አዲስ አበባ‼️
"በአዲስ አበባ የክረምቱን ማብቃትና የጸደይ (ብራ) መግባት የሚያበስረው የጎቤ እና ሽኖዬ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።"
ወጣቶች ባህላዊ አልባሳት አጊጠው በየጎዳናው፣ በታዋቂ ግለሰቦችና በመንግሥት ኃላፊዎች መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር መልካም ምኞት እየገለፁና ስጦታዎችን እየተቀበሉ ይገኛሉ።
@Addis_Reporter

🤣39❤10👍10🌚2🤔1
የአሜሪካ የግሪን ካርድ ሎተሪ ዕድለኞች የፍርድ ቤት ድል እና አዲስ እገዳ
የአሜሪካ ፌዴራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያና በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ አሳለፈ።
በካሊፎርኒያ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ኤድዋርድ ዳቪላ የቪዛ ሂደቱን አግደው የነበሩ መመሪያዎችን በጊዜያዊነት እንዲቆሙ ወስነዋል።
ይህ ውሳኔ በዲቪ-2026 ፕሮግራም ከተመዘገቡት ከ53 ሺህ በላይ አፍሪካውያን መካከል ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 41 ሺህ የሚጠጉ አመልካቾች ተስፋ የፈነጠቀ ነው።
ሆኖም ይህን ፍትህ ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከጸጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የቪዛ አሰጣጡን በድጋሚ ማገዱ አዳዲስ ስጋቶችን ፈጥሯል። አመልካቾች ሰነዶችን ማቅረብ እና ቃለ መጠይቅ ማድረግ ቢችሉም፣ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከመጠናቀቁ በፊት ቪዛ ካልተሰጣቸው እድሉ ሊባክን ይችላል የሚል ስጋት አለ። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ህጋዊ እንቅፋቶችን ያስወገደ ቢሆንም፣ አዲሱ እገዳ ዕድለኞቹን ባለበት እንዲቆሙ አድርጓል።

