አዲስ ሪፖርተር - NEWS
37K subscribers
17.5K photos
434 videos
23 files
3.04K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የድሮን አሰሳ እና ጥቃት‼️
በራያ አካባቢ በህወሓት ወታደራዊ ቦታዎች ላይ የሚፈፀመው የድሮን ጥቃት እና አሰሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዛሬው ዕለት በአካባቢው ከፍተኛ የተባለ የድሮን አሰሳ ሲደረግ መዋሉን የአካባቢው ምንጮች ከምስል ጋር ገልፀውልናል። ህወሃት የትራንስ ኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎችን በድርቅ ሰበብ ለወታደራዊ አገልግሎት እያዋላቸው መሆኑን፣የአዲግራት እና የአክሱም ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን ወታደራዊ የህክምና መስጫ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍6🕊5
የኢሕአፓ አመራርና አባል ተጨማሪ ምስክር እንዲያቀርቡ ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ተጠርጣሪዎቹ ተጨማሪ ምስክር እንዲያቀርቡ በማለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለነሐሴ  28 ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩት፤ የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው  ይስሐቅ ወልዳይ፣ የፓርቲው አባል አበበ አካሉ እንዲሁም ጠበቃ አበራ ንጉሥ በዛሬው ዕለት  በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበር ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የከፍተኛ  ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት ተከሳሾቹ  የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ማጠናቀቁን እና የቴክኒክና የፎረንሲክ መረጃዎች በቂ ስለሆኑ የፌደራል ፖሊስም መረጃዎችን ወደ ማጠናቀቁ  እንደደረሠ አሰረድቷል።

ነገር ግን ተከሳሾቹ ያቀረቧቸው ምስክሮች በቁጥር ሁለት ብቻ  በመሆናቸው ፍርድ ቤቱ ለመጨረሻ ጊዜ በሚል ለቀጣይ ሳምንት ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ እንደተሠጣቸው ጠበቃ ሰለሞን አስረድተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤12🤔4👍2
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት በምዕራብ ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎችንና መንደሮችን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ጉዳት እያደረሠ ይገኛል በማለት ለአልጀዚራ በሠጡት ቃል ከሰሱ።

ጌታቸው፣ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች ይረዳል በማለት ጭምር መወንጀላቸውን ዜና አውታሩ ማምሻውን ዘግቧል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከኢትዮጵያ ግዛት እየተነሳ በሱዳን ጦር ሠራዊት ላይ ጥቃት ይፈጽማል የሚለውን የሱዳን ባለሥልጣናት ውንጀላ ያስተባበሉት ጌታቸው፣ ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንደምታከብር ተናግረዋል ተብሏል።

ሱዳን ጦሯን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር ወደሚዋሠነው ብሉናይል ግዛት ደማዚን ከተማ አካባቢ በብዛት እያንቀሳቀሰች መኾኗንም ዘገባው የሱዳን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20🤣8👍2
የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ ለመቀየር የሚያሥፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤3👍2
ተሸንፎም ድርጅቶች ለማስታወቂያ በሩን በሰልፍ እያንኳኩለት ያለው ሴዶ ማርሻል::

በቅርቡ በተደረገው የኤምኤምኤ (MMA) ፍልሚያ በመጀመሪያው ዙር በጆኒ የተሸነፈው ሴዶ ማርሻል፣ ከተሸነፈ በኋላ ያየው ነገር ግን ከድል በላይ የሆነ ድንቅ እድል ሆኖለታል!

ብዙ ጊዜ በተዋጊዎች ዓለም ውድድር መሸነፍ ከስፖንሰሮችና ማስታወቂያዎች መራቅን እያመጣ፣

በሴዶ ላይ ግን የሆነው ተአምር ነው! ሴዶ በተሸነፈ ማግስት ብቻ ከ4 በላይ ትልልቅ ማስታወቂያዎችን የሰራ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን በእሱ ለማስራት በረጅም ተራ እየጠበቁ እንደሚገኙ ተሰምቷል!

