በካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ግለሰብ የመኪና ዕድለኛ ሆነ
በደቡብ ወሎ ኩታበር ወረዳ ነዋሪ የሆነው ወጣት ሰለሞን ብርሃን በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የቶምቦላ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆን የዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ባለቤት ሆኗል። በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው በርክከብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ወጣት ሰለሞን የመኪናውን ቁልፍ እና ህጋዊ ሊብሬ ተረክቧል።
በግል ካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራው ወጣት ሰለሞን ብርሃን ከዕለት ተዕለት ሥራው በተጓዳኝ አዘውትሮ ሎተሪ የመግዛት የቆየ ልማድ እንደነበረው ገልጿል። ላለፉት በርካታ ዓመታት ተስፋ ሳይቆርጥ ዕድሉን ሲሞክር የቆየው ወጣቱ፣ አሁን ላይ የ3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማውና የዘመናት ትልቅ ሕልሙ እንደተሳካለት ተናግሯል።
ይህ በዕድል የደረሰውን ዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ለግል አገልግሎት ከመጠቀም ይልቅ ቀጣይ ሕይወቱን ለማሻሻል በሚያስችለው መልኩ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሰማራት ማቀዱን ገልጿል።
@Addis_Reporter

❤28🫡2
ተሽከርካሪዎች የለጠፉትን ጥቁር ስቲከር እንዲያነሱ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ አሳሰበ
****
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተለዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ወይም VIP ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ከተማ ፣ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ ማናቸውም ተሽከርካሪዎች መስታወት ላይ የተደረጉ ጥቁር ስትኬሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነቀሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።
ኮሚሽኑ በክልሉ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጸጥታ ቁጥጥር ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ፣ የግል ፣ የንግድ ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
ይህ የጸጥታ መመሪያ በሁሉም የክልሉ አወቃቀሮች በጥብቅ የሚተገበር ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሰው በተሽከርካሪዎቻቸው መስታወት ላይ ጥቁር ስትኬር ይዘው በተገኙ አካላት ላይ ኮሚሽኑ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል።
የመንግሥት አመራሮች፣ ሕብረተሰቡና የድርጅት ኃላፊዎች ለሕግ ማስከበር ሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል።

❤15🥰1
"የግብረሰዶማውያን ማህበር ፕሬዚዳንት " ተደበደበ !
በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ " የግብረሰዶማውያን ማህበር ፕሬዚዳንት " እንደሆነ የተነገረለት እና እራሱም የፖሊስ መኮንን የሆነው ፒየር ፒካቬት የተባለ ግለሰብ በጠርሙስ ተቀጥቅጦ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል መግባቱን ከፍራንስ 24 ዘገባ ተመልክተናል።
ፒካቬት በፓሪስ መሃል በሚገኘው ማራይስ አካባቢ ከአንድ ባር ከወጣ በኋላ በአንድ ግለሰብ በጠርሙስ መቀጥቀጡ ተገልጿል።
ጥቃቱ በሰውነቱ ላይ በርካታ ጉዳቶችን እንዲደርስበት ያደረገ ሲሆን የውስጥ ደም መፍሰስና የጭንቅላት ቁስልም እንደደረሰበት ተዘግቧል።
ፓሪስ ውስጥ የግብረሰዶማውያን መብት ተሟጋች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ፒካቬት እራሱን የፖሊስ መኮንን መሆኑን በመግለጽ የፖሊስ መታወቂያውን ቢያሳይም፣ ተጠርጣሪው ጥቃቱን እንዳላቆመ ተመላክቷል።
በጥቃቱ ወቅትም ጥቃት አድራሹ " አጸያፊ ነው " ስላለው የግብረሰዶማዊነት ተግባር በስድብና በኃይለ ቃል ግለሰቡን ሲናገረው እንደነበር ተመላክቷል።
ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከዚህ በፊት የወንጀል መዝገብ እንደሌለው ተገልጿል።
የፓሪስ ከንቲባ ኤማኑኤል ግሬጎዋር ጥቃቱን አውግዘዋል። " ፓሪስ ለሁሉም ሰዎች የነፃነትና የደህንነት ከተማ ሆና ትቀጥላለች " ሲሉ መናገራቸው ነው የተሰማው።