❤8👍4🤔2
ከወራት በፊት ህይወቱ ያለፈዉ ብሪታንያ ናይጄሪያዊ ኢጎ ቲኒ የሞቱ ምክኒያት ከብልት ማስተለቅ ህክምና በኋላ የገጠመዉ ተጓዳኝ የጤና ችግር ነዉ ተባለ
የድምጻዊ ዴቪዶ የቅርብ ጓደኛ ነበር የተባለዉና በናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እዉቅና ያለዉ
የጎልማሳዉ ታዋቂ ሰዉ ህልፈት እስካሁን ይፋ ሳይደረግ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም ምክኒያቱ ከታወቀ በኋላ የአለም መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።
ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት በታይላንድ ባንክሆክ የብልቅ ማስተለቅ ህክምና አድርጎ ነበር ተብሏል።
ግለሰቡ ከህክምናዉ በኋላ የልብ ህመም አጋጥሞት ነበር ተብሏል። በተጨማሪም በህክምዉ ሀኪሞች ተጠቅመዉት የነበረዉ 40 ሚሊ ሊትር ሀይሉሮኒክ የተሰኘ አሲድ በሳንባዉ ላይ ተገኝቷል መባሉ ተሰምቷል።
ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ማሳጅ በሚደረግበት ወቅት ሁለት ጊዜ ራሱን ስቶ ነበርም ተብሏል። ግለሰቡ ወዲያዉ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ሳንባዉ የደም ዝዉዉር በመቋረጡ ህይወቱ አልፏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
የድምጻዊ ዴቪዶ የቅርብ ጓደኛ ነበር የተባለዉና በናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እዉቅና ያለዉ
ኢጎ ቲኒ በመጋቢት ወር ነበር በ 43 አመቱ ህይወቱ ማለፉ የተሰማዉ።የጎልማሳዉ ታዋቂ ሰዉ ህልፈት እስካሁን ይፋ ሳይደረግ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም ምክኒያቱ ከታወቀ በኋላ የአለም መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።
ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት በታይላንድ ባንክሆክ የብልቅ ማስተለቅ ህክምና አድርጎ ነበር ተብሏል።
ግለሰቡ ከህክምናዉ በኋላ የልብ ህመም አጋጥሞት ነበር ተብሏል። በተጨማሪም በህክምዉ ሀኪሞች ተጠቅመዉት የነበረዉ 40 ሚሊ ሊትር ሀይሉሮኒክ የተሰኘ አሲድ በሳንባዉ ላይ ተገኝቷል መባሉ ተሰምቷል።
ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ማሳጅ በሚደረግበት ወቅት ሁለት ጊዜ ራሱን ስቶ ነበርም ተብሏል። ግለሰቡ ወዲያዉ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ሳንባዉ የደም ዝዉዉር በመቋረጡ ህይወቱ አልፏል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣15❤11😢6🌚4👍2🤔1👀1
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ዓለማቀፍ ቢሮውን ሊከፍት ነው። የተቋሙ አዲሱ ቢሮ በቀጣዩ ሳምንት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ቢሮው፣ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የውጭ አገር ዜጎችን ሠነዶች የማረጋገጥ፣ የሠነድ ማጭበርበር ድርጊቶችን የመመርመርና የስጋ ዝምድናን ለማረጋገጥ የሚረዱ የዘረመል መረጃዎችን የማጠናቀር ሃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል። እነዚህ ሥራዎች እስካሁን በዋናነት ሲከናወኑ የቆዩት፣ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አማካኝነት ነበር።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤6👍2
ከጦር መርከቦች እስከ ወርቃማ አዳራሽ፤ ትራምፕ
ሁሉም ነገር በስማቸው እንዲጠራ ይፈልጋሉ
"እኔ ከሄድኩ በኋላ የሚያስታውሰኝ የለም"
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ ትላልቅ ሕንፃዎችና መታሰቢያዎች ላይ ስማቸውን ለማስጻፍ አጣዳፊ ሥራ ውስጥ መሆናቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል። ትራምፕ ከኒውዮርክ ማጋዚን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «እኔ ከሄድኩ በኋላ ስሜን ማንም አይጽፈውም» ሲሉ እውነቱን ተናግረዋል። አሁኑኑ ስማቸው እንዲነሳ በማሰብም በሕንፃዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በሳንቲሞችና በጦር መርከቦች ላይ ስማቸውንና ምስላቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
ከእነዚህ ሥራዎቻቸው መካከል ትልቁ የኋይት ሀውስን አንድ ክንፍ በማፍረስ እየገነቡት ያለው ወርቃማ የመዝናኛ አዳራሽና የጦር ማዕከል ነው። ጥይት የማይበሳውና ከመሬት በታች ምሽግ ያለው ይህ ትልቅ ሕንፃ፣ የእሳቸውን ስም ሊይዝ እንደሚገባው ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሰራሩ ሕጋዊ አይደለም በሚል ክስ ቢቀርብበትም፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግንባታው እንዲቀጥል ፈቅዷል።
ትራምፕ ከዚህ በተጨማሪ የሕክምናና የፋይናንስ ፕሮግራሞችን በስማቸው መሰየም ጀምረዋል። አሜሪካ ከእንግዲህ የምትሰራቸውን አዳዲስ የጦር መርከቦችም በስማቸው እንዲጠሩ ይፈልጋሉ። ይህ ሁሉ አጣዳፊ እንቅስቃሴ ከሥልጣን በኋላ ስማቸውና ታሪካቸው ሳይጠፋ እንዲኖር የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን የኢንዲፔንደንት ዘገባ ያመለክታል፡፡

❤16🤣16👍3
26 ስልክና 34 ሺህ ብር የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሉማሜ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች አደረጃጀት ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት 26 ስልክ እና 34,000 ብር የሰረቀን ግለሠብ በቁጥጥር ስር አውለዋል።

❤16👍9😢2
አቶ አማኑኤል አሰፋ ምን አሉ❓
የፌደራል መንግሥቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የህልውና አደጋ በመሆኑ በትግል መገርሰስ ያለበት ሀይል ነው:-የህወሓት ምክትል ፕረዚደንት አቶ አማኒኤል አሰፋ‼️
አቶ አማኒኤል አሰፋ ዛሬ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም ምሽት ከትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ የፌደራል መንግስቱ ወንጀለኛ እና ሰላማዊ ንግግር ማድረግ የማይችል ሀይል በመሆኑ በኢትዮጵያ ትብብር ሀይሎች መወገድ ያለበት እንደሆነ ስምምነት ላይ መደረሱም ገልፀዋል።
አቶ አማኑኤል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁናዊ ትግልም አብዪ አህመድ በሌላ ሰው የመቀየር እና ግለ ሰዎች በስልጣን የመቀያየር ጉዳይ ሳይሆን እውነተኛ ለውጥ የመምጣት ትግል ነው ብሏል።
አቶ አማኑኤል አሰፋ ይህንን ማለታቸው በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተወራ ያለውን የድርድር ተስፋ ያጨለመ ሆኗል።
የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ሁለቱን አካላት ለማደራደር ጥረት መጀመራቸው ይታወቃል።