"መሸነፍ የውድቀት መጨረሻ ሳይሆን ለአዲስ መንገድ በር ከፋች ነው" የሚሉትን ወገኖች እውነት የሚያስመስለው የሴዶ ማርሻል ነገር፣ አሁን ላይ በማህበራዊ ሚዲያ እና በንግዱ ዓለም ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል!

እውነትም ኢትዮጵያ ውስጥ ተሸንፎ እንደ ሴዶ ማተርፍ የትም የለም!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍22❤19🙉9🤣3👀1😡1
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው የንግድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ስምምነቱን በቀዳሚነት ከፈረሙና ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ እ.ኤ.አ ጥቅምት 9 ቀን 2025 በይፋ ንግድ መጀመሯ ይታወሳል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው መረጃ ንግዱ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ማዝያ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ባደረገችው የንግድ ልውውጥ፦ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ የላከች ሲሆን፤
ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ ምርቶችን ደግሞ ወደ አገር ውስጥ አስገብታለች።

በወጪ ንግድ የቅባት እህሎች፣ በቆሎና የኬሚካል ምርቶች ተጠቃሽ ናቸው።

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድመዳረሻዎችም ከነበሩበት አራት ወደ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት (ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና እና አልጄሪያ) ከፍ ማለታቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም 37 የግል ድርጅቶች በወጪ እና 76 ድርጅቶች በገቢ ንግድ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ አህጉራዊ ስኬት ኢትዮጵያ ወደ ዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ተቋማዊና ፖሊሲያዊ ግብዓት የሚፈጥር መሆኑም ተመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪14❤12👍4
የጎጃም ፋኖ ቃል አቀባይ የነበረው ማርሸት ጸሀዩ ለመንግሥት እጅ መስጠቱ ተሰምቷል።

ማርሸት ከወራት በፊት በፋኖ አመራሩ ዝናቡ ልንገረው ታስሮ እንደነበር ይታወሳል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣17🙊14❤11👍5😱1🕊1👀1🤪1
ኢትዮጵያዊው ምሁር ለግብጽያስተላለፉት ጠንካራ መልዕክት

አባይ የጋራ ሀብት እንጂ የአንድ ወገን ብቻ መብት ሊሆን አይገባም ያሉት ታዋቂው ማህበራዊ ተመራማሪ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ፣ የግብፅ የውሃ ስጋት ሊከበር የሚገባው ቢሆንም፣ ይህ ስጋት ግን የሌሎች ሀገራትን የልማት መብት ሊያፍን እንደማይገባ አሳሰቡ።

ኢትዮጵያ በታሪክ ከፍተኛ የውሃ መጠን ወደ አባይ ስታበረክት የቆየች ቢሆንም፣ ከሀብቱ በበቂ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዳልነበረች ገልጸዋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውሃዋን ለኃይል፣ ለምግብ ዋስትና እና ለልማት ማዋሏ የጠላትነት ተግባር ሳይሆን የተፈጥሮ መብቷ መሆኑን ተመራማሪው አስረድተዋል።

ግብፅ ውሃን በብቃት በመጠቀም ረገድ ያላት ልምድ የሚደነቅ ቢሆንም፣ “ታሪካዊ ድርሻ” በሚል ሰበብ የሌሎችን ሀገራት ልማት ለመቆጣጠር ማሰብ ተቀባይነት እንደሌለው ተመራማሪው ጠቁመዋል። የውሃ ጉዳይ በወታደራዊ ዛቻ ሊፈታ እንደማይችል የገለጹት ዶ/ር ብርሃኑ፣ ዋናው ትኩረት መሆን የሚገባው የሁሉንም የተፋሰስ ሀገራት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የጋራ ልማት ማረጋገጥ ላይ እንደሆነ አብራርተዋል።

