አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.4K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ በህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ አካላት እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደሚቀጡ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
 
ባለስልጣኑ እንደገለጸው፤ ያለፈቃድ ማዕድን የሚያመርቱ፣ ከፈቃድ ውጭ የሚንቀሳቀሱ እና የአካባቢ ጥበቃ ህጎችን የማይተገብሩ አካላት ተጠያቂ ይሆናሉ።
 
በዚህም መሰረት፡-ያለፈቃድ ማዕድን ሲያመርቱ የተገኙ አካላት ከ300,000 እስከ 400,000 ብር ቅጣት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
 
ህገ-ወጥ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት የገንዘብ ቅጣቱ እንደ ጥፋቱ ክብደት እስከ 500,000 ብር ሊደርስ እንደሚችልና መሳሪያዎቻቸውም በመንግስት እንደሚወረሱ ተመላክቷል።
 
ከተማዋንና መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ በማዕድን ማምረቻ ቦታዎች ላይ የሲሲቲቪ ካሜራዎችን የመግጠም ስራ የግዴታ እንደሚሆንና አልሚዎችም የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት ማቅረብ እንዳለባቸው ተሳስቧል።
 
ይህ ጥብቅ የህግ ማዕቀፍ የከተማዋን ደህንነትና ሰላም ለማረጋገጥ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍2😡1
ቀን 29/12/2018
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 09 17 48 53/09 07 36  23 85
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉   የስራ መደብ:# NGO
👉የት/ደረጃ ዲፕሎማ / ድግሪ
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞዝ:- 40.000_50.000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው  መደብ =- ሀውስ ኪፒግ
👉የትምርት ደረጃ 8 +
👉የስራ ልምድ 0-3
👉ደሞዝ 7000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ሆስተስ
👉የትምርት ደረጃ 10 +
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 15000 / 20000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =-መስተግዶ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0/2
👉ጾታ ወንድ /ሴት
👉ደሞዝ ማራኪ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የስራው መደብ /ፓስታ ፋብሪካ=-የእሸጋ ሰራተኛ
👉  የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
👉ደሞዝ:-  17000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
👉ደሞዝ ፡ 15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ሹፌር ደ/1 2 ህ/1/ሞተረኛ
👉የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
👉ደሞዝ:- 7000_17000
👉ፆታ :- ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ትኬተር/ለባስ/
👉የሰራ ልምድ :- 0አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
👉ደሞዝ:- 0አመት
👉ደሞወዝ   :- 9000~20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
👉የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
👉ደሞዝ:-8000_30000+
👉የስራ ልምድ: 0አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ :markting
👉የት ደረጃ ፡- degree 
👉የስራ ልምድ ፡- 0~5 አመት
👉ደሞዝ :-13000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ Accountant
👉የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
👉ደሞዝ ፡  8,000-16,000 
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ IT
👉የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
👉የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
👉ፆታ:- ሴ/ወ
👉ደሞዝ:- 8000-15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ካሸር
👉የት/ደረጃ፦10 +
👉የሰራ ልምድ 0~3 አመት
👉ደሞዝ:- 7000-12000
👉ፆታ፦ሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#nurse//ላብራቶሪ/ጠቅላላ
👉 ለክሊኒክ እና ለሆስፒታል
👉የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
👉የስራ ልምድ: 0~8አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉ፆታ፦ሴት/ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ 8
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-1
👉ደሞዝ :7000-20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
👉የትምርት ደረጃ 8+
👉የስራ ልምድ 0 -1 አመት
👉ደሞዝ 10000-25000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ=- ፀሀፊ
👉የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
👉የስራ ልምድ ያላት
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 8000/13000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው አይነት =- ባርቴንደር
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልድ 1/3
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 10000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ብስኩት ፋብሪካ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 16000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
👉የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት
👉ደሞዝ:-9000-35000
👉ፆታ፦ወንድ/ሴት
👉የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ እሪል እስቴት ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ ዲፕ/ዲግሪ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ ፡  9000-50000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ሁለገብ ሰራተኛ
👉የደረጃ ፡- 8_10
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞወዝ :- 10000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ reception
👉የት ደረጃ ፡ 10/12
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ 8000/15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#ተላላኪና ፅዳት ለባንክ
👉የት/ደረጃ፦8/12 /ዲፕ
👉 የሰራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
👉ፆታ: ሴ/ወ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
👉ደሞዝ ፡  15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉መረጃና መዝገበ አያያዝ 
👉 የት ደረጃ ፡ dip-degree
👉የስራ ልምድ ፡ 0_1አመት
👉ደሞዝ ፡  13500
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ወደ 24 በሚወስደው መንገድ  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305  👇👇👇👇👇
         ☎️ 0907362385
         ☎️  0909174853
     