👍13🤣11❤7🤪1
አርሰናል 3ኛ ተከታታይ ድሉን አሳካ
በሦስተኛ ሳምንት እጅግ ተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ቼልሲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በኢምሬትስ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ አስቆጥረዋል።
ቼልሲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በሊጉ ያደረጋቸውን ተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ድል አድርጓል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል።
አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቱ ይታወቃል።

👍22❤17🤪4🥰2🍾2🤔1😢1🎉1🏆1
ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊለቁ ነው!
ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት አቶ ልደቱ፤ ሀሳብን በዜማ በሚል ለአዲስ አመት የሙዚቃ አልበም ሊያሰራጩ መሆኑን ገልጸዋል።
ፖለቲከኛው አዲስ የከፈቱትን የዩቲዩብ ገጽ ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንዳሳወቁት የሙዚቃ አልበሙን ያዘጋጁት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ነው።
እንደሚታወሰው ቴዲ አፍሮ ኢቶሪካ አልበሙን ካሰራጨ በኋላ የፈጠረውን ተጽእኖ ተከትሎ አቶ ልደቱ በወቅቱ፣ "የመንፈስ ቅናት አደረብኝ" ሲሉ ገልጸው ነበር።

🤣80❤15👍11🙈2🤪2👀1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-
✅ከጠዋቱ 2፡00-9፡30
👉ጎፋ ካምፕ ፣ ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ መብራት ፣ ቆሬ አደባባይ ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም በከፊል፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው፣
👉ኮዬ 05 ፕሮጀክት 16 በከፊል፣ ፕሮጀክት 12 ፣ ፕሮጀክት 17 እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

👍5❤4
በመቀሌ እና ድሬዳዋ ከተሞች አበባ'ን የማምረት እንቅስቃሴ የተቀዛቀዘ እንደሆነ ተነገረ
በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የአበባ ምርት በስፋት እየተካሄደባቸው ያሉ ምቹ አካባቢዎች መኖራቸውን የተገለጸው ሲሆን በመቀሌ እና ድሬዳዋ ከተሞች ግን መቀዛቀዝ እንደታየባቸዉ ተገልጿል።
ከኢትዮ ኤፌም ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ አበባ ፥ ፍራፍሬ እና አትክልት አምራቾች ማህበር ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ ዘዉዴ እንደሚሉት አዳዲስ የአበባ ምርት ኢንቨስትመንት ሀኔታዎች መኖራቸውን ይገልጻል።
ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲገቡ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነዉ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ መቀሌ ላይ ብዙም እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀዋል በተመሳሳይ መልኩ ድሬዳዋ ከተማ አበባን በተመለከተ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እንዳለ ተናግረዋል።
በባቱ ፣ቢሾፍቱ ፥ሆለታ እና ሰበታ ሰፋፊ የአበባ እርሻ የሚካሄድባቸው መሆኑን ያነሱት የማህበሩ ዳይሬክተር በባህርዳር ዙሪያ አየር መንገዱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸዉን እና ለዉጪ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ያሉ ኩባንያዎች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።
አሁን ላይ በጉራጌ ዞን አካባቢ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መሬቶች መኖራቸዉን ተለይቶ ሂደቶች መጀመራቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በሀዋሳ ከ100 ሄክታር በላይ የአበባ እርሻ የሚገኝበት አካባቢ መሆኑ ተጠቅሷል።
የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ የአበባ ምርት ከሌሎች የሆልቲካልቸር ምርቶች በገዘፈ መልኩ እድገቱ መሻሻሎች እንደታየበት መሆኑን ጠቅሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሎጀስቲክ አቅሙን ከፍ ማድረጉን ተከትሎ ለምርቱ ተፎካካሪነት እድል ፈጥሯል ሲሉም ይገልፃሉ።

