አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አሜሪካ የ200,000 ሰዎችን ቪዛ ልትሰርዝ ነው

​የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በታሪክ ትልቁን የቪዛ ስረዛ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

እርምጃው በንግድ (B1) እና በቱሪዝም (B2) ቪዛ ወደ አሜሪካ ገብተው የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ወይም በመጠየቅ ላይ ያሉ እስከ 200,000 የሚደርሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን ዓላማ ያደረገ ነው።

​የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ከ2016 እስከ 2026 የተሰጡ ቪዛዎችን ለመሰረዝ ዝግጅቱን አጠናቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንደተናገሩት፣ እርምጃው ለአጭር ጊዜ ጉብኝት መጥተው ቪዛውን ለቋሚ መኖሪያነት የተጠቀሙበትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተወሰደ ነው።

​ይህ የቪዛ ስረዛ ሰዎች ወዲያውኑ ከሀገር እንዲወጡ ባያደርግም፣ ህጋዊ የጉዞ ሁኔታቸውን የሚያሳጣ በመሆኑ ከፍተኛ የህግ ክስና ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይገመታል።

የትራምፕ አስተዳደር ከዚህ ቀደምም በቪዛ አመልካቾች ላይ በርካታ ጠንካራ ገደቦችን ሲጥል መቆየቱ ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍6👀2
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤

እንኳን ለ1501 ኛው የነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍6
የድሮን ጥቃት ተፈፀመ

በትግራይ ክልል በምስራቅ ዞን አፅቢ ወረዳ በፈለገ ወይኒ ጣቢያ፣ መብራህቶም በሚባል ቀጠና ልዩ ስሙ « በሊጋ» በተባለው ስፍራ በሚገኘው የሱር ኮንስትራክሽን ካምፕ ላይ ትናንት ነሐሴ 18 ከለሊቱ 7:30 አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በሱር ኮንስትራክሽን ካምፕ ላይ ሲሆን በካምፑ ውስጥ የጦር መሳሪያ ክምችት መኖሩ ተዘግቧል።
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍6🤔3😢1
ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ አቅንተው ነበር‼️
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሶጉን ኦባሳንጆ ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ መቐለ አቅንተው ነበር።
ከዚህ በመነሳት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ውይይት የሚጀመር ከሆነ፣ የሚከተሉት ጉዳዮች መመለስ መሠረታዊና ቁልፍ እንደሆኑ ህወሓት አጽንኦት ሰጥቷዋል፦

* የኢኮኖሚ ማዕቀብና እገዳ መነሳት፤
* ወታደራዊ ከበባ ማቆምና የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ፤
* የትግራይ ሉዓላዊ ግዛት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለስ፤
* ተፈናቃዮችን ደህንነታቸውና ክብራቸው በተጠበቀ መንገድ መመለስ፤
* የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ፖለቲካዊና ሕጋዊ ማንነት መመለስ።የሚሉ ናቸው።
በዚህም ኦሊሶጉን ኦባሳንጆ ከመንግሥት ጋር ተወያይቼ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ሳምንታት ድጋሚ እመለሳለሁ”ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍138🤔2
የ12ኛ ክፍል ዉጤት ሲለቀቅ በፍጥነት መረጃ ምታገኙበት እንዲሁም ውጤታችሁን ያለሰርቨር መጨናነቅ እንድታዩ የሚያግዛችሁን ቻናል አሁኑኑ ይቀላቀሉ! 👇
https://t.me/addlist/dLx_2YaQlwFmNjQ8
😡10🤣43
3ኛው የአፍሪካ ስታር ዋይድ አዋርድ በመስከረም ወር ይካሄዳል!

“ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ፤ መመሰጋገን ባሕላችን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነው 3ኛው ዙር የአፍሪካ ስታርዋይድ አዋርድ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በመጪው መስከረም ወር እንደሚካሄድ አዘጋጁ ከለር ፉል ኢቨንት ኦርጋናይዘር በዛሬዉ እለት በአምባሳደር ሆቴል በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል።

በዝግጅቱ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከአፍሪካ ህብረት (Aሀ) የተወጣጡ ተወካዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት እንግዶች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንደሚታደሙ ተጠቅሷል።

የዘንድሮው ዝግጅት ከአምናው በበለጠ አድማሱን በማስፋት አህጉራዊ ተደራሽነት ያለው እንዲሆን መደረጉ ተገልፆ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ምሁራንና ባለሙያዎች በዳኝነትና በኮሚቴነት መካተታቸዉም ነዉ የተገለፀዉ።

