አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
416 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በኢሮብ ወረዳ 35 ሺህ ህዝብ ለከባድ ድርቅ ተጋልጧል።

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኘው ኢሮብ ወረዳ ከባድ ድርቅ እየተጋፈጠ ሲሆን በአካባቢው የሚኖሩ 35 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለድርቅ አደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

በወረዳው የክረምት ዝናብ በበቂ ሁኔታ ባለመዝነቡ የውሃ ጉድጓዶች መድረቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በውሃ እጥረቱም የቤት እንስሳት መሞት መጀመራቸውን አስረድተዋል።

በወረዳው የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በከፍተኛ ተራራና ተዳፋት አካባቢዎች መሆናቸው የተጀመረውን የእርዳታ ማዳረስ ስራ ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል።

የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደሚሉት፣ ከዚህ በፊት እንደ ዘንድሮ ያለ ከባድ ድርቅ አጋጥሟቸው አያውቅም።

የዝናብ እጥረቱ በማሳ ላይ የተዘራው እህል እንዲደርቅ ከማድረጉም በላይ በክረምት ዝናብ ይሞሉ የነበሩ የውሃ ጉድጓዶች እንዲደርቁ አድርጓል።

የኢሮብ አካባቢ የኢሮብ ብሄረሰብ የሚኖርበት ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች አንዱ ነው። አካባቢው በ2013 ዓ.ም. በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን እስካሁንም አንዳንድ የቀበሌ ገበሬ ማህበራት በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

የድርቁ አደጋ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ለጋሽ ድርጅቶች፣ ባለሀብቶችና ግለሰቦች የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ወረዳው ቀደም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ ጥሪ መሰረት አንዳንድ ግለሰቦች የእርዳታ እህል ማቅረብ መጀመራቸው ተገልጿል። ሆኖም የእንስሳት መኖ፣ የሰዎችና የእንስሳት መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት አሁንም የድርቁን ተጽዕኖ ለመቀነስ የሚደረገውን ስራ ከባድ እያደረገው እንደሆነ ተጠቁሟል።

የአካባቢው ህዝብ የውሃ፣ የምግብ እና የእንስሳት መኖ አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲጠናከር ጥሪ እያቀረበ ነው።

@Addis_Reporter
😢195👍2💔2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ እና የመንግስት አካውንቶች ወደ ስኬት ባንክ መዛወሩ ተሰማ።
ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት፣ ቢሮዎች እና ትምህርት ቤቶች በተላለፈው ጥብቅ ትእዛዝ ሠራተኞች በንግድ ባንክ የነበራቸውን አካውንት ዘግተው በደብዳቤ እንዲያሳውቁና በስኬት ባንክ አዲስ አካውንት በአስቸኳይ እንዲከፍቱ ተነግሯቸዋል።

Via :- መሰረት ሚዲያ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤔12😢4👍32🤪1
"ከቡርኪና ፋሶ ውጡ ካልሆ ትሞታላችሁ‼️

የቡርኪና ፋሶው መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ከሽብርተኞች ጋር ድርድር አላደርግም አሉ።

የቡርኪና ፋሶ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ አገራቸውን እያተራመሱ ካሉ ታጣቂ እና አሸባሪ ቡድኖች ጋር ምንም ዓይነት ድርድር አናደርግም ብለዋል።

ከቡድኖቹ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር የማድረግ ፍላጎት እንደሌላቸውና የማያወላውል ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ይፋ አድርገዋል።

ካፒቴን ትራውሬ ለታጣቂ ቡድኖቹ ግልጽና ወሳኝ የሆነ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከቡርኪና ፋሶ ውጡ ካልሆነ ትሞታላችሁ ብለዋል።

