አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.9K subscribers
17.5K photos
434 videos
23 files
3.03K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የኬንያ አየረ መንገድ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ‼

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘው የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሠራተኞች የጀመሩት የተቀናጀ የሥራ ማቆም አድማ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የዓለም አቀፍ መንገደኞች በበረራ መዘግየት ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ።

የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች ማኅበር (KAWU) በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተካሄደው የሥራ ማቆም አድማ የተቀሰቀሰው በርካታ ቅሬታዎች በመደራረባቸው መሆኑን ገልጿል። 

ከእነነዚህም መካከል ከኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጋር ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉ፣ እንዲሁም ከኬንያ አውሮፕላን ማረፊያዎች ባለሥልጣን (KAA) እና ከኬንያ ኤርዌይስ እህት ኩባንያ ከሆነው ጃምቦጄት (Jambojet) በኩል የታየው የትብብር እጥረት ዋነኞቹ መሆናቸውን ማኅበሩ አስታውቋል።

የኬንያ አየር መንገድ ባለሥልጣን እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ምክንያቱን ሳይገልጽ አንዳንዶች በረራዎች መዘግየታቸውን ተናግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ሰኞ ዕለት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ  ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል። 

የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እና ጃምቦጄት በበኩላቸው አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍7❤4🤔2
የአሜሪካ እና ኢራን አዲስ ውጥረት‼️
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት በማገረሹ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ‼️

ከሳምንታት አንጻራዊ ሰላም በኋላ፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል የተጀመረው አዲስ ወታደራዊ ፍጥጫ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ስጋት ዳግም ቀስቅሶታል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢራን በድርጊቷ የምትቀጥል ከሆነ "በከባድ ሁኔታ" እንደሚያጠቋት መዛታቸውን ተከትሎ፣ በዛሬው ዕለት በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ፍጥጫ እና የቃላት ምልልስ፣ ሁኔታው ወደ ሰፊ ቀጠናዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት በኢንቨስተሮች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል።

በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ማክሰኞ ዕለትም ጭማሪውን ቀጥሎ ውሏል።

የነዳጅ ገበያ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት በቀጠለ ቁጥር የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት የዋጋ ግሽበትን ሊያባብሰው ይችላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍5🤔1😢1
ውሸት ነው‼️
ከላይ የተያያዘው አድሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማሻሻያ ነዉ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ይገኛል።
ይህ ፍፁም ውሸት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤9🤩4👍3
በካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ግለሰብ የመኪና ዕድለኛ ሆነ

​በደቡብ ወሎ ኩታበር ወረዳ ነዋሪ የሆነው ወጣት ሰለሞን ብርሃን በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የቶምቦላ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆን የዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ባለቤት ሆኗል። በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው በርክከብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ወጣት ሰለሞን የመኪናውን ቁልፍ እና ህጋዊ ሊብሬ ተረክቧል።

​በግል ካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራው ወጣት ሰለሞን ብርሃን ከዕለት ተዕለት ሥራው በተጓዳኝ አዘውትሮ ሎተሪ የመግዛት የቆየ ልማድ እንደነበረው ገልጿል። ላለፉት በርካታ ዓመታት ተስፋ ሳይቆርጥ ዕድሉን ሲሞክር የቆየው ወጣቱ፣ አሁን ላይ የ3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማውና የዘመናት ትልቅ ሕልሙ እንደተሳካለት ተናግሯል።

​ይህ በዕድል የደረሰውን ዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ለግል አገልግሎት ከመጠቀም ይልቅ ቀጣይ ሕይወቱን ለማሻሻል በሚያስችለው መልኩ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሰማራት ማቀዱን ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤28🫡2
ተሽከርካሪዎች የለጠፉትን ጥቁር ስቲከር እንዲያነሱ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ አሳሰበ
****

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከተለዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ወይም VIP ተሽከርካሪዎች በስተቀር ከዛሬ  ማክሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ከተማ ፣ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ ማናቸውም ተሽከርካሪዎች መስታወት ላይ የተደረጉ ጥቁር ስትኬሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነቀሉ ማሳሰቢያ ሰጠ።

ኮሚሽኑ በክልሉ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጸጥታ ቁጥጥር ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ፣ የግል ፣ የንግድ ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች በሙሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ይህ የጸጥታ መመሪያ በሁሉም የክልሉ አወቃቀሮች በጥብቅ የሚተገበር ሲሆን፤ መመሪያውን ጥሰው በተሽከርካሪዎቻቸው መስታወት ላይ ጥቁር ስትኬር ይዘው በተገኙ አካላት ላይ ኮሚሽኑ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑንም አስገንዝቧል።

የመንግሥት አመራሮች፣ ሕብረተሰቡና የድርጅት ኃላፊዎች ለሕግ ማስከበር ሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15🥰1
"የግብረሰዶማውያን ማህበር ፕሬዚዳንት " ተደበደበ !

በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ " የግብረሰዶማውያን ማህበር ፕሬዚዳንት " እንደሆነ የተነገረለት እና እራሱም የፖሊስ መኮንን የሆነው ፒየር ፒካቬት የተባለ ግለሰብ በጠርሙስ ተቀጥቅጦ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል መግባቱን ከፍራንስ 24 ዘገባ ተመልክተናል።

ፒካቬት በፓሪስ መሃል በሚገኘው ማራይስ አካባቢ ከአንድ ባር ከወጣ በኋላ በአንድ ግለሰብ በጠርሙስ መቀጥቀጡ ተገልጿል።

ጥቃቱ በሰውነቱ ላይ በርካታ ጉዳቶችን እንዲደርስበት ያደረገ ሲሆን የውስጥ ደም መፍሰስና የጭንቅላት ቁስልም እንደደረሰበት ተዘግቧል።

ፓሪስ ውስጥ የግብረሰዶማውያን መብት ተሟጋች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነው ፒካቬት እራሱን የፖሊስ መኮንን መሆኑን በመግለጽ የፖሊስ መታወቂያውን ቢያሳይም፣ ተጠርጣሪው ጥቃቱን እንዳላቆመ ተመላክቷል።

በጥቃቱ ወቅትም ጥቃት አድራሹ " አጸያፊ ነው " ስላለው የግብረሰዶማዊነት ተግባር በስድብና በኃይለ ቃል ግለሰቡን ሲናገረው እንደነበር ተመላክቷል።

ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከዚህ በፊት የወንጀል መዝገብ እንደሌለው ተገልጿል።

የፓሪስ ከንቲባ ኤማኑኤል ግሬጎዋር ጥቃቱን አውግዘዋል። " ፓሪስ ለሁሉም ሰዎች የነፃነትና የደህንነት ከተማ ሆና ትቀጥላለች " ሲሉ መናገራቸው ነው የተሰማው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤81👍31🤣7🍾5🤪5🤝3🙏2🎉1🌚1👀1
በላይቭ (Live) ግድያ የፈፀሙት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

"100 ተጠርጣሪዎች ታፈሱ! የሳውዲው ግድያ መረጃ...

"በሳውዲ አረቢያ ድንበር ላይ በኢትዮጵያውያን መካከል የተፈፀመው አስደንጋጭ ግድያ አዲስ መረጃ ወጥቷል።

• ግድያውን የፈፀመው ግለሰብና 5 ግብረ አበሮቹ ተይዘዋል።

• በሶሻል ሚዲያ ጉዳዩን በማራገብ ተጠርጣሪ የሆኑ ከ100 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

• የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሳውዲ የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ወንጀለኞችን የማደን ስራውን አጠናክሯል።

የኢትዮጵያዊነትን ባህል ያረከሰው ይሄ ድርጊት የህግ የበላይነት ሊረጋገጥበት ይገባል።

ድምፅ ለሆናችሁና መረጃ ለሰጣችሁ ሁሉ ኤምባሲው ምስጋና አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤38👍17🤣3🌚1
አባይ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ተሰጠው!

"የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በአባይ ቴሌቪዥን ላይ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ባለስልጣኑ ባለፉት ሦስት ወራት ባደረገው ክትትል፣ ጣቢያው በዜናዎቹና በፕሮግራሞቹ ላይ ከባድ የሕግና የሙያ ስነ-ምግባር ጥሰቶችን ፈጽሟል ብሏል።

ከጥሰቶቹ መካከል፦ከባህላችን ያፈነገጡ ፀያፍ ንግግሮችን ማሰራጨት፣የሴቶችን ክብር የሚነኩ ይዘቶች፣እና ያልተረጋገጡ የዜና ምንጮችን መጠቀም ይጠቀሳሉ።

የጣቢያው ኃላፊዎች ጥፋቱን አምነው ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን፣ በአፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱም ቃል ገብተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤27👍21🙉5🤪4😡4🤩3🤡2🤔1😢1🙊1
"መንግሥት ከተጠያቂነት ሊያመልጥ አይችልም!" — አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በንጹኃን ላይ የተፈጸሙትን ማንነትና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች፣ የእምነት ተቋማት ውድመትና እገታዎችን በጽኑ ኮንኗል።

ንቅናቄው ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን አልተወጣም ሲል ከሷል። ጥቃቱን በታጣቂዎች ላይ ብቻ በማሳበብ መንግሥት ከተጠያቂነት ነፃ ሊሆን እንደማይችል የገለጸው አብን፣ በጸጥታ መዋቅሩ ላይ ላለው ውድቀት የባለሥልጣናት ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እንደሚገባ አሳስቧል።

አብን አክሎም፣ የዜጎች የመኖር መብት ባልተከበረበት ሁኔታ ስለ አገራዊ ብልፅግና ማውራት እውነታውን መካድ ነው ብሏል። ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የፌደራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት የተቀናጀ እርምጃ እንዲወስዱ፣ ገለልተኛ አካላት የሚሳተፉበት የምርመራ ሥርዓት እንዲዘረጋና ተፈናቃዮች በአስቸኳይ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍42❤16🥱2🤪2👌1🏆1
የአስመራ ነዋሪዎች በንጹህ ውሃ አጥረት
ምክንያት ቀይ ባህርን ለመጠጣት ተገደዋል ተባለ‼️
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚኖሩ ዜጎች በከባድ የውሃ እጥረት ምክንያት የዕለት ተዕለት ህይወታቸው መስተጓጎሉንና ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ልብስ ማጠብ እና የንጽህና መጠበቂያ የሚሆኑ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ ሲሉ የውሃ አጠቃቀማቸውን እጅግ ለመቀነስና አማራጭ የውሃ ምንጮችን በፍለጋ ለመንከራተት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

​የችግሩ አሳሳቢነት የከፋባቸው አያሌ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት መደበኛ የቧንቧ ውሃ ማግኘት ካቆመ ቆይቷል፤ በዚህም ምክንያት የውሃ ቦቴዎችን በመጠበቅ በውድ ዋጋ ውሃ ለመግዛት ተገደዋል። ሁኔታው ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ደግሞ አቅም በሌላቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ሲሆን አንዳንዶቹ የዝናብ ውሃ ለመሰብሰብ ሲጠባበቁ ሌሎች ደግሞ ከቀይ ባህር የሚጓጓዘውን የጨው ውሃ ለተለያዩ ፍጆታዎች ለማዋል እስከመገደድ ደርሰዋል።

​ባለፈው ሐምሌ ወር የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በኤርትራ እየተባባሰ ለመጣው የውሃ አቅርቦት ችግር በምክንያትነት የተጠቀሱት የአየር ንብረት ለውጥ፣ የቆዩና የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ደካማ የውሃ አስተዳደር ስርዓት ናቸው።

ጥናቱ አክሎም በአሁኑ ወቅት የሚገኘው የውሃ አቅርቦት መደበኛ ያልሆነና ለጤና አስተማማኝ እንዳልሆነ በማስገንዘብ ሊከሰት የሚችለውን የጤና አደጋ ጠቁሟል።

​ይህ ደረቅ ወቅቶች በመጡ ቁጥር ተደጋገሞ የሚከሰተው የውሃ እጥረት በነዋሪዎች የኢኮኖሚ አቅም ላይም የከፋ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የውሃ ግዥ ወጪ እየጨመረ መምጣቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ያላቸውን ትንሽ ገቢ ለውሃ እንዲያወጡ በማስገደድ ተጨማሪ የኑሮ ውድነት ፈጥሮባቸዋል።

አሁን ላይ በአስመራ እየታየ ያለው ይህ ቀውስ በከተማዋ ያለውን የዘለቀ የመሰረተ ልማት ውድቀትና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ማጣት አጉልቶ የሚያሳይ አሳሳቢ ክስተት ሆኗል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢14❤7👍4🕊1
በጠለምት ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ፤ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ

​በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ “ግልቤና” ቀበሌ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ ከባድ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በአራት ሰዎች ላይ ደግሞ አካል ጉዳት ደርሷል።

​በአደጋው ሳቢያ 411 አባወራዎች ወይም ከ2,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም 26 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተደረመሱ ሲሆን፣ 31 የቤት እንስሳትም ሞተዋል።

​የመሬት መንሸራተቱ አሁንም እየተስፋፋ ቢሆንም፣ ሕዝቡ ቀድሞ ወደ ቀበሌው ማእከል እንዲወርድ በመደረጉ ተጨማሪ የሰው ሕይወት ማዳን ተችሏል።

​ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ማእከል ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ አስቸኳይ የምግብና የቁሳቁስ እርዳታ የሚፈልጉ ቢሆንም እስካሁን ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳልደረሳቸው ተገልጻል።

ምንጭ: ቲክቫህ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔11❤6😢6👍3😱1
የኮሊደር ልማት ይቀጥላል‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በቀጣዩ ዓመት በከተማዋ የኮሪደር ልማት የሚካሄድባቸው አካባቢዎች እንደተለዩ በከተማዋ አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመትና የቀጣይ አምስት ዓመታት ዕቅድ የግምገማ መድረክ ላይ ተናገሩ። አዳነች የኮሪደር ልማት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የወንዞችን ዳርቻ ማደስና "የወደቁ" ሠፈሮችን የማንሳት ሥራ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በቁጥር ተለይቶ መቀመጡን አዳነች ገልጠዋል። አዳነች አያይዘውም፣ ያረጁ ሠፈሮችን የማደስ ሥራ ነዋሪዎችን በንጽህና እንዲኖሩ ከመደገፉ ባሻገር፤ በተደጋጋሚ የሚከሠቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በቀጣዩ የኮሊደር ልማት የትኞቹ ሰፈሮች እንደሚነሱ በግልፅ አልታወቀም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡22👍7❤5😢3🤪2👌1🤣1
የዘንድሮ የጳጒሜ ቀናት 'የማንሰራራት ቀን' በሚል ርዕስ በሚከተሉት ስያሜዎች ይከበራሉ፡-
​ጳጉሜ .1 - የእመርታ ቀን
​ጳጉሜን.2 - የማንሰራራት ቀን
​ጳጉሜን.3 - የጽናት ቀን
​ጳጉሜን 4 - የኅብር ቀን
​ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚል እንደሚከበር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣43❤14👍6🤔4🤪4✍1👀1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የደቡብ ኮሪያ ጠንቋዮች AI ገቢያችንን ክፋኛ ቀንሶብናል ብለው አማረሩ

በቴክኖሎጂ ምጥቀት ቀዳሚ ከሆኑት የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ደቡብ ኮሪያ፣ የቅርብ ጊዜው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዕድገት የዘመናት ታሪክ ባለው የባህላዊ ዕድል ትንበያ (ጥንቆላ) ኢንደስትሪ ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ መሆኑ ተሰማ።

በአገሪቱ የሚገኙ ታዋቂ ዕድል ተንባዮችና ጠንቋዮች ወደ እነርሱ ይመጡ የነበሩ ደንበኞቻቸው ፊታቸውን ወደ AI ቴክኖሎጂ በማዞራቸው ምክንያት ሥራቸው ክፉኛ እንደ ተቀዛቀዘባቸው በምሬት በመግለጽ ላይ ናቸው።

በዋና ከተማዋ ሴኡል ዳርቻ በሚገኘውና በባህላዊ ዕድል ተንባዮች (ጠንቋዮች) መንደርነቱ በሚታወቀው ‘ሚያ መንደር’ ውስጥ አሁን ላይ የደንበኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል።

ቀደም ባሉ ዓመታት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎች ስለ ጤናቸው፣ ትዳር፣ ፍቅር፣ ገንዘብ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ለመጠየቅ ወደዚህ መንደር በብዛት ይጎርፉ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ አብዛኞቹ ዜጎች በአካል ወደ መንደሩ ከመሄድ ይልቅ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ የ-AI መተግበሪያዎችን በመጠቀም ዕድላቸውን መተንበይ መምረጣቸው ተገልጿል።