ሽልማቱ በተለያዩ 11 ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን የአመራር አባልና ኢንቨስትመንት ዘርፍ፣ የኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ፣አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ባንክ፣ አቪየሽንና ቱሪዝም፣ሴትና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች፣ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንደሆኑ ተገልጿል።

የአዋርዱ ዋነኛ አላማ በዘርፉ የለፉና የደከሙ ግለሰቦችንና ተቋማትን ፈልፍሎ በማዉጣት የሃገር ባለዉለታ ስለመሆናቸዉና በትዉልዱ ዘንድ ሊመሰገኑ ሊዘከሩ እንደሚገባና ትዉልዱም ከመልካም ሥራቸዉና ከዘወትር ትጋታቸዉ ልምድ እንዲቀስም እድሉን ለማመቻቸት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት አቅም ለውጭ ሀገር አልሚዎች ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ አሸናፊዎችን በትክክል ለመለየት ከሙያተኞች ግምገማ በተጨማሪ ህዝቡ በድረገፅ አማካኝነት በስልክ፣ በአሜይል፣ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ጥቆማዎችን መስጠቱን እንዲቀጥል አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የአፍሪካ ስታርዋይድ አዋርድ ለሕዝብ እና ለአገር በጎ ነገር ያበረከቱ ግለሰቦችና ስኬታማ የኢኮኖሚ ጃግኖች፣ በትጋት በቅንነት እና በሀገር ፍቅር መስራት ተምሳሌት የሆኑ አመራሮች፣ ዉስጥ በመሳተፍ በሙያቸዉ አንቱ ለተባሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና የሚያበረክት ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍2
በታይላንድ በዝናብ ወቅት ብቻ የሚከሰተው አስደናቂው የምድር "የድንጋይ ዓይን" የተፈጥሮ ክስተት ትኩረት ሳበ
 
በሰሜን ምስራቅ ታይላንድ ቡኤንግ ካን ግዛት የሚገኘው እና "የምድር ዓይን" በመባል የሚታወቀው አስደናቂው የአሸዋ ድንጋይ ምድር፣ በክረምት ወቅት በሚጥለው የመንሶን የዝናብ ውኃ ሲሞላ ሙሉ በሙሉ ሰዋዊ ዓይን የሚመስል ምስል እንደሚፈጥር ተገለጸ። ይህ ተፈጥሯዊ ክስተት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በውኃ መሸርሸር ምክንያት በድንጋዩ ላይ በተፈጠረው ጥልቅ ጉድጓድ ምክንያት የሚከሰት ነው።
 
በዝናብ ወቅት ውኃው በድንጋዩ ጉድጓድ ውስጥ በሚጠራቀምበት ጊዜ፣ የጉድጓዱ ጥልቅ ማዕከል ጥቁሩን የዓይን ብሌን የሚመስል ሲሆን፤ በዙሪያው ያለው አጭር የውኃ ገጽታ ደግሞ ውጫዊውን የዓይን ክፍል ይፈጥራል። በተጨማሪም የፀሐይ ብርሃን በውኃው ላይ ሲያርፍ የሚፈጥረው ነፀብራቅ ከሰው ልጅ ዓይን ጋር ተመሳሳይነት ያለው እይታ እንዲኖረው ያደርገዋል።
 
የዝናብ ወቅት ሲያልቅ ውኃው የሚደርቅ በመሆኑ ይህ አስደናቂ ክስተት የሚታየው በክረምት ወቅት ብቻ እንደሆነ ተጠቅሷል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26🤯5👍2🥰2🤔1
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍2
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።

ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-

ከጠዋቱ 11፡00-11፡00

👉ኢዮ ጠቢብ ሆስፒታል፣ አበበ ቢቂላ ስታድየም፣ መድሀኒዓለም ት/ቤት ጀርባ፣ መድሀኒዓለም ኮንዶሚኔም፣ ቦናት እና አካባቢው፣                                                                                                 
👉ሸጎሌ ቴሌ፣ ሩፋኤል ፊናንስ፣  አንበሳ ጋራጅ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀርባ፣ ውሃ ጋኑ አካባቢ ( ጎማ አደባባይ) እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡30-10፡30

