አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በጦርነቱ የተጎዱ ወደ ዩኒቨርስቲ‼️
ህወሃት በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን እና የአካል ጉዳተኞችን ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች እያጓጓዘ ይገኛል።
ከላይ የተያያዘው ምስል ጉዳት የደረሰባቸው እና የአካል ጉዳተኞች ከኩሓ መለስ ካምፓስ ወደ አክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲጫኑ የሚያሳይ ምስል ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍7🤪4🕊2✍1🤔1
ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ከነሐሴ 21 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አደረኩት ባለው ክትትል፣ 470.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ እና 81 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችን በድምሩ 551.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታውቋል።

ከተያዙት እቃዎች መካከል ጨርቃጨርቅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ መዋቢያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል።

በኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ የጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚ ሲሆኑ  ቅርንጫፎቹ በቅደም ተከተል 186 ሚሊዮን፣ 117 ሚሊዮን እና 116 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን ይዘዋል።

እቃዎቹ በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ ላይ በተደረገ ክትትል የተያዙ ሲሆን፣ 26 ተጠርጣሪዎችና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ መግለፁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች ።

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚሠራ ሲሆን፣ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍3
ኢትዮጵያ በ83 ቢ. ብር ወጪ 16
ግዙፍ መርከቦችን ልትገዛ ነው

ኢትዮጵያ የውጪና የገቢ ምርቶቿን የሎጂስቲክስ አቅርቦት ለማቀላጠፍ በ83 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ወጪ 16 አዳዲስ መርከቦችን ለመግዛት አቅዳለች። በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የሚከናወነው ይህ የግዥ እቅድ አሁን ካሉት 10 መርከቦች በተጨማሪ የሚከናወን ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከነበሩት ከ25 ሺህ እስከ 28 ሺህ ቶን አቅም በበለጠ ከ50 ሺህ እስከ 63 ሺህ ቶን የመሸከም አቅም ያላቸው ግዙፍ መርከቦችን የሚያካትት ነው።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት መርከቦች በላይ ሕጋዊ የግዥ ሥርዓት በሂደት ላይ ይገኛል። አዲሶቹ መርከቦች ስትራቴጂክ ግብዓቶችን በብቃት በማስገባትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በወቅቱ በመላክ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14🤪4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት የተረፈው ግለሰብ !

በአሜሪካን፣ ኒውዮርክ ውስጥ " ስታተን አይላንድ " የተባለ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ቶማስ ፋህሚ የተባለ ግለሰብ ከመኪናው 15 እስከ 20 ጫማ ርቀት ላይ ሳለ በድንገት በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት ተርፏል።

ቪዲዮውን ከላይ  እንደምትመለከቱት  ግለሰቡ ከመኪናው ወርዶ ብዙም ሳይሄድ ነው በከባድ መብረቅ ተመትቶ ከሞት አፋፍ የተረፈው።

በአካባቢው በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ የተከሰተው ይህ አስደንጋጭ አደጋ ፋህሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የስነ-ልቦና ስቃይ ፈጥሯል።

በመብረቅ በተመታበት ወቅት በሁለቱም እግሮቹ ላይ ከባድ የመቃጠል ስሜት፣ የመደንዘዝ እና ከፍተኛ የህመም ስሜት እንደተሰማው ምስክርነቱን ሰጥቷል።

አደጋው ከተከሰተ በኋላ " በሌላ መብረቅ እመታለሁ " የሚል ከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት አድሮበት እንደነበር ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት በህክምና ክትትል ከጉዳቱ በማገገም ላይ ያለው ቶማስ ፋህሚ፣ ይህ አስከፊ አደጋ በህይወት ላይ ያለውን አመለካከት ሙሉ በሙሉ እንደቀየረው ይናገራል።

አደጋው ህይወትን ማድነቅ፣ ንጹህ አየርን መተንፈስ፣ ለዕለት ተዕለት ኑሮ ትልቅ ዋጋን መስጠት እንዳለበት አስተምሮታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤24👍3🤯2🙏2🤔1🙈1🙊1
አፍሪካ ታሪካዊ ድል ተቀዳጀች፤ የተዛባው የዓለም ካርታ ሊቀየር ነው!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የአፍሪካን ትክክለኛ የቆዳ ስፋት በአግባቡ የሚያሳየውን አዲሱን "Equal Earth" የዓለም ካርታ ለመጠቀም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ በሚባል ደረጃ አጽድቋል።
የድምፅ አሰጣጥ ውጤት፦

• 164 ሀገራት፦ ደግፈው አድቅቀዋል
• 1 ሀገር፦ ተቃውሟል እሷም አሜሪካ ነች
• 6 ሀገራት፦ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል

ውሳኔው በቶጎ አስተባባሪነት፣ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትና በአፍሪካ ህብረት አጋርነት የቀረበ ታሪካዊ እርምጃ ነው።
ይህ ውሳኔ ለምን አስፈለገ?