❤8👍5😢2
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች ሀገራት የዲቪ-2026 አመልካቾች ተስፋ ሰጪ ውሳኔ አስተላለፈ
የካሊፎርኒያ ክልላዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ኤድዋርድ ዳቪላ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚስቴር በዲቪ አመልካቾች ላይ ተጥለው የነበሩ የቪዛ እገዳዎችን የሚያነሳ ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ48 ሀገራት አመልካቾች የቪዛ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ መንገድ መከፈቱ ተገለጸ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚስቴር ቀደም ሲል ጥሎት የነበረውን እገዳ ያነሳ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ አመልካቾች እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የዲቪ-2026 ፕሮግራም ገደብ ውስጥ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ እና የተያዙላቸውን ቃለ-መጠይቆች መከታተል እንደሚችሉ አስታውቋል።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ሲሆን፣ ከ49 የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 53 ሺህ 939 ሰዎች በDV-2026 ተመዝግበው ይገኛሉ።
ከእነዚህ መካከል ግብፅ በ5,527 ከፍተኛውን ቁጥር ስትይዝ፣ አልጄሪያ በ5,457፣ ሱዳን በ5,226፣ ኬንያ በ3,949 እንዲሁም ኢትዮጵያ በ3,287 አመልካቾች ቀጣዩን ደረጃ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
ባለፉት አምስት ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ የላኩ እንደ ናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ አልተካተቱም።
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ20.8 ሚሊዮን በላይ ብቁ ተወዳዳሪዎች መካከል 129,516 ሰዎች ለዲቪ-2026 የተመረጡ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በየዓመቱ እስከ 55 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የአሜሪካ ቋሚ መኖሪያ ቪዛ ይሰጣል።