መንግስት የአገሪቱን አንድ ስንዝር መሬት እንኳ ለሽብርተኞች አሳልፎ እንደማይሰጥና ሀገሪቷ ሉአላዊነቷ እስኪረጋገጥ ድረስ ውጊያው እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ ሰላም የሚረጋገጠው በድርድር ሳይሆን በመከላከያ ሰራዊት ጥንካሬ ነው ሲሉ ጠንካራ አቋማቸውን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
54👍28🤣3🥰1🤔1💔1👀1
የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት፣ ከኢትዮጵያ አቅጣጫ ወደ ሱዳን ግዛት ገብቷል ያለውን ድሮን ዛሬ ጧት መትቶ መጣሉን አስታወቀ፡፡

የሱዳን ጦር ኃይል ድሮኑን መትቶ የጣለው፣ ከኢትዮጵያው ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ጋር በሚዋሠነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ መኾኑን እንደገለጠ የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ኾኖም የሱዳን ጦር ኃይል መትቼ ጣልኩት ባለው ድሮን ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ አንዳልሠጠ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

የአገሪቱ ጦር ኃይል ከቀናት በፊትም በዚሁ ግዛት ውስጥ ኩርሙክ ከተማ አካባቢ ከኢትዮጵያ በኩል የገባ ድሮን መትቼ ጥያለሁ ማለቱ  አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ውንጀላዎች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በይፋ ምላሽ አልሠጠም።(ዋዜማ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3🤔3
ቀን 22/12/2018
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 09 17 48 53/09 07 36  23 85
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉   የስራ መደብ:# NGO
👉የት/ደረጃ ዲፕሎማ / ድግሪ
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞዝ:- 40.000_50.000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው  መደብ =- ሀውስ ኪፒግ
👉የትምርት ደረጃ 8 +
👉የስራ ልምድ 0-3
👉ደሞዝ 7000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ሆስተስ
👉የትምርት ደረጃ 10 +
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 15000 / 20000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =-መስተግዶ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0/2
👉ጾታ ወንድ /ሴት
👉ደሞዝ ማራኪ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የስራው መደብ /ፓስታ ፋብሪካ=-የእሸጋ ሰራተኛ
👉  የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
👉ደሞዝ:-  17000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
👉ደሞዝ ፡ 15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ሹፌር ደ/1 2 ህ/1/ሞተረኛ
👉የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
👉ደሞዝ:- 7000_17000
👉ፆታ :- ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ትኬተር/ለባስ/
👉የሰራ ልምድ :- 0አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
👉ደሞዝ:- 0አመት
👉ደሞወዝ   :- 9000~20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
👉የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
👉ደሞዝ:-8000_30000+
👉የስራ ልምድ: 0አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ :markting
👉የት ደረጃ ፡- degree 
👉የስራ ልምድ ፡- 0~5 አመት
👉ደሞዝ :-13000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ Accountant
👉የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
👉ደሞዝ ፡  8,000-16,000 
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ IT
👉የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
👉የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
👉ፆታ:- ሴ/ወ
👉ደሞዝ:- 8000-15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ካሸር
👉የት/ደረጃ፦10 +
👉የሰራ ልምድ 0~3 አመት
👉ደሞዝ:- 7000-12000
👉ፆታ፦ሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#nurse//ላብራቶሪ/ጠቅላላ
👉 ለክሊኒክ እና ለሆስፒታል
👉የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
👉የስራ ልምድ: 0~8አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉ፆታ፦ሴት/ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ 8
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-1
👉ደሞዝ :7000-20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
👉የትምርት ደረጃ 8+
👉የስራ ልምድ 0 -1 አመት
👉ደሞዝ 10000-25000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ=- ፀሀፊ
👉የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
👉የስራ ልምድ ያላት
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 8000/13000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው አይነት =- ባርቴንደር
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልድ 1/3
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 10000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ብስኩት ፋብሪካ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 16000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
👉የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት
👉ደሞዝ:-9000-35000
👉ፆታ፦ወንድ/ሴት
👉የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ እሪል እስቴት ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ ዲፕ/ዲግሪ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ ፡  9000-50000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ሁለገብ ሰራተኛ
👉የደረጃ ፡- 8_10
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞወዝ :- 10000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ reception
👉የት ደረጃ ፡ 10/12
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ 8000/15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#ተላላኪና ፅዳት ለባንክ
👉የት/ደረጃ፦8/12 /ዲፕ
👉 የሰራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
👉ፆታ: ሴ/ወ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
👉ደሞዝ ፡  15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉መረጃና መዝገበ አያያዝ 
👉 የት ደረጃ ፡ dip-degree
👉የስራ ልምድ ፡ 0_1አመት
👉ደሞዝ ፡  13500
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ወደ 24 በሚወስደው መንገድ  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305  👇👇👇👇👇
         ☎️ 0907362385
         ☎️  0909174853
     