❤11👍2🤔1🤣1
የ16 ዓመት ታዳጊን  በመጥለፍ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ::

በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ የ16 ዓመት ታዳጊን በመጥለፍና በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ  በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሽ ዘላለም ዘለቀ የተባለ ሲሆን በክስ መዝገቡ ላይ ስሟ ያልተጠቀሰችውን የ16 ዓመት ታዳጊን በመጥለፍ በባጃጅ ውስጥ አስገብቶ ወደ ሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ነጮ ቀበሌ ይወስዳታል።

በመቀጠልም ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ታዳጊዋ እንዳትጮህ አፏን በማፈን እና በጉልበት በመያዝ ወንጀሉን መፈጸማቸው ተገልጿል::

የጌሻ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ጉዳዩን በጥልቀት ካጣራ በኋላ የምርመራ መዝገቡን ለወረዳው ዐቃቤ ሕግ ያስተላልፋል።ዐቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን ከመረመረ በኋላ በተከሳሹ ላይ ክስ ይመሰርታል።ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግንና የተከሳሹን ክርክር ከሰማ በኋላ የቀረቡለትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን ማረጋገጡን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

በዚህም የጌሻ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ዘላለም ዘለቀን  በ10 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9👍6
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲን (በጽሑፋቸው 'ፖተምኪን ፓርቲ' ሲሉ የገለጹትን ብልጽግናን) እና የፓርቲውን ልሳኖች በኤርትራ ላይ የከረረ የሀሰት መረጃ እና የጥላቻ ዘመቻ ከፍተዋል ሲሉ አውግዘዋል። አቶ የማነ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው (ኤክስ) ላይ ባሰፈሩት ጠንከር ያለ መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ አመራሮች በኤርትራ ላይ የሚያካሂዱትን የስም ማጥፋት ዘመቻ መጠን በማሳደግ "እንደተበላሸ የሸክላ ማጫወቻ" አንድ ዓይነት ድምጽ ደጋግመው እያሰሙ ይገኛሉ ብለዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ይህ ከኢትዮጵያ በኩል የሚሰነዘረው ዘመቻ በዋናነት ሦስት "አሰልቺ" እና "ተደጋጋሚ ጭብጦች" ላይ ያተኮረ ነው። የመጀመሪያው የኤርትራን ሉዓላዊ የመንግስትነት ታሪክ ጥላሸት የሚቀባ የታሪክ ክለሳ ማድረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ገዥው ፓርቲ በገዛ እጁ ለፈጠራቸው ውስብስብ ሀገራዊ ቀውሶች ኤርትራን በሐሰት ተጠያቂ የማድረግ ሙከራ ነው። ሦስተኛው የዘመቻቸው ዓላማ ደግሞ፣ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ እና በሰፊው የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና የምትከተለውን መደበኛ የቀጠናዊ ትብብር ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ማጣመም መሆኑን አስምረውበታል።

