አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.5K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የዘንድሮ የጳጒሜ ቀናት 'የማንሰራራት ቀን' በሚል ርዕስ በሚከተሉት ስያሜዎች ይከበራሉ፡-
​ጳጉሜ .1 - የእመርታ ቀን
​ጳጉሜን.2 - የማንሰራራት ቀን
​ጳጉሜን.3 - የጽናት ቀን
​ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀን
​ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚል እንደሚከበር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣43❤14👍6🤔4🤪4✍1👀1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የደቡብ ኮሪያ ጠንቋዮች AI ገቢያችንን ክፋኛ ቀንሶብናል ብለው አማረሩ

በቴክኖሎጂ ምጥቀት ቀዳሚ ከሆኑት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ደቡብ ኮሪያ፣ የቅርብ ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዕድገት የዘመናት ታሪክ ባለው የባህላዊ ዕድል ትንበያ (ጥንቆላ) ኢንደስትሪ ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ መሆኑ ተሰማ።

በአገሪቱ የሚገኙ ታዋቂ ዕድል ተንባዮችና ጠንቋዮች ወደ እነርሱ ይመጡ የነበሩ ደንበኞቻቸው ፊታቸውን ወደ AI ቴክኖሎጂ በማዞራቸው ምክንያት ሥራቸው ክፉኛ እንደ ተቀዛቀዘባቸው በምሬት በመግለጽ ላይ ናቸው።

በዋና ከተማዋ ሴኡል ዳርቻ በሚገኘውና በባህላዊ ዕድል ተንባዮች (ጠንቋዮች) መንደርነቱ በሚታወቀው ‘ሚያ መንደር’ ውስጥ አሁን ላይ የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

ቀደም ባሉ ዓመታት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎች ስለ ጤናቸው፣ ትዳር፣ ፍቅር፣ ገንዘብ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ለመጠየቅ ወደዚህ መንደር በብዛት ይጎርፉ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ አብዛኞቹ ዜጎች በአካል ወደ መንደሩ ከመሄድ ይልቅ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ የ-AI መተግበሪያዎችን በመጠቀም ዕድላቸውን መተንበይ መምረጣቸው ተገልጿል።

በዚሁ መንደር ውስጥ ከቀሩት ጥቂት ዕድል ተንባዮች መካከል አንዷ የሆኑት የ86 ዓመቷ አዛውንት ሶንግ ኦ-ሱን ሁኔታውን ሲያስረዱ፣ እሳቸው አሁንም ከዘመናዊው የኢንተርኔት ዓለም ርቀው እንደሚኖሩና ዕድልን ለመተንበይ “አራቱ የዕጣ ፈንታ ምሰሶዎች” (Saju) የሚባለውን የኮሪያ ጥንታዊ ኮከብ ቆጠራ ዘዴ በብሬይል መጽሐፍ እያነበቡ እንደሚጠነቁሉ ገልጸዋል።

አዛውንቷ ባለፉት 40 ዓመታት ያካበቱት ይህ የሰዎች ስነ-ልቦና የመረዳትና የማማከር ልምድ AI በቀላሉ ሊተካው የማይችለው የላቀ ሰብአዊ ችሎታ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ። “በሕይወት የመኖር ተስፋ ቆርጠው ለመሞት እንኳ ወደ እኔ የመጡ ሰዎችን አሳምኜና አጽናንቼ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ አድርጌያለሁ” ሲሉም የሥራቸውን ማኅበራዊ ፋይዳ ያስረዳሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣25❤13👍5😈1🤪1
የደመወዝ ወለል ተስፋ አለው‼️
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን አሁንም የውትወታ ሥራዬን አላቆምኩም ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ።

በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በተለይ በቋሚ ደመወዝ ኑሯቸውን ለሚገፉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኮንፌዴሬሽኑ ተናግሯል።

የኑሮ ውድነቱ የሚያድግበት ፍጥነት ሠራተኛው ከሚያገኘው ቋሚ ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ደመወዝተኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፍ እያስገደደው ነው ተብሏል።