በዚሁ መንደር ውስጥ ከቀሩት ጥቂት ዕድል ተንባዮች መካከል አንዷ የሆኑት የ86 ዓመቷ አዛውንት ሶንግ ኦ-ሱን ሁኔታውን ሲያስረዱ፣ እሳቸው አሁንም ከዘመናዊው የኢንተርኔት ዓለም ርቀው እንደሚኖሩና ዕድልን ለመተንበይ “አራቱ የዕጣ ፈንታ ምሰሶዎች” (Saju) የሚባለውን የኮሪያ ጥንታዊ ኮከብ ቆጠራ ዘዴ በብሬይል መጽሐፍ እያነበቡ እንደሚጠነቁሉ ገልጸዋል።

አዛውንቷ ባለፉት 40 ዓመታት ያካበቱት ይህ የሰዎች ስነ-ልቦና የመረዳትና የማማከር ልምድ AI በቀላሉ ሊተካው የማይችለው የላቀ ሰብአዊ ችሎታ መሆኑን በጽኑ ያምናሉ። “በሕይወት የመኖር ተስፋ ቆርጠው ለመሞት እንኳ ወደ እኔ የመጡ ሰዎችን አሳምኜና አጽናንቼ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ አድርጌያለሁ” ሲሉም የሥራቸውን ማኅበራዊ ፋይዳ ያስረዳሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣25❤13👍5😈1🤪1
የደመወዝ ወለል ተስፋ አለው‼️
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን አሁንም የውትወታ ሥራዬን አላቆምኩም ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ።

በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በተለይ በቋሚ ደመወዝ ኑሯቸውን ለሚገፉ ተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ኮንፌዴሬሽኑ ተናግሯል።

የኑሮ ውድነቱ የሚያድግበት ፍጥነት ሠራተኛው ከሚያገኘው ቋሚ ገቢ ጋር ሊመጣጠን ባለመቻሉ ደመወዝተኛው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፍ እያስገደደው ነው ተብሏል።

በዚህም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰንና የግብር ቅናሽ እንዲደረግ ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አሰታውሰዋል።

የአሰሪና ሠራተኛ አዋጁ ሲሻሻል ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን የተደረገው የውትወታ ሥራ መሳካቱን ተናግረው ይሁንና ተግባራዊ እንዲሆን አሁንም እየጠየቅን ነው ሲሉ ያብራራሉ።

ሌላኛው በተደጋጋሚ ከሚጠየቁት መካከል የሥራ ግብር እንዲቀነስ የሚለው ይገኝበታል።

በዚህም በኩል ኢሠማኮ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሰራ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ግብር እንዲቀነስ ከማይፈልጉት መካከል አንዱ IMF ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እና የIMF ኢትዮጵያ ተወካይም ሆነ ዋና የIMF ዳይሬክተርን አግኝተን ለምን ግብር እንዲቀነስ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳለበት ለማስረዳት ሞክረናል ያሉት አቶ ካሳሁን በመጨረሻ መስማማት ላይ መድረሳቸውን ለሸገር ሬዲዬ አስረድተዋል::
አሁን ተስፋ ሰጭ ነገሮች እንዳሉት አክለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤36👍8🙏2🤪1
ግብፅ ኢትዮጵያን ከቀይባሕር ለመቁረጥ
አሲራለች - -አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ

የቀድሞው የውኃ ሚኒስትር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ክፍተቶች እና ተቃዋሚ ኃይሎች በመጠቀም ሀገሪቱን ለማዳከም አሁንም እየሠራች መሆኑን ገለጹ። ኢትዮጵያ የዓባይ ምንጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የግብጽ ባለሥልጣናት እና ሽርኮቻቸው ሀገሪቱን ለማዳከም እና ከቀይ ባሕር እንድትርቅ ለማድረግ ሸርበዋል ሲሉ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከባሕር በር ተቆርጣ ልትቀር አትችልም ያሉት አምባሳደሩ፤ ኤርትራ ከመገንጠሏ በፊት በታሪክ ምፅዋን እና ዓሰብን ማስተዳደሯን እንዲሁም የባሕር ኃይል እንደነበራት አስታውሰዋል። ለዚህም የሀገሪቱን የሕዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ፣ የገቢና ወጪ ንግድ ዕድገት፣ ለቀይ ባሕር ቅርብ መሆኗን እና ከአካባቢው ወደቦች ጋር ያላትን ታሪካዊ ትስስር በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12👍5🤣4🤪1