አርሰናል 3ኛ ተከታታይ ድሉን አሳካ
በሦስተኛ ሳምንት እጅግ ተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ቼልሲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በኢምሬትስ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ አስቆጥረዋል።
ቼልሲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በሊጉ ያደረጋቸውን ተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ድል አድርጓል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል።
አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቱ ይታወቃል።
@Addis_Reporter

👍22❤17🤪4🥰2🍾2🤔1😢1🎉1🏆1
ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊለቁ ነው!
ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ልደቱ፤ ሀሳብን በዜማ በሚል ለአዲስ አመት የሙዚቃ አልበም ሊያሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖለቲከኛው አዲስ የከፈቱትን የዩቲዩብ ገጽ ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንዳሳወቁት የሙዚቃ አልበሙን ያዘጋጁት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ነው።
እንደሚታወሰው ቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ አልበሙን ካሰራጨ በኋላ የፈጠረውን ተጽእኖ ተከትሎ አቶ ልደቱ በወቅቱ፣ "የመንፈስ ቅናት አደረብኝ" ሲሉ ገልጸው ነበር።

🤣80❤15👍11🙈2🤪2👀1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-
✅ከጠዋቱ 2፡00-9፡30
👉ጎፋ ካምፕ ፣ ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ መብራት ፣ ቆሬ አደባባይ ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም በከፊል፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው፣
👉ኮዬ 05 ፕሮጀክት 16 በከፊል፣ ፕሮጀክት 12 ፣ ፕሮጀክት 17 እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

👍5❤4
በመቀሌ እና ድሬዳዋ ከተሞች አበባ'ን የማምረት እንቅስቃሴ የተቀዛቀዘ እንደሆነ ተነገረ
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአበባ ምርት በስፋት እየተካሄደባቸው ያሉ ምቹ አካባቢዎች መኖራቸውን የተገለጸው ሲሆን በመቀሌ እና ድሬዳዋ ከተሞች ግን መቀዛቀዝ እንደታየባቸዉ ተገልጿል።
ከኢትዮ ኤፌም ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ አበባ ፥ ፍራፍሬ እና አትክልት አምራቾች ማህበር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ ዘዉዴ እንደሚሉት አዳዲስ የአበባ ምርት ኢንቨስትመንት ሀኔታዎች መኖራቸውን ይገልጻል።
ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲገቡ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነዉ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ መቀሌ ላይ ብዙም እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀዋል በተመሳሳይ መልኩ ድሬዳዋ ከተማ አበባን በተመለከተ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እንዳለ ተናግረዋል።
በባቱ ፣ቢሾፍቱ ፥ሆለታ እና ሰበታ ሰፋፊ የአበባ እርሻ የሚካሄድባቸው መሆኑን ያነሱት የማህበሩ ዳይሬክተር በባህርዳር ዙሪያ አየር መንገዱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉን እና ለዉጪ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ያሉ ኩባንያዎች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በጉራጌ ዞን አካባቢ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መሬቶች መኖራቸዉን ተለይቶ ሂደቶች መጀመራቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በሀዋሳ ከ100 ሄክታር በላይ የአበባ እርሻ የሚገኝበት አካባቢ መሆኑ ተጠቅሷል።
የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ የአበባ ምርት ከሌሎች የሆልቲካልቸር ምርቶች በገዘፈ መልኩ እድገቱ መሻሻሎች እንደታየበት መሆኑን ጠቅሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሎጀስቲክ አቅሙን ከፍ ማድረጉን ተከትሎ ለምርቱ ተፎካካሪነት እድል ፈጥሯል ሲሉም ይገልፃሉ።