👉ሱሉልታ መሀል ከተማ ፣ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ወሌ ፣ ጎሮ አርባ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ሱሉልታ መዘጋጃ፣ ኪዳነ ምህረት መውጫ ፣ ሱሉልታ ቄራ ፣ ሱሉልታ ስላሴ፣ አለሙ ማደያ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉 ብሄረ ጽጌ፣ ሳሪስ ነጋ ቦንገር ፣ ስላሴ ቤተክርስቲያን፣ቀይ አፈር፣ ቡራዩ ፣ አኔ ዲማ፣ ወታቤቻ ፣ ሀሙስ ገበያ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉 መካኒሳ አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ጀሞ ሚካኤል፣ አፍሪካ ህንጻ ፣ ዱላ ማርያም ፣

👉 ጭሮ ቤካ፣ ኮራ፣ ኮሞና፣ ጮሮራ፣አንጫር፣ ቦሮዳ፣ ድንድር ፣ ሲዳማ ክልል ይርጋለም፣ ለኩ እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍3
በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጢያ፣ ሱተን እና ኧሽከዲየ ቀበሌዎች የጸጥታ ችግር መከሰቱ ተገለጸ።

በጢያ፣ ሱተን እና ኧሽከዲየ ቀበሌዎች የጸጥታ ችግር መከሰቱን፤ በዚህም ከባድ የጦር መሣሪያ ተኩስ እንደሚሰማና ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እየሸሹ መሆኑ ከአካባቢው የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የወረዳው የጸጥታ ኃይል በአጥቂዎቹ ጫና ወደ ቡኢ ከተማ ማፈግፈጉን እና አንዳንድ ነዋሪዎችም አካባቢውን ለቀው ወደ ቡኢ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።

በተለይ "አቅም-አጠር አረጋውያን፣ እናቶች፣ ሕፃናትና ሕሙማን በግጭቱ መካከል ቀርተዋል" የሚል መረጃ የተሰማ ሲሆን መረጃውም ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በክስተቱ እስካሁን ምን ያህል የሰው ሕይወት መጥፋቱ ወይም የደረሰውን የጉዳት መጠን ማወቅ ያልተቻለ ሲሆን ሁኔታውን በተመለከተ በይፋ የወጣ መንግሥታዊ መረጃም የለም፡፡ ሆኖም የጸጥታ ችግሩ በፍጥነት እንዲቀረፍና በአካባቢው የሚገኙ ንጹሐን ዜጎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ነዋሪዎች እየጠየቁ ነው፡፡

የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ የጸጥታ ተቋማት እንዲሁም  የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች በአካባቢው የሚገኙ ንጹሐንን ለመጠበቅ ፈጣን እርምጃ ይውሰዱ የሚል ጥሪም ቀርቧል።

በዚህ ቀጣና ቀደም ብሎም መሰል የጸጥታ ችግሮች ሲከሰቱ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁን የተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ ችግሩ በተለያየ ጊዜና ቦታ መከሰቱን እንደቀጠለ ለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍4🤔2
በኩዌት ኢትዮጵያዊት ሴት በባሏ አሰቃቂ ግድያ ተፈጸመባት

እንደ ኩዌት ታይምስ ዘገባ ከሆነ ​በኩዌት ጃህራ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት በገዛ ኢትዮጵያዊ ባለቤቷ በቢላዋ ሶስት ቦታ ተወግታ ህይወቷ አልፏል።

​ተጠርጣሪው ባለቤት ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው መሰወሩን አቃቤ ህግ እና የወንጀል ምርመራ ቡድን ባደረጉት የመጀመሪያ ደረጃ ማረጋገጫ ታውቋል።

ዘገባው እንደሚያመለክተው የፖሊስ እና የአምቡላንስ ሰራተኞች ጥቆማው እንደደረሳቸው ወዲያውኑ ቦታው ላይ ቢደርሱም የሴቲቱን ህይወት ማዳን አልተቻለም።

​የአስከሬን ምርመራ ለማካሄድ እና የሟቿን አካል ለማንሳት አቃቤ ህግ እና የፎረንሲክ ባለሙያዎች በቦታው ተገኝተዋል።

የአካባቢው ፖሊስ የድርጊቱን መንስኤ ለማወቅ እና ከአካባቢው ያመለከተውን ተጠርጣሪ ባለቤት አድኖ ለመያዝ ሰፊ የምርመራ ስራ እየሰራ ይገኛል።

የወንጀሉ አሰቃቂነት በቦታው በነበሩ ነዋሪዎች ዘንድ ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13😢12👍4
በደቡብ ሱዳን ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ ምርመራ ጠየቀ

ትናንት ሰኞ ​በደቡብ ሱዳን በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃት ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ሮይተርስ እንደዘገበው ​የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMISS) ባወጣው መግለጫ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ሰላም አስከባሪዎቹ መደበኛ የተሽከርካሪ ጥበቃ እና ቅኝት በማድረግ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።

