አዲስ ሪፖርተር - NEWS
37K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ቡና ላይ የአዕምሮ  ታማሚ ነሽ ብላኛለች በሚል ቂም  የ1ዓመት ከ7ወር ልጇን  የገደለችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

በቡና መጠጣት ስነ-ስርዓት ላይ በተነሳ የሐሜት ወሬ ሳቢያ፣ ሁለት ዓመት ባልሞላው ጨቅላ ህፃን ላይ ከባድ የግድያ ወንጀል የፈጸመችው ግለሰብ በ19 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣለች።

ጉዳዩን አስመልክቶ ከጅማ ዞን አቃቢ ሕግ ፅፈት ቤት የሴቶች, የሕፃናት, የሕገወጥ የሠዎች ዝውውር እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቃቤ ሕግ ሰሚራ ሙሊሣ በተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ወንጀሉ የተፈጸመው በጅማ ዞን ጮራ ቦተሪ ወረዳ ሐሮ ሌጂሣ ቀበሌ ዋ ዱዴ በተባለ ስፍራ ሲሆን በሰላሳዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ተከሳሽ ራቢያ ልዑል ሁንዴ፣ ቀደም ሲል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነትና ማህበራዊ ተሳትፎ የነበራት ነበረች።

ይሁን እንጂ ከጎረቤቷ ጋር በቡና መጠጣት ወቅት “የአእምሮ መታወክ ያለባት ናት” በሚል በተነሳ የሐሜት ወሬ ምክንያት ሁለቱ ግለሰቦች ግጭት ውስጥ ገብተዋል። ችግሩን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በተገናኙ ቁጥር በአሽሙርና በስድብ ውጥረቱን በማባባሳቸው፣ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ዱላ ቀረሽ ፀብ አምርተው በገላጋይ ተለያይተዋል።

በነጋታው ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ሶፍያ ፋሪስ የተባለው የ1 ዓመት ከ7 ወር ህፃን ከራቢያ ልጆች ጋር በጓሮ በመጫወት ላይ በነበረበት ወቅት፣ ተከሳሿ የትላንትናውን ቂም ለመወጣት ህፃኑን ከልጆቿ ነጥላ በመውሰድ በጓሮ በኩል በቢላዋ አንገቱን በመቁረጥ አርዳዋለች። ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላ በሯን ዘግታ ለማምለጥ ስትሞክር፣ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ስፍራው ላይ ደርሶ በቁጥጥር ስር አውሏታል። ተከሳሿም የወንጀሉን አፈጻጸም ለፖሊስ መርታ አሳይታለች።

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ውጤት እና በሌሎች ማስረጃዎች አጠናክሮ ለአቃቤ ሕግ በመላኩ በወንጀሉ ላይ ከባድ የግድያ ክስ ተመስርቷል። ጉዳዩን የተመለከተው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ በሌለው ጨቅላ ህፃን ላይ የተፈጸመ እጅግ ጨካኝ፣ ነውረኛ እና አደገኛ መሆኑን አረጋግጧል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ራቢያ ልኡል ሁንዴ ባቀረበችው ሁለት የክስ ማቅለያ ምክንያቶች መሠረት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12😢8👍3💔3😱1
ቢያንስ 12 ሀገራት በሱዳን ጦርነት የጦር መሣሪያ ድጋፍ እያደረጉ ነው - አሜሪካ

ለሱዳን ተጋጣሚ ወገኖች ቢያንስ 12 ሀገራት ወታደራዊ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ እና ይህም በመላ ሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ግጭት ይበልጥ እያባባሰው መሆኑን የአፍሪካ እና ኤሺያ ጉዳዮች የአሜሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማስአድ ቡሎስ ገለጹ።

ከቢቢሲ «ፎከስ ኦን አፍሪካ» ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፣ ማስአድ ቡሎስ ለሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) እና ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) የሚደረገው የውጭ ወታደራዊ ድጋፍ ባለፉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል።

«በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ወታደራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ቢያንስ 12 ሀገራት አሉ» ያሉት ቡሎስ፣ ይህ የጦር መሣሪያ እና የድጋፍ ፍሰት «እጅግ አሳዛኝ» እና በአስቸኳይ ሊቆም የሚገባው ኩነት እንደሆነ ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ቡሎስ፣ በድጋፉ ላይ የተሳተፉትን ሀገራት ስም ለመጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የእነዚህ ሀገራት ማንነት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ አስቀድሞ በግልጽ የሚታወቅ መሆኑን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍6
ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ግዛት የነበረው ጦራቸውን የጎበኙት አልቡርሀን ከኢሳያስ ጋር ተገናኝተዋል።

ምጽዋ ወደብ የሚራገፈው የጦር መሳሪያ በጨመረበት ወቅት የተደረገ ጉብኝት መሆኑ ትልቅ ትኩረት ስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍9🕊1
ህወሃት የፌደራል መንግስትን በድሮን ጥቃት ሲከስ የአላማጣ ባለስልጣናት ደግሞ ህወሃትን ወቀሱ
 
ህወሃት የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህወሃት ታጣቂዎች የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕነት ቀይረዋል የሚሉ የአካባቢው ሪፖርቶች መውጣታቸውን ዶቼ ቬሌ  ዘግቧል።
 
የህወሃት ቃል አቀባይ ሚካኤል አሰግዶም በድሮን እና በሚግ ተዋጊ አውሮፕላኖች የታገዘው የአየር ጥቃት በአምስት ዞኖች በሚገኙ የህዝብ ተቋማት ላይ ማረፉን የገለጹ ሲሆን፣ በሰሜን ምዕራብ ዞን ደጀን ከተማ የሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ መውደሙን፣ እንዲሁም በእንደርታ እና በራያ አዘቦ አርሶ አደሮችና የመኖሪያ መንደሮች መመታታቸውን ጠቅሰዋል።
 
ይሁን እንጂ ከአላማጣ ከተማ የተገኙ አንድ የቀድሞ የአካባቢው ባለስልጣን ለዶቼ ቬሌ በሰጡት ተቃራኒ መረጃ፣ የህወሃት ኃይሎች አራት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በአላማጣ የሚገኙ ስምንት ትምህርት ቤቶችን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የማዘጋጃ ቤት ህንፃዎችን በአሁኑ ወቅት ወደ ታጠቁ ወታደራዊ ይዞታነት እና መፈጠሪያነት ቀይረዋቸዋል ሲሉ ከሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍2🤔2
በኔፓሉ የጎርፍ አደጋ ከዘጠኝ ቀን ፍለጋ ቡሀላ ሁለት ሰዎች በህይወት ተገኙ፡፡

በኔፓል በድንገተኛ ጎርፍ ምክንያት በዋሻ ውስጥ ለዘጠኝ ቀናት ተይዘው የነበሩ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ሠራተኞች በሕይወት መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በኔፓል በደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከ አንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉና ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸው የሚታወስ ነው።

ሳንጃያ ሻህ እና ካቢር ማሃርጃን ከትሪሹሊ 3A የኃይል ማመንጫ ዋሻ ውስጥ በአዳኝ ቡድኖች የተገኙ ሲሆን፤ በእጅና በእግራቸው ጉዳት ቢደርስባቸውም በአምቡላንስ ወደ ካትማንዱ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በዚያው ዋሻ ውስጥ ወደ 40 የሚጠጉ ሰዎች አሁንም ተይዘው እንዳሉ ሲገመት፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች የፍለጋ ሥራቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤25👍5😢4
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
❤6👍4
ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩት አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አስተዳደር በመጠጥ ግሮሰሪ ንግድ ፈቃድ ሽፋን ሴቶችን ያለ ፍላጎታቸው ለወሲብ ንግድ ሲዳርጉና ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን የከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ በዘይበላ ወላሼ ቀበሌ «ኤል ክላሲኮ» የተባለ የምሽት ጭፈራ ቤት በመክፈት ሴቶችን በአስተናጋጅነት ካስቀጠሩ በኋላ በግዳጅ ለዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ አድርገዋል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት አንደኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ የንግድ ፈቃዱን በማውጣትና ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የተቀጠሩ አስተናጋጆችን ያለፍላጎታቸው የግብረ-ሥጋ ድፍረት ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ማድረጉ በበቂ ማስረጃ ተረጋግጧል።የቀረበውን የዐቃቤ ሕግ ክስና የፖሊስ ማስረጃ የመረመረው የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፋል።