❤8👍5😢2
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች ሀገራት የዲቪ-2026 አመልካቾች ተስፋ ሰጪ ውሳኔ አስተላለፈ
የካሊፎርኒያ ክልላዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ኤድዋርድ ዳቪላ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚስቴር በዲቪ አመልካቾች ላይ ተጥለው የነበሩ የቪዛ እገዳዎችን የሚያነሳ ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ48 ሀገራት አመልካቾች የቪዛ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ መንገድ መከፈቱ ተገለጸ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚስቴር ቀደም ሲል ጥሎት የነበረውን እገዳ ያነሳ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ አመልካቾች እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የዲቪ-2026 ፕሮግራም ገደብ ውስጥ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ እና የተያዙላቸውን ቃለ-መጠይቆች መከታተል እንደሚችሉ አስታውቋል።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ሲሆን፣ ከ49 የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 53 ሺህ 939 ሰዎች በDV-2026 ተመዝግበው ይገኛሉ።
ከእነዚህ መካከል ግብፅ በ5,527 ከፍተኛውን ቁጥር ስትይዝ፣ አልጄሪያ በ5,457፣ ሱዳን በ5,226፣ ኬንያ በ3,949 እንዲሁም ኢትዮጵያ በ3,287 አመልካቾች ቀጣዩን ደረጃ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
ባለፉት አምስት ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ የላኩ እንደ ናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ አልተካተቱም።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ20.8 ሚሊዮን በላይ ብቁ ተወዳዳሪዎች መካከል 129,516 ሰዎች ለዲቪ-2026 የተመረጡ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በየዓመቱ እስከ 55 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የአሜሪካ ቋሚ መኖሪያ ቪዛ ይሰጣል።