የአባይ ወንዝ ዕጣ ፈንታ የሚጠበቀው በጦርነትና በዛቻ ሳይሆን በሳይንስ፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በትብብር ላይ የተመሰረተ መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ አስገንዝበዋል። ግብፅ የባህር ውሃን በማጣራት እና የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀምን በማሻሻል አዳዲስ መንገዶችን መከተል እንዳለባት ተመላክቷል። በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት ዘላቂ ሰላም እና የጋራ ብልጽግና ሊረጋገጥ የሚችለው በዛቻ ሳይሆን በጋራ መረዳዳት እና በትብብር ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26👍6
የእሬት መድኃኒትነት እና የምርት መጠን ከሚበቅልበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት እንዳለው አዲስ ጥናት ይፋ አደረገ።
🇪🇹 በኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች በሰሜን ሸዋ ዞን በተካሄደው ጥናት፣ የእሬት ተክል የሚበቅልበት ወረዳ እና ዝርያው ተክሉ የሚኖረውን የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድናት መጠን እና የቅጠል ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚወስነው ተረጋግጧል።

ዋና ዋና መረጃዎች

🟠 የተጠኑ አካባቢዎች (3 ወረዳዎች)፦ ከአንኮበር፣ ከመርሃቤቴ እና ከከዎት የተሰበሰቡ 6 የተለያዩ የእሬት ዝርያዎች በጋራ አንድ ቦታ ተተክለው ተመዝግበዋል።

🟠የከዎት እና የአንኮበር የእሬት ዝርያዎች ከፍተኛ የመድኃኒትነት ይዘት፣ የማዕድን ስብጥር እና ከፍተኛ የቅጠል ምርት በማስመዝገብ በግንባር ቀደምነት ተለይተዋል።

🟠 ጥናቱ አርሶ አደሮች ተክሉን "ወንዴ" እና "ሴቴ" እሬት ብለው የሚለዩበትን ባህላዊ እውቀት ሳይንሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን አረጋግጧል።

🟠 ለመድኃኒት፣ ለሥነ-ውበት እና ለምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እሬትን የዝርያ ጥራቱን ተመልክቶ መግዛት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።

"በተመሳሳይ እንክብካቤ የበቀሉ የእሬት ዓይነቶች እንኳን በመጡበት ቦታ እና በዘረመል ልዩነታቸው ምክንያት የሚሰጡት የጄል (የዝልግልግ ቅባት) መጠን እና የመድኃኒትነት ኃይል የተለያየ ነው፤ ይህም ለአርሶ አደሮች እና ለፋብሪካዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይሰጣል" ሲል ዓለም አቀፉ 'ዲስከቨር ፕላንትስ' ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት አመላክቷል።


@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤22👍8
ቀን 25/12/2018
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 09 17 48 53/09 07 36  23 85
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉   የስራ መደብ:# NGO
👉የት/ደረጃ ዲፕሎማ / ድግሪ
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞዝ:- 40.000_50.000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው  መደብ =- ሀውስ ኪፒግ
👉የትምርት ደረጃ 8 +
👉የስራ ልምድ 0-3
👉ደሞዝ 7000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ሆስተስ
👉የትምርት ደረጃ 10 +
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 15000 / 20000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =-መስተግዶ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0/2
👉ጾታ ወንድ /ሴት
👉ደሞዝ ማራኪ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የስራው መደብ /ፓስታ ፋብሪካ=-የእሸጋ ሰራተኛ
👉  የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
👉ደሞዝ:-  17000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
👉ደሞዝ ፡ 15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ሹፌር ደ/1 2 ህ/1/ሞተረኛ
👉የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
👉ደሞዝ:- 7000_17000
👉ፆታ :- ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ትኬተር/ለባስ/
👉የሰራ ልምድ :- 0አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
👉ደሞዝ:- 0አመት
👉ደሞወዝ   :- 9000~20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
👉የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
👉ደሞዝ:-8000_30000+
👉የስራ ልምድ: 0አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ :markting
👉የት ደረጃ ፡- degree 
👉የስራ ልምድ ፡- 0~5 አመት
👉ደሞዝ :-13000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ Accountant
👉የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
👉ደሞዝ ፡  8,000-16,000 
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ IT
👉የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
👉የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
👉ፆታ:- ሴ/ወ
👉ደሞዝ:- 8000-15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ካሸር
👉የት/ደረጃ፦10 +
👉የሰራ ልምድ 0~3 አመት
👉ደሞዝ:- 7000-12000
👉ፆታ፦ሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#nurse//ላብራቶሪ/ጠቅላላ
👉 ለክሊኒክ እና ለሆስፒታል
👉የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
👉የስራ ልምድ: 0~8አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉ፆታ፦ሴት/ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ 8
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-1
👉ደሞዝ :7000-20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
👉የትምርት ደረጃ 8+
👉የስራ ልምድ 0 -1 አመት
👉ደሞዝ 10000-25000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ=- ፀሀፊ
👉የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
👉የስራ ልምድ ያላት
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 8000/13000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው አይነት =- ባርቴንደር
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልድ 1/3
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 10000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ብስኩት ፋብሪካ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 16000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
👉የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት
👉ደሞዝ:-9000-35000
👉ፆታ፦ወንድ/ሴት
👉የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ እሪል እስቴት ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ ዲፕ/ዲግሪ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ ፡  9000-50000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ሁለገብ ሰራተኛ
👉የደረጃ ፡- 8_10
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞወዝ :- 10000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ reception
👉የት ደረጃ ፡ 10/12
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ 8000/15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#ተላላኪና ፅዳት ለባንክ
👉የት/ደረጃ፦8/12 /ዲፕ
👉 የሰራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
👉ፆታ: ሴ/ወ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
👉ደሞዝ ፡  15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉መረጃና መዝገበ አያያዝ 
👉 የት ደረጃ ፡ dip-degree
👉የስራ ልምድ ፡ 0_1አመት
👉ደሞዝ ፡  13500
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ወደ 24 በሚወስደው መንገድ  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305  👇👇👇👇👇
         ☎️ 0907362385
         ☎️  0909174853
     