በዚህም መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ ድርጊቱን በዋናነት በመምራትና በግዳጅ የመድፈር ጥቃት በመፈጸሙ በ23 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ200 ሺህ ብር መቀጮ፤ 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ደሴ በ10 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር መቀጮ፤ 3ኛ ተከሳሽ ወርቁ ደሜ በ6 ዓመት እስራት እና በ45 ሺህ ብር መቀጮ፤ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ተመስገን ፍቃዱ እና ቤክና መሐመድ ደግሞ እያንዳንዳቸው በ1 ዓመት ከ8 ወር እስራትእንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍7🤔1
የህወሓት ድሮን ሰልጣኞች‼️
ህወሃት የድሮን ስልጠና የወሰዱ ከ15 በላይ ሰዎችን ወደ ራያ ማሰማራቱ ተሰማ።
ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት አረብኛ የሚናገሩ ነጮች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በራያ አላማጣ እንዲሁም ቅልሻ በሚባል አካባቢ ታይተዋል ብለዋል።
የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሶንጎ ኦባሳንጆ ህወሓት እና የፌደራል መንግስቱን ለማደራደር ጥረት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍22🤣10❤7👀2✍1
በክልል ንግድ ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ መስራት አይቻልም ሲል ቢሮው አሳወቀ‼️

በክልል ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ አስመጪዎች ንግድ ፈቃዳቸውን ወደ አዲስ አበባ ማዛዋወር አለባቸው ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በመኪና ሽያጭ ዘርፍ በሚደረጉ ህገወጥ አሰራሮች እና የታክስ ስወራዎች ላይ ጥብቅ እርምጃና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በክልል ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ አስመጪዎች ንግድ ፈቃዳቸውን ወደ አዲስ አበባ ማዛወር አለባቸው ተብሏል።

ደረሰኝ መለየት የሽያጭ ማሽን ማስተካከል እና ወርሃዊና ዓመታዊ ግብር መክፈል አለባቸው ነው የተባለው።

ህገወጥ ደረሰኝ መጠቀም ወይም የውጭ ሀገር ፈቃድ ብቻ ይዞ መንቀሳቀስ በህግ ያስጠይቃል።

አስመጪዎችና የመኪና ማሳያ ባለቤቶች ፈቃድ ከሌላቸው ደላሎች ጋር በመተባበር ህገወጥ የሽያጭ ሰነድ ከመፈራረም እንዲቆጠቡ ተሳስቧል።

ቢሮው ከዚህ አሰራር ውጭ በሚንቀሳቀሱ አስመጪዎች ፈቃድ የሌላቸው ደላሎች በኦንላይን ህገወጥ ንግድ የሚያካሂዱ ግለሰቦች እና ከተዋናዮቹ ጋር በሚተባበሩ አካላት ላይ ቢሮው ክትትልና ምርመራ በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ሲል አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9👍3🤩3🙊2👀1🤪1
ብልፅግና ከ70-80% አዲስ ተሿሚዎች‼️
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በሚመሰርተው መንግስት ውስጥ ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ለአዲስ ተሿሚዎች ለመስጠት መወሰኑ ተሰማ።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ውሳኔያቸውን በሚንስትር እንዲሁም ሚንስትር ዲኤታ ቦታዎች ላይ እየሠሩ ለሚገኙ ተሿሚዎች ማሳወቃቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ ረዘም ላሉ ዓመታት በአመራርነት ያገለገሉ ተሿሚዎች ራሳቸውን ለሌላ ተልዕኮ እንዲያዘጋጁ እንደተነገራቸው ጠቁመዋል።