👍14❤13🤯2🙏1👌1
ህወሓት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በፌደራል መንግስት ይሁንታ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ለአሸማጋይነት ብቁ አይደሉም አለ‼️
የትግራይ ክልል መንግስትን በኃይል የተቆጣጠረው እና በምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን የተነፈገው ህወሓት፤ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከፌደራል መንግስት ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚቀበሉ፣ ግልፅ የሆነ የሰላም አጀንዳ እንዲሁም የሰላም ሃሳብ ሳይዙ የሚንቀሳቀሱ፣ የዓለም አቀፍ አሸማጋይነት ዋና መመሪያ የሆኑትን ነጻ እና ገለልተኝነት፣ ተከታታይነት ያለው ጥረት የማያደርጉ እና ይህን መስፈርት የማያሟሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ለአሸማጋይነት ብቁ እንዳልሆኑ አስታወቀ።
ድርጀቱ፤ ኦባሳንጆ በፌደራል መንግስት ስር እንደወደቁ በመጠቆም ለሌላ አሸማጋይ በሩ ክፍት እንደሆነ አስታውቋል።
በትናንትናው ዕለት ማምሻውን ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ የአፍሪካ ኅብረት የቀንዱ ልዩ መልዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በተያያዘ ያለውን ጠንካራ ቅሬታ አንስቶ፣ የሰላም ሂደቱ ነፃ እና ገለልተኛ አሸማጋይ እንደሚያስፈልገው አጽዕኖት ሰጥቷል።
ህወሓት ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የክልሉ ምክር ቤት ወደ ስራ ከመለሰ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚለውን መጠሪያ ማቆሙ የሚታወስ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኦባሳንጆ መቀለ ሲገቡ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰሩ ያሉት የቀድሞው የፓርቲው አመራሮች ይሁንታን ችረውት ነበር።
ሕወሓት እና የፌዴራላዊ መንግሥቱ የፕሪቶሪያን ስምምነት ከተፈረመ ከጥቂት ወራት በኋላ አራት ዓመት ሊያስቆጥር መሆኑን ያስታወሰው ህወሓት፤ የስምምነቱ ትግበራ በአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ችላ ተብሏል ያለ ሲሆን የስምምነቱ ዕድል በፌዴራል መንግሥቱ ውሳኔ ስር ወድቋል ብሏል።
በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥቱ ስምምነቱን ከመፈጸም ይልቅ ክልሉን በኢኮኖሚ እና ከበባ በማድረግ ከፍተኛ ወድመት አየፈፀመት ነው ሲል ወንጅሏል፡፡
ህወሓት፤ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን፣ ወታደራዊ ከበባን፣ የሥነ-ልቦና ጦርነትን እና ያልተቋረጠ የድሮን ቅኝትን አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ፌደራል መንግስቱን ወቅሷል።
በተጨማሪም ከወር በፊት የተከሰተውን ግጭት በማንሳት ህወሓት “በምዕራብ ትግራይ” በሚገኘው ሸረሪና በተባለ ቦታ በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር እና በልዩ ልዩ አካባቢዎች የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በተደጋጋሚ ጥሷል ብሏል።
አክሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር)ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አደረጉት ባለው ንግግር የስምምነቱን ይዘት ሙሉ በሙሉ መረሳቱን “ሁሉም ነገር ተርስቷል” ማለታቸውን የጠቀሰ ሲሆን፣ ስምምነቱ የተፈረመው በተቋማት ሳይሆን “በሦስት ግለሰቦች” መሆኑን በመግለጽ ስምምነቱ ህያው እንዳልሆነ አሳይተዋል፣ በማለት ወንጅሏቸዋል።
ኦባሳንጆን በተመለከተ ደግሞ በተናጠልና በነፃነት ከመንቀሳቀስ ይልቅ በፌዴራል መንግሥቱ ፍላጎት እየተመሩ እንደሆነ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ኦባሳንጆ በናይጄሪያ የቢያፍራ የእርስ በእርስ ጦርነት የታየውን ሂደት እንደ የሰላም ሞዴል ማቅረባቸውን አግባብ አይደለም ብሏል። ይህን አሉ ያለው ደግሞ የምክክር ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው።
ህወሓት የቢያፍራ ታሪክ ወታደራዊ ከበባን፣ የኢኮኖሚ እገዳን፣ ረሃብን፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ አስከፊ መከራን እና በኃይል የተጫነ ውልን የሚያስታውስ እንጂ በተደራዳሪዎች መካከል የተደረገ የሰላም ስምምነት አይደለም ሲል ገልጾታል።
ኦባሳንጆ በሰኔ ወር ወደ ትግራይ መጥተው ውይይት ካደረጉ በኋላ በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚመለሱ ቃል ገብተው ነበር ያለው ድርጅቱ፣ የፌዴራል መንግሥቱ “የሀገራዊ የምክክር መድረክ” እስከሚያጠናቅቅ ድረስ እንዲጠብቁ ባዘዛቸው መሠረት ጉዟቸውን ሳያሳውቁ ለሁለት ወራት ያህል ዘግይተዋል፤ ይህም ለማደራደር ሳይሆን ቀጥተኛ የመንግስትን ትዕዛዝ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ብሏል።
ህወሓት ኦባሳንጆ ወደ ትግራይ በተመለሱበት ሰዓት ያለ ምንም ቅድመ ማሳወቅ እንዲሁም ጭብጥ ሳይዙ ነው እንደመጡ አስታውቋል።
በተጨማሪም ያለ ተጨባጭ የሰላም ሀሳብ እና ግልጽ የሆነ አጀንዳ ሳይዙ በመምጣታቸው ለሰላም ሂደቱ ያመጡት አዎንታዊ ለውጥ የለም ብሏል።
የዓለም አቀፍ አሸማጋይነት ዋና መመሪያ ገለልተኝነት፣ ነፃነት እና ተከታታይነት ያለው ጥረት መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፤ ኦባሳንጆ እነዚህን መሠረታዊ ባህሪያት ሳያሟሉ ቀርተዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን በማሳወቅ ክልሉ አሁንም ቢሆን ለአስተማማኝ፣ ፍትሐዊና በጊዜ ገደብ የተደገፈ የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