4👍4
የምሽቱ ትልቁን ፍልሚያ ጆኒ አሸነፈ

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ሲካሄድ የሰነበተው የኢቲኤፍሲ 2 (ETFC 2) ኮከቦች ምሽት በጉጉት በተጠበቀውና በዋናው የዋንጫ ፍልሚያ (Main Event) በይፋ ፍጻሜ አግኝቷል!

በሚድል ዌይት (Middleweight MMA Bout) ዘርፍ በጆኒ እና በሴዶ መካከል የተደረገው ይህ አስደናቂና አቃጣጣኝ ፍልሚያ የመላው ተመልካች ቀልብ የሳበ ነበር።

በከፍተኛ የኤምኤምኤ (MMA) ቴክኒክ፣ የላቀ ብቃትና ፍጹም የድል ወኔ ተጋጣሚውን ሴዶን ያሸነፈው ጆኒ፡ የምሽቱን ትልቅ ድል በመቀዳጀት አዲሱ የ ETFC 2 ቻምፒዮን (Champion) በመሆን ዘውዱን ደፍቷል!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍187🤣7🤪2🎉1😡1
የገቢዎች ሚኒስቴር የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች የ2018 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ለእያንዳንዱ የንግድ ስራ መስክ በተናጠል እና ሁሉንም የንግድ መስኮች ያካተተ የተጠቃለለ ሪፖርት ማቅረብ እንዳለባቸው አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳሰበ።

የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከአንድ በላይ የንግድ መስክ ላይ ለተሰማሩ የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋዮች ለእያንዳንዱ የንግድ ዘርፍ የተለየ የሂሳብ መዝገብ መያዝ እንዳለባቸው አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ይህ አሰራር ተግባራዊ የሚደረገው በገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 86 እና በሠንጠረዥ "ሐ" በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2
የሳይነስ ህመም (Sinusitis) ሲያጋጥም መደረግ እና መደረግ የሌለባቸው ወሳኝ የህክምና ጥንቃቄዎች ይፋ ሆኑ

በአፍንጫ አካባቢ የሚገኙ የአየር ክፍሎች በባክቴሪያ፣ በቫይረስ ወይም በአለርጂ ምክንያት ሲያብጡ እና በፈሳሽ ሲታፈኑ የሚከሰተው አጣዳፊ የሳይነስ ኢንፌክሽን፣ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ የፊት ምታት እና የእስትንፋስ መዘጋት እንደሚያስከትል የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የህመሙን ጽኑነት ለመቀነስ እና ፈጣን መፍትሄ ለማግኘት ህመምተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ አበይት መመሪያዎች ተዘርዝረዋል።

የሳይነስ ህመምን በፍጥነት ለማስታገስ ውሃ፣ ሞቅ ያሉ የዕፅዋት ሻዮች እና ንጹህ ሾርባዎችን አብዝቶ መጠጣት በአፍንጫ እና በሳይነስ ውስጥ የተከማቸውን ወፍራም ፈሳሽ በማቅጠል አየር መንገዱ እንዲከፈት ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሞቀ ውሃ እንፋሎት መታጠን ታፍኖ የቆየውን የሳይነስ መስመር በማላላት የፊት እብጠት እና ምታትን በፍጥነት ያቀልላል።