አቶ የማነ አክለውም እነዚህ አሳሳች የፖለቲካ ሴራዎች ዋነኛ ግባቸው ሌላ የተደበቀ አጀንዳን መሸፈን ነው ሲሉ ይሞግታሉ። ይኸውም የኢትዮጵያ መንግስት "ወደ ባህር የሚያስገባ ሉዓላዊ የባለቤትነት መብት" ለማግኘት፣ እንዲሁም "በቀይ ባህር ላይ ስትራቴጂካዊ ጥልቀት ያለው የባህር ላይ ኃይል" ለመገንባት በማሰብ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲያሰላስለው የቆየውን አደገኛ እና አጥፊ የጦርነት አጀንዳ ትክክለኛ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል። ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ደግሞ ዓለም አቀፍ ህጎችን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን እና የአፍሪካ ህብረትን መመስረቻ ህግን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የገዥው ፓርቲ "ባዶ እና ቅዥት የተሞላበት" መግለጫ የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችንም ሆነ ሰፊውን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያታልል አይችልም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ሁሉ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የአስመራ ምላሽ አንድ እና አጭር ነው ሲሉ "ዘረባ ኣደይ ለቱ፡ ኣየውፍር ኣየእቱ!" (ትርጉሙም፡ ፋይዳ ቢስ እና ምንም ውጤት የማያመጣ ወሬ) የሚለውን የትግርኛ አባባል ተጠቅመው መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14🤪8👍5🤣2🤔1
ቡና ላይ የአዕምሮ  ታማሚ ነሽ ብላኛለች በሚል ቂም  የ1ዓመት ከ7ወር ልጇን  የገደለችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

በቡና መጠጣት ስነ-ስርዓት ላይ በተነሳ የሐሜት ወሬ ሳቢያ፣ ሁለት ዓመት ባልሞላው ጨቅላ ህፃን ላይ ከባድ የግድያ ወንጀል የፈጸመችው ግለሰብ በ19 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣለች።

ጉዳዩን አስመልክቶ ከጅማ ዞን አቃቢ ሕግ ፅፈት ቤት የሴቶች, የሕፃናት, የሕገወጥ የሠዎች ዝውውር እና ድንበር የማሻገር ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቃቤ ሕግ ሰሚራ ሙሊሣ በተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ወንጀሉ የተፈጸመው በጅማ ዞን ጮራ ቦተሪ ወረዳ ሐሮ ሌጂሣ ቀበሌ ዋ ዱዴ በተባለ ስፍራ ሲሆን በሰላሳዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው ተከሳሽ ራቢያ ልዑል ሁንዴ፣ ቀደም ሲል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነትና ማህበራዊ ተሳትፎ የነበራት ነበረች።

ይሁን እንጂ ከጎረቤቷ ጋር በቡና መጠጣት ወቅት “የአእምሮ መታወክ ያለባት ናት” በሚል በተነሳ የሐሜት ወሬ ምክንያት ሁለቱ ግለሰቦች ግጭት ውስጥ ገብተዋል። ችግሩን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በተገናኙ ቁጥር በአሽሙርና በስድብ ውጥረቱን በማባባሳቸው፣ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ዱላ ቀረሽ ፀብ አምርተው በገላጋይ ተለያይተዋል።

በነጋታው ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ ሶፍያ ፋሪስ የተባለው የ1 ዓመት ከ7 ወር ህፃን ከራቢያ ልጆች ጋር በጓሮ በመጫወት ላይ በነበረበት ወቅት፣ ተከሳሿ የትላንትናውን ቂም ለመወጣት ህፃኑን ከልጆቿ ነጥላ በመውሰድ በጓሮ በኩል በቢላዋ አንገቱን በመቁረጥ አርዳዋለች። ድርጊቱን ከፈጸመች በኋላ በሯን ዘግታ ለማምለጥ ስትሞክር፣ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ስፍራው ላይ ደርሶ በቁጥጥር ስር አውሏታል። ተከሳሿም የወንጀሉን አፈጻጸም ለፖሊስ መርታ አሳይታለች።

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በአስክሬን ውጤት እና በሌሎች ማስረጃዎች አጠናክሮ ለአቃቤ ሕግ በመላኩ በወንጀሉ ላይ ከባድ የግድያ ክስ ተመስርቷል። ጉዳዩን የተመለከተው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ በሌለው ጨቅላ ህፃን ላይ የተፈጸመ እጅግ ጨካኝ፣ ነውረኛ እና አደገኛ መሆኑን አረጋግጧል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ራቢያ ልኡል ሁንዴ ባቀረበችው ሁለት የክስ ማቅለያ ምክንያቶች መሠረት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12😢8👍3💔3😱1
ቢያንስ 12 ሀገራት በሱዳን ጦርነት የጦር መሣሪያ ድጋፍ እያደረጉ ነው - አሜሪካ