በዚህም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰንና የግብር ቅናሽ እንዲደረግ ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አሰታውሰዋል።

የአሰሪና ሠራተኛ አዋጁ ሲሻሻል ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን የተደረገው የውትወታ ሥራ መሳካቱን ተናግረው ይሁንና ተግባራዊ እንዲሆን አሁንም እየጠየቅን ነው ሲሉ ያብራራሉ።

ሌላኛው በተደጋጋሚ ከሚጠየቁት መካከል የሥራ ግብር እንዲቀነስ የሚለው ይገኝበታል።

በዚህም በኩል ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሰራ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ግብር እንዲቀነስ ከማይፈልጉት መካከል አንዱ IMF ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እና የIMF ኢትዮጵያ ተወካይም ሆነ ዋና የIMF ዳይሬክተርን አግኝተን ለምን ግብር እንዲቀነስ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳለበት ለማስረዳት ሞክረናል ያሉት አቶ ካሳሁን በመጨረሻ መስማማት ላይ መድረሳቸውን ለሸገር ሬዲዬ አስረድተዋል::
አሁን ተስፋ ሰጭ ነገሮች እንዳሉት አክለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤36👍8🙏2🤪1
ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይባሕር ለመቁረጥ
አሲራለች - -አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ

የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ክፍተቶች እና ተቃዋሚ ኃይሎች በመጠቀም ሀገሪቱን ለማዳከም አሁንም እየሠራች መሆኑን ገለጹ። ኢትዮጵያ የዓባይ ምንጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የግብጽ ባለሥልጣናት እና ሽርኮቻቸው ሀገሪቱን ለማዳከም እና ከቀይ ባሕር እንድትርቅ ለማድረግ ሸርበዋል ሲሉ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከባሕር በር ተቆርጣ ልትቀር አትችልም ያሉት አምባሳደሩ፤ ኤርትራ ከመገንጠሏ በፊት በታሪክ ምፅዋን እና ዓሰብን ማስተዳደሯን እንዲሁም የባሕር ኃይል እንደነበራት አስታውሰዋል። ለዚህም የሀገሪቱን የሕዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ፣ የገቢና ወጪ ንግድ ዕድገት፣ ለቀይ ባሕር ቅርብ መሆኗን እና ከአካባቢው ወደቦች ጋር ያላትን ታሪካዊ ትስስር በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍5🤣4🤪1
በህንድ የቲክቶክ እይታ ለማግኘት ወደ አንበሳ ማቆያ የዘለለው ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል

በህንድ ላሆር መካነ አራዊት ውስጥ አንድ የቲክቶክ ተጠቃሚ ለማህበራዊ ሚዲያ የሚሆን ቪዲዮ ለመቅረጽ ወደ አንበሶች ማቆያ ስፍራ ዘሎ ሲገባ በመታየቱ፣ ከፍተኛ የደህንነት ጉድለት ተከስቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨው ይህ ቪዲዮ፣ በስፍራው ስላለው የደህንነት አጠባበቅ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

አንድ የቲክቶክ ተጠቃሚ የአንበሶች ማቆያ አቅራቢያ ወደሚገኘው የተከለከለ ቦታ እና ወደ አንበሳ ማቆያው ውስጥ በተደጋጋሚ የገባ ሲሆን፣ በስፍራው የነበሩት የደህንነት ሰራተኞችም እርምጃውን ማስቆም አልቻሉም። ይህ ክስተት በስፍራው ስለሚተገበሩት የደህንነት አሰራሮች እና የደህንነት ሰራተኞች አፈጻጸም ላይ ጥያቄዎችን አስነስቷል።

የአራዊት መናፈሻው አስተዳደር፣ የደህንነት አሰራሮችን ለማጠናከር እንዲሁም የጎብኚዎችን እና የእንስሳትን ደህንነት ለማረጋገጥ አዲስ የደህንነት ኩባንያ እየተቀጠረ መሆኑን ገልጿል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተወዳጅነትን ለማትረፍ (ቫይራል ለመሆን) ሲባል አንድ ግለሰብ ህይወቱን ለአደጋ ሲያጋልጥ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።