በዚሁ ጥቃት አሰቃቂ ድርጊት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን የገለጸው ድርጅቱ፣ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት በፍጥነት ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ እና አጣዳፊ ምርመራ እንዲደረግ ጥብቅ ጥሪ አቅርቧል።

​እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ፣ በዚህ ዓመት (2026) ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የነበሩ ዘጠኝ የሰላም አስከባሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

​ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የሰላም አስከባሪዎች ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ሲሆን፣ ድርጅቱ በአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢136👍3
የዓለም የልደት ምጣኔ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚያስፈልገው ዝቅተኛ ደረጃ በታች ወደቀ

​በዓለም ታሪክ በጦርነትም ሆነ በወረርሽኝ ወቅት አጋጥሞ የማያውቅ የልደት ምጣኔ ቅናሽ መመዝገቡን የ ZME Science ጥናት ይፋ አደረገ።

የሕዝብ ቁጥርን ሳይቀንስ በተረጋጋ ሁኔታ ለማስቀጠል በአማካይ ለአንዲት ሴት 2.1 – 2.2 ልጅ መውለድ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ አሁን ያለው መረጃ ግን ከዚያ በእጅጉ የወረደ ነው።

​እንደ አዲሱ መረጃ፣ በታይዋን 0.69፣ በደቡብ ኮሪያ 0.8፣ በሲንጋፖር 0.87 እና በቻይና 0.93 ልጅ ብቻ ይወለዳል።

በሩሲያም የልደት ምጣኔው 1.4 አካባቢ ይገኛል።

​በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለ የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ 2056 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) 9 ቢሊዮን አካባቢ ደርሶ ከፍተኛው ቦታ ላይ ይደርሳል ተብሏል።