👍14❤13🤯2🙏1👌1
ህወሓት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በፌደራል መንግስት ይሁንታ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ለአሸማጋይነት ብቁ አይደሉም አለ‼️
የትግራይ ክልል መንግስትን በኃይል የተቆጣጠረው እና በምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን የተነፈገው ህወሓት፤ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ከፌደራል መንግስት ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚቀበሉ፣ ግልፅ የሆነ የሰላም አጀንዳ እንዲሁም የሰላም ሃሳብ ሳይዙ የሚንቀሳቀሱ፣ የዓለም አቀፍ አሸማጋይነት ዋና መመሪያ የሆኑትን ነጻ እና ገለልተኝነት፣ ተከታታይነት ያለው ጥረት የማያደርጉ እና ይህን መስፈርት የማያሟሉ መሆናቸውን በመጥቀስ ለአሸማጋይነት ብቁ እንዳልሆኑ አስታወቀ።
ድርጀቱ፤ ኦባሳንጆ በፌደራል መንግስት ስር እንደወደቁ በመጠቆም ለሌላ አሸማጋይ በሩ ክፍት እንደሆነ አስታውቋል።
በትናንትናው ዕለት ማምሻውን ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ የአፍሪካ ኅብረት የቀንዱ ልዩ መልዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በተያያዘ ያለውን ጠንካራ ቅሬታ አንስቶ፣ የሰላም ሂደቱ ነፃ እና ገለልተኛ አሸማጋይ እንደሚያስፈልገው አጽዕኖት ሰጥቷል።
ህወሓት ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የክልሉ ምክር ቤት ወደ ስራ ከመለሰ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚለውን መጠሪያ ማቆሙ የሚታወስ ሲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኦባሳንጆ መቀለ ሲገቡ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰሩ ያሉት የቀድሞው የፓርቲው አመራሮች ይሁንታን ችረውት ነበር።
ሕወሓት እና የፌዴራላዊ መንግሥቱ የፕሪቶሪያን ስምምነት ከተፈረመ ከጥቂት ወራት በኋላ አራት ዓመት ሊያስቆጥር መሆኑን ያስታወሰው ህወሓት፤ የስምምነቱ ትግበራ በአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እና በዓለም አቀፍ አጋሮች ችላ ተብሏል ያለ ሲሆን የስምምነቱ ዕድል በፌዴራል መንግሥቱ ውሳኔ ስር ወድቋል ብሏል።
በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥቱ ስምምነቱን ከመፈጸም ይልቅ ክልሉን በኢኮኖሚ እና ከበባ በማድረግ ከፍተኛ ወድመት አየፈፀመት ነው ሲል ወንጅሏል፡፡
ህወሓት፤ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን፣ ወታደራዊ ከበባን፣ የሥነ-ልቦና ጦርነትን እና ያልተቋረጠ የድሮን ቅኝትን አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ፌደራል መንግስቱን ወቅሷል።
በተጨማሪም ከወር በፊት የተከሰተውን ግጭት በማንሳት ህወሓት “በምዕራብ ትግራይ” በሚገኘው ሸረሪና በተባለ ቦታ በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር እና በልዩ ልዩ አካባቢዎች የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በተደጋጋሚ ጥሷል ብሏል።
አክሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን (ዶ/ር)ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አደረጉት ባለው ንግግር የስምምነቱን ይዘት ሙሉ በሙሉ መረሳቱን “ሁሉም ነገር ተርስቷል” ማለታቸውን የጠቀሰ ሲሆን፣ ስምምነቱ የተፈረመው በተቋማት ሳይሆን “በሦስት ግለሰቦች” መሆኑን በመግለጽ ስምምነቱ ህያው እንዳልሆነ አሳይተዋል፣ በማለት ወንጅሏቸዋል።
ኦባሳንጆን በተመለከተ ደግሞ በተናጠልና በነፃነት ከመንቀሳቀስ ይልቅ በፌዴራል መንግሥቱ ፍላጎት እየተመሩ እንደሆነ ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ኦባሳንጆ በናይጄሪያ የቢያፍራ የእርስ በእርስ ጦርነት የታየውን ሂደት እንደ የሰላም ሞዴል ማቅረባቸውን አግባብ አይደለም ብሏል። ይህን አሉ ያለው ደግሞ የምክክር ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው።
ህወሓት የቢያፍራ ታሪክ ወታደራዊ ከበባን፣ የኢኮኖሚ እገዳን፣ ረሃብን፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ አስከፊ መከራን እና በኃይል የተጫነ ውልን የሚያስታውስ እንጂ በተደራዳሪዎች መካከል የተደረገ የሰላም ስምምነት አይደለም ሲል ገልጾታል።
ኦባሳንጆ በሰኔ ወር ወደ ትግራይ መጥተው ውይይት ካደረጉ በኋላ በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚመለሱ ቃል ገብተው ነበር ያለው ድርጅቱ፣ የፌዴራል መንግሥቱ “የሀገራዊ የምክክር መድረክ” እስከሚያጠናቅቅ ድረስ እንዲጠብቁ ባዘዛቸው መሠረት ጉዟቸውን ሳያሳውቁ ለሁለት ወራት ያህል ዘግይተዋል፤ ይህም ለማደራደር ሳይሆን ቀጥተኛ የመንግስትን ትዕዛዝ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ብሏል።
ህወሓት ኦባሳንጆ ወደ ትግራይ በተመለሱበት ሰዓት ያለ ምንም ቅድመ ማሳወቅ እንዲሁም ጭብጥ ሳይዙ ነው እንደመጡ አስታውቋል።
በተጨማሪም ያለ ተጨባጭ የሰላም ሀሳብ እና ግልጽ የሆነ አጀንዳ ሳይዙ በመምጣታቸው ለሰላም ሂደቱ ያመጡት አዎንታዊ ለውጥ የለም ብሏል።
የዓለም አቀፍ አሸማጋይነት ዋና መመሪያ ገለልተኝነት፣ ነፃነት እና ተከታታይነት ያለው ጥረት መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፤ ኦባሳንጆ እነዚህን መሠረታዊ ባህሪያት ሳያሟሉ ቀርተዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን በማሳወቅ ክልሉ አሁንም ቢሆን ለአስተማማኝ፣ ፍትሐዊና በጊዜ ገደብ የተደገፈ የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

❤12👍9🤔2😈2🤣1
ከጀሞ - ፒያሳ ፈጣን አውቶቡስ መስመር ሊገነባ ነው ተባለ
የአአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳኛቸዉ ሽፈራዉ ከጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ የጀሞ-ፒያሳ የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታን በልዩ ትኩረት እየከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ይህ 15 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት አውቶቡሶች ብቻ የሚጓዙበት የተለየ መስመር የሚኖረው ይሆናል ብለዋል።
ወደ አገልግሎት ሲገባ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ የማጓጓዝ አቅም ስለሚኖረው፣ በአካባቢው የሚታየውን የታክሲ ሰልፍ በእጅጉ እንደሚያቃልል ይጠበቃል።
የትራንስፖርት ቢሮው እንደገለጸው፣ ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክትትል ስርዓት የሚኖረው ሲሆን፣ አውቶቡሶቹ የሚመጡበትን ሰዓት ተሳፋሪዎች አስቀድመው እንዲያውቁ የሚያስችል አሰራርም ይኖረዋል ብለዋል።
ይህ የትራንስፖርት ስርዓት በሌሎች የከተማዋ ዋና ዋና መስመሮች ላይም ተሞክሮው እንዲሰፋ እቅድ ተይዞለታል ተብሏል።