ከዚህ ቀደም በክይበር ፓክቱንክዋ ግዛት ስዋት ወረዳ፣ አንድ ወጣት የቲክቶክ ተጠቃሚ ቪዲዮ እየቀረጸ ሳለ ሽጉጡን በድንገት በመተኮሱ ሕይወቱ አልፏል። ለማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም ለቲክቶክ) አዳዲስ እና ልዩ በሆኑ መንገዶች ቪዲዮ የመቅረጽ አዝማሚያ የሚያስከትለውን የሞት አደጋ መቀነስ አልተቻለም፤ ልዩ በሆነ መልኩ ቪዲዮ የመቅረጽ ከፍተኛ ፍላጎትም ሕይወት ቀጥፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤19👍3🤣2🥰1😢1👀1🤪1
በአዲስ አበባ የመኪና ንግድ ማዕከላት ላይ ሰፊ የግብር ስወራ መኖሩ ተጋለጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በሚገኙ የመኪና ንግድ ማዕከላትና የመኪና ድለላ ዘርፍ ላይ ባካሄደው ምርመራ ሰፊ የሆነ የግብር ስወራ መኖሩን እንደደረሰበት ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

በመኪና ንግድና ደላላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ዓመታዊ የገቢ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግዴታቸውን በአግባቡ እንደማይወጡ የቢሮው ጥናት አሳይቷል።

ይህን ተከትሎም በመኪና ደላላነት / በኮሚሽን ንግድ የሚሰሩ ነጋዴዎች በግቢያቸው ያስቀመጧቸውን መኪኖች እንዲያስወጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ነበር።

ቢሮው እንደገለጸው፣ መኪናዎችን ለሽያጭ በማይፈቀድላቸው ቦታዎች ማስቀመጥና መሸጥ ከሕጋዊ የንግድ ደንቦች ጋር የሚጋጭ ነው።

ቢሮው ባወጣው መመሪያ፣ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የመኪና አስመጪ ድርጅቶች ብቻ በተፈቀደላቸው የንግድ ቦታ መኪና መሸጥ እንደሚችሉ በግልጽ አስቀምጧል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በትክክል አስመጪ ያልሆኑና በኮሚሽን የሚሰሩ እጅግ በርካታ የመኪና መሸጫዎች ተዘግተው ነበር።

አሁን ላይ በተሻሻለ መመሪያ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተፈቅዶላቸዋል። ሆኖም የመኪና ነጋዴዎች የሚሰሩበት ሥርዓት ላይ ገደቦች ተጥለዋል።

በተለይም አዲስና ያልተነዱ "Zero-Mile" መኪኖችን በግል ኮሚሽን ወይም ትርፍ ላይ ተመስርቶ መሸጥ እንዲሁም እነዚህን መኪኖች በራሳቸው ግቢ ውስጥ መሸጥ አይፈቀድም።

አዲስ መኪኖችን የማስመጣትና የመሸጥ መብት ሕጋዊ ፈቃድ ላላቸው አስመጪዎች ብቻ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል፥ የመኪና ደላላዎች በግለሰቦች የተያዙ ያገለገሉ መኪኖችን በኮሚሽን መሸጥ ወይም መኪና በራሳቸው ገዝተው እንደገና መሸጥ ይችላሉ፤ ይህም ግን የተቀመጡትን የግብርና የንግድ ሕጎች በመከተል ብቻ መሆን አለበት።

የመረጃው ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤3👍2🤔1
በሀሰተኛ ሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።

​ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ ጠዋት ከእስር ተፈተው በአሁኑ ሰዓት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

​ግለሰቡ በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት በመሞከራቸው፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የአምስት ዓመት እስራት እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

​ከእሳቸው ጋር አብረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው እንደነበር አይዘነጋም።

ተከሳሾቹ የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ተላልፈዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው በኋላ፣ ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ ከእስር ተለቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤13🤯5😡3👍2🥰1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጊዜው ከስራ ታገዱ‼️
2ቱ የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ መደረጉ ተገለፀ::

