አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የደረቀ ውቅያኖስ የለም‼️
“በሱማሊያ በኩል ያለው ቀይ ባህር ደረቀ” የሚለው መረጃ ውሸት ነው‼️
​በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ “በሱማሊያ በኩል ያለው ቀይ ባህር ደረቀ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ አሳሳች እና የሐሰት መረጃ (Fake News / Misleading) እንጂ እውነት አይደለም።

​በጂኦግራፊ፣ በውቅያኖስ ጥናት (Oceanography) እና በአካባቢ ጥበቃ ሳይንሳዊ መረጃዎች መሠረት በቀይ ባህርም ሆነ በአደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ ምንም ዓይነት የውኃ መድረቅ አልተከሰተም።

​◉ ሳይንሳዊ እና ጂኦግራፊያዊ እውነታዎች

​ሱማሊያ ከቀይ ባህር ጋር ድንበር የላትም፦ ሱማሊያ የምትገኘው በህንድ ውቅያኖስ እና በአደን ባሕረ ሰላጤ (Gulf of Aden) ዳርቻ ላይ እንጂ በቀይ ባህር (Red Sea) ወሰን ላይ አይደለም። የቀይ ባህር መውጫ (ባብ ኤል-መንደብ) የሚያበቃው በጅቡቲ እና በየመን የባህር ወሰን ላይ ነው።

​የውኃ መጠኑ አልቀነሰም፦ የቀይ ባህር እና የአደን ባሕረ ሰላጤ ውኃ ከታላቁ ህንድ ውቅያኖስ ጋር የተያያዘ በመሆኑ እንደ ተነጠሉ የቤት ውስጥ ሐይቆች (ለምሳሌ እንደ አራል ባህር) የመድረቅ ዕድል የለውም።

​◉ የተሳሳተው መረጃ ምንጭ እና ሳይንሳዊ ምክንያቶች

​የሞገድ መሸሽ (Low Tide) በጨረቃ እና በፀሐይ የስበት ኃይል ምክንያት በየቀኑ የባህር ውኃ ወደ ኋላ የመሸሽ (Low Tide) ክስተት ያጋጥማል።በዚህ ወቅት የባህሩ ዳርቻ ሰፊ ሆኖ ስለሚታይ፣ አጋጣሚውን በቪዲዮ ቀርፀው "ባህሩ ደረቀ" የሚል አሳሳች መረጃ ያሰራጫሉ።

​የባህር ወለል መስፋፋት (Seafloor Spreading)፦ የአፍሪካ እና የአረቢያ ቴክቶኒክ ፕሌቶች እየተራራቁ በመሆናቸው ቀይ ባህር እና የአደን ባሕረ ሰላጤ በየዓመቱ በጥቂት ሚሊሜትር እየሰፉና እየጠለቁ እንጂ እየደረቁ አይደሉም።

​የባህር ወለል መጨመር (Sea Level Rise)፦በአለም አቀፍ ደረጃ በሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ እና የዋልታዎች በረዶ መቅለጥ ምክንያት የባህር ወለል መጠን (Sea level) እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም።

​◉ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት ምስሎች እና ቪዲዮዎች ላይ የሚታየው እውነተኛ ቦታው የት ነው?

​ትክክለኛ ቦታው ምስሎቹ የሚያሳዩት በህንድ (India) ጉጃራት ግዛት የሚገኘውን አላንግ (Alang Ship Breaking Yard) የተባለውን የዓለማችን ትልቁን አሮጌ መርከቦች ማፍረሻ ቦታ ነው።

​በምስሉ ላይ የሚታዩት መርከቦች ​በግራ በኩል የሚታየው ትልቅ የነዳጅ መጫኛ መርከብ (Tanker) ነው።​በቀኝ በኩል የምትታየው ደግሞ "Marco Polo" የተባለች አርጅታ ለመበጣጠስ የመጣች የሽርሽር መርከብ (Cruise Ship) ናት።​ከበስተጀርባ የሚታዩት መርከቦቹን ለመቁረጥ የተዘጋጁ ክሬኖች (Cranes) እና የመበጣጠሻ መሳሪያዎች ናቸው።

◉ መርከቦቹ ደረቅ መሬት ላይ እንዴት አረፉ?