❤10👍7🤪3👌2
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሰሰሰበ
ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀሌ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ግቢ ውስጥ የሚገኙ የጦር ቄስፎች እና ታጣቂዎች በአስቸኳይ እንዲነሱና ግቢዎቹ ከማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ እንዲደረጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።
ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች በላኩት ደብዳቤ፣ በካምፓሶቹ ውስጥ የወታደራዊ ኃይሎችና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው የተማሪዎችን ደህንነትና ሰላማዊ የመማር-ማስተማር ሂደት አደጋ ላይ እንደሚጥል ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ አክሎም፣ የዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢዎች ሙሉ በሙሉ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ መሆናቸው በበቂ ሁኔታ ካልተረጋገጠ ሚኒስቴሩ ወደ ተቋማቱ ተማሪዎችን እንደማይመድብ አስታውቋል።

❤19👍3🤔1
ከማረሚያ ቤት ከተፈታ በሦስተኛ ቀኑ የአምቡላንስ ተሽከርካሪ ቁልፍ የሰረቀው ግለሰብ በጽኑ እሥራት ተቀጣ።
ከዚህ ቀደም በተጣለበት የፍርድ ውሳኔ መሠረት በማረሚያ ቤት ቆይታ የእስር ጊዜውን አጠናቆ በወጣ በሦስተኛው ቀን በድጋሚ በስርቆት ወንጀል የተከሰሰው አቶ ያሬድ ገብረሚካኤል የተባለው ግለሰብ መሆኑ የአክሱም ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
የማዕከላዊ ዞን ዓቃቤ ሕግ ቢሮ እንዳስታወቀው ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው፣ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ያለችን እህቱን ለመጠየቅ የመጓጓዣ ገንዘብ እንደሌለው በመግለጽ በዓድዋ ከተማ ቀይ መስቀል ማህበር አምቡላንስ ተሳፍሮ በመጓዝ ላይ በነበረበት ወቅት ነው።
ግለሰቡ በተሳፈረበት አምቡላንስ ውስጥ ተቀምጦ የነበረውን የተሽከርካሪውን ቁልፍ ሰርቆ ከተሰወረ በኋላ በጸጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በአክሱም ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።የአክሱም ከተማ ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዉን እጅ ከፍንጅ ይዞ በቁጥጥር ስር በማዋሉ አስፈላጊውን ማጣራት በማጠናቀቅ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ አቅርቧል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤትም ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የቀረበበትን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ መርምሮ ግለሰቡ በተከሰሰበት የስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

❤14👍3😍1👀1
አምባሳደር ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
የሶማሊላንድ መንግሥት ልምድ ያላቸውን ዲፕሎማትና የህዝብ አስተዳደር ማሻሻያ ባለሙያ አምባሳደር ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድን በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
አዲሱ አምባሳደር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቁልፍ ግንኙነት የማጠናከርና ቀጣናዊ ትስስርን የማሳደግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ሻርማርክ አሕመድ ሙሁመድ ማናቸው?
🔶 የሥራ ልምድ፦ በሶማሊላንድ መንግሥት የቤተ-መንግሥት የካቢኔ ሴክሬተሪዎች ዋና ስራ አስፈጻሚ (2015–2016)፣ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር እና በኬንያ የሶማሊላንድ ምክትል አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።
🔶 የትምህርት ዝግጅት፦ በትምህርት ጥናት የመጀመሪያ ዲግሪ እና በፕሮጀክት ፕላኒንግና ማኔጅመንት ማስተርስ የተመረቁ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ–አፍሪካ የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
👉 የሹመቱ ዋና ዓላማ በአዲስ አበባ እና ሀርጌሳ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ማደራጀትና ማፋጠን መሆኑን የሶማሊላንድ መንግሥት ይፋዊ መግለጫ አመላክቷል።

❤23👍10🤣2