ለሱዳን ተጋጣሚ ወገኖች ቢያንስ 12 ሀገራት ወታደራዊ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ እና ይህም በመላ ሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ግጭት ይበልጥ እያባባሰው መሆኑን የአፍሪካ እና ኤሺያ ጉዳዮች የአሜሪካ ከፍተኛ አማካሪ ማስአድ ቡሎስ ገለጹ።

ከቢቢሲ «ፎከስ ኦን አፍሪካ» ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፣ ማስአድ ቡሎስ ለሱዳን መደበኛ ጦር (SAF) እና ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) የሚደረገው የውጭ ወታደራዊ ድጋፍ ባለፉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል።

«በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ወታደራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ቢያንስ 12 ሀገራት አሉ» ያሉት ቡሎስ፣ ይህ የጦር መሣሪያ እና የድጋፍ ፍሰት «እጅግ አሳዛኝ» እና በአስቸኳይ ሊቆም የሚገባው ኩነት እንደሆነ ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ቡሎስ፣ በድጋፉ ላይ የተሳተፉትን ሀገራት ስም ለመጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲሆን፣ የእነዚህ ሀገራት ማንነት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ አስቀድሞ በግልጽ የሚታወቅ መሆኑን ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍6
ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ግዛት የነበረው ጦራቸውን የጎበኙት አልቡርሀን ከኢሳያስ ጋር ተገናኝተዋል።

ምጽዋ ወደብ የሚራገፈው የጦር መሳሪያ በጨመረበት ወቅት የተደረገ ጉብኝት መሆኑ ትልቅ ትኩረት ስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍9🕊1
ህወሃት የፌደራል መንግስትን በድሮን ጥቃት ሲከስ የአላማጣ ባለስልጣናት ደግሞ ህወሃትን ወቀሱ
 
ህወሃት የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህወሃት ታጣቂዎች የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕነት ቀይረዋል የሚሉ የአካባቢው ሪፖርቶች መውጣታቸውን ዶቼ ቬሌ  ዘግቧል።
 
የህወሃት ቃል አቀባይ ሚካኤል አሰግዶም በድሮን እና በሚግ ተዋጊ አውሮፕላኖች የታገዘው የአየር ጥቃት በአምስት ዞኖች በሚገኙ የህዝብ ተቋማት ላይ ማረፉን የገለጹ ሲሆን፣ በሰሜን ምዕራብ ዞን ደጀን ከተማ የሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ መውደሙን፣ እንዲሁም በእንደርታ እና በራያ አዘቦ አርሶ አደሮችና የመኖሪያ መንደሮች መመታታቸውን ጠቅሰዋል።
 
ይሁን እንጂ ከአላማጣ ከተማ የተገኙ አንድ የቀድሞ የአካባቢው ባለስልጣን ለዶቼ ቬሌ በሰጡት ተቃራኒ መረጃ፣ የህወሃት ኃይሎች አራት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በአላማጣ የሚገኙ ስምንት ትምህርት ቤቶችን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የማዘጋጃ ቤት ህንፃዎችን በአሁኑ ወቅት ወደ ታጠቁ ወታደራዊ ይዞታነት እና መፈጠሪያነት ቀይረዋቸዋል ሲሉ ከሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13👍2🤔2
በኔፓሉ የጎርፍ አደጋ ከዘጠኝ ቀን ፍለጋ ቡሀላ ሁለት ሰዎች በህይወት ተገኙ፡፡

በኔፓል በድንገተኛ ጎርፍ ምክንያት በዋሻ ውስጥ ለዘጠኝ ቀናት ተይዘው የነበሩ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ሠራተኞች በሕይወት መገኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በኔፓል በደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከ አንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉና ወደ አምስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸው የሚታወስ ነው።

