“አይፎን 15” ካልገዛችሁልኝ ያለው ወጣት ራሱን ጨምሮ የቤተሰቡን ነፍስ ቀጥፏል።
በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ዕድሜው 18 ዓመት የሆነ ወጣት አዲስ “አይፎን 15” (iPhone 15) ስልክ እንዲገዛለት ያነሳው ጥያቄ ቤተሰቦቹ ባለመቀበላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በመውጣት እራሱን ከገደል አፋፍ ላይ አቁሞ ቆይቷል።
ወላጆቹ ለሰዓታት ሲለምኑት እና ለማሳመን ሲሞክሩ ከቆዩ በኋላ አባቱ ሊያድኑት ወደ እሱ ሲጠጉ፣ ወጣቱ አባቱን ጨብጦ በመሳቡ ሁለቱም ከገደል ወድቀው ህይዎታቸው አልፏል።
ልጇን እና ባለቤቷን በድንገት ያጣችው እናቷም በደረሰባት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤ ከተመሳሳይ የገደል አፋፍ ላይ እራሷን በመጣሏ የሷም ህይወት ማለፉ ተዘግቧል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት በዛሬው ዕለት በርካቶች ሲመለከቱት፥ በወጣቶች የአዕምሮ ጤና ዙሪያ ያለውን ስጋት አጉልቶ ያሳየ ስለመሆኑ ተነግሯል።
@Addis_Reporter

😢36❤11👍3
አንድ የክርስቲያን እምነት ተከተይ የቁርዓን ውድድር አሸንፎ የዑምራ ጉዞ ተሸለመ
በግብፅ የሚኖር ሚና የተባለ የክርስቲያን እምነት ተከተይ በቁርዓን አፈጻጸም ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን አሸናፊ መሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ትኩረትስቧል።
ሚና በውድድሩ የተሳተፈው ሙና የተባለችው ሙስሊም ጎረቤቱ ለውድድሩ ስታደርግ የነበረውን ጥረት ከተመለከተ በኋላ እሷን የመርዳት እና የማበረታታት አላማ ሰንቆ እንደነበር ተገልጿል።
የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የተበረከተለትን የዑምራ (የመካ) ነፃ የጉዞ ሽልማት፣ እሱ በሃይማኖታዊ ምክንያት ሊጠቀምበት ስለማይችል ሙሉ በሙሉ ለጎረቤቱ ለሙና አበረክቶላታል።
ይህ አርአያነት ያለው የእርስ በርስ መከባበር እና የጎረቤትነት ፍቅር ድርጊት በግብፅ እና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል።

❤61🤣24👍5🎉2😎1
#እንዲታወቅ
****
ከአያት 49 ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ ላይ 72 ድልድይ አካባቢ የመንገድ ጥገና ሥራ ይካሄዳል።
በመሆኑም በተጠቀሰው ሥፍራ የሚካሄደውን የጥገና ሥራ በፍጥነት ለማከናወን፤ ከነገ ሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል።
ስለሆነም አሸከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ ማለፍና እና አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ትጠየቃላችሁ።
@ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

❤7👍4👌1
“አንዲት ጠብታ ነዳጅ በሆርሙዝ አታልፍም” ኢራን
ኢራን ጎረቤቶቿ “በአሜሪካ የኢኮኖሚ ጫና ዘመቻ ላይ ከተሳተፉ ሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ ለሙሉ እዘጋዋለሁ“ አለች።
ጎረቤት ሀገራት ከአሜሪካ ጋር ግንባር ፈጥረው ኢኮኖሚያዊ አደጋ የሚያመጡ ከሆነ “አንዲት ጠብት ነዳጅ ከፐርዢያ ባህረ ሰላጤ አያልፍም አታልፍም“ ብላለች።
አማራጭ መስመሮችን ሊጠቀሙ ቢችሉም ወታደራዊ ዕርምጃ እንደምትወስድም ኢራን ዝታለች።
ቴህራን ይህን ሀሳቧን ይፋ ያደረገችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ዋና ፀሐፊ ስኮት ቢሰንት ሀገራት አሜሪካን እንዲደግፉ እና በኢራን ላይ ብርቱ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ለመፍጠር ጥሪ ካቀረቡ በኃላ ነው ።
የዋሽንግተን አጋሮች እና ሌሎች ሀገራትም ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ራሳቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሳሰቢያ መስጠታቸው የሚዘነጋ አይደለም።
እንደቻይና ያሉ ሀገራት ደግሞ የአሜሪካን ጥሪ አንቀበለውም በሚል ውድቅ አድርገውታል።
ከቴህራን ጋር ንግድ የሚለዋወጡ ሀገራትም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዋይት ሀውስ አስጠንቅቋል።
የኢራን ከፍተኛው ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀኃላፊ ሞህሰን ረዛኢ ከአሜሪካ ጎን በምጣኔ ሀብታዊ ዘመቻው ላይ ለመሰለፉ የሚሞክሩ ሀገራት “አደብ ቢገዙ መልካም ነው “ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
የትኛወም ሀገር በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳይሳተፉ ብለዋል።
ከዋሽንግተን ጋር አብረው የሚሰሩ ካሉ ቴህራን እንደጠላት ትቆጥራቸዋለች ብለዋል ሞህሰን ረዛኢ ሲሉ አር ቲ እና አልጀዚራ አስነብበዋል።