❤12👍9🤔2😈2🤣1
ከጀሞ - ፒያሳ ፈጣን አውቶቡስ መስመር ሊገነባ ነው ተባለ
የአአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳኛቸዉ ሽፈራዉ ከጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ የጀሞ-ፒያሳ የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታን በልዩ ትኩረት እየከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ይህ 15 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት አውቶቡሶች ብቻ የሚጓዙበት የተለየ መስመር የሚኖረው ይሆናል ብለዋል።
ወደ አገልግሎት ሲገባ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ የማጓጓዝ አቅም ስለሚኖረው፣ በአካባቢው የሚታየውን የታክሲ ሰልፍ በእጅጉ እንደሚያቃልል ይጠበቃል።
የትራንስፖርት ቢሮው እንደገለጸው፣ ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክትትል ስርዓት የሚኖረው ሲሆን፣ አውቶቡሶቹ የሚመጡበትን ሰዓት ተሳፋሪዎች አስቀድመው እንዲያውቁ የሚያስችል አሰራርም ይኖረዋል ብለዋል።
ይህ የትራንስፖርት ስርዓት በሌሎች የከተማዋ ዋና ዋና መስመሮች ላይም ተሞክሮው እንዲሰፋ እቅድ ተይዞለታል ተብሏል።

❤10👍7🤪3👌2
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሰሰሰበ
ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ግቢ ውስጥ የሚገኙ የጦር ቄስፎች እና ታጣቂዎች በአስቸኳይ እንዲነሱና ግቢዎቹ ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንዲደረጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።
ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች በላኩት ደብዳቤ፣ በካምፓሶቹ ውስጥ የወታደራዊ ኃይሎችና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው የተማሪዎችን ደህንነትና ሰላማዊ የመማር-ማስተማር ሂደት አደጋ ላይ እንደሚጥል ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ አክሎም፣ የዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢዎች ሙሉ በሙሉ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ መሆናቸው በበቂ ሁኔታ ካልተረጋገጠ ሚኒስቴሩ ወደ ተቋማቱ ተማሪዎችን እንደማይመድብ አስታውቋል።

❤19👍3🤔1
ከማረሚያ ቤት ከተፈታ በሦስተኛ ቀኑ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ቁልፍ የሰረቀው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ።
ከዚህ ቀደም በተጣለበት የፍርድ ውሳኔ መሠረት በማረሚያ ቤት ቆይታ የእስር ጊዜውን አጠናቆ በወጣ በሦስተኛው ቀን በድጋሚ በስርቆት ወንጀል የተከሰሰው አቶ ያሬድ ገብረሚካኤል የተባለው ግለሰብ መሆኑ የአክሱም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
የማዕከላዊ ዞን ዓቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ያለችን እህቱን ለመጠየቅ የመጓጓዣ ገንዘብ እንደሌለው በመግለጽ በዓድዋ ከተማ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው።
ግለሰቡ በተሳፈረበት አምቡላንስ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የተሽከርካሪውን ቁልፍ ሰርቆ ከተሰወረ በኋላ በጸጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በአክሱም ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።የአክሱም ከተማ ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዉን እጅ ከፍንጅ ይዞ በቁጥጥር ስር በማዋሉ አስፈላጊውን ማጣራት በማጠናቀቅ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ አቅርቧል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤትም ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቀረበበትን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ መርምሮ ግለሰቡ በተከሰሰበት የስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

❤14👍3😍1👀1
አምባሳደር ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
የሶማሊላንድ መንግሥት ልምድ ያላቸውን ዲፕሎማትና የህዝብ አስተዳደር ማሻሻያ ባለሙያ አምባሳደር ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድን በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
አዲሱ አምባሳደር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቁልፍ ግንኙነት የማጠናከርና ቀጣናዊ ትስስርን የማሳደግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድ ማናቸው?
🔶 የሥራ ልምድ፦ በሶማሊላንድ መንግሥት የቤተ-መንግሥት የካቢኔ ሴክሬተሪዎች ዋና ስራ አስፈጻሚ (2015–2016)፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር እና በኬንያ የሶማሊላንድ ምክትል አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
🔶 የትምህርት ዝግጅት፦ በትምህርት ጥናት የመጀመሪያ ዲግሪ እና በፕሮጀክት ፕላኒንግና ማኔጅመንት ማስተርስ የተመረቁ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ–አፍሪካ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
👉 የሹመቱ ዋና ዓላማ በአዲስ አበባ እና ሀርጌሳ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ማደራጀትና ማፋጠን መሆኑን የሶማሊላንድ መንግሥት ይፋዊ መግለጫ አመላክቷል።