❤81👍31🤣7🍾5🤪5🤝3🙏2🎉1🌚1👀1
በላይቭ (Live) ግድያ የፈፀሙት በቁጥጥር ስር ዋሉ።
"100 ተጠርጣሪዎች ታፈሱ! የሳውዲው ግድያ መረጃ...
"በሳውዲ አረቢያ ድንበር ላይ በኢትዮጵያውያን መካከል የተፈፀመው አስደንጋጭ ግድያ አዲስ መረጃ ወጥቷል።
• ግድያውን የፈፀመው ግለሰብና 5 ግብረ አበሮቹ ተይዘዋል።
• በሶሻል ሚዲያ ጉዳዩን በማራገብ ተጠርጣሪ የሆኑ ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
• የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሳውዲ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ወንጀለኞችን የማደን ስራውን አጠናክሯል።
የኢትዮጵያዊነትን ባህል ያረከሰው ይሄ ድርጊት የህግ የበላይነት ሊረጋገጥበት ይገባል።
ድምፅ ለሆናችሁና መረጃ ለሰጣችሁ ሁሉ ኤምባሲው ምስጋና አቅርቧል።

❤38👍17🤣3🌚1
አባይ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ተሰጠው!
"የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በአባይ ቴሌቪዥን ላይ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ባለስልጣኑ ባለፉት ሦስት ወራት ባደረገው ክትትል፣ ጣቢያው በዜናዎቹና በፕሮግራሞቹ ላይ ከባድ የሕግና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶችን ፈጽሟል ብሏል።
ከጥሰቶቹ መካከል፦ከባህላችን ያፈነገጡ ፀያፍ ንግግሮችን ማሰራጨት፣የሴቶችን ክብር የሚነኩ ይዘቶች፣እና ያልተረጋገጡ የዜና ምንጮችን መጠቀም ይጠቀሳሉ።
የጣቢያው ኃላፊዎች ጥፋቱን አምነው ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን፣ በአፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱም ቃል ገብተዋል።

❤27👍21🙉5🤪4😡4🤩3🤡2🤔1😢1🙊1
"መንግሥት ከተጠያቂነት ሊያመልጥ አይችልም!" — አብን
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በንጹኃን ላይ የተፈጸሙትን ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች፣ የእምነት ተቋማት ውድመትና እገታዎችን በጽኑ ኮንኗል።
ንቅናቄው ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን አልተወጣም ሲል ከሷል። ጥቃቱን በታጣቂዎች ላይ ብቻ በማሳበብ መንግሥት ከተጠያቂነት ነፃ ሊሆን እንደማይችል የገለጸው አብን፣ በጸጥታ መዋቅሩ ላይ ላለው ውድቀት የባለሥልጣናት ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እንደሚገባ አሳስቧል።
አብን አክሎም፣ የዜጎች የመኖር መብት ባልተከበረበት ሁኔታ ስለ አገራዊ ብልፅግና ማውራት እውነታውን መካድ ነው ብሏል። ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የፌደራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት የተቀናጀ እርምጃ እንዲወስዱ፣ ገለልተኛ አካላት የሚሳተፉበት የምርመራ ሥርዓት እንዲዘረጋና ተፈናቃዮች በአስቸኳይ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

👍42❤16🥱2🤪2👌1🏆1
የአስመራ ነዋሪዎች በንጹህ ውሃ አጥረት
ምክንያት ቀይ ባህርን ለመጠጣት ተገደዋል ተባለ‼️
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚኖሩ ዜጎች በከባድ የውሃ እጥረት ምክንያት የዕለት ተዕለት ህይወታቸው መስተጓጎሉንና ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ልብስ ማጠብ እና የንጽህና መጠበቂያ የሚሆኑ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ ሲሉ የውሃ አጠቃቀማቸውን እጅግ ለመቀነስና አማራጭ የውሃ ምንጮችን በፍለጋ ለመንከራተት መገደዳቸውን ገልጸዋል።
የችግሩ አሳሳቢነት የከፋባቸው አያሌ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት መደበኛ የቧንቧ ውሃ ማግኘት ካቆመ ቆይቷል፤ በዚህም ምክንያት የውሃ ቦቴዎችን በመጠበቅ በውድ ዋጋ ውሃ ለመግዛት ተገደዋል። ሁኔታው ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ደግሞ አቅም በሌላቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ሲሆን አንዳንዶቹ የዝናብ ውሃ ለመሰብሰብ ሲጠባበቁ ሌሎች ደግሞ ከቀይ ባህር የሚጓጓዘውን የጨው ውሃ ለተለያዩ ፍጆታዎች ለማዋል እስከመገደድ ደርሰዋል።
ባለፈው ሐምሌ ወር የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በኤርትራ እየተባባሰ ለመጣው የውሃ አቅርቦት ችግር በምክንያትነት የተጠቀሱት የአየር ንብረት ለውጥ፣ የቆዩና የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ደካማ የውሃ አስተዳደር ስርዓት ናቸው።
ጥናቱ አክሎም በአሁኑ ወቅት የሚገኘው የውሃ አቅርቦት መደበኛ ያልሆነና ለጤና አስተማማኝ እንዳልሆነ በማስገንዘብ ሊከሰት የሚችለውን የጤና አደጋ ጠቁሟል።
ይህ ደረቅ ወቅቶች በመጡ ቁጥር ተደጋገሞ የሚከሰተው የውሃ እጥረት በነዋሪዎች የኢኮኖሚ አቅም ላይም የከፋ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የውሃ ግዥ ወጪ እየጨመረ መምጣቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ያላቸውን ትንሽ ገቢ ለውሃ እንዲያወጡ በማስገደድ ተጨማሪ የኑሮ ውድነት ፈጥሮባቸዋል።
አሁን ላይ በአስመራ እየታየ ያለው ይህ ቀውስ በከተማዋ ያለውን የዘለቀ የመሰረተ ልማት ውድቀትና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ማጣት አጉልቶ የሚያሳይ አሳሳቢ ክስተት ሆኗል።