ከዚያ በኋላ ግን ዓለም አቀፍ የሰራተኛ እጥረት የሚያጋጥም ሲሆን፣ በጡረታ እና በጤና ስርአቶች ላይ ደግሞ የገንዘብና የግብአት ጫና ከፍተኛ ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍52😢2
ቀን 20/12/2018
አስቸኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ
09 09 17 48 53/09 07 36  23 85
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉   የስራ መደብ:# NGO
👉የት/ደረጃ ዲፕሎማ / ድግሪ
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞዝ:- 40.000_50.000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/ክልል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው  መደብ =- ሀውስ ኪፒግ
👉የትምርት ደረጃ 8 +
👉የስራ ልምድ 0-3
👉ደሞዝ 7000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ሆስተስ
👉የትምርት ደረጃ 10 +
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 15000 / 20000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =-መስተግዶ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0/2
👉ጾታ ወንድ /ሴት
👉ደሞዝ ማራኪ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የስራው መደብ /ፓስታ ፋብሪካ=-የእሸጋ ሰራተኛ
👉  የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
👉ደሞዝ:-  17000
👉ፆታ:-   ወ/ሴ
👉የሰራ ቦታ  አአ/
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ስልክ ኦፕሬተር 
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/ዲፕ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 -አመት 
👉ደሞዝ ፡ 15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ሹፌር ደ/1 2 ህ/1/ሞተረኛ
👉የሰራ ልምድ :- 2-10አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 8/10/12
👉ደሞዝ:- 7000_17000
👉ፆታ :- ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ:- #ትኬተር/ለባስ/
👉የሰራ ልምድ :- 0አመት
👉የት/ት ደረጃ :- 10/12/ዲፕሎማ
👉ደሞዝ:- 0አመት
👉ደሞወዝ   :- 9000~20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሽያጭ /ለፈርኒቸር
👉የት/ደረጃ፦10/12/diploma/
👉ደሞዝ:-8000_30000+
👉የስራ ልምድ: 0አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ :markting
👉የት ደረጃ ፡- degree 
👉የስራ ልምድ ፡- 0~5 አመት
👉ደሞዝ :-13000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ Accountant
👉የት ደረጃ ፡ Degree/"Dip
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0 - 8አመት
👉ደሞዝ ፡  8,000-16,000 
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ IT
👉የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
👉የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
👉ፆታ:- ሴ/ወ
👉ደሞዝ:- 8000-15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ካሸር
👉የት/ደረጃ፦10 +
👉የሰራ ልምድ 0~3 አመት
👉ደሞዝ:- 7000-12000
👉ፆታ፦ሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#nurse//ላብራቶሪ/ጠቅላላ
👉 ለክሊኒክ እና ለሆስፒታል
👉የት/ደረጃ፦ዲፕልማ / ዲግሪ
👉የስራ ልምድ: 0~8አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉ፆታ፦ሴት/ወንድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ ቡቲክ ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ 8
👉ፆታ: ሴ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-1
👉ደሞዝ :7000-20,000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- የጥፍር እና አይላሽ
👉የትምርት ደረጃ 8+
👉የስራ ልምድ 0 -1 አመት
👉ደሞዝ 10000-25000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ=- ፀሀፊ
👉የትምርት ደረጃ ዲፕሎም
👉የስራ ልምድ ያላት
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 8000/13000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው አይነት =- ባርቴንደር
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልድ 1/3
👉ፆታ ሴት
👉ደሞዝ 10000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራው መደብ =- ብስኩት ፋብሪካ
👉የትምርት ደረጃ 8/10/12
👉የስራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ 16000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦ሼፍ ዋና / እረዳት
👉የት/ደረጃ፦ ሰርተፍኬት
👉ደሞዝ:-9000-35000
👉ፆታ፦ወንድ/ሴት
👉የስራ ልምድ ፡ 0_5አመት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ እሪል እስቴት ሴልስ
👉የት ደረጃ ፡ ዲፕ/ዲግሪ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ ፡  9000-50000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ሁለገብ ሰራተኛ
👉የደረጃ ፡- 8_10
👉የስራ ልምድ ፡- 0አመት
👉ደሞወዝ :- 10000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ reception
👉የት ደረጃ ፡ 10/12
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2
👉ደሞዝ 8000/15000
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ፦#ተላላኪና ፅዳት ለባንክ
👉የት/ደረጃ፦8/12 /ዲፕ
👉 የሰራ ልምድ 0 አመት
👉ደሞዝ:- በስምምነት
👉የስራ ቦታ: በሰፈር አቅራብያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉የስራ መደብ ፡ ጉዳይ አስፈፃሚ ፖስተኛ
👉የት ደረጃ ፡ 10/12/"Dip
👉ፆታ: ሴ/ወ
👉የስራ ልምድ ፡ 0-2አመት
👉ደሞዝ ፡  15000+
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉መረጃና መዝገበ አያያዝ 
👉 የት ደረጃ ፡ dip-degree
👉የስራ ልምድ ፡ 0_1አመት
👉ደሞዝ ፡  13500
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇
አድራሻ:-  መገናኛ ደራርቱ ህንፃ ወደ 24 በሚወስደው መንገድ  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305  👇👇👇👇👇
         ☎️ 09 07 36 23 85
         ☎️  09 09 17 48  53
     
10👍5
ኢራን የዶናልድ ትራምፕ ትንሹ ልጅን የሆነውን ባሮን ትራምፕን ለገደለ  የ10 ሚሊዮን ዶላር እከፍላለው አለች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትንሹ ልጅ የሆነውን ባሮን ትራምፕን ለመግደል የታለመ ሴራ የሚያሳይ ቪዲዮ በኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ከተሰራጨ በኋላ የአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት (Secret Service) ጉዳዩን ማጣራት ጀምሯል።

​በቴሌቪዥን የተሰራጨው ባለ 3 ደቂቃ ቪዲዮ የ20 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ እንቅስቃሴ በቅርብ እንደሚከታተል የገለፀ ሲሆን፣ እሱን ለገደለ ሰው የ10 ሚሊዮን ዶላር  የጉርሻ ክፍያ እንደተዘጋጀ ገልጿል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ኔት ሄሪንግ እንደተናገሩት፣ ኤጀንሲው ስለ ቪዲዮው መኖር የሚያውቅ ሲሆን ከደህንነት ጥበቃ ጋር በተያያዘ ስጋት የሚፈጥሩ ማናቸውንም ነገሮች ይመረምራል።

​ይህ ማስፈራሪያ የመጣው አሜሪካ እና እስራኤል በየካቲት ወር በኢራን ላይ ጥቃት ካሰነዘሩ በኋላ ሁለቱ ሀገራት በጦርነት ውስጥ ባሉበት ወቅት ነው።

የኢራን መንፈሳዊ  መሪ አያቶላ አሊ ኻመኔይ በአሜሪካ ጥቃት ከተገደሉ ወዲህ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በትራምፕ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የማስፈራሪያ መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18🤣10👍4
በናይጄሪያ የ101 ዓመቷ አያት በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ታሰሩ