❤23👍10🤣2
በኢትዮጵያ ከ46 በመቶ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በሱስ ተጠቂ መሆናቸው ተነገረ::
በኢትዮጵያ የወጣቶች የሱስ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን በቅርቡ የተደረገ አንድ ሀገራዊ ጥናት አመላክቷል።
በጥናቱ መሰረት ከ15 እስከ 24 በሚሆን የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶች የሱስ ተጠቂ መሆናቸዉ ተረጋግጧል ሲሉ በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር አስካለማሪያም ቢክስ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
እንደ ዶክተር አስካለማሪያም ገለፃ በወጣቶች ዘንድ የአልኮል ተጠቃሚነት ሱስ ከፍተኛዉን ድርሻ ይይዛል ። ሲጓራ እና ጫትን ጨምሮ ለማስታገሻነት በጥንቃቄ የሚወሰዱ መድኃኒቶችን ወጣቶች ለሱስ እንደሚጠቀሙበት ተገልጿል ።
ወጣቶች ራሳቸዉን ከሱስ ለመጠበቅ እርስ በእርስ መረዳዳት ፣ጊዜያቸዉን ትርጉም ባላቸዉ ነገሮች ላይ ማሳለፍ ፣ስፖርት መስራት እና በሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ መሳተፍ እንዳለባቸዉ ተነግሯል።የሱስ ተጠቂነት የሚያስከትለው ጫና ቀላል አለመሆኑን የሚያስረዱት ስፔሻሊስቷ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ለራሳቸዉ ቅድሚያ በመስጠት ህክምና ማድረግ እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል ።
ሱስ በአካል እንዲሁም በአእምሮ ላይ የሚያሳድረዉን ተፅዕኖ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተገንዝቦ ከመፈረጅ ይልቅ በዙሪያው ያሉ የሱስ ተጠቂዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል ።

❤15🤣6👍4😢2🤔1

❤7👍4😢3🤪2😱1🤣1👀1
ለአዲስ አመት ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የዘንድሮውን የአዲስ አመት በዓል አስመልክቶ በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ተቋሙ በመጪው የአዲስ ዓመት በዓል 4 ሺህ 500 የቁም የእንስሳትን እርድ ለማከናወን ዝግጅት አጠናቋል።
ከእነዚህም መካከል ከ3 ሺህ በላይ በሬዎች እና ከ1 ሺህ 500 በላይ በግና ፍየሎች እርድ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎችም በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬዎችን ደግሞ በ2ሺ 100 ብር የቄራ የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የተጠቀሰው።
ሕብረተሰቡ ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ ሥጋዎችን እንዲያገኝ ወደ ቄራዎች ድርጅት መምጣት እንደሚገባው ጥሪ ቀርቧል።
በበዓሉ የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በአዲስ አበባ በሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች 1 ኪሎ የበሬ ሥጋ 1 ሺህ 200 ብር ሆኖ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተቋሙ ገልጿል።

🤪10👍8❤4😢1
ያለባህር በር ውጤታማ አንሆንም‼️
ያለ ባሕር በር ባለቤትነት በሎጂስቲክስ ዘርፍ ውጤታማ አገር መሆን አይቻልም - የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ዋና ሥራ አስፈጻሚ።
ታከለ ኡማ፣ "የባሕር በር ባለቤትነትን ካላሳካን፣ የፈለግነውን ቴክኖሎጂ ብናለማ፣ የፈለግነውን ያህል መርከብ፣ ባቡር እና የጭነትተሸከርካሪዎችን ብንገዛ ውጤታማ አገር አንሆንም፡፡"ሲሉ ተደምጠዋል።