ሳንጃያ ሻህ እና ካቢር ማሃርጃን ከትሪሹሊ 3A የኃይል ማመንጫ ዋሻ ውስጥ በአዳኝ ቡድኖች የተገኙ ሲሆን፤ በእጅና በእግራቸው ጉዳት ቢደርስባቸውም በአምቡላንስ ወደ ካትማንዱ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በዚያው ዋሻ ውስጥ ወደ 40 የሚጠጉ ሰዎች አሁንም ተይዘው እንዳሉ ሲገመት፣ የነፍስ አድን ሰራተኞች የፍለጋ ሥራቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤25👍5😢4
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
❤6👍4
ያለፍላጎታቸው ሴቶችን በወሲብ ንግድ ላይ ያሰማሩት አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፡፡

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አስተዳደር በመጠጥ ግሮሰሪ ንግድ ፈቃድ ሽፋን ሴቶችን ያለ ፍላጎታቸው ለወሲብ ንግድ ሲዳርጉና ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ አምስት ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና የገንዘብ መቀጮ መቀጣታቸውን የከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ ተከሳሾቹ በዘይበላ ወላሼ ቀበሌ «ኤል ክላሲኮ» የተባለ የምሽት ጭፈራ ቤት በመክፈት ሴቶችን በአስተናጋጅነት ካስቀጠሩ በኋላ በግዳጅ ለዝሙት አዳሪነት እንዲሰማሩ አድርገዋል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት አንደኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ የንግድ ፈቃዱን በማውጣትና ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በመሆን የተቀጠሩ አስተናጋጆችን ያለፍላጎታቸው የግብረ-ሥጋ ድፍረት ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ማድረጉ በበቂ ማስረጃ ተረጋግጧል።የቀረበውን የዐቃቤ ሕግ ክስና የፖሊስ ማስረጃ የመረመረው የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፋል።

በዚህም መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ተሬሳ ፍቃዱ ድርጊቱን በዋናነት በመምራትና በግዳጅ የመድፈር ጥቃት በመፈጸሙ በ23 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ200 ሺህ ብር መቀጮ፤ 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ደሴ በ10 ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር መቀጮ፤ 3ኛ ተከሳሽ ወርቁ ደሜ በ6 ዓመት እስራት እና በ45 ሺህ ብር መቀጮ፤ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ተመስገን ፍቃዱ እና ቤክና መሐመድ ደግሞ እያንዳንዳቸው በ1 ዓመት ከ8 ወር እስራትእንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍7🤔1
የህወሓት ድሮን ሰልጣኞች‼️
ህወሃት የድሮን ስልጠና የወሰዱ ከ15 በላይ ሰዎችን ወደ ራያ ማሰማራቱ ተሰማ።
ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት አረብኛ የሚናገሩ ነጮች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በራያ አላማጣ እንዲሁም ቅልሻ በሚባል አካባቢ ታይተዋል ብለዋል።
የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሶንጎ ኦባሳንጆ ህወሓት እና የፌደራል መንግስቱን ለማደራደር ጥረት ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍22🤣10❤7👀2✍1
በክልል ንግድ ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ መስራት አይቻልም ሲል ቢሮው አሳወቀ‼️

በክልል ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ አስመጪዎች ንግድ ፈቃዳቸውን ወደ አዲስ አበባ ማዛዋወር አለባቸው ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በመኪና ሽያጭ ዘርፍ በሚደረጉ ህገወጥ አሰራሮች እና የታክስ ስወራዎች ላይ ጥብቅ እርምጃና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታወቀ።

በክልል ፈቃድ አዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ አስመጪዎች ንግድ ፈቃዳቸውን ወደ አዲስ አበባ ማዛወር አለባቸው ተብሏል።