​በናይጄሪያ ደቡብ ምዕራብ ክፍል በምትገኘው ግዛት ነዋሪ የሆኑ የ101 ዓመቷ ኤስተር ኦጉንማቦ የተባሉ አረጋዊት ማሪዋና (ካናቢስ) ሲሸጡ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

​የናይጄሪያ የዕፅ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (NDLEA) እንዳስታወቀው፣ አያት ኤስተር በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች በትንሽ በትንሹ የታሸገ 'ስከንክ' የተባለ የማሪዋና አይነት ሲሸጡ ተደርሶባቸዋል።

አረጋዊቷ ለፖሊስ በሰጡት ቃል፤ ቀደም ሲል የነበራቸው የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቃቸው በእሳት ከተቃጠለባቸው በኋላ ገቢ ለማግኘት ሲሉ ወደ እፅ ንግዱ መግባታቸውን ተናግረዋል።

​እንደ ኤጀንሲው ገለጻ፣ በሌጎስ የምትኖረው ሴት ልጃቸው በየአራት ቀኑ ዕፁን አዘጋጅታ የምታቀርብላቸው ሲሆን፣ እሷም ለምርመራ በቁጥጥር ስር ውላለች።

​የዕፅ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ስራ አስፈፃሚ ሞሐመድ ማርዋ አረጋዊቷን በእድሜያቸው ምክንያት በዋስ እንዲፈቱና የምክር አገልግሎት እንዲሰጣቸው አዝዘዋል።

ሆኖም በዋስ መፈታታቸው ከህጋዊ ተጠያቂነት እንደማያድናቸውና ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚችል ተገልጿል ሲል የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3🤣3😎3😢1
ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ሊቀመንበርነትን ተረከበች

ኢትዮጵያ በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን ተመረጠች። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሀገሪቱን በመወከል የሊቀመንበርነት ስልጣኑን ከማሊ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ከኮሎኔል አሳ ባዲያሎ ቱሬ መረከባቸው ተነግሯል።

በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ ላይ የተረከበው ይህ ኃላፊነት፣ አህጉራዊ የጤና ፖሊሲዎችን በመምራት ረገድ ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም የሚሰጥ ነው ተብሏል።

በዚሁ ጉባኤ የኒጀር የህዝብ ጤና እና ንፅህና ሚኒስትር ዶ/ር ጋርባ ሃኪሚ እንዲሁም የዚምባብዌ የጤና እና ህፃናት እንክብካቤ ሚኒስትር ዶ/ር ዳግላስ ሞምቦሾራ የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር በመሆን አጽድቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8
የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን  የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ!

በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር ብቻ ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ።አገልግሎቱ ባወጣው የወርሃዊ የዋጋ ንረት መረጃ፣ በሐምሌ ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ከባለፈው አመት ጋር ከነበረው 13.7 በመቶ  ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አድርጓል።  ሰኔ ወር ላይ የነበረው 14.8 በመቶ ነበር።

በዚህ ወር የምግብ ዋጋ ንረት 15.7 በመቶ ሲሆን፣ የምግብ ያልሆኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የዋጋ ንረት ደግሞ 14.8 በመቶ ደርሷል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።የዋጋ ንረቱ በ2018 ዓ.ም. መጀመሪያ ወራት ላይ በመቀነስ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ዳግም እየጨመረ የመጣ ሲሆን በመጋቢት ወር የነበረው የዋጋ ንረት ከወራት ዝቅተኛ ደረጃዎች አንዱ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ወራት ግን ጭማሪ ታይቷል።

በተለይም የምግብ ዋጋ ጭማሪ ለአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ መጨመር ዋነኛ አስተዋጽዖ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ሲሆን የምግብ ዋጋ ንረት 15.7 በመቶ መድረሱ የዋጋ ጭማሪው በቤተሰቦች የዕለት ተዕለት ወጪ ላይ ጫና መፍጠሩን ያሳያል።

ባለፈው አመት ከነበረው የዋጋ ግሽበት ከ13.7 በመቶ ጀምሮ በዓመቱ መካከል እስከ 9 በመቶ አካባቢ ዝቅ ብሎ ነበር።ይሁን እንጂ ነገር ዳግም በመጨመር በሰኔ 14.8 በመቶ እና በሐምሌ 15.3 በመቶ ደርሷል። በመሆኑም የቅርብ ወራት የዋጋ ንረት አዝማሚያ በኢትዮጵያ የእቃና የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪው እንደገና እየተፋጠነ መምጣቱን ያሳያል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5😢1