እስከዛሬ ስንጠቀምበት የነበረው "Mercator" በመባል የሚታወቀው የዓለም ካርታ የሀገራትን ትክክለኛ ስፋት አዛብቶ የሚያሳይ ነበር። 

በካርታው ምክንያት በምድር ወገብ አቅራቢያ የሚገኙ እንደ አፍሪካ ያሉ አህጉራት በጣም አነስተኛ ሆነው ሲታዩ፣ ወደ ሰሜንና ደቡብ ዋልታ የተጠጉ ሀገራት ደግሞ ካላቸው ስፋት በላይ ገዝፈው ይታዩ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤32🥱10👍3🤷3🤣2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ምሽት መርካቶ 4ኛ አካባቢ አደገኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን በሱቆች እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።።
እሳቱ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍9😢9🤔6💔3😱1
በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው
የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 «ሸማ ተራ» አካባቢ ተከስቶ  የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንደገለጹት፤ አደጋውን በፍጥነት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ትብብር አድርገዋል።

በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤና የደረሰው የጉዳት መጠን  እየተጣራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ የተደረገው ፈጣን ርብርብ አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍7😢6
#AddisAbaba

"እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል" - ቢሮው

የአከራይና ተከራይ የውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል።

ቢሮው የውል ምዝገባና እድሳት ስራው እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ጊዜ ገደብ አስቀምጦ ነበር።

ይሁን እንጅ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በጊዜው አሟልተው ያልቀረቡ፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ ምክንያት ከአዲስ አበባና ከሀገር ውጭ የነበሩ ተዋዋዮች መኖራቸውን አስታውቋል።

በህብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት የመጨረሻ ተጨማሪ እድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ገልጿል።

በመሆኑም እስካሁን ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮችና ተከራዮች ይህንን በተሰጠው የመጨረሻ እድል በክፍለ ከተሞች፣ በሁሉም የመሶብ አንድ ማዕከላት እና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ቦታዎች  በመቅረብ ውላቸውን እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍4🤔2
የፊርማ ውዝግብ ሳቮር አዲስ ሆቴልን ስራ እንዲያቆም ሊዳርገው ነው ተባለ

​በአዲስ አበባ ኤምባሲዎችንና ዓለም አቀፍ ተቋማትን በማስተናገድ የሚታወቀው ሳቮር አዲስ የሬስቶራንት ንግድ፣ በደንበኞች ማጣት ሳይሆን በባለቤቶቹ የፊርማ ውዝግብ ምክንያት የመዘጋት አደጋ ተጋርጦበታል።

​ከስድስት ዓመት በፊት የተፋቱት ሁለቱ መሥራች ባለአክሲዮኖች የ50 በመቶ ድርሻቸውን ሳያካፍሉ በመቆየታቸው፣ ፍርድ ቤት ለማንኛውም የገንዘብ እንቅስቃሴ የሁለቱም ፊርማ አስፈላጊ መሆኑን ወስኗል።

በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የባንክ ሂሳቦች በመታገዳቸው ሥራው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል።

​በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ወገኖች የሥራ ባልደረቦችን ደሞዝ፣ የግብር ክፍያ እና ለአቅርቦት ሰጪዎች የሚከፈል የ32 ሚሊዮን ብር ዕዳን በተመለከተ እርስ በእርስ በመካሰስ ላይ ይገኛሉ።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማጽናቱና የሂሳብ እንቅስቃሴዎች በመታገዳቸው፣ 157 ሠራተኞችን የሚያስተዳድረው ይህ ድርጅት በቅርቡ በሩን ሙሉ በሙሉ ሊዘጋ እንደሚችል ተስጋቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍3😢2
ናይጄሪያውያን ወጣቶች ኩላሊታቸውን
በ1,000 ዶላር እየሸጡ ነው

"ኩላሊታችሁን ሳይሆን ሀሳባችሁን ሽጡ"

በናይጄሪያ በተከሰተው  የከፋ የኑሮ ውድነትና ድህነት ሳቢያ ወጣቶች ኩላሊታቸውን  በ1,100 ዶላር  እየሸጡ መሆኑ ተሰምቷል። የቀድሞው የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቲኩ አቡበከር ይህን አሳዛኝ ሁኔታ በማንሳት ጥልቅ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የችግሩ መንስኤ እና ወቅታዊ ሁኔታ፡