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለማስፈጸም በሚያከናውናቸው የመስክ ቁጥጥር ስራዎች ወቅት ከመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር አለመግባባቶች እንደሚከሰቱ ገልጿል።

በዛሬው ዕለት (ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም) በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲሰራጭ የዋለውን ምስል አስመልክቶ ተቋሙ ባወጣው መረጃ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርቷል፦

• የቁጥጥር ባለሙያዎች ደንብ የተላለፈን አሽከርካሪ የመንጃ ፈቃድ በሚጠይቁበት ወቅት "አልሰጥም" በማለት ስራ ማስተጓጎል፣ ስድብ፣ ዛቻ ወይም ሃይል መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል።

• ተቋሙ በምስሉ ላይ የታየውን አለመግባባት ግራና ቀኝ ያለውን አካል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በማጣራት ላይ እንደሚገኝና እስከዚያው ድረስ በክስተቱ ላይ የተሳተፉት ሁለቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ ማድረጉን አስታውቋል።

ህብረተሰቡ የችግሩን የማጣራት ሂደት በስክነት እንዲከታተልና ትክክለኛ ካልሆኑ መረጃዎች እንዲቆጠብ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣23❤20👍5🙊5🤔2⚡1👌1👀1🙈1
የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚዋሠነው ብሉ ናይል ግዛት በርካታ ተዋጊዎችን በማንቀሳቀስ ላይ መኾኑን አስታወቀ።

ወደ ብሉ ናይል ግዛት ደማዚን ከተማ አካባቢ የተንቀሳቀሱት ተዋጊዎች የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ለመውጋት ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር የወገኑ ኃይሎች እንደሆኑ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ በግዛቲቱ በርካታ አካባቢዎች በመንግሥት ወታደሮችና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቅራቢያ ስትራቴጂካዊቷን ኩርሙክ ከተማ ከአንድ ሳምንት በፊት ከሱዳን ጦር ሠራዊት መንጠቁ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍4❤2🤔1🕊1
ቀን 28/12/2018
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 09 17 48 53/09 07 36  23 85
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉   የስራ መደብ:# NGO
👉የት/ደረጃ ዲፕሎማ / ድግሪ
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞዝ:- 40.000_50.000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው  መደብ =- ሀውስ ኪፒግ
👉የትምርት ደረጃ 8 +
👉የስራ ልምድ 0-3
👉ደሞዝ 7000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ሆስተስ
👉የትምርት ደረጃ 10 +
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 15000 / 20000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =-መስተግዶ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0/2
👉ጾታ ወንድ /ሴት
👉ደሞዝ ማራኪ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የስራው መደብ /ፓስታ ፋብሪካ=-የእሸጋ ሰራተኛ
👉  የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
👉ደሞዝ:-  17000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
👉ደሞዝ ፡ 15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ሹፌር ደ/1 2 ህ/1/ሞተረኛ
👉የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
👉ደሞዝ:- 7000_17000
👉ፆታ :- ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ትኬተር/ለባስ/
👉የሰራ ልምድ :- 0አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
👉ደሞዝ:- 0አመት
👉ደሞወዝ   :- 9000~20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
👉የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
👉ደሞዝ:-8000_30000+
👉የስራ ልምድ: 0አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ :markting
👉የት ደረጃ ፡- degree 
👉የስራ ልምድ ፡- 0~5 አመት
👉ደሞዝ :-13000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ Accountant
👉የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
👉ደሞዝ ፡  8,000-16,000 
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ IT
👉የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
👉የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
👉ፆታ:- ሴ/ወ
👉ደሞዝ:- 8000-15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ካሸር
👉የት/ደረጃ፦10 +
👉የሰራ ልምድ 0~3 አመት
👉ደሞዝ:- 7000-12000
👉ፆታ፦ሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#nurse//ላብራቶሪ/ጠቅላላ
👉 ለክሊኒክ እና ለሆስፒታል
👉የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
👉የስራ ልምድ: 0~8አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉ፆታ፦ሴት/ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ 8
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-1
👉ደሞዝ :7000-20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
👉የትምርት ደረጃ 8+
👉የስራ ልምድ 0 -1 አመት
👉ደሞዝ 10000-25000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ=- ፀሀፊ
👉የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
👉የስራ ልምድ ያላት
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 8000/13000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው አይነት =- ባርቴንደር
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልድ 1/3
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 10000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ብስኩት ፋብሪካ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 16000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
👉የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት
👉ደሞዝ:-9000-35000
👉ፆታ፦ወንድ/ሴት
👉የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ እሪል እስቴት ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ ዲፕ/ዲግሪ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ ፡  9000-50000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ሁለገብ ሰራተኛ
👉የደረጃ ፡- 8_10
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞወዝ :- 10000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ reception
👉የት ደረጃ ፡ 10/12
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ 8000/15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#ተላላኪና ፅዳት ለባንክ
👉የት/ደረጃ፦8/12 /ዲፕ
👉 የሰራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
👉ፆታ: ሴ/ወ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
👉ደሞዝ ፡  15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉መረጃና መዝገበ አያያዝ 
👉 የት ደረጃ ፡ dip-degree
👉የስራ ልምድ ፡ 0_1አመት
👉ደሞዝ ፡  13500
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ወደ 24 በሚወስደው መንገድ  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305  👇👇👇👇👇
         ☎️ 0907362385
         ☎️  0909174853
     