❤13🤔8👍2🥱2
ዓመተ ምህርት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱ ተገለጸ
ዓመት ምሕረት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር እንዲቀር የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ለ4ሺሕ ጉባያተኞች ተነቦ ኮሚሽኑ በተረከበው ሰነድ፣ ዓ.ም የሚለው ቀርቶ የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱን ተመካካሪዎች ገልጸዋል። ሒጅራ እንደ ካላንደር ይካተት ተብሎ መያዙም ተገልጿል።

💔60😡33👍19❤15🥰5😢5🎉4🤪3😍2🙊2👀1
በረያ አዘቦ ከባድ የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም በራያ አዘቦ ከአላማጣ ወደ ራያ ዓዘቦ መንገድ ካራ ዓዲ ሻቦ ➡️ ሩፋኤል ➡️ ዶውኣልጋ ወደ ፀሃይ መውጫ አቅጣጫ ራያ ዓዘቦ ልዩ ስሙ #ጋሳራ በተባለ ቦታ ከባድ የድሮን ድብደባ ተፈፅሟል።
ህወሃት ከአራት ቀን በፊት ከባድ መሳሪያዎችን በቅጠል ሸፍኖ አስቀምጧቸው እንደነበር ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
Via : አዩዘሀበሻ

❤9👍8🤔1😢1🕊1🤡1
ትራምፕ ካናዳ የአሜሪካ ክፍለ ሀገር ሳትሆን የክፍለ ሀገርነት ጥቅሞችን ትፈልጋለች ሲሉ ወቀሱ
👉በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ውጥረት ተባብሷል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ዕለት በካናዳ ላይ ጠንካራ ወቀሳ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሀገሪቱ የአሜሪካ ክፍለ ሀገር ሳትሆን የክፍለ ሀገርነት ጥቅሞችን ትፈልጋለች ብለዋል።
ይህ አስተያየት የተሰጠው የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ የተሰናከለውን የንግድ ድርድር ተከተሎ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የአጸፋ ታሪፍ እንደሚጣሉ ካስታወቁ በኋላ ነው።
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ በሁለቱ የቆዩ ወዳጆች መካከል የተፈጠረው ክፍተት እየሰፋ በሄደበት ወቅት ከመጥፎ የንግድ ስምምነት ራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸው ቅዳሜ ዕለት በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ታሪፍ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል።
በጎረቤታሞቹ ሀገራት መካከል በዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረው ድርድር አርብ ዕለት ተቋርጧል። ይህም 20 ቢሊዮን ዶላር ግምት ባላቸው እና ወደ አሜሪካ ከሚላኩ የካናዳ ምርቶች ውስጥ 5.5 በመቶ ድርሻን በያዙ የካናዳ ዕቃዎች ላይ አዲሱ የአሜሪካ 50 በመቶ ታሪፍ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።
ታሪፉ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ከሆኪ እንጨት እስከ ሲሚንቶ ይገኙበታል።
ጥቃት ሲሰነዘርብህ በጦርነት ውስጥ ነህ ማለት ነው። እኛም ጥቃት ተሰንዝሮብናልሲሉ ካርኒ ተናግረዋል። ትራምፕ በማህበራዊ ገጻቸው ትሩዝ ሶሻል ላይ ባሰፈሩት መልእክት፥ ለብዙ ዓመታት በታላላቅ ገበሬዎቻችን ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ሲያስከፍሉ ቆይተዋል። ከእንግዲህ ይህ ይበቃል ብለዋል።