ደረሰኝ መለየት የሽያጭ ማሽን ማስተካከል እና ወርሃዊና ዓመታዊ ግብር መክፈል አለባቸው ነው የተባለው።

ህገወጥ ደረሰኝ መጠቀም ወይም የውጭ ሀገር ፈቃድ ብቻ ይዞ መንቀሳቀስ በህግ ያስጠይቃል።

አስመጪዎችና የመኪና ማሳያ ባለቤቶች ፈቃድ ከሌላቸው ደላሎች ጋር በመተባበር ህገወጥ የሽያጭ ሰነድ ከመፈራረም እንዲቆጠቡ ተሳስቧል።

ቢሮው ከዚህ አሰራር ውጭ በሚንቀሳቀሱ አስመጪዎች ፈቃድ የሌላቸው ደላሎች በኦንላይን ህገወጥ ንግድ የሚያካሂዱ ግለሰቦች እና ከተዋናዮቹ ጋር በሚተባበሩ አካላት ላይ ቢሮው ክትትልና ምርመራ በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ሲል አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9👍3🤩3🙊2👀1🤪1
ብልፅግና ከ70-80% አዲስ ተሿሚዎች‼️
ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በሚመሰርተው መንግስት ውስጥ ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ለአዲስ ተሿሚዎች ለመስጠት መወሰኑ ተሰማ።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ውሳኔያቸውን በሚንስትር እንዲሁም ሚንስትር ዲኤታ ቦታዎች ላይ እየሠሩ ለሚገኙ ተሿሚዎች ማሳወቃቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ ረዘም ላሉ ዓመታት በአመራርነት ያገለገሉ ተሿሚዎች ራሳቸውን ለሌላ ተልዕኮ እንዲያዘጋጁ እንደተነገራቸው ጠቁመዋል።

ይህም በሚንስትር እንዲሁም በሚንስትር ዲኤታነት እያገለገሉ ከሚገኙ ተሿሚዎች መካከል በአምባሳደርነት የሚሾሙ እንደሚኖሩ ጠቋሚ መሆኑን ሰምተናል። 
   
ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሚንስትሮችንና ሚንስትር ዲኤታዎችን በሰበሰቡበት መድረክ “ከ70 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ለውጥ ይደረጋል” ሲሉ መናገራቸውን የገለጡልን ምንጫችን፤ ከዚህ ውሳኔያቸው በኋላ ከሚንስትሮች እና ሚንስትር ዲኤታዎች ጋር ለቀናት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ነግረውናል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአምስት ዓመታት በፊት ካቢኔያቸውን ባዋቀሩበት ወቅት፤ ከ22ቱ የሚንስትርነት ቦታዎች መካከል ሦስቱን ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በአሁኑ የካቢኔ ምርጫም የሚንስትርነት ሹመት የሚሰጣቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የሚኖሩበት ዕድል ሰፊ መሆኑን ምንጮች ነግረውናል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የፓርቲዎች አመራሮች፤ ከሹመት ጋር በተያያዘ እስካሁን ለፓርቲያቸው የቀረበ ጥያቄ አለመኖሩን የገለጹ ቢሆንም፤ ሹመት እንደሚሰጣቸው ቃል እንደተገባላቸው የሚገልጡ የፓርቲ አመራሮች መኖራቸውን ሰምተናል።

እየተካሄዱ ያሉ ስብሰባዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሚንስትሮችን ለብቻ፤ ሚንስትር ዲኤታዎችንም ለብቻ ሰብስበው ማነጋገራቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ በስብሰባዎቹ ያለፉት ዓመታትን ከመገምገም ባለፈ አዲስ የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ነው።

በስብሰባዎቹ ከሚቀርቡ ሰነዶች ባሻገር፤ የቡድን ውይይቶች እየተካሄዱ መሆናቸውንም ሰምተናል።

ሚንስትሮች ስብሰባ ማድረግ ከጀመሩ ሁለተኛ ሳምንት ያስቆጠሩ ሲሆን በዚህኛው ሳምንት የተጀመረው የሚንስትር ዲኤታዎች ስብሰባ ደግሞ ስልክ ይዞ መግባት የተከለከለበት መሆኑን አውቀናል።

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስብሰባ ለተጨማሪ ቀናት እንደሚቀጥልም ምንጮች ጠቁመዋል።