❤6👍5😢2🤣1😡1
ኢራን ፤አሜሪካ ለፈፀመችባት ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ ሰጥቻለሁ ሰጠች።

የአሜሪካው ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንት ኮም ) የአብዮታዊ ዘቡን የባህር ውስጥ ፈንጂ አጥማጅ ኃይልን መትቻለሁ ብሏል።

በላራክ ደሴት ላይ ዒላማውን የጠበቀ ጥቃት ዋሽንግተን ብትፈፅምም ቴህራን ከባድ አፀፋዊ ዕርምጃ  ሰጥቻለሁ ብላለች ።

የኢራን ጦር በዐረብ ኤሚሬቶች የሚገኘውን የአሜሪካን አል-ሚንሃድ የጦር ሰፈርን በሰው አልባ አውሮፕላን ደብድቧል።

በዮርዳኖስ የሚገኝ የዋሽንግተን ጦር ሰፈርም ዒላማ ሆኗል።

ማለዳውን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ድሮኖች ወደ ኤሚሬቶች ልከናል በሚል የጦሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል መግለጫ ሰጥቷል።

በጦር ሰፈሩ ላይ የአሜሪካ ኃይሎች እና ሄሊኮፕተሮች የሚገኙበት እንደሆነም ተነግሯል።

በኢራኗ ላራክ ደሴት ላይ የአሜሪካ ጦር ላደረሰው ጉዳት የተሰጠ ምላሽ መሆኑንም ኢራን አፅንዖት ሰጥታለች።

አዲሱ ጥቃት በአሜሪካና ኢራን መካከል ያለውን አለመግባባት ዳግም ወደ ከፋ ግጭት ሊወስድ የሚችልና የዲፕሎማሲውን ጭላንጭል የሚያጠፋ ነው እየተባለ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤15👍8🤔1
ካሜራ መግጠም ተጀመረ‼️
የገቢዎች ሚኒስቴር የኤክሳይዝ ታክስ ከፋይ የሆኑ የማምረቻ ተቋማት፣ በተለይም የቢራና የታሸጉ መጠጦች ፋብሪካዎች ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የክትትል ካሜራዎችን መግጠም መጀመሩ ታወቀ።
መንግሥት ለዲጂታል የክትትል ሥርዓቱ ወደ 300 ሚሊዮን ብር የሚገመት በጀት መድቧል።

ካሜራዎቹ የምርት መስመሮችን፣ የማሸጊያ ክፍሎችን፣ መጋዘኖችን፣ የጭነት መውጫዎችንና የምርት መጓጓዣን በቅጽበት ለመከታተል እንደሚውሉ ተገልጿል።

