልክቷል።

❤8💔8👍5🤔1😢1👀1
የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ከቀረበው አቅርቦት በ5 ሚሊዮን ዶላር ማነሱ ተነገረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው 28ተኛ ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ያልተጠበቀ የገበያ ለውጥ አሳይቷል። ማዕከላዊ ባንኩ ረቡዕ ባካሄደው በዚህ ጨረታዉ ያቀረበው የገንዘብ መጠን ከባንኮች የቀረበውን የጥያቄ መጠን ብልጫ ማሳየቱ ካፒታል ተመልክቷል።
በዕለቱ የጨረታ መርሃ ግብር ብሔራዊ ባንክ ለገበያ ያቀረበው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን 125 ሚሊዮን ዶላር ነበር። ይሁን እንጂ በሂደቱ ተሳታፊ የነበሩ የንግድ ባንኮች ያስገቡት አጠቃላይ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት 120 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ሆኗል፣ ይህ አቅርቦቱ ከፍላጎቱ በ5 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ማሳየቱ ነዉ ለመረዳት የተቻለው።
ይህ ከቀደምት መደበኛ ጨረታዎች አዝማሚያ በተለየ መልኩ በገበያ የቀረበው አቅርቦት ከፍላጎቱ የሰፋበት ሁኔታ መስተዋሉን የውጤቱ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በጨረታው ላይ የተሳተፉት 20ቱ የባንክ ተቋማትም ያቀረቡትን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ማግኘት ችለዋል።
በዕለቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 160 ብር ከ53 ሳንቲም ሲሆን፣ ይህም በ27ተኛ ዙር ከነበረዉ አማካይ ዋጋዉ 160.20 ሳንቲም አንፃር በተወሰነ ደረጃ የብር የመግዛት አቅም መቀዛቀዙን የሚያሳይ ሆኗል።

❤7👍1
በኤራትራ በወጣ አዲስ መመሪያ ግለሰቦች ከ25 ሺህ፣ ተቋማት ከ150 ሺሕ ናቅፋ በላይ ጥሬ ገንዘብ በእጅ እንዳይዙ ታዘዘ።
የኤርትራ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ከባንክ ሥርዓት ውጭ ለተወሰነ ጊዜ መያዝ የሚችሉትን የጥሬ ገንዘብ መጠን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ማውጣቷን የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።
በአገሪቱ መንግሥታዊ የሕግ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ይፋ በተደረገው መመሪያ፣ ማንኛውም ዓይነት የኤርትራ ገንዘብ፣ ናቅፋ ዝውውር በባንኮች እና በገንዘብ ተቋማት ብቻ መሆን እንዳለበት ያዛል።
መመሪያው ግለሰቦች ከ25 ሺህ ናቅፋ በላይ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ከ15 ቀናት በላይ በእጃቸው ማቆየት እንደማይችሉ ገደብ ጥሏል።
እንዲሁም በተለያዩ ሦስት ደረጃዎች የተመደቡ የንግድ ተቋማትም በ50 ሺህ፣ በ100 ሺህ እና በ150 ሺህ ናቅፋ መጠን የተገደበ ጥሬ ገንዘብ ለሁለት ሳምንታት ብቻ መያዝ እንዲችሉ ተፈቅዷል።
ከተፈቀደላቸው የጥሬ ገንዘብ መጠን እና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ተቀባይነት ካለው ምክንያት ውጭ ይዘው የተገኙ ተቋማትና ግለሰቦች #ሕጋዊ_እርምጃ" እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል።
አሁን የኤርትራ ማዕከላዊ ባንክ ያወጣው በግለሰቦች እና በተቋማት ይዞታ ስር ሊቀመጥ የሚችልን የገንዘብ መጠንን የሚገድበው መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ነው።
የመዋዕለ ነዋይ ዘርፍ በመንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር በሚገኘባት ኤርትራ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ዋነኛው እና በስፋት ጥቅም የሚውል ነው። የባንክ አገልግሎቶች በመላዋ አገሪቱ የተስፋፋ አይደለም።

❤15👍3😢2
የጥሬ ወተት ጉዳይ‼️
በተለይ በከተሞች ለገበያ የሚቀርብ ወተት ለአፍላቶክሲን እና ለተለያየ እክል የተጋለጠ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡
በአዲስ አበባ የሚቀርበው ወተት ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን የህግ ማዕቀፍ እየተሰናዳ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ከከብቶች ማደሪያ ፣ ከመኖ እና ሌሎች ሂደቶች ላይ መሟላት ያለባቸው ደረጃዎች በህጉ መደንገጋቸውን ሰምተናል፡፡
ጥራትን የማረጋገጡ ስራ ከወተት በተጨማሪ ሌሎችም የግብርና ምርቶችን የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡
ወተት በተለይ ለህፃናት በሰፊው የሚቀርብ እንደመሆኑ ተዘጋጅቶ ለገበያ እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ ለብክለት የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ሲሉ በአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶ/ር ፀጋለማ በቀለ ተናግረዋል፡፡
የህግ ማዕቀፉ አሁን ለሚያፀድቀው አካል መላኩን እና ተግባራዊ ሲሆን ሂደቱን የማይከተሉት ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ምክትል ኮሚሽነሩ ፀጋለማ በቀለ አክለዋል፡፡
በተለይ ወተትን በተመለከተ የሚወጣው የህግ ማዕቀፍ ተግባራዊ ሲሆን በከተማዋ በከብቶች እርባታ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ህጉ የሚጠይቀውን ሁሉ ለማሟላት ይገደዳሉ ተብሏል፡፡
ይህ ካልሆነ ግን በአዲስ አበባ ጥሬ ወተት መሸጥ ሊከለከል እንደሚችል ሃላፊው አስረድተዋል፡፡

❤25👍4🤔1😢1