Via : ዋዜማ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤17👍7🤪4🤷‍♂2🤔1👀1🙊1
ለአዲስ ዓመት የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 1,200 ብር እንዲሆን ከሥጋ ቤቶቹ ጋር ስምምነት መደረጉ ተገለጸ

ለተቃረበው የ2019 አዲስ ዓመት በዓል የሸማቹን እንግልትና ያልተገበበ የዋጋ ጭማሪ ለመግታት ያለመ አዲስ ውሳኔ ተ አስተላለፈ።

የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በመዲናዋ ከሚገኙ 274 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ጋር ባደረገው ዝርዝር ውይይት፣ አንድ ኪሎ የበሬ ሥጋ በ1,200 ብር ብቻ ለሕዝብ እንዲቀርብ መግባባት ላይ መድረሱን አስታውቋል።

የበዓላት ወቅት የመገበያያ ዋጋ ንረትና የአቅርቦት እጥረት የሚፈጥረውን ጫና ለማቃለል ሰፊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ሸማቾች በየአካባቢያቸው በሚገኙ ማኅበራት በኩል ምርቱን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ አረጋግጧል።

በሁሉም 274 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች አንድ ኪሎ ሥጋ ከ1,200 ብር በላይ እንዳይሸጥ ስምምነት ተደርሷል።

መንግሥት ከአርሶ አደሮችና ከበሬ አቅራቢዎች ጋር ቀጥተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠሩ በሥጋ ቤቶች በኩል የነዳጅና የአቅርቦት ምክንያት አቤቱታ እንደማይኖር ተገልጻል።

ከሥጋ በተጨማሪ ሌሎች የበዓል ሸመታዎችን ከእሁድ ገበያዎችና ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ሱቆች በቅናሽ ዋጋ መገበያየት እንደሚቻል ጥሪ ቀርቧል።

ከተቀመጠው የዋጋ ተመን በላይ በሚሸጡ ሥጋ ቤቶች ላይ ኅብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣18❤9👍4😢3
ቡና አብዝቶ መጠጣት የእንቅልፍ ጊዜን ቢያሳጥርም ጥልቀቱን እንደሚጨምር ተነገረ

​በቀን አራት ወይም ከዚያ በላይ ሲኒ ቡና መጠጣት የእንቅልፍ ቆይታን ያሳጥራል፤ ሆኖም በእንቅልፍ ወቅት የሚገኘውን ጥልቅ እረፍት እንደሚጨምር አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።

​በስዊዘርላንዱ ተመራማሪ በቤንጃሚን ስተኪ የተመራው ይህ ጥናት፣ የዩኬ ባዮባንክ እና የHypnoLaus መረጃዎችን በመተንተን የተሰራ ነው።

ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ካፌይን መውሰድ የእንቅልፍ ሰዓትን በ11 ደቂቃ ያህል ያሳጥራል።

​ነገር ግን፣ የሰውነት ህዋሳትን ለማደስ እና ኃይልን ለማገገም ወሳኝ የሆነው "የዝቅተኛ ሞገድ እንቅልፍ"  ጥልቀት ይጨምራል።

ሳይንቲስቶች እንደሚሉት፣ ይህ የሰውነት ተፈጥሯዊ ምላሽ ሲሆን፣ ያጣውን አጭር የእንቅልፍ ሰዓት በጥልቅ እንቅልፍ ለማካካስ የሚያደርገው ጥረት ነው።

​ጥናቱ ቡና የእንቅልፍ መጠንን ቢቀንስም፣ የጥራት መጠኑ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21👍3🙉2
ለስራ አጦች ደመወዝ መክፈል ተጀመረ‼️
አልጀርያ ስራ አጥ ለሆኑ ወጣቶቿ ደምሞዝ መክፈል ጀመረች
የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር አልጄሪያ ለዜጎቿ የዘረጋችው አስደናቂ የማህበራዊ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመላው አፍሪካ ከፍተኛ አድናቆትን እያተረፈ ይገኛል።

ሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብቷን እና የኢኮኖሚ አቅሟን ቀጥታ የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል በሚያስችሉ ዘመናዊ ውሳኔዎች ላይ በመመደብ በአፍሪካ አዲስ ምሳሌነቷን እያሳየች ነው።

ሀገሪቷ ስራ ለሌላቸው ወጣቶች በወር 96 ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች።

ይህ ድጋፍ ወጣቶች ስራ እስኪያገኙ ድረስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲሸፍኑ የሚያስችል ሲሆን ከገንዘቡ በተጨማሪ ነፃ የጤና መድህን አገልግሎትም ያካትታል ተብሏል።

በወር ከ 216 ዶላር በታች የሚያገኙ ዜጎች ምንም አይነት የገቢ ግብር እንዳይከፍሉ አድርጋለች።

በተጨማሪም አነስተኛ የደመወዝ ወለል ወደ 170 ዶላር ከፍ በማድረግ የዜጎችን የመግዛት አቅም እንዲሻሻል አድርጋለች።

ከዚህ በተጨማሪም ለህዝቧ በሙሉ ነፃ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አረጋግጣለች።

አልጄሪያ ግዙፍ የተፈጥሮ ጋዝ እና የሃይል አቅሟን በመጠቀም 100 በመቶ ለሚጠጉ ዜጎቿ ሙሉ በሙሉ ተራሽ እና ነፃ የሆነ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ማድረስ ችላለች።

ይህም በገጠር እና በከተማ የሚኖሩ ዜጎቿ በእኩል መሰረታዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል ነው የተባለው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍67❤20🏆13👌1🕊1💯1
በጦርነቱ የተጎዱ ወደ ዩኒቨርስቲ‼️
ህወሃት በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን እና የአካል ጉዳተኞችን ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች እያጓጓዘ ይገኛል።
ከላይ የተያያዘው ምስል ጉዳት የደረሰባቸው እና የአካል ጉዳተኞች ከኩሓ መለስ ካምፓስ ወደ አክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሲጫኑ የሚያሳይ ምስል ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍7🤪4🕊2✍1🤔1
ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የጉሙሩክ ኮሚሽን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ከነሐሴ 21 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አደረኩት ባለው ክትትል፣ 470.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ እና 81 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችን በድምሩ 551.5 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን መያዝ መቻሉን አስታውቋል።

ከተያዙት እቃዎች መካከል ጨርቃጨርቅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ መዋቢያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል።

በኮንትሮባንድ ቁጥጥሩ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ የጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚ ሲሆኑ  ቅርንጫፎቹ በቅደም ተከተል 186 ሚሊዮን፣ 117 ሚሊዮን እና 116 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ እቃዎችን ይዘዋል።

እቃዎቹ በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ ላይ በተደረገ ክትትል የተያዙ ሲሆን፣ 26 ተጠርጣሪዎችና 10 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ መግለፁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች ።

ጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላትና ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር የሚሠራ ሲሆን፣ ሕገወጥ ንግድን ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍3
ኢትዮጵያ በ83 ቢ. ብር ወጪ 16
ግዙፍ መርከቦችን ልትገዛ ነው

ኢትዮጵያ የውጪና የገቢ ምርቶቿን የሎጂስቲክስ አቅርቦት ለማቀላጠፍ በ83 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ወጪ 16 አዳዲስ መርከቦችን ለመግዛት አቅዳለች። በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ የሚከናወነው ይህ የግዥ እቅድ አሁን ካሉት 10 መርከቦች በተጨማሪ የሚከናወን ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከነበሩት ከ25 ሺህ እስከ 28 ሺህ ቶን አቅም በበለጠ ከ50 ሺህ እስከ 63 ሺህ ቶን የመሸከም አቅም ያላቸው ግዙፍ መርከቦችን የሚያካትት ነው።

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት መርከቦች በላይ ሕጋዊ የግዥ ሥርዓት በሂደት ላይ ይገኛል። አዲሶቹ መርከቦች ስትራቴጂክ ግብዓቶችን በብቃት በማስገባትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በወቅቱ በመላክ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14🤪4👍2