🤣34❤13👍5🤷♂1🙈1🤪1
ኤኮን በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ሶስት ባለፀጋ ሰዎች ብቻ “Lonely” የተሰኘውን አንድ ዘፈን ብቻ ለአንድ ሰዓት ያህል ደጋግሞ እንዲዘፍን 1 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈለው ገለፀ
ታዋቂው የዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮከብ ኤኮን (Akon) በቅርቡ በነበረው የFlagrant ፖድካስት ቆይታው፥ በአንድ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኝ አንድ ባለጸጋ ቤተሰብ የሙዚቃ ኮንሰርት እንዲዘፍንተቀጥሮ ያስተናገደውን እጅግ አስገራሚ እና እንግዳ የሆነ የኮንሰርት ታሪክ ይፋ አድርጓል።
ድምፃዊው ለግል የሙዚቃ ዝግጅቱ የ1 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ተፈፅሞለት በቅንጦት ቦይንግ 747 የግል አውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ ስፍራው ቢያቀናም፤ ታላቅ መድረክ እና የሌዘር መብራቶች በተዘጋጁበት ግዙፍ አዳራሽ ውስጥ የጠበቁት ግን ሶስት ተመልካቾች ብቻ ነበሩ። በወቅቱ በአዳራሹ መሃል በተቀመጡ ሶስት ወንበሮች ላይ የነበሩት ባለጸጋዋ እናት ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ብቻ የነበሩ ሲሆን፤ ዝግጅቱ እንደተጀመረ የባለጸጋው ቤተሰብ ሴት ልጅ ኤኮን በ2005 ዓ.ም ያወጣውንና ዝነኛ ያደረገውን “Lonely” የተሰኘውን ዘፈን እንዲጫወት ጠየቀችው።
ዘፈኑ ባለቀ ቁጥር እየሳቀች “ድገመው” በማለት ለአንድ ሰዓት ያህል ያንንኑ አንድ ዘፈን ብቻ ደጋግሞ እንዲዘፍን እንዳደረገችው ያስታወሰው ኤኮን፥ ሌላ ዘፈን ለመዝፈን ሲዘጋጅ ፣ እጅግ ተዝናንተናል እናመሰግናለን ይበቃናል ብለዉ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ገልጿል።
ኤኮን ክስተቱን ሲያስታውስ፦ “እጅግ ከፍተኛ ሀብት ሰውን እንደ ‘ግል ሲዲ ማጫወቻ’ (Personal CD Player) ሊያደርግ እንደሚችል የተረዳሁበት ነበር፤ ግን ክፍያዬን በደስታ ይዤ ወጥቻለሁ” ብሏል።

🤣32❤21👍3🤯1
የድሮን ጥቃት‼
አዳሩን በሕንጣሎ ወረዳ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
በትግራይ ክልል ሕንጣሎ ወረዳ ጣብያ ፍረወይኒ «ማይ ሽመት» ልዩ ቦታ ላይ ሌሊት 8:30 ሰዓት ተደጋጋሚ የድሮን ደብደባ መፈፀሙ ታውቋል።
የድሮን ጥቃቱ ኢላማ የህውሃት የጦር መሳሪያ ክምችት ላይ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ህውሃት በበኩሉ በጥቃቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎች (የአራት ዓመት ሕፃንን ጨምሮ) ሲሞቱ፣ የሟቾች እናት ደግሞ በጽኑ መቁሰላቸውንና በንብረት ላይም ከባድ ውድመት መድረሱ አሳውቋል።
ህውሃት መኖሪያ መንደሮችን አስታኮ የጦር መሳሪያ ስለሚያከማች በንፅሃን ላይ ጉዳት እየደረሰ ያለው ክምችቱ በድሮን ሲመታ የሚወድመው ጦር መሳሪያ ፍንዳታ ነው ሲሉ ገለልተኛ ወገኖች እየገለፁ ነው።