በጨው ውሃ የተዘጋጁ የአፍንጫ ማጽጃዎችን መጠቀም በአፍንጫ ውስጥ የተከማቹ ባክቴሪያዎችን እና አለርጂዎችን አጥቦ ለማስወገድ የሚረዳ ሲሆን፣ ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙን አጠናክሮ ህመሙን እንዲያሸንፍ በቂ እረፍት እና እንቅልፍ ማግኘት ወሳኝ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል አፍንጫን በኃይል ተጭኖ መያዝ ፈሳሹን እና ባክቴሪያውን ወደ ጥልቅ የሳይነስ ክፍሎች ወይም ወደ ጆሮ አየር መንገድ በመግፋት ተጨማሪ ኢንፌክሽን ስለሚያመጣ ሊወገድ ይገባል ነው የተባለው።

እንደ Otrivin ያሉ የአፍንጫ ማታገሻ ስፕሬዮችን ከ3 እስከ 5 ቀናት በላይ መጠቀም መድኃኒቱ ሲቆም ህመሙ በባሰ ሁኔታ ተመልሶ እንዲመጣ ያደርጋል።

በተጨማሪም ቡና፣ ሻይ እና አልኮል የሰውነትን ፈሳሽ በማዳከም የአፍንጫ ፈሳሽ ይበልጥ እንዲወፍር ስለሚያደርጉ መተው አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

አብዛኞቹ የሳይነስ ህመሞች በቫይረስ ወይም በአለርጂ ምክንያት የሚመጡ በመሆናቸው ያለ ሐኪም ትዕዛዝ አንቲባዮቲክስ መውሰድ ምንም አይነት ውጤት አይኖረውም።

ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?ህመሙ ከ10 ቀናት በላይ ካልተሻለ፣ ከፍተኛ ትኩሳት ከተጨመረበት፣ ወይም በአይን አካባቢ እብጠት እና የእይታ መደብዘዝ ካጋጠመ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
ህወሃት ጦርነቱን የሚመራና ውሳኔ የሚሰጥ አስራ አንድ አባላት ያሉት ሴንትራል ኮማንድ ማቋቋሙ ተነገረ።

ይህ ሴንትራል ኮማንድ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ከሲቪል አስተዳደር አምስት ከወታደራዊ አመራሮች ደግሞ ስድስት አባላት እንዳሉት የተነገረ ሲሆን የሚመጣውን ጦርነት አመራር ሰጪ ነው ተብሏል።

በተያያዘ የአማራ ሀይሎችም ለቀጣዩ ጦርነት የአደረጃጀት ለውጥ ማድረጋቸው የተዘገበ ሲሆን ይሄም በሌላ የጦርነት ግንባር ቢሆንም ከጥምር ጦሩ ጋር እንደአንድ ሰራዊት ሆነው በጋራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት አደረጃጀት ነው ተብሏል።

ከህወሓት
1) ዶ/ር ደብረፅየን ገ/ሚካኤል
2) ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ሄር (ሞንጀሪኖ)
3) አቶ አማኑኤል አሰፋ
4) ዶ/ር አብርሃም ተኸስተ
5) አቶ ጌታቸው አሰፋ ሲሆኑ

ከወታደራዊ አዛዦች ደግሞ

1) ሌፍተናል ጀነራል ፍስሃ ኪዳኑ(ፍስሃ ማንጁስ)
2) ብርጋዴር ጀነራል ሃ/ስላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ)
3) ሜጀር ጀነራል የውሃንስ ወ/ጅወርግስ (ጆን መዲድ)
4) ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሃይለ(መርዘን) ራሴ ያወጣሁለት ቅፅል ስም ወይም ሳጓ ነው)
5) ሜጀር ጀነራል ብርሃነ ነጋሽ ( ወዲ መድህን)
6) ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍119😢2🥱1😡1
ትናንት ማታ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም በራያ አላማጣ ከተማ ላይ የህወሓት ታጣቂዎች ከፍተኛ አፈሳ መፈፀማቸው ታውቋል።
ብዛት ያላቸው የወያኔ ወታደሮች አላማጣ ከተማ ከገቡ በኋላ ጭምብል በመልበስ አፈሳ ጀምረዋል ፊታቸውን ጭምብል አጥልቀው በርካታ ወጣቶችን ወስደዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍82
የታሪኩ ጋንጋሲ አነጋጋሪ መልእክት

ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ

እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ (ታሪኩ ጋንጋሲ)

በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታፕ ፋይት ቻምፒዮና (ETFC 002፤ Adwa Fight Night) ዋና ፍልሚያ ጆኒ ጁጁትሱ ሰዶን ማሸነፉን ተከተሎ፣ ታዋቂው ድምፃዊ ታሪቁ ጋንክሲ በማህበራዊ ሚዲያው ያስተላለፈው የትችት መልእክት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በሳበው በዚህ ውድድር ዙሪያ ድምፃዊው «ማደሪያ የሌለው ህዝብ - ሲገፋ የኖረ፣ እርግጫ ለማየት - ጎዳና አደረ» የሚል ግጥማዊ ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይኸውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን የፍትህ ማጣት፣ የጦርነት ስቃይ፣ ተቋማዊ የሌብነትና የዘረፋ ወንጀል እንዲሁም የከፋ የኢኮኖሚ ውደቀት ችላ በማለት ህዝቡ ጥልቅ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ውስጥ እያለ በእንደዚህ አይነት የትግል ትዕይንቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመኮነን እንደሆነ ተገልጿል።

ድምፃዊው ይህን ማህበራዊ ተቃርኖ በማንሳት የሰጠው አስተያየት በበርካቶች ዘንድ ድጋፍና የተለያየ ትችት በማስተናገድ በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሰፊ አከራካሪ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍4114
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ 39.5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ

ተቋሙ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 96.5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የዘንድሮው ትርፍ ካለፉት ዓመታት አንጻር የ23 በመቶ ልዩነት እንዳለውም ተገልጿል። ተቋሙ አሁን ላይ በጥቅሉ እስከ 9,730 ሜጋ ዋት ያህል የማመንጨት አቅም እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ አጠቃላይ የተቋሙ አፈጻጸም 92 በመቶ መድረሱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 585 ቢሊዮን ብር ሀብት እንዳለውና መንግሥት አለኝ ከሚላቸው ተቋማት ግንባር ቀደሙ እንደሆነም ተናግረዋል።

በያዝነው ዓመት ያልተሳኩትን ጨምሮ አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በቀጣይ 2019 ዓ.ም እንደሚያከናውንም አገልግሎቱ አስታውቋል። በዚህም 121 ቢሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ 9,770 ሜጋ ዋት ለማመንጨት መታቀዱንም ኢንጂነር አሸብር ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4😢1
የሟቾች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል

በኔፓልና በቻይና ቲቤት በተከሰተ ከባድ ጎርፍ ከ390 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲቀጠፍ፥ ከ1ሺ 500 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

አደጋው በሂማሊያ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ ከፍተኛ የጭቃና የድንጋይ ናዳ በመውደቁ የተነሳ ሲሆን፣ በአካባቢው ከተሞችና ሸለቆዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ አስከትሏል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች ሰዎችን በህይወት ለማትረፍ መረባረባቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ተብሏል።

የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ በቲቤት የደረሰውን አደጋ በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።

የኔፓል ቱሪዝም መምሪያ ትላንት ባወጣው መረጃ፣ ከ34 አገራት የመጡ 668 ቱሪስቶች ከረቡዕ ጠዋት ጀምሮ የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጿል።

ከእነዚህም መካከል ቢያንስ 177 ከህንድ፣ 90 ከአሜሪካ፣ 34 ከአውስትራሊያ፣ 33 ከብሪታንያ እና 25 ከካናዳ የመጡ ናቸው ብሏል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በኔፓል ከጠፉት መካከል 100 የቻይና ዜጎች እንደሚገኙበት እወቁልኝ ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5😢5