ይህም በሚንስትር እንዲሁም በሚንስትር ዲኤታነት እያገለገሉ ከሚገኙ ተሿሚዎች መካከል በአምባሳደርነት የሚሾሙ እንደሚኖሩ ጠቋሚ መሆኑን ሰምተናል። 
   
ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሚንስትሮችንና ሚንስትር ዲኤታዎችን በሰበሰቡበት መድረክ “ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ለውጥ ይደረጋል” ሲሉ መናገራቸውን የገለጡልን ምንጫችን፤ ከዚህ ውሳኔያቸው በኋላ ከሚንስትሮች እና ሚንስትር ዲኤታዎች ጋር ለቀናት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ነግረውናል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአምስት ዓመታት በፊት ካቢኔያቸውን ባዋቀሩበት ወቅት፤ ከ22ቱ የሚንስትርነት ቦታዎች መካከል ሦስቱን ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአሁኑ የካቢኔ ምርጫም የሚንስትርነት ሹመት የሚሰጣቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሚኖሩበት ዕድል ሰፊ መሆኑን ምንጮች ነግረውናል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የፓርቲዎች አመራሮች፤ ከሹመት ጋር በተያያዘ እስካሁን ለፓርቲያቸው የቀረበ ጥያቄ አለመኖሩን የገለጹ ቢሆንም፤ ሹመት እንደሚሰጣቸው ቃል እንደተገባላቸው የሚገልጡ የፓርቲ አመራሮች መኖራቸውን ሰምተናል።

እየተካሄዱ ያሉ ስብሰባዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሚንስትሮችን ለብቻ፤ ሚንስትር ዲኤታዎችንም ለብቻ ሰብስበው ማነጋገራቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ በስብሰባዎቹ ያለፉት ዓመታትን ከመገምገም ባለፈ አዲስ የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ነው።

በስብሰባዎቹ ከሚቀርቡ ሰነዶች ባሻገር፤ የቡድን ውይይቶች እየተካሄዱ መሆናቸውንም ሰምተናል።

ሚንስትሮች ስብሰባ ማድረግ ከጀመሩ ሁለተኛ ሳምንት ያስቆጠሩ ሲሆን በዚህኛው ሳምንት የተጀመረው የሚንስትር ዲኤታዎች ስብሰባ ደግሞ ስልክ ይዞ መግባት የተከለከለበት መሆኑን አውቀናል።

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስብሰባ ለተጨማሪ ቀናት እንደሚቀጥልም ምንጮች ጠቁመዋል።

Via : ዋዜማ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤17👍7🤪4🤷‍♂2🤔1👀1🙊1
ለአዲስ ዓመት የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 1,200 ብር እንዲሆን ከሥጋ ቤቶቹ ጋር ስምምነት መደረጉ ተገለጸ

ለተቃረበው የ2019 አዲስ ዓመት በዓል የሸማቹን እንግልትና ያልተገበበ የዋጋ ጭማሪ ለመግታት ያለመ አዲስ ውሳኔ ተ አስተላለፈ።

የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በመዲናዋ ከሚገኙ 274 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ጋር ባደረገው ዝርዝር ውይይት፣ አንድ ኪሎ የበሬ ሥጋ በ1,200 ብር ብቻ ለሕዝብ እንዲቀርብ መግባባት ላይ መድረሱን አስታውቋል።

የበዓላት ወቅት የመገበያያ ዋጋ ንረትና የአቅርቦት እጥረት የሚፈጥረውን ጫና ለማቃለል ሰፊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ሸማቾች በየአካባቢያቸው በሚገኙ ማኅበራት በኩል ምርቱን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ አረጋግጧል።