​መርከቦቹ አሸዋው ላይ ያረፉት ባህር ደርቆ ሳይሆን ሆን ተብሎ በተደረገ ቴክኒካዊ አሰራር (Beaching Process) ነው። ​ውኃው በጣም በሚሞላበት ጊዜ (High Tide) መርከቦቹን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አሸዋማው ዳርቻ ያስጠጉዋቸዋል። ​ውኃው ወደ ኋላ በሚሸሽበት ጊዜ (Low Tide) መርከቦቹ በደረቁ አሸዋ/ጭቃ ላይ ስለሚቀሩ ሰራተኞች በእግራቸው ሄደው ለመቁረጥ ይመችቸዋል።

​በቪዲዮው ላይ የሚታየው ክስተት በህንድ አገር አሮጌ መርከቦችን ለማፍረስ በባህር ውኃ መሸሽ ወቅት (Low tide) የተቀረፀ ተራ የመርከብ ማፍረሻ ቦታ እንጂ የቀይ ባህር መድረቅ አይደለም። መረጃው ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍21
የማርሻል አርት አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ከጆኒ ጋር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

በሀገር ውስጥ የኤምኤምኤ (MMA) ስፖርት ዘርፍ አዲስ ውጥረት የሚያነሳስ መረጃ ወጥቷል። የአፋር ክልል ተወላጅ እና የዳካይቶ ሪዩ (Dakayto Ryu) ማርሻል አርት አሰልጣኝ ማስተር ሀሰን ሞሚን፡ በቅርቡ ትልቅ ትኩረት ከሳበው ተፎካካሪ ጆኒ (Johnny) ጋር በሪንግ ውስጥ ለመጋጠም ጥሪ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ማስተር ሀሰን የሀገር በቀል የትግል ስፖርት እና የባህል ማርሻል አርት ጥንካሬን በኦክታጎን ውስጥ ለማሳየት ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን የገለፁ ሲሆን፡ አሁን ላይ የግጥሚያው መካሄድ በETFC አዘጋጆች እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ሆኗል።

የሁለቱ ተወዳዳሪዎች የክህሎት ልዩነትና የተለያየ የስፖርት መነሻ የብዙዎችን ትኩረትስቧል።

የስፖርት ቤተሰቡ ግምት፦

• የዳካይቶ ሪዩ አሰልጣኙ ማስተር ሀሰን ሞሚን ያሸንፋሉ?
• ወይንስ የጆኒ የኤምኤምኤ ቴክኒክ የበላይነቱን ይይዛል?
እርስዎ የትኛውን ተወዳዳሪ ይደግፋሉ?

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪14👍93🤯1
የዉሃ መስመር በመሰበሩ በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ የዉሃ አቅርቦት ተቋረጠ

በአዲስ አበባ ከተማ በባለ 800 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ስፋት ያለዉ የዉሃ ግፊት መስጫ መስመር ላይ ስብራት ማጋጠሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል ።

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሰርካለም ጌታቸዉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደገለፁት ከገላን የጋራ መኖሪያ ቤት አከባቢ የሚገኝ እና በተለምዶ አቃቂ ክፍለ ከተማ 3ሀ ተብሎ ከሚጠራዉ የግፊት መስጫ ጣቢያ ወደ ሀና ማሪያም የግፊት መስጫ ጣቢያ የሚወስደው ባለ 800 ሚሊ ሜትር ከባድ የግፊት መስጫ መስመር ግንባታ በሚገነቡ ባለሀብቶች ምክንያት ተሰብሯል ።

በዚህም የተነሳ ሀና ሰፈራ፣ሀና ማሪያም፣ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ሀና ፉሪ፣ ላፍቶ፣ ጀሞ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና አካባቢው እንዲሁም ቫርኔሮ እና ለቡ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ውሃ ማሰራጨት እንዳልተቻለ ተገልጿል ።

ባለስልጣኑ መስመሩን ለመጠገን ሙሉ የከባድ መስመር ባለሙያዎችን ማሰማራቱን ገልጿል ። መስመሩን ተጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትእግስት እንዲጠባበቁ መልዕክቱን አስተላልፏል ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2😢2🤣1👀1
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎችን ቅበላ በፍጥነት እንዲያከናውኑ እየተሠራ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላና ቅበላ ካከናወኑ በኋላ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በፍጥነት ጥሪ እንዲያደርጉ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም እንዲጀምር መርሐ ግብር የተያዘ ሲሆን እሱን ለመጠበቅ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍4
የደም ግፊት መጠን መጨመር (Hypertension) ሲያጋጥም መደረግ እና መደረግ የሌለባቸው ወሳኝ የህክምና ጥንቃቄዎች ይፋ ሆኑ
 