😢14❤7👍4🕊1
በጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ “ግልቤና” ቀበሌ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በአራት ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው ሳቢያ 411 አባወራዎች ወይም ከ2,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም 26 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተደረመሱ ሲሆን፣ 31 የቤት እንስሳትም ሞተዋል።
የመሬት መንሸራተቱ አሁንም እየተስፋፋ ቢሆንም፣ ሕዝቡ ቀድሞ ወደ ቀበሌው ማእከል እንዲወርድ በመደረጉ ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማዳን ተችሏል።
ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ማእከል ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አስቸኳይ የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ የሚፈልጉ ቢሆንም እስካሁን ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳልደረሳቸው ተገልጻል።
ምንጭ: ቲክቫህ

💔11❤6😢6👍3😱1
የኮሊደር ልማት ይቀጥላል‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በቀጣዩ ዓመት በከተማዋ የኮሪደር ልማት የሚካሄድባቸው አካባቢዎች እንደተለዩ በከተማዋ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመትና የቀጣይ አምስት ዓመታት ዕቅድ የግምገማ መድረክ ላይ ተናገሩ። አዳነች የኮሪደር ልማት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የወንዞችን ዳርቻ ማደስና "የወደቁ" ሠፈሮችን የማንሳት ሥራ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በቁጥር ተለይቶ መቀመጡን አዳነች ገልጠዋል። አዳነች አያይዘውም፣ ያረጁ ሠፈሮችን የማደስ ሥራ ነዋሪዎችን በንጽህና እንዲኖሩ ከመደገፉ ባሻገር፤ በተደጋጋሚ የሚከሠቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በቀጣዩ የኮሊደር ልማት የትኞቹ ሰፈሮች እንደሚነሱ በግልፅ አልታወቀም።

😡22👍7❤5😢3🤪2👌1🤣1
የዘንድሮ የጳጒሜ ቀናት 'የማንሰራራት ቀን' በሚል ርዕስ በሚከተሉት ስያሜዎች ይከበራሉ፡-
ጳጉሜ .1 - የእመርታ ቀን
ጳጉሜን.2 - የማንሰራራት ቀን
ጳጉሜን.3 - የጽናት ቀን
ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀን
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚል እንደሚከበር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