በሁሉም 274 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች አንድ ኪሎ ሥጋ ከ1,200 ብር በላይ እንዳይሸጥ ስምምነት ተደርሷል።

መንግሥት ከአርሶ አደሮችና ከበሬ አቅራቢዎች ጋር ቀጥተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠሩ በሥጋ ቤቶች በኩል የነዳጅና የአቅርቦት ምክንያት አቤቱታ እንደማይኖር ተገልጻል።

ከሥጋ በተጨማሪ ሌሎች የበዓል ሸመታዎችን ከእሁድ ገበያዎችና ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ሱቆች በቅናሽ ዋጋ መገበያየት እንደሚቻል ጥሪ ቀርቧል።

ከተቀመጠው የዋጋ ተመን በላይ በሚሸጡ ሥጋ ቤቶች ላይ ኅብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣18❤9👍4😢3
ቡና አብዝቶ መጠጣት የእንቅልፍ ጊዜን ቢያሳጥርም ጥልቀቱን እንደሚጨምር ተነገረ

​በቀን አራት ወይም ከዚያ በላይ ሲኒ ቡና መጠጣት የእንቅልፍ ቆይታን ያሳጥራል፤ ሆኖም በእንቅልፍ ወቅት የሚገኘውን ጥልቅ እረፍት እንደሚጨምር አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።

​በስዊዘርላንዱ ተመራማሪ በቤንጃሚን ስተኪ የተመራው ይህ ጥናት፣ የዩኬ ባዮባንክ እና የHypnoLaus መረጃዎችን በመተንተን የተሰራ ነው።

ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ካፌይን መውሰድ የእንቅልፍ ሰዓትን በ11 ደቂቃ ያህል ያሳጥራል።

​ነገር ግን፣ የሰውነት ህዋሳትን ለማደስ እና ኃይልን ለማገገም ወሳኝ የሆነው "የዝቅተኛ ሞገድ እንቅልፍ"  ጥልቀት ይጨምራል።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ይህ የሰውነት ተፈጥሯዊ ምላሽ ሲሆን፣ ያጣውን አጭር የእንቅልፍ ሰዓት በጥልቅ እንቅልፍ ለማካካስ የሚያደርገው ጥረት ነው።

​ጥናቱ ቡና የእንቅልፍ መጠንን ቢቀንስም፣ የጥራት መጠኑ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21👍3🙉2
ለስራ አጦች ደመወዝ መክፈል ተጀመረ‼️
አልጀርያ ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶቿ ደምሞዝ መክፈል ጀመረች
የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር አልጄሪያ ለዜጎቿ የዘረጋችው አስደናቂ የማህበራዊ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመላው አፍሪካ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈ ይገኛል።

ሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብቷን እና የኢኮኖሚ አቅሟን ቀጥታ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል በሚያስችሉ ዘመናዊ ውሳኔዎች ላይ በመመደብ በአፍሪካ አዲስ ምሳሌነቷን እያሳየች ነው።

ሀገሪቷ ስራ ለሌላቸው ወጣቶች በወር 96 ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች።

ይህ ድጋፍ ወጣቶች ስራ እስኪያገኙ ድረስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲሸፍኑ የሚያስችል ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ ነፃ የጤና መድህን አገልግሎትም ያካትታል ተብሏል።

በወር ከ 216 ዶላር በታች የሚያገኙ ዜጎች ምንም አይነት የገቢ ግብር እንዳይከፍሉ አድርጋለች።

በተጨማሪም አነስተኛ የደመወዝ ወለል ወደ 170 ዶላር ከፍ በማድረግ የዜጎችን የመግዛት አቅም እንዲሻሻል አድርጋለች።

ከዚህ በተጨማሪም ለህዝቧ በሙሉ ነፃ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አረጋግጣለች።