ደም በደም መላሾች ውስጥ በከፍተኛ ኃይል ሲፈስ የሚከሰተው እና ብዙ ጊዜ ምንም አይነት ግልጽ ምልክት ሳይያሳይ የልብ እና የኩላሊት ህመሞችን የሚያስከትለው የደም ግፊት መጨመር፣ በብዙዎች ዘንድ "ጸጥተኛው ገዳይ" በመባል እንደሚታወቅ የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
 
የህመሙን ስጋት ለመቀነስ እና የደም ግፊትን በጤናማ ደረጃ ውስጥ ለማቆየት ህመምተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ አበይት መመሪያዎች ተዘርዝረዋል።
 
የደም ግፊትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር በፖታሺየም የበለፀጉ ምግቦችን፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን አብዝቶ መመገብ እና በየቀኑ ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ያህል ቀልጣፋ የእግር ጉዞ ወይም ቀላል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የደም መላሾችን በማስፋት ግፊቱን ይቀንሳል።
 
ከዚህ በተጨማሪ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ ጭንቀትን የሚቀንሱ የአእምሮ እረፍቶችን መውሰድ እና የደም ግፊት መጠንን በቤት ውስጥ በየጊዜው በመለካት መመዝገብ የህክምና ክትትሉን ውጤታማ ያደርገዋል ተብሏል።
 
በሌላ በኩል ጨው እና ከፍተኛ የሶዲየም መጠን ያላቸውን የታሸጉ ምግቦች አብዝቶ መመገብ የሰውነት ፈሳሽ እንዲከማች በማድረግ ግፊቱን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጨምር ሊወገድ ይገባል ነው የተባለው።
 
ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ የህመም ማስታገሻዎች (እንደ Ibuprofen እና Diclofenac ያሉ) የደም ግፊትን ይበልጥ ስለሚቀሰቅሱና የኩላሊት ስራን ስለሚጎዱ ያለ አግባብ መጠቀም አይገባም።
 
በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት እና ከመጠን በላይ ቡና ማብዛት የደም መላሾችን በማጥበብ ግፊቱ እንዲያቅበዘብዝ ስለሚያደርጉ መተው አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።
 
ከታዘዘ የደም ግፊት መድኃኒት ውጭ የባህላዊ ህክምናዎችን ብቻ አምኖ የመድኃኒት መጠን መቀነስ ወይም ማቋረጥ ለድንገተኛ የልብ ድካም እና የአእምሮ ደም መፈሰስ (Stroke) ያጋልጣል።
 
ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው? የደም ግፊት መጠኑ ድንገት ከፍ ብሎ ከጽኑ የራስ ምታት፣ የደረት ህመም፣ የእይታ መደብዘዝ ወይም የመተንፈስ ችግር ጋር ከተያያዘ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። 

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍9
በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማራቹ  ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተጠንቀቁ ።

በ3 የሻይ ሲኒ  ደረሰኝ  ምክንያት 300 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

በአዲሱ የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ደረሰኝ አለመስጠት ንብረትዎን ሊያሳጣዎት ይችላል!

አንድ ሰራተኛዎ ቸልተኛ ሆና 100 ብር ለሚያወጣ 'ሻይ' ደረሰኝ ባትቆርጥ... ቅጣቱ 100 ብር ሳይሆን 100 ሺህ ብር ነው ተብሏል።

ይባስ ብሎ ደግሞ... ሰራተኛዋ ለ3 ደንበኞች ደረሰኝ ካልሰጠች፣ ለድርጅቱ ባለቤት የ300 ሺህ ብር መብረቅ የመሰለ ቅጣት ይወርድበታል።

ይህ ቅጣት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 125 ንኡስ ቁጥር 2 መሰረት በባለስልጣኑ ሊነሳ ወይም 'ይቅር' ሊባል አይችልም!

መፍትሄው መክፈል ብቻ ነው! ነጋዴዎች ተጠንቀቁ፣ ሰራተኞቻችሁን አስተምሩ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍12😡6😢2🥱2🙉2🤣1👀1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ ቁማር አስከፊነት 💔💔💔😭😭😭

ይህቺ ልጅ እንዲህ የምታለቅሰው የሴዶ መሸነፍ አበሳጭቷት ብቻ አይደለም። እርሱ ያሸንፋል ብላ ለስራ መስሪያ ከባንክ የተበደረቺውን ብር ሳይቀር አሲዛ በቁማር ተበልታ ነው።💔💔💔(via seid social)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪36🤣244👍3👌3😢2🤡1🙊1
"እግዚአብሔር ይመስገን አለሁ"
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ
ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከመገናኛ ብዙኃን ራቅ ማለታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ዜናዎች ሲሰራጭ ሰንብቷል። በዛሬው እለት ብልጽግና ፓርቲ በይፋዊ የቲክቶክ ገጹ ለሰሞንኛው አጀንዳ መልስ የሚመስል ቪዲዮ ለቋል። በቪዲው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ! "አለሁ እግዚአብሔር ይመስገን" በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3615💔11🤪4👍3🤷‍♂2🥰1
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው።