🤣43❤14👍6🤔4🤪4✍1👀1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የደቡብ ኮሪያ ጠንቋዮች AI ገቢያችንን ክፋኛ ቀንሶብናል ብለው አማረሩ
በቴክኖሎጂ ምጥቀት ቀዳሚ ከሆኑት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ደቡብ ኮሪያ፣ የቅርብ ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዕድገት የዘመናት ታሪክ ባለው የባህላዊ ዕድል ትንበያ (ጥንቆላ) ኢንደስትሪ ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ መሆኑ ተሰማ።
በአገሪቱ የሚገኙ ታዋቂ ዕድል ተንባዮችና ጠንቋዮች ወደ እነርሱ ይመጡ የነበሩ ደንበኞቻቸው ፊታቸውን ወደ AI ቴክኖሎጂ በማዞራቸው ምክንያት ሥራቸው ክፉኛ እንደ ተቀዛቀዘባቸው በምሬት በመግለጽ ላይ ናቸው።
በዋና ከተማዋ ሴኡል ዳርቻ በሚገኘውና በባህላዊ ዕድል ተንባዮች (ጠንቋዮች) መንደርነቱ በሚታወቀው ‘ሚያ መንደር’ ውስጥ አሁን ላይ የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።
ቀደም ባሉ ዓመታት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎች ስለ ጤናቸው፣ ትዳር፣ ፍቅር፣ ገንዘብ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ለመጠየቅ ወደዚህ መንደር በብዛት ይጎርፉ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ አብዛኞቹ ዜጎች በአካል ወደ መንደሩ ከመሄድ ይልቅ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ የ-AI መተግበሪያዎችን በመጠቀም ዕድላቸውን መተንበይ መምረጣቸው ተገልጿል።
በዚሁ መንደር ውስጥ ከቀሩት ጥቂት ዕድል ተንባዮች መካከል አንዷ የሆኑት የ86 ዓመቷ አዛውንት ሶንግ ኦ-ሱን ሁኔታውን ሲያስረዱ፣ እሳቸው አሁንም ከዘመናዊው የኢንተርኔት ዓለም ርቀው እንደሚኖሩና ዕድልን ለመተንበይ “አራቱ የዕጣ ፈንታ ምሰሶዎች” (Saju) የሚባለውን የኮሪያ ጥንታዊ ኮከብ ቆጠራ ዘዴ በብሬይል መጽሐፍ እያነበቡ እንደሚጠነቁሉ ገልጸዋል።
አዛውንቷ ባለፉት 40 ዓመታት ያካበቱት ይህ የሰዎች ስነ-ልቦና የመረዳትና የማማከር ልምድ AI በቀላሉ ሊተካው የማይችለው የላቀ ሰብአዊ ችሎታ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ። “በሕይወት የመኖር ተስፋ ቆርጠው ለመሞት እንኳ ወደ እኔ የመጡ ሰዎችን አሳምኜና አጽናንቼ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ አድርጌያለሁ” ሲሉም የሥራቸውን ማኅበራዊ ፋይዳ ያስረዳሉ።

🤣25❤13👍5😈1🤪1
የደመወዝ ወለል ተስፋ አለው‼️
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን አሁንም የውትወታ ሥራዬን አላቆምኩም ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ።
በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በተለይ በቋሚ ደመወዝ ኑሯቸውን ለሚገፉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኮንፌዴሬሽኑ ተናግሯል።
የኑሮ ውድነቱ የሚያድግበት ፍጥነት ሠራተኛው ከሚያገኘው ቋሚ ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ደመወዝተኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፍ እያስገደደው ነው ተብሏል።
በዚህም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰንና የግብር ቅናሽ እንዲደረግ ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አሰታውሰዋል።
የአሰሪና ሠራተኛ አዋጁ ሲሻሻል ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን የተደረገው የውትወታ ሥራ መሳካቱን ተናግረው ይሁንና ተግባራዊ እንዲሆን አሁንም እየጠየቅን ነው ሲሉ ያብራራሉ።
ሌላኛው በተደጋጋሚ ከሚጠየቁት መካከል የሥራ ግብር እንዲቀነስ የሚለው ይገኝበታል።
በዚህም በኩል ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሰራ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ግብር እንዲቀነስ ከማይፈልጉት መካከል አንዱ IMF ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁን እና የIMF ኢትዮጵያ ተወካይም ሆነ ዋና የIMF ዳይሬክተርን አግኝተን ለምን ግብር እንዲቀነስ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳለበት ለማስረዳት ሞክረናል ያሉት አቶ ካሳሁን በመጨረሻ መስማማት ላይ መድረሳቸውን ለሸገር ሬዲዬ አስረድተዋል::
አሁን ተስፋ ሰጭ ነገሮች እንዳሉት አክለዋል።