❤10👍3
«የሆርሙዝን ስም ወደ "ትራምፕ ስትሬት" ብንቀይረውሳ?» — ፕሬዝዳንት ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው የሶሻል ሚዲያ መድረክ Truth Social ባሰፈሩት አነጋጋሪ መልእክት፣ ስትራቴጂካዊውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ  ስም ለመቀየር ሀሳብ አቅርበዋል።

ትራምፕ ባሰፈሩት መልእክት «አሁን አካባቢውን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ቁጥጥር ስር ስላደረግነው፣ የሆርሙዝን ስም ወደ "ትራምፕ ስትሬት" ብንቀይረውሳ?» ሲሉ ጠይቀዋል

አክለውም እንደ አሜሪካ ሀገር ሁሉ ቦታው «ከመቼውም ጊዜ በላይ ሳቢና ተፈላጊ  ይሆናል!» ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።ይህ የትራምፕ አስተያየት የመጣው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በሆርሙዝ የባህር መስመር እና በላራክ ደሴት አካባቢ ከፍተኛ የሚሳኤል እና የባህር ኃይል ፍጥጫ እና ጥቃት በተካሄደበት ወቅት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣31👍12❤7😡2🤷‍♂1😎1
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተከስተዋል‼️
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአንድ ወር ገደማ ከእይታ እረቀው በመቆየታቸው የተለያዩ መረጃዎች ሲሰራጩ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በይፋ ታይተዋል።
በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ጋር ማከናወናቸውን ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤪8👍6🤷‍♂1👌1🤣1💔1
ዱቲ መመሪያ ቁጥር 682018 (2) (1) (1).pdf
4.8 MB
መልካም ዜና‼️
የትርፍ ስዓት ክፍያ‼️
የአማራ ክልል የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ስዓት ክፍያ (#Duty) ጥያቄ መፍትሔ አግኝቷል።
ሙሉ መመሪያው ከላይ ተያይዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍7❤3🙏3👌2🎉1🤝1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 10 የቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከስምምነት ሊደርስ ነው

እንደ አሜሪካ ጆርናል ኦፍ ትራንስፖርቴሽን ዘገባ መሰረት ​የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 10 የሚደርሱ ቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት ለማጠናቀቅ መቃረቡን ምንጮች ገለጹ።

ይህ ውል አየር መንገዱ ከአረብ ኤምሬትስ እና ቀጣናው አየር መንገድ ኩባንያዎች ጋር ያለውን ውድድር ለማጠናከር እና አዲስ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ማዕከል  ለመገንባት ለያዘው እቅድ ትልቅ ማበረታቻ ነው ተብሏል።

​እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ግዢው ሁለት የነባሩን '777F' ሞዴል እና የተቀሩትን ደግሞ አዲስ ምርት የሆኑትን '777-8F' የጭነት አውሮፕላኖች ያካተተ ነው።

ቦይንግ የ '777X' አውሮፕላን ማረጋገጫ በመዘገየቱ ምክንያት ነባሩን ሞዴል የማምረት ፈቃድ ለማራዘም ከአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር እየተነጋገረ ይገኛል።

​አየር መንገዱ እና ቦይንግ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጡት ይፋዊ አስተያየት ባይኖርም፣ ውሉ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የካርጎ ኤክስፖርት አገልግሎት ያለውን የበላይነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤10👍4🥰1😢1👌1🫡1
እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደገለጸው አሁን ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው  የኤል ኒኖ ክስተት በ70 ዓመታት ውስጥ ከታዩት በጣም ኃይለኛ ክስተቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ያስታወቀ ሲሆን፥ክስተቱም ቢያንስ እስከ የካቲት 2027 ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከፍተኛ የአየር ሁኔታ አደጋ ወደሚበዛበት ደረጃ እየገባች መሆኑን አንስተው፥ኤል ኒኖ እየጠነከረ በመምጣቱ የድርቅ፣ የጎርፍ፣ የመሬት ናዳ እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋዎች ሊባባሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል የባሕር ሙቀት በቅርብ ወራት በከፍተኛ ሁኔታ  የጨመረ ሲሆን፥በተለይም የባሕር ወለል ሙቀት ከመደበኛው በ2 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰው ልጅ ከሚመነጨው የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ሙቀት መጨመር ላይ ተደምሮ የከፋ የአየር ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

ባለሙያዎች በበኩላቸው የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ የሕክምና ድጋፍና የአደጋ ዝግጅት ሥርዓቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤11👍4😢2👀1
መግቢያ ውጤት ላመጣችሁ‼️
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ምርጫቸው የሚያስገቡበት ቀን ይፋ ሆነ 

የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያስገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ምርጫቸውን ትምህርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ።

የምርጫ ማስገቢያ ድረ-ገጹ፦ student.ethernet.edu.et ነው።

- በሕክምና ምክንያት ልዩ ሁኔታ ያላቸው፣
- የአካል ጉዳተኛ የሆኑ፣
- ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች
- ከ6 ወር በታች ሕፃን የሚያጠቡ እናቶች ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍8🙏1👌1
ህፃን አግታ 3 ሚ. ብር የጠየቀችው
የቤት ሰራተኛ በጎንደር ተያዘች!


አዲስ አበባ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የሰባት ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን በማገት ወደ ጎንደር ከተማ የወሰደችው መቅደስ ሞገስ የተባለች ወጣት፣ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዋ ህፃኗን በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ደብቃ በነበረበት ወቅት በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋል ችላለች።

ከአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር ወንጀሉን የፈፀመችው ተጠርጣሪዋ፣ ለቤተሰብ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች ሲሆን፣ ከ370 ሺህ ብር በላይ መቀበሏ ተረጋግጧል፤ ፖሊስም ቀሪ ተባባሪዎችን ለመያዝ ክትትል እያደረገ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍7🙏3👌1
295 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዷል‼
​
ኢትዮ ቴሌኮም “ቀጣዩ አድማስ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” የተሰኘውን የሶስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታውን ሁለተኛ ዓመት (የ2019 በጀት ዓመት) አጠቃላይ የቢዝነስ እቅድ ይፋ አድርጓል።

📌​በእቅዱ የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
​💰 የገቢ እና የውጭ ምንዛሪ ግብ
​አጠቃላይ ገቢ፦ የ36.7% (የ79.2 ቢሊዮን ብር) እድገት በማስመዝገብ 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል።

​የውጭ ምንዛሪ፦ 253.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

📌​👥 የደንበኞች ቁጥር እድገት
​አጠቃላይ ደንበኞች፦ በ6.7% በማሳደግ 96.2 ሚሊዮን ለማድረስ፤

​የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች፦ የሞባይል ዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በ16.5% በማሳደግ 60.01 ሚሊዮን ለማድረስ ግብ ተይዟል።

📌​📱 የቴሌብር እና የዲጂታል ፋይናንስ እድገት
​የቴሌብር ደንበኞች፦ 67.69 ሚሊዮን ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​የግብይት መጠን፦ የንቁ ግብይቶች መጠን 7.4 ትሪሊዮን ብር (በብዛት 4.99 ቢሊዮን) ይደርሳል ተብሏል።

​አነስተኛ ብድር፦ በቴሌብር የሚሰጠው የዲጂታል አነስተኛ ብድር ከ19.51 ቢሊዮን ብር ወደ 35.04 ቢሊዮን ብር ከፍ ይላል።

📌​📡 የመሰረተ ልማት እና የኔትወርክ

​የ4G ኔትወርክ፦ 5,417 አዳዲስ የ4ጂ ጣቢያዎችን በመገንባት ሽፋኑን ከ82.23% ወደ 95% ለማሳደግ ታቅዷል።

​የ5G አገልግሎት፦ ተደራሽ የሚሆንባቸውን ከተሞች ቁጥር ከ33 ወደ 73 በማሳደግ የጣቢያዎቹን ቁጥር 648 ለማድረስ ዝግጅት ተጠናቋል።

​📱 ስማርት ስልኮች እና የአገራዊ ልማት ድጋፍ
​"ዘኔክሰስ" ስማርት ስልኮች፦ ዲጂታል አካታችነትን ለማረጋገጥ 1 ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ስልኮች ለገበያ ያቀርባል።

​የመንግስት ገቢ፦ 43.1 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል እና 83.8 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግብር ገቢ ለማድረግ ማቀዱን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በስካይላይት ሆቴል ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤔10😢7😡5🙈3👍2🤩1👀1🤪1💊1
"ጦርነቱ ከተጀመረ የኤርትራ ጄኔራሎች ይደመሰሳሉ፤ተመለሱ የሚለንም የለም!"  - ኮሎኔል ነጋሽ‼️

የኤርትራ አመራሮች እጣ-ፈንታ፦** ጦርነት ከተቀሰቀሰ የኤርትራ ጄኔራሎች እና አመራሮች ሙሉ በሙሉ እንደሚደመሰሱና ኤርትራም በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ሥር እንደምትገባ ኮሎኔል ነጋሽ አስጠንቅቀዋል።

የኢትዮጵያ የማያዳግም እርምጃ፦** የኢትዮጵያ ቀዳሚ ፍላጎት ሰላም መሆኑ ቢገለጽም፤ ሀገርን የሚያፈርሱ እና የሚያበጣብጡ ኃይሎችን ግን ዝም ብሎ ከመመልከት አልፎ፣ባሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ተገቢውን ዋጋ እንደሚያስከፍሏቸው ቁርጡን ተናግረዋል።

የተቀየረው የጦርነት አውድ፦** እንደ ቀደመው ጊዜ "ተራራ የመያዝ፣ የመልቀቅ፣የማፈግፈግና የማጥቃት" ዘመን አብቅቷል። አሁን ያለው ውጊያ ከፍተኛ የሰው ኃይልን ማዕከል ያደረገ ሳይሆን፣በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅም ጦርነቱን ማጠናቀቅ ወደሚቻልበት ደረጃ መሸጋገሩን አብራርተዋል።

የ1990ው ታሪክ አይደገምም፦** በ1990 ዓ.ም ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ተከባ የነበረ ቢሆንም፤የኤርትራ አመራሮች ከሞት የዳኑት "በጥቂት የኛ አመራሮች" (ወደ ኋላ ተመለሱ ባሉ) ምክንያት እንደነበር ኮሎኔሉ አስታውሰዋል። አሁን ግን ያ ታሪክ እንደማይደገምና "ተመለሱ የሚሉንም የሉም" ሲሉ የማያዳግም መልዕክት አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪18❤13👍6🤣3😎2🫡1