አልጄሪያ ግዙፍ የተፈጥሮ ጋዝ እና የሃይል አቅሟን በመጠቀም 100 በመቶ ለሚጠጉ ዜጎቿ ሙሉ በሙሉ ተራሽ እና ነፃ የሆነ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማድረስ ችላለች።

ይህም በገጠር እና በከተማ የሚኖሩ ዜጎቿ በእኩል መሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ነው የተባለው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍67❤20🏆13👌1🕊1💯1
በጦርነቱ የተጎዱ ወደ ዩኒቨርስቲ‼️
ህወሃት በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን እና የአካል ጉዳተኞችን ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች እያጓጓዘ ይገኛል።
ከላይ የተያያዘው ምስል ጉዳት የደረሰባቸው እና የአካል ጉዳተኞች ከኩሓ መለስ ካምፓስ ወደ አክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲጫኑ የሚያሳይ ምስል ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍7🤪4🕊2✍1🤔1
ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ከነሐሴ 21 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አደረኩት ባለው ክትትል፣ 470.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ እና 81 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችን በድምሩ 551.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታውቋል።

ከተያዙት እቃዎች መካከል ጨርቃጨርቅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ መዋቢያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል።

በኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ የጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚ ሲሆኑ  ቅርንጫፎቹ በቅደም ተከተል 186 ሚሊዮን፣ 117 ሚሊዮን እና 116 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን ይዘዋል።

እቃዎቹ በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ ላይ በተደረገ ክትትል የተያዙ ሲሆን፣ 26 ተጠርጣሪዎችና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ መግለፁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች ።

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚሠራ ሲሆን፣ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍3
ኢትዮጵያ በ83 ቢ. ብር ወጪ 16
ግዙፍ መርከቦችን ልትገዛ ነው

ኢትዮጵያ የውጪና የገቢ ምርቶቿን የሎጂስቲክስ አቅርቦት ለማቀላጠፍ በ83 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ወጪ 16 አዳዲስ መርከቦችን ለመግዛት አቅዳለች። በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የሚከናወነው ይህ የግዥ እቅድ አሁን ካሉት 10 መርከቦች በተጨማሪ የሚከናወን ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከነበሩት ከ25 ሺህ እስከ 28 ሺህ ቶን አቅም በበለጠ ከ50 ሺህ እስከ 63 ሺህ ቶን የመሸከም አቅም ያላቸው ግዙፍ መርከቦችን የሚያካትት ነው።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት መርከቦች በላይ ሕጋዊ የግዥ ሥርዓት በሂደት ላይ ይገኛል። አዲሶቹ መርከቦች ስትራቴጂክ ግብዓቶችን በብቃት በማስገባትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በወቅቱ በመላክ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14🤪4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት የተረፈው ግለሰብ !

በአሜሪካን፣ ኒውዮርክ ውስጥ " ስታተን አይላንድ " የተባለ አካባቢ ነዋሪ የሆነው ቶማስ ፋህሚ የተባለ ግለሰብ ከመኪናው 15 እስከ 20 ጫማ ርቀት ላይ ሳለ በድንገት በመብረቅ ተመቶ በተአምር ከሞት ተርፏል።

ቪዲዮውን ከላይ  እንደምትመለከቱት  ግለሰቡ ከመኪናው ወርዶ ብዙም ሳይሄድ ነው በከባድ መብረቅ ተመትቶ ከሞት አፋፍ የተረፈው።

በአካባቢው በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ የተከሰተው ይህ አስደንጋጭ አደጋ ፋህሚ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የስነ-ልቦና ስቃይ ፈጥሯል።

በመብረቅ በተመታበት ወቅት በሁለቱም እግሮቹ ላይ ከባድ የመቃጠል ስሜት፣ የመደንዘዝ እና ከፍተኛ የህመም ስሜት እንደተሰማው ምስክርነቱን ሰጥቷል።