❤20👍2🤩1
የትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ራሳቸውን ወደ ማስተዳደር ለመሸጋገር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሃብት ዕገዳ ጣለ
በሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የተፈረመው ውሳኔ ዩኒቨርሲቲዎቹ ንብረት እንዳይሸጡ፣ በሃብታቸው እንዳይበደሩ እና ትልልቅ የኮንስትራክሽንና የግዥ ውሎችን እንዳይፈፅሙ ያግዳል።
አሰራሩ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅና የአዲሶቹ አመራሮች ስልጣን እስኪረጋገጥ ጥንቃቄ ለማድረግ የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ዕገዳው የተጣለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፡
ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ አርባ ምንጭ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ASTU) እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ናቸው።
ሚኒስቴሩ በጅማ፣ ጎንደርና AASTU የነበሩ አመራሮችን በማዛወር ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቶችን የሾመ ሲሆን፣ በቀጣይ በውድድር ለመመደብ አቅዷል።
የራስ ገዝነት ዝግጅትን ለመመዘን ከተቀመጡ አራት መስፈርቶች 60% እና ከዚያ በላይ ያመጡት እነዚህ ተቋማት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ ሙሉ ነፃነት ያገኛሉ።
ነገር ግን ባለሙያዎች የራሳቸውን ገቢ ለማሰብ የትምህርት ክፍያ ላይ ብቻ ከተደገፉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተማሪዎች እንዳይገለሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

❤27👍2🤔1
የ12ኛ ክፍል ዉጤት ሲለቀቅ በፍጥነት መረጃ ምታገኙበት እንዲሁም ውጤታችሁን ያለሰርቨር መጨናነቅ እንድታዩ የሚያግዛችሁን ቻናል አሁኑኑ ይቀላቁ!👇👇
https://t.me/addlist/dLx_2YaQlwFmNjQ8
https://t.me/addlist/dLx_2YaQlwFmNjQ8
👍3❤2🤯1
መውሊድ‼
ነገ ማክሰኞ 1,501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሀገራችን በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።
📌 የዘንድሮው መሪ ቃል፦
"የፍትሃዊው ነብይ"
በዓሉ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በተለያዩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ መርሐ-ግብሮች ይከበራል።
መውሊድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ሆነው ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው።
፡፡
ነገ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
መልካም የመውሊድ በዓል!

❤12🤣6🤪3👍2🎉2🤔1
ተጨማሪ የድሮን ጥቃት‼️
በዛሬው ዕለት በራያ አዘቦ ከተፈፀመው የድሮን ጥቃት በተጨማ በሽሬ በአዲ ገብሩ (ከአውራ ጎዳና አቅራቢያ) በሚገኘው እንዳ ባጉና ልዩ መውጫ ላይ ተፈጽሟል። በዚህ ጥቃት አንድ ወታደራዊ ተሽከርካሪ (ኦራል) እና አንድ ታንክ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮች ገልፀዋል።

👍13❤5🤪2✍1🤔1🕊1🤣1🫡1
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 125 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ሊሸጥ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቡዕ፣ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው የ27ኛው ዙር የውጭ ሀገር ገንዘብ (FX) ጨረታ ይፋ አድርጓል።
በዚህ ጨረታ ላይ 125 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ባንኮች የተዘጋጀውን መመሪያ ተከተለው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል።
የጨረታ ሰዓት: ከጠዋቱ 4:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት
የማስገቢያ መንገድ: በCSD ኤሌክትሮኒክ የሐራጅ ሥርዓት በኢሜይል
ውጤት የሚገለጽበት: በዕለቱ ከሰዓት በ9:00 ሰዓት
ክፍያና ሂሳብ ማጣሪያ : ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የሥራ ቀን ማጠቃለያ ላይ ይፈጸማል።

❤7👍2
👍2
እንድታውቁት‼️
በሀገራዊ ምከክሩ ላይ ለምክክር በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አልተደረሰም፣አልተሰጠም። እስካሁን ያለው ምክረሀሳብና አስተያየት ነው የተሰጠው። ተመካካሪዎች የተስማሙበት ሀሳብ ለብቻው ይመዘገባል፣ተቃውሞ የቀረበበት አጀንዳ ደግሞ በልዩነት ይመዘገባል።
ተመካካሪዎች በየትኛውም አጀንዳ ላይ ቢስማሙም ወይም ቢቃወሙ የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም። በሁለም አጀንዳዎች ላይ ለሀገር ይጠቅማል የሚለውን የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው እራሱ የምክክር ኮሚሽኑ መሆኑ የምክክሩ ተሳታፊዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