❤14😢10👍6
ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የፍልሰት ጉዳዮች ለማስተናገድ፤ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ሊጀምር ነው።
በቢሮው ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ ገልጿል።
መቀመጫውን በአዲስ አበባ የሚያደርገው አዲሱ ቢሮ ለቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔ የሚሰጥ እንዳልሆነ የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
ሆኖም ቢሮው ኢትዮጵያውያን ለፍልሰት ማመልከቻዎቻቸው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራን የሚያከናውን መሆኑን አገልግሎቱ አስገንዝቧል።
የተጠረጠሩ የሰነድ “ማጭበርበሮችን” የሚመረምሩት እና የቤተሰቦችን ዝምድና ለማረጋገጥ የዘረ-መል (DNA) ናሙናዎችን የሚሰበስቡት በአዲስ አበባ የሚከፈተው የአገልግሎቱ ቢሮ ሰራተኞች ይሆናሉ።
እነዚህ ስራዎች ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የነበረው፤ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት እንደነበር ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።
የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት “ወሳኝ የስራ ኃላፊነቶች” ያላቸውን እነዚህን ተግባራት፤ አዲሱ ቢሮ “በቀጥታ ለማከናወን የሚያስችለውን ልዩ ውክልና ይሰጠዋል” ተብሏል።

👍6❤4
ለአዲስ ዓመት በዓል የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተሰርቷል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር እንዳሉት፤ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስና ድንገተኛ ችግሮች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተሰርቷል፡፡
በበዓሉ ዋዜማና በበዓሉ ዕለት ሊከሰቱ የሚችሉ የኃይል መቆራረጦችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የተቋሙ መዋቅሮች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በቅንጅት የተደራጀ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ 24 ሰዓት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክ ቡድን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀት ወደ ሥራ መግባቱንም ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም በሁሉም የአገልግሎቱ ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አጣዳፊ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ የጥገና ቡድኖች መደራጀታቸውን አመልክተዋል።
በበዓሉ ወቅት የሚፈጠረውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ለማመጣጠን ደንበኞች ኃይል ቆጣቢ ቁሳቁሶችን እንዲጠቀሙና የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶቻቸው ለአደጋ የማያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

🤣10❤7👍7
📣[ታላቅ ቅናሽ]
መጪዉን አዲስ አመት በማስመልከት
🌼 ማስተዋወቅ የሚፈልጉት ነገር አለ ?
🌻የምንሠጣቸዉ አገልግሎቶች
🌻 የድርጅት ማስታወቂያ
🌻 የተለያዮ አልባሳት
🌻 የ መድሀኒቶችን ማስታወቂያ
🌻 የክፍት ስራ ቦታ ማስታወቂያ
🌻 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
🌻 የስልክ እና የlaptop
🌻የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
🌻 የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
🌻ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች
🌻የትምህርት ተቋማት…...
🌻 የህክምና ማዕከላት
🌻የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች……
⚡️ ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
🌻 ህጋዊነት ያለውን ማንኛውም ማስታወቂያ እዚህ ቻናላችን ላይ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ
👇
@Addis_reporter_bot

❤3👍2🥰1👌1
መንታ ሆና የተወለደች እናት አምስት (5) ህፃናት በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏን ባለሙያዎች ገለጹ።
በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አበርገለ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ ሲሆኑ በየጭላ መባእታዊ ሆስፒታል አምስት ህፃናትን ወልደዋል።
የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ እናቲቱ ራሷ መንታ ሆና የተወለደች መሆኗን የሚያሳይ የህክምና ታሪክ አላት።
ከአምስቱ ህፃናት መካከል አራቱ የእድገት ሂደታቸውን ሙሉ በሙሉ አጠናቀው የተወለዱ ሲሆን፣ አምስተኛው ህፃን ግን ከአምስተኛው ወር በኋላ የእድገት ሂደቱ በመስተጓጎሉ የተነሳ የእድሜውን እድገት ሳያጠናቅቅ መወለዱን ባለሙያዎቹ አስረድተዋል።
አዋላጅ የጤና ባለሙያዎች እንዳስረዱት፣ እናቲቱም ሆነች አምስቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፣ ተገቢውን የጤና ክትትልም እያገኙ ነው።
ባለሙያዎቹ አክለውም፣ እናቲቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የወለደች መሆኗን ጠቁመው፣ አምስቱን ህፃናት በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ የሚያስችል የተመቻቸ ኑሮና በቂ ገቢ ስለሌላት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

❤18👍6🙈6🥰1