ሥርዓቱም የፋብሪካዎች ትክክለኛ ምርት ከሚያሳውቁት የምርት መጠን ጋር ያለውን ልዩነት በመቆጣጠር የግብር ማምለጫን ለመቀነስ ያለመ ነው።

በመመሪያዎቹ መሠረት አልኮል፣ ቢራ፣ ወይን፣ የታሸገ ውሃ፣ ትምባሆ፣ ሽቶ እና ጣፋጭ ወይም ካርቦኔትድ መጠጦችን ጨምሮ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው ምርቶች በዲጂታል ኮድ ወይም በኤክሳይዝ ማህተም እንዲለዩ ይደረጋል።

በተጨማሪም ፋብሪካዎች የምርት እና የማጓጓዣ ሂደታቸውን በርቀት ለመከታተል የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ሥርዓቶችን በራሳቸው ወጪ እንዲያስገቡ መመሪያ መኖሩ ተጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18🤣8👍6😱1
በይቅርታ የሚፈታ የለም‼️
በዚህ በዓል ከእስር ቤት የሚፈታ 'ታራሚ' የለም! 🚫‼️

"አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ብዙዎች 'ዘመዶቻችን ከእስር ይፈቱልናል' ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።

ነገር ግን የፍትህ ሚኒስቴር ያሰማው ዜና ለብዙዎች አስደንጋጭ ሆኗል።

ሚኒስቴሩ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደገለጸው፤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ብቻ በይቅርታ የሚፈታ አንድም ታራሚ የለም! 'ይቅርታ' የሚደረገው በአዲሱ መመሪያ መሠረት በቦርድ ሲወሰን ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ብዙዎቻችን 'ምህረት' እና 'ይቅርታ' አንድ ይመስለናል። ነገር ግን ምህረት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሲሆን፣ ይቅርታ ግን ጥብቅ የሆነ ሕጋዊ አካሄድ አለው።
ክልሎች በራሳቸው ርዕሳነ-መስተዳድሮች አማካኝነት ታራሚዎችን ሊፈቱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18😢7👍4🌚2
ለጋብቻ ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል ፍቅረኛውን የገደለው ግለሰብ ተያዘ
 
በሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ቀበሌ ሳድንስ መንደር ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው።
 
ተከሳሽ ፍቃዱ ግሽናብ የተባለ ሲሆን ከተበዳይ ጋር ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ይተዋወቁ እንደነበርና በኋላም የፍቅር ግንኙነት መስርተው እንደነበር ተገልጿል።
 
በ2016 ዓ.ም ተከሳሹ የተበዳይን ፈቃድ ሳያገኝ ለማግባት በማሰብ የጠለፋ ወንጀል ይፈፅማል።
 
ተበዳይዋ ወደፊት ከተከሳሹ ጋር ለመጋባት ፈቃደኛ አለመሆኗንና ሌላ የፍቅር ግንኙነት መጀመሯን ተከትሎ ተከሳሹ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያወጣውን ገንዘብ በማመካኘት በተበዳይዋ ላይ ቂም ይዞ መቆየቱ ተነግሯል፡፡
 
በዚህም ምክኒያት የግድያ ወንጀሉን እንደፈጸመ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡
 
ተከሳሹ ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው ለመሰወር ሙከራ ቢያደርግም ከአካባቢው ማኅበረሰብ በተገኘ ጥቆማና በፖሊስ በተደረገው ጠንካራ ክትትል መሰረት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል፡፡
 
የምርመራ ሂደቱም በሰው ማስረጃ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን  ቀሪ የሕክምና ማስረጃዎችን በመጠባበቅ መዝገቡን አጠናቅቆ ተጠርጣሪውን ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ሂደቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ተናግረዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤20😢6👍5😡1
ተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል ውጤት ያስመዘገቡት መንትዮች   👏

የባሕር ዳር ከተማ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሆኑት መንትዮቹ በዕምነት መልካሙ እና ዮርዳኖስ መልካሙ ተመሳሳይ ውጤት ማስመዝገባቸው አስደናቂ ክስተት ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች የሆኑት መንትዮቹ፣ ተመሳሳይ 413 ከ 600 ውጤት ማስመዝገባቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍29❤9👌2🙏1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