ጋርሺያ ባለፈው ግንቦት ወር ከተሾሙ ወዲህ ኢትዮጵን ሲጎበኙ የአሁኑ የመጀመሪያቸው ይሆናል።ፍራንክ ጋርሺያ ወደ አዲስ አበባ የሚያቀኑት አገራቸው አሜሪካ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ውጥረት እንዲረግብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች በምትገኝበት ወቅት ነው።

ረዳት ሚኒስትሩ በጉዟቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ዛምቢያና ኬንያን እንደሚጎበኙ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2018 በኤክስ በኩል አስታውቋል።በቢሮው መረጃ መሠረት የጋርሺያ ጉብኝት “ቁልፍ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር፣ የጋራ ኢኮኖሚያዊና የደሕንነት አጋርነቶችን ለማሳደግ” ያለመ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍5
የአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች ክምችት በአሳሳቢ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ‹‹ዎል ስትሪት ጆርናል›› የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ።

በመካከለኛው ምስራቅ ከኢራን ጋር ያለው ግጭት በአውሮፓ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር መሣሪያዎች ክምችት ክፉኛ እየጎዳው መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም የ‹ፓክ-3 ፓትሪዮት› ሚሳኤል መከላከያዎች እና የረዥም ርቀት ሚሳኤሎች ክምችት ከወትሮው በበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተመላክቷል።

በዚህም ግጭት እስካሁን፦ 1 ሺህ 7 መቶ የፓትሪዮት ሚሳኤል መከላከያዎች፣ 2 መቶ የታድ መከላከያዎች፣ እና 150 የባህር ኃይል ስታንዳርድ ሚሳኤሎች አገልግሎት ላይ ውለዋል።

ይህንኑ እጥረት ለማቃለል ሲባልም፤ በርካታ የታድ ስርዓቶች እና ድሮን ተከላካይ መሣሪያዎች ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተዛውረዋል።

ይህ የመሣሪያዎች እጥረት አሁን በጦርነት እቅድ ዝግጅት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ፣ የአሜሪካ አውሮፓ እዝ የተግባር እቅዶቹን ማስተካከሉ ተሰምቷል።

ነጩ ቤተ መንግስት እና ፔንታጎን ግን “እጥረት አለ” የሚለውን ዘገባ በመቃወም፣ ያለው ክምችት ለስትራቴጂካዊ አላማዎች በቂ እንደሆነ አስምረው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍54🤯2
አጋቾችንና ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️
በደብረ ብርሃን ከተማ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ህገወጥ ተግባራትን በመከታተል አጋቾችንና ዘራፊዎችን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።

ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት አንድ ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ ከልጅ ቤተሰብ ጋር በመደራደር 3 ሚሊዮን ብር መቀበላቸው ታውቋል።

የክፍለ ከተማው የፀጥታ መዋቅር በወቅቱ የተገኘውን መረጃ ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ መረጃ በማሰባሰብና ክትትል በማድረግ ቆይቶ፣ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ማስረጃዎቻቸው በቁጥጥር ስር አውሏል።

በእርምጃውም በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ የሞባይል ስልኮች፣የተለያዩ የባንክ አካውንት ደብተሮችና የተለያዩ መጠን ያላቸው ጥሬ ገንዘቦች መያዛቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍2
#ትኩረት ያሸዋል ተባለ

"አዲስ አበባ ሜክሲኮ ደብረወርቅ ታወር ፊት ለፊት፣ ከቡናና ሻይ አጠገብ ባለው ዋና መንገድ ላይ የሚገኝ ይህ 'ፖል' የብዙዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል ነው የተባለው ። 😱

በተለይ በምሽት እይታው ስለሚቀንስ፣ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለማይፈለግ አደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ።

ይህ ፖል ከመንገዱ ተነስቶ ሌላ ምቹ ቦታ ላይ ካልተተከለ የከፋ አደጋ ሊያደርስ ይችላል።

የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ እና የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
⚠️⚠️
ይህ መረጃ ለሚመለከተው አካል እስኪደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩ!"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍4🙏1