አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ወለጋ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ከትላንት በስተያ ረቡዕ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ኦዲተርን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። በጥቃቱ የአዋሽ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ኦዲተር ለሚ መንግሥቱ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ማሙሽ ማሩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በወረዳው ቱሉ ሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ "መቀ ለሊ" በተባለ ሥፍራ ጸጥታ ኃይሎች ከባንኮቹ የተሠበሠበ ጥሬ ብር በተሽከርካሪ አጅበው በመጓዝ ላይ ሳሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ሰሞኑን በዞኑ አንገር ጉቴ ከተማ ተፈጽሞ የነበረውን ጥቃት በመሸሽ ነቀምት ከተማ ቆይተው ወደ ቀያቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ነዋሪዎችን ጭምር ከመኪና በማስውረድ  መግደላቸውንና ቀሪዎችን አፍነው መውሠዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢2418👍12🤪3🙉3🕊1
የአዲስ አበባ ጉዳይ‼️
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው 300 ያህል የኦሮሚያ ክልል ተመካካሪዎች፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ መኾኗን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ በሕገመንግሥቱ ይካተት የሚለው ጥያቄያችን አማራጭ የሌለው ምክረ ሀሳብ ኾኖ ካልተያዘ ከጉባኤው እንወጣለን በማለት ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል። የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንም፣ የጋራ ማረጋገጫ ቡድኑ ያመሳከራቸውን ምክረ ሀሳቦች ከማቅረቡ በፊት ስብሰባ ያልጠራውን የክልል ተወካዮች ጉባኤ ትናንት ሰብስቦ የኦሮሚያ ተመካካሪዎችን ቅሬታ አቅርቧል። የክልል ተወካዮች ጉባኤ፣ ቅሬታውን መርምሮ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ የ11 ክልሎች ፕሬዝዳንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ሦስት የትግራይ ተወካዮች፣ አምስት የሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት የወጣቶች ተወካዮች የተካተቱበት ኮሚቴ አቋቁሟል።

ኾኖም በርካታ ተመካካሪዎች፣ የኦሮሚያ ተመካካሪዎች ቅሬታ ከምክክር ሂደቱ የወጣና ሂደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ነው የሚል ተቃውሞ አሠምተዋል ተብሏል። ለሥራ ቡድኖች ከቀረቡት 476 ምክረ ሀሳቦች ውጭ አዲስ የሚጨመር ወይም የሚቀነስ ምክረ ሀሳብ ካለ፣ ራሳቸውን ከጉባኤው ለማግለል የወሠኑ ተመካካሪዎች መኖራቸውም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የምክክር ጉባኤው በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የተጠናቀሩትን የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች በማዳመጥ ላይ መኾኑን ዛሬ ነሐሴ 15 ማምሻውን ገልጧል። የምክክር ጉባኤው የተጠራው፣ የኦሮሚያ ተወካዮችን ቅሬታ ይመረምራል የተባለው የክልል ተወካዮች ገባኤ ምን መፍትሄ አቅርቦ እንደኾነ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2622😢4👍3
ከቤተሰብ 850 ሺህ ብር ለማግኘት ሳትታገት ታግቻለሁ ያለችው ተጠርጣሪና ተባባሪዋ ተያዙ

ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ራሄል መለሰ የተባለች ወጣት ከቤት ወጥታ ባለመመለሷ ቤተሰቦቿ ለፖሊስ ያመለክታሉ። 

ፖሊስ ፍለጋ እያደረገ ባለበት ሰዓት ለአባቷ ስልክ ተደውሎ «ልጅቷን  አግተናል፤ እንድትለቀቅ 850 ሺህ ብር ላኩ» የሚል ማስፈራሪያ ደረሰ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል የታገተችው የተባለችው ወጣት በባህር ዳር ከተማ ስማዳ አካባቢ ከሰለሞን ቁምላቸው ከተባለ ወንድ ጋር ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር ውላለች። 

በምርመራውም ግለሰቦቹ የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው፣ ከሀገር ለመውጣት አስበው 850 ሺህ ብር ከቤተሰቦቿ ለመቀበል ሲሉ የሠሩት የእገታ ድራማ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ የምርመራ ስራውን መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች እየታዩ በመምጣታቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ  አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🙉8🤔5👍4
አለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታውን ይስበር-ህወሓት‼️
'ህወሃት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዝምታ ወጥቶ የፌደራል መንግሥቱ የሚፈፅመውን የድሮን ጥቃት እንዲያወግዝ እና እንዲያደራደር ጥሪ አቀረበ።
ህወሃት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን የድሮን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ያለ ሲሆን ነገር ግን ሁኔታውን ላለማባባስና ቀጠናውን ወደ ሌላ ጦርነት ላለመውሰድ ለጥቃቱ ወታደራዊ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበናል ብሏል።
ህወሃት አሁንም ቢሆን ለሰላም እና ድርድር ያለው አቋም አልተለወጠም፣ነገር ግን ትዕግስትም ልክ አለው፣ትዕግስት እንደፍርሃት መቆጠር የለበትም፣ትግራይን ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን' ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3410👍5🤪3🤔1🤡1👀1🙈1
ከንቲባው በሳይክል ስለተገጩ ሳይክል ከለከሉ‼️
በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሳይክል የተገጩት የጣልያኗ ኮሞ ከተማ ከንቲባ ከእንግዲህ በከተማዋ ሳይክል እንዳይነዳ ማገዳቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ከንቲባ አሌሳንድሮ ራፒንስ ጅምላ እገዳው የተጣለው የከተማዋና ሕዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል። በከንቲባው ውሳኔ መሰረት ከቀናት በኋላ በአነስተኛ ከተማዋ 30 ጐዳናዎች ላይ ሳይክል ጋላቢዎች ዝር እንዲሉ አይፈቀድላቸውም።

ከንቲባ ራፒንስ ለጣልያን ዜና አገልግሎት እንደነገሩት ሰዎች ከልምዳቸው ተነስተው ነው ውሳኔ የሚሰጡት እኔም በእነዚህ አውሬ ሳይክሎች የደረሰብኝን አውቀዋለሁ ብለዋል።

በሌላ በኩል በርካታ የአውሮፓ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሳይክሎች የትና እንዴት እንደሚጋለቡ የሚወስን ድንጋጌ ያወጡ ሲሆን በሌላ በኩል ሰዎች በእግራቸው የሚያሽከረክሯቸው ሳይክሎች ግን እገዳ አልተጣለባቸውም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣276👍3