✅ከጠዋቱ 2:00-10:30

👉ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል፣ጋቦን ኢንባሲ፣ 24 ስፖርት ኮሚሽን ፣አደይ አበባ ስታዲየም ፣ 24 ኮንዶሚኒየም ጨጨሆ የባህል አዳራሽ ፣ መሶብ ፣ ቦሌ መድሀኒአለም ፣ ቦሌ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አካባቢው ፣

👉ሬድዋን ህንጻ ፣ ሞኢንኮ ጀርባ፣ ሰላም ህንጻ ፣ ኦሮሚያ ታወር ፣ ዮጎ ቸርች ፣ ቀነኒሳ ሆቴል ፣ ብርሀነ አደሬ ህንጻ ፣ አርመን ሆቴል ፣ ሞሞና ሆቴል ፣ ካሌብ ሆቴል ፣ መድሀኒአለም ታወር እና አካባቢው

👉ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር በከፊል ፣ቶልቻ፣ ሰሪፊ፣ ጉጄ ፣ ቶልቻ ፣ታጠቅ ኢንዱስትሪ ፣ ፌስቱላ ማዕከል እና አካባቢው ፣

👉ለገጣፎ ፣ የካ ሰዲ ፣ የካ አባዶ ጀርባ ፣ 44 ማዞሪያ ፣ ፍሬ ጎዩ ፣ ሮጌ ፣ ድሬ ሶኮሩ ፣ ለገበሪ ፣ ግራር ገብር ኤል ፣ አዲስ አበባ ውሃ በከፊል ፣ ዳቢ ጎርጊስ ፣ ሰንዳፋ ሙሉ ከተማ ፣ ለገጣፎ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው  የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤7👍3
የአዲስ አበባው የአድዋ ድልድይ መንገድ ተዘጋ


ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት መንገዱ መዘጋቱን ነው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያስታወቀው።

በመንገዱ ላይ ያጋጠመው ችግር በጥናትና ዲዛይን የተደገፈ፣ ዘላቂ መፍትሄ እስኪሰጠው ድረስ፤ ባለስልጣኑ ከሴቶች አደባባይ ወደ ባልድራስ ትራፊክ መብራት የሚወስደው መንገድ፤ ከዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሆነ እወቁልኝ ብሏል፡፡

በመሆኑም አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤4👍4😢3
በሱዳን ሰብዓዊ ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉ የአር ኤስ ኤፍ መሪዎች ከእስራኤል ባለሥልጣናት ተገናኙ‼️

በሱዳን የርስበርስ ጦርነት ውስጥ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ከፍተኛ ባለሥልጣናት በግጭቱ ወቅት ወደ እስራኤል ምስጢራዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸውን «አፍሪካ ኢንቴሊጀንስ» ያወጣው የምርመራ ዘገባ አመላከተ።

መገናኛ ብዙኃኑ እንደገለጸው ከሆነ ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ጋር ትስስር ያላቸው ሁለት ልዑካን ቡድኖች በመጀመሪያ በግንቦት 2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በየካቲት 2018 ዓ.ም ወደ ቴል አቪቭ ተጉዘዋል።

ልዑካኑ ከእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መመሪያ ባለሥልጣናት እና ከስለላ አገልግሎት ተወካዮች ጋር መክረዋል ተብሏል።

የመጀመሪያው ልዑክ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ሁለተኛ ሰው እና የድርጅቱ መሪ የሙሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ወንድም የሆኑትን አብዱል ረሒም ሐምዳን ዳጋሎን እንዲሁም ሌላኛውን የቤተሰብ አባል አልጎኔ ሐምዳን ዳጋሎን ያካተተ እንደነበር ተገልጿል።

ሁለቱ ግለሰቦች በየካቲት 2018 ዓ.ም በነበረው ሁለተኛ ጉብኝታቸው ወቅት ከድርጅቱ የሕግ አማካሪ ጋር በመሆን ወደ እስራኤል ተመልሰው እንደነበር ተጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8👍5🤔2