🤣29❤12👍3🙈3✍1👌1🥱1🤪1
የንግድ ባንክ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ለወንዶች ያደሉ መሆናቸውን ዓለም ባንክ አረጋገጠ
በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በሥራ ዕድገትና በደመወዝ ክፍያ ረገድ ለወንዶች ያደላ አሠራር መከተሉን የዓለም ባንክ አሳወቀ። ባንኩ ከ50 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የባንክ ሠራተኞች አንድ ሦስተኛውን ይይዛል። ሆኖም በውስጡ ያለው የሥራ ድልድል ፍትሐዊ እንዳልሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በባንኩ ዘርፍ በብዛት ሴቶች ቢቀጠሩም፣ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎችን መያዝ ላይ ግን ትልቅ ችግር አለ። የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በንግድ ባንክ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው ሲሆን፤ እንደ ኃላፊ ወይም ተቆጣጣሪ ያሉ የሥራ መደቦችን የማግኘት ዕድላቸውም እጅግ ጠባብ ነው።
ይህ በፆታ መካከል የሚታየው ልዩነት በትምህርት፣ በሥራ ልምድ ወይም በብቃት እጥረት የመጣ አይደለም። ባንኩ መደበኛ ደንቦች ቢኖሩትም፣ ሴቶች ከወንዶች ባነሰ ፍጥነት እንዲያድጉ የሚያደርግ አሠራር መኖሩን ሪፖርቱ አትቷል።

🤪8❤6👍6🤣4💯1
አሜሪካ የ200,000 ሰዎችን ቪዛ ልትሰርዝ ነው
የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በታሪክ ትልቁን የቪዛ ስረዛ እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።
እርምጃው በንግድ (B1) እና በቱሪዝም (B2) ቪዛ ወደ አሜሪካ ገብተው የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ወይም በመጠየቅ ላይ ያሉ እስከ 200,000 የሚደርሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን ዓላማ ያደረገ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ከ2016 እስከ 2026 የተሰጡ ቪዛዎችን ለመሰረዝ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንደተናገሩት፣ እርምጃው ለአጭር ጊዜ ጉብኝት መጥተው ቪዛውን ለቋሚ መኖሪያነት የተጠቀሙበትን ለመቆጣጠር ታስቦ የተወሰደ ነው።
ይህ የቪዛ ስረዛ ሰዎች ወዲያውኑ ከሀገር እንዲወጡ ባያደርግም፣ ህጋዊ የጉዞ ሁኔታቸውን የሚያሳጣ በመሆኑ ከፍተኛ የህግ ክስና ተቃውሞ እንደሚገጥመው ይገመታል።
የትራምፕ አስተዳደር ከዚህ ቀደምም በቪዛ አመልካቾች ላይ በርካታ ጠንካራ ገደቦችን ሲጥል መቆየቱ ይታወቃል።

❤8👍6👀2
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤
እንኳን ለ1501 ኛው የነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
እንኳን ለ1501 ኛው የነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤16👍6
የድሮን ጥቃት ተፈፀመ
በትግራይ ክልል በምስራቅ ዞን አፅቢ ወረዳ በፈለገ ወይኒ ጣቢያ፣ መብራህቶም በሚባል ቀጠና ልዩ ስሙ « በሊጋ» በተባለው ስፍራ በሚገኘው የሱር ኮንስትራክሽን ካምፕ ላይ ትናንት ነሐሴ 18 ከለሊቱ 7:30 አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በሱር ኮንስትራክሽን ካምፕ ላይ ሲሆን በካምፑ ውስጥ የጦር መሳሪያ ክምችት መኖሩ ተዘግቧል።
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም

❤14👍6🤔3😢1
ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ አቅንተው ነበር‼️
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሶጉን ኦባሳንጆ ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ መቐለ አቅንተው ነበር።
ከዚህ በመነሳት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ውይይት የሚጀመር ከሆነ፣ የሚከተሉት ጉዳዮች መመለስ መሠረታዊና ቁልፍ እንደሆኑ ህወሓት አጽንኦት ሰጥቷዋል፦
* የኢኮኖሚ ማዕቀብና እገዳ መነሳት፤
* ወታደራዊ ከበባ ማቆምና የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብ፤
* የትግራይ ሉዓላዊ ግዛት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለስ፤
* ተፈናቃዮችን ደህንነታቸውና ክብራቸው በተጠበቀ መንገድ መመለስ፤
* የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ፖለቲካዊና ሕጋዊ ማንነት መመለስ።የሚሉ ናቸው።
በዚህም ኦሊሶጉን ኦባሳንጆ ከመንግሥት ጋር ተወያይቼ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ሳምንታት ድጋሚ እመለሳለሁ”ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

👍13❤8🤔2
የ12ኛ ክፍል ዉጤት ሲለቀቅ በፍጥነት መረጃ ምታገኙበት እንዲሁም ውጤታችሁን ያለሰርቨር መጨናነቅ እንድታዩ የሚያግዛችሁን ቻናል አሁኑኑ ይቀላቀሉ! 👇
https://t.me/addlist/dLx_2YaQlwFmNjQ8
https://t.me/addlist/dLx_2YaQlwFmNjQ8
😡10🤣4❤3