*የምግብ፣ የትራንስፖርትና የቤት ኪራይ ዋጋዎች እጅግ መናራቸው ለዚህ ችግር ዳርጓቸዋል።

* ፖሊስ ሁለት የህክምና  ባለሙያዎችን ጨምሮ በአራት ግለሰቦች ላይ ህገ-ወጥ የሰዎች አካል ዝውውር ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

  ምንም እንኳን ሪፖርቶቹ ሙሉ በሙሉ ባይረጋገጡም፣ የኢኮኖሚ ቀውሱ የሰውን አካል እስከ መሸጥ ማድረሱ ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።

የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት መልእክት፡  ወጣቶች መሸጥ የሚገባቸው አካላቸውን ሳይሆን የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን ሊሆን ይገባል ሲሉ አቲኩ አቡበከር አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢35❤16👍5
አዲስ አበባ‼️
"በአዲስ አበባ የክረምቱን ማብቃትና የጸደይ (ብራ) መግባት የሚያበስረው የጎቤ እና ሽኖዬ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።"

ወጣቶች ባህላዊ አልባሳት አጊጠው በየጎዳናው፣ በታዋቂ ግለሰቦችና በመንግሥት ኃላፊዎች መኖሪያ ቤቶች በመዘዋወር መልካም ምኞት እየገለፁና ስጦታዎችን እየተቀበሉ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣39❤10👍10🌚2🤔1
የአሜሪካ የግሪን ካርድ ሎተሪ ዕድለኞች የፍርድ ቤት ድል እና አዲስ እገዳ

የአሜሪካ ፌዴራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያና በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የዲቪ ሎተሪ ዕድለኞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ አሳለፈ።

በካሊፎርኒያ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ኤድዋርድ ዳቪላ የቪዛ ሂደቱን አግደው የነበሩ መመሪያዎችን በጊዜያዊነት እንዲቆሙ ወስነዋል።

ይህ ውሳኔ በዲቪ-2026 ፕሮግራም ከተመዘገቡት ከ53 ሺህ በላይ አፍሪካውያን መካከል ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 41 ሺህ የሚጠጉ አመልካቾች ተስፋ የፈነጠቀ ነው።

ሆኖም ይህን ፍትህ ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከጸጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የቪዛ አሰጣጡን በድጋሚ ማገዱ አዳዲስ ስጋቶችን ፈጥሯል። አመልካቾች ሰነዶችን ማቅረብ እና ቃለ መጠይቅ ማድረግ ቢችሉም፣ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከመጠናቀቁ በፊት ቪዛ ካልተሰጣቸው እድሉ ሊባክን ይችላል የሚል ስጋት አለ። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ህጋዊ እንቅፋቶችን ያስወገደ ቢሆንም፣ አዲሱ እገዳ ዕድለኞቹን ባለበት እንዲቆሙ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍4🤔2
ከወራት በፊት ህይወቱ ያለፈዉ ብሪታንያ ናይጄሪያዊ ኢጎ ቲኒ የሞቱ ምክኒያት ከብልት ማስተለቅ ህክምና በኋላ የገጠመዉ ተጓዳኝ የጤና ችግር ነዉ ተባለ

የድምጻዊ ዴቪዶ የቅርብ ጓደኛ ነበር የተባለዉና በናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እዉቅና ያለዉ ኢጎ ቲኒ በመጋቢት ወር ነበር በ 43 አመቱ ህይወቱ ማለፉ የተሰማዉ።

የጎልማሳዉ ታዋቂ ሰዉ ህልፈት እስካሁን ይፋ ሳይደረግ ቆይቶ የነበረ ቢሆንም ምክኒያቱ ከታወቀ በኋላ የአለም መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።

ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት በታይላንድ ባንክሆክ የብልቅ ማስተለቅ ህክምና አድርጎ ነበር ተብሏል።

ግለሰቡ ከህክምናዉ በኋላ የልብ ህመም አጋጥሞት ነበር ተብሏል። በተጨማሪም በህክምዉ ሀኪሞች ተጠቅመዉት የነበረዉ 40 ሚሊ ሊትር ሀይሉሮኒክ የተሰኘ አሲድ በሳንባዉ ላይ ተገኝቷል መባሉ ተሰምቷል።