አደጋው ከተከሰተ በኋላ " በሌላ መብረቅ እመታለሁ " የሚል ከፍተኛ ስጋትና ፍርሃት አድሮበት እንደነበር ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት በህክምና ክትትል ከጉዳቱ በማገገም ላይ ያለው ቶማስ ፋህሚ፣ ይህ አስከፊ አደጋ በህይወት ላይ ያለውን አመለካከት ሙሉ በሙሉ እንደቀየረው ይናገራል።

አደጋው ህይወትን ማድነቅ፣ ንጹህ አየርን መተንፈስ፣ ለዕለት ተዕለት ኑሮ ትልቅ ዋጋን መስጠት እንዳለበት አስተምሮታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤24👍3🤯2🙏2🤔1🙈1🙊1
አፍሪካ ታሪካዊ ድል ተቀዳጀች፤ የተዛባው የዓለም ካርታ ሊቀየር ነው!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የአፍሪካን ትክክለኛ የቆዳ ስፋት በአግባቡ የሚያሳየውን አዲሱን "Equal Earth" የዓለም ካርታ ለመጠቀም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ በሚባል ደረጃ አጽድቋል።
የድምፅ አሰጣጥ ውጤት፦

• 164 ሀገራት፦ ደግፈው አድቅቀዋል
• 1 ሀገር፦ ተቃውሟል እሷም አሜሪካ ነች
• 6 ሀገራት፦ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል

ውሳኔው በቶጎ አስተባባሪነት፣ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትና በአፍሪካ ህብረት አጋርነት የቀረበ ታሪካዊ እርምጃ ነው።
ይህ ውሳኔ ለምን አስፈለገ?

እስከዛሬ ስንጠቀምበት የነበረው "Mercator" በመባል የሚታወቀው የዓለም ካርታ የሀገራትን ትክክለኛ ስፋት አዛብቶ የሚያሳይ ነበር። 

በካርታው ምክንያት በምድር ወገብ አቅራቢያ የሚገኙ እንደ አፍሪካ ያሉ አህጉራት በጣም አነስተኛ ሆነው ሲታዩ፣ ወደ ሰሜንና ደቡብ ዋልታ የተጠጉ ሀገራት ደግሞ ካላቸው ስፋት በላይ ገዝፈው ይታዩ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤32🥱10👍3🤷3🤣2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ምሽት መርካቶ 4ኛ አካባቢ አደገኛ የእሳት አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን በሱቆች እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።።
እሳቱ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍9😢9🤔6💔3😱1
በአዲስ ከተማ «ሸማ ተራ» ተከስቶ የነበረው
የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 «ሸማ ተራ» አካባቢ ተከስቶ  የነበረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው እንደገለጹት፤ አደጋውን በፍጥነት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ትልቅ ትብብር አድርገዋል።

በአሁኑ ወቅት የአደጋው መንስኤና የደረሰው የጉዳት መጠን  እየተጣራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፣ የተደረገው ፈጣን ርብርብ አደጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ አድርጓል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍7😢6
#AddisAbaba

"እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ ተራዝሟል" - ቢሮው

የአከራይና ተከራይ የውል እድሳት ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ለመጨረሻ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት አገልግሎት ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል።

ቢሮው የውል ምዝገባና እድሳት ስራው እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ጊዜ ገደብ አስቀምጦ ነበር።

ይሁን እንጅ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በጊዜው አሟልተው ያልቀረቡ፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ በልዩ ልዩ ምክንያት ከአዲስ አበባና ከሀገር ውጭ የነበሩ ተዋዋዮች መኖራቸውን አስታውቋል።

በህብረተሰቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት የመጨረሻ ተጨማሪ እድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ገልጿል።

በመሆኑም እስካሁን ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮችና ተከራዮች ይህንን በተሰጠው የመጨረሻ እድል በክፍለ ከተሞች፣ በሁሉም የመሶብ አንድ ማዕከላት እና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ቦታዎች  በመቅረብ ውላቸውን እንዲያድሱ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍4🤔2