❤36👍8🙏2🤪1
ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይባሕር ለመቁረጥ
አሲራለች - -አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ
የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ክፍተቶች እና ተቃዋሚ ኃይሎች በመጠቀም ሀገሪቱን ለማዳከም አሁንም እየሠራች መሆኑን ገለጹ። ኢትዮጵያ የዓባይ ምንጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የግብጽ ባለሥልጣናት እና ሽርኮቻቸው ሀገሪቱን ለማዳከም እና ከቀይ ባሕር እንድትርቅ ለማድረግ ሸርበዋል ሲሉ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከባሕር በር ተቆርጣ ልትቀር አትችልም ያሉት አምባሳደሩ፤ ኤርትራ ከመገንጠሏ በፊት በታሪክ ምፅዋን እና ዓሰብን ማስተዳደሯን እንዲሁም የባሕር ኃይል እንደነበራት አስታውሰዋል። ለዚህም የሀገሪቱን የሕዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ፣ የገቢና ወጪ ንግድ ዕድገት፣ ለቀይ ባሕር ቅርብ መሆኗን እና ከአካባቢው ወደቦች ጋር ያላትን ታሪካዊ ትስስር በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

❤12👍5🤣4🤪1
በህንድ የቲክቶክ እይታ ለማግኘት ወደ አንበሳ ማቆያ የዘለለው ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል
በህንድ ላሆር መካነ አራዊት ውስጥ አንድ የቲክቶክ ተጠቃሚ ለማህበራዊ ሚዲያ የሚሆን ቪዲዮ ለመቅረጽ ወደ አንበሶች ማቆያ ስፍራ ዘሎ ሲገባ በመታየቱ፣ ከፍተኛ የደህንነት ጉድለት ተከስቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨው ይህ ቪዲዮ፣ በስፍራው ስላለው የደህንነት አጠባበቅ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
አንድ የቲክቶክ ተጠቃሚ የአንበሶች ማቆያ አቅራቢያ ወደሚገኘው የተከለከለ ቦታ እና ወደ አንበሳ ማቆያው ውስጥ በተደጋጋሚ የገባ ሲሆን፣ በስፍራው የነበሩት የደህንነት ሰራተኞችም እርምጃውን ማስቆም አልቻሉም። ይህ ክስተት በስፍራው ስለሚተገበሩት የደህንነት አሰራሮች እና የደህንነት ሰራተኞች አፈጻጸም ላይ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
የአራዊት መናፈሻው አስተዳደር፣ የደህንነት አሰራሮችን ለማጠናከር እንዲሁም የጎብኚዎችን እና የእንስሳትን ደህንነት ለማረጋገጥ አዲስ የደህንነት ኩባንያ እየተቀጠረ መሆኑን ገልጿል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተወዳጅነትን ለማትረፍ (ቫይራል ለመሆን) ሲባል አንድ ግለሰብ ህይወቱን ለአደጋ ሲያጋልጥ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።
ከዚህ ቀደም በክይበር ፓክቱንክዋ ግዛት ስዋት ወረዳ፣ አንድ ወጣት የቲክቶክ ተጠቃሚ ቪዲዮ እየቀረጸ ሳለ ሽጉጡን በድንገት በመተኮሱ ሕይወቱ አልፏል። ለማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም ለቲክቶክ) አዳዲስ እና ልዩ በሆኑ መንገዶች ቪዲዮ የመቅረጽ አዝማሚያ የሚያስከትለውን የሞት አደጋ መቀነስ አልተቻለም፤ ልዩ በሆነ መልኩ ቪዲዮ የመቅረጽ ከፍተኛ ፍላጎትም ሕይወት ቀጥፏል።