ግለሰቡ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ማሳጅ በሚደረግበት ወቅት ሁለት ጊዜ ራሱን ስቶ ነበርም ተብሏል። ግለሰቡ ወዲያዉ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ሳንባዉ የደም ዝዉዉር በመቋረጡ ህይወቱ አልፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣15❤11😢6🌚4👍2🤔1👀1
የአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት፣ አዲስ አበባ ውስጥ ዓለማቀፍ ቢሮውን ሊከፍት ነው። የተቋሙ አዲሱ ቢሮ በቀጣዩ ሳምንት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር መስሪያ ቤቱ ሰሞኑን ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። ቢሮው፣ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የውጭ አገር ዜጎችን ሠነዶች የማረጋገጥ፣ የሠነድ ማጭበርበር ድርጊቶችን የመመርመርና የስጋ ዝምድናን ለማረጋገጥ የሚረዱ የዘረመል መረጃዎችን የማጠናቀር ሃላፊነት ይኖረዋል ተብሏል። እነዚህ ሥራዎች እስካሁን በዋናነት ሲከናወኑ የቆዩት፣ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አማካኝነት ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤6👍2
ከጦር መርከቦች እስከ ወርቃማ አዳራሽ፤ ትራምፕ
ሁሉም ነገር በስማቸው  እንዲጠራ ይፈልጋሉ

"እኔ ከሄድኩ በኋላ የሚያስታውሰኝ የለም"

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙ ትላልቅ ሕንፃዎችና መታሰቢያዎች ላይ ስማቸውን ለማስጻፍ አጣዳፊ ሥራ ውስጥ መሆናቸውን ዘ ኢንዲፔንደንት  ዘግቧል። ትራምፕ ከኒውዮርክ ማጋዚን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «እኔ ከሄድኩ በኋላ ስሜን ማንም አይጽፈውም» ሲሉ እውነቱን ተናግረዋል። አሁኑኑ ስማቸው እንዲነሳ በማሰብም በሕንፃዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በሳንቲሞችና በጦር መርከቦች ላይ ስማቸውንና ምስላቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።

ከእነዚህ ሥራዎቻቸው መካከል ትልቁ የኋይት ሀውስን አንድ ክንፍ በማፍረስ እየገነቡት ያለው ወርቃማ የመዝናኛ አዳራሽና የጦር ማዕከል ነው። ጥይት የማይበሳውና ከመሬት በታች ምሽግ ያለው ይህ ትልቅ ሕንፃ፣ የእሳቸውን ስም ሊይዝ እንደሚገባው ተናግረዋል። ምንም እንኳን አሰራሩ ሕጋዊ አይደለም በሚል ክስ ቢቀርብበትም፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግንባታው እንዲቀጥል ፈቅዷል።

ትራምፕ ከዚህ በተጨማሪ የሕክምናና የፋይናንስ ፕሮግራሞችን በስማቸው መሰየም ጀምረዋል። አሜሪካ ከእንግዲህ የምትሰራቸውን አዳዲስ የጦር መርከቦችም በስማቸው እንዲጠሩ ይፈልጋሉ። ይህ ሁሉ አጣዳፊ እንቅስቃሴ ከሥልጣን በኋላ ስማቸውና ታሪካቸው ሳይጠፋ እንዲኖር  የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን የኢንዲፔንደንት ዘገባ ያመለክታል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16🤣16👍3
26 ስልክና 34 ሺህ ብር የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሉማሜ ከተማ አስተዳደር  የወጣቶች አደረጃጀት ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት 26 ስልክ እና 34,000 ብር የሰረቀን ግለሠብ በቁጥጥር ስር አውለዋል።
‎
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍9😢2
አቶ አማኑኤል አሰፋ ምን አሉ❓
የፌደራል መንግሥቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የህልውና አደጋ በመሆኑ በትግል መገርሰስ ያለበት ሀይል ነው:-የህወሓት ምክትል ፕረዚደንት አቶ አማኒኤል አሰፋ‼️
አቶ አማኒኤል አሰፋ ዛሬ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም ምሽት ከትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ የፌደራል መንግስቱ ወንጀለኛ እና ሰላማዊ ንግግር ማድረግ የማይችል ሀይል በመሆኑ በኢትዮጵያ ትብብር ሀይሎች መወገድ ያለበት እንደሆነ ስምምነት ላይ መደረሱም ገልፀዋል።
አቶ አማኑኤል፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁናዊ ትግልም አብዪ አህመድ በሌላ ሰው የመቀየር እና ግለ ሰዎች በስልጣን የመቀያየር ጉዳይ ሳይሆን እውነተኛ ለውጥ የመምጣት ትግል ነው ብሏል።
አቶ አማኑኤል አሰፋ ይህንን ማለታቸው በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተወራ ያለውን የድርድር ተስፋ ያጨለመ ሆኗል።
የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ሁለቱን አካላት ለማደራደር ጥረት መጀመራቸው ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍13🤣11❤7🤪1
አርሰናል 3ኛ ተከታታይ ድሉን አሳካ

በሦስተኛ ሳምንት እጅግ ተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ቼልሲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በኢምሬትስ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ አስቆጥረዋል።

ቼልሲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በሊጉ ያደረጋቸውን ተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ድል አድርጓል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በሊጉ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል።

አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቱ ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍22❤17🤪4🥰2🍾2🤔1😢1🎉1🏆1