❤19👍3🤣2🥰1😢1👀1🤪1
በአዲስ አበባ የመኪና ንግድ ማዕከላት ላይ ሰፊ የግብር ስወራ መኖሩ ተጋለጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በሚገኙ የመኪና ንግድ ማዕከላትና የመኪና ድለላ ዘርፍ ላይ ባካሄደው ምርመራ ሰፊ የሆነ የግብር ስወራ መኖሩን እንደደረሰበት ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
በመኪና ንግድና ደላላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ዓመታዊ የገቢ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግዴታቸውን በአግባቡ እንደማይወጡ የቢሮው ጥናት አሳይቷል።
ይህን ተከትሎም በመኪና ደላላነት / በኮሚሽን ንግድ የሚሰሩ ነጋዴዎች በግቢያቸው ያስቀመጧቸውን መኪኖች እንዲያስወጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸው ነበር።
ቢሮው እንደገለጸው፣ መኪናዎችን ለሽያጭ በማይፈቀድላቸው ቦታዎች ማስቀመጥና መሸጥ ከሕጋዊ የንግድ ደንቦች ጋር የሚጋጭ ነው።
ቢሮው ባወጣው መመሪያ፣ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገቡ የመኪና አስመጪ ድርጅቶች ብቻ በተፈቀደላቸው የንግድ ቦታ መኪና መሸጥ እንደሚችሉ በግልጽ አስቀምጧል።
ከሰሞኑን በአዲስ አበባ በትክክል አስመጪ ያልሆኑና በኮሚሽን የሚሰሩ እጅግ በርካታ የመኪና መሸጫዎች ተዘግተው ነበር።
አሁን ላይ በተሻሻለ መመሪያ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተፈቅዶላቸዋል። ሆኖም የመኪና ነጋዴዎች የሚሰሩበት ሥርዓት ላይ ገደቦች ተጥለዋል።
በተለይም አዲስና ያልተነዱ "Zero-Mile" መኪኖችን በግል ኮሚሽን ወይም ትርፍ ላይ ተመስርቶ መሸጥ እንዲሁም እነዚህን መኪኖች በራሳቸው ግቢ ውስጥ መሸጥ አይፈቀድም።
አዲስ መኪኖችን የማስመጣትና የመሸጥ መብት ሕጋዊ ፈቃድ ላላቸው አስመጪዎች ብቻ ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል፥ የመኪና ደላላዎች በግለሰቦች የተያዙ ያገለገሉ መኪኖችን በኮሚሽን መሸጥ ወይም መኪና በራሳቸው ገዝተው እንደገና መሸጥ ይችላሉ፤ ይህም ግን የተቀመጡትን የግብርና የንግድ ሕጎች በመከተል ብቻ መሆን አለበት።
የመረጃው ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

❤3👍2🤔1
በሀሰተኛ ሰነድ ማጭበርበር ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የነበሩት ቀሲስ በላይ መኮንን ከእስር መፈታታቸው ተገለጸ።
ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ ጠዋት ከእስር ተፈተው በአሁኑ ሰዓት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
ግለሰቡ በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማውጣት በመሞከራቸው፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የአምስት ዓመት እስራት እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑ ይታወሳል።
ከእሳቸው ጋር አብረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ሌሎች ሁለት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው የአራት ዓመት እስራት እና የ3 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ተከሳሾቹ የወንጀል ሕጉን እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ተላልፈዋል በሚል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው በኋላ፣ ቀሲስ በላይ ከ 2 አመት የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ በይፋ ከእስር ተለቀዋል።

❤13🤯5😡3👍2🥰1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጊዜው ከስራ ታገዱ‼️
2ቱ የትራፊክ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ መደረጉ ተገለፀ::
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለማስፈጸም በሚያከናውናቸው የመስክ ቁጥጥር ስራዎች ወቅት ከመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር አለመግባባቶች እንደሚከሰቱ ገልጿል።
በዛሬው ዕለት (ነሀሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም) በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲሰራጭ የዋለውን ምስል አስመልክቶ ተቋሙ ባወጣው መረጃ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርቷል፦
• የቁጥጥር ባለሙያዎች ደንብ የተላለፈን አሽከርካሪ የመንጃ ፈቃድ በሚጠይቁበት ወቅት "አልሰጥም" በማለት ስራ ማስተጓጎል፣ ስድብ፣ ዛቻ ወይም ሃይል መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል።
• ተቋሙ በምስሉ ላይ የታየውን አለመግባባት ግራና ቀኝ ያለውን አካል ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በማጣራት ላይ እንደሚገኝና እስከዚያው ድረስ በክስተቱ ላይ የተሳተፉት ሁለቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ እንዲታገዱ ማድረጉን አስታውቋል።
ህብረተሰቡ የችግሩን የማጣራት ሂደት በስክነት እንዲከታተልና ትክክለኛ ካልሆኑ መረጃዎች እንዲቆጠብ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

🤣23❤20👍5🙊5🤔2⚡1👌1👀1🙈1
የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚዋሠነው ብሉ ናይል ግዛት በርካታ ተዋጊዎችን በማንቀሳቀስ ላይ መኾኑን አስታወቀ።
ወደ ብሉ ናይል ግዛት ደማዚን ከተማ አካባቢ የተንቀሳቀሱት ተዋጊዎች የፈጥኖ ደራሹን ኃይል ለመውጋት ከሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር የወገኑ ኃይሎች እንደሆኑ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ በግዛቲቱ በርካታ አካባቢዎች በመንግሥት ወታደሮችና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።
ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቅራቢያ ስትራቴጂካዊቷን ኩርሙክ ከተማ ከአንድ ሳምንት በፊት ከሱዳን ጦር ሠራዊት መንጠቁ ይታወሳል።

👍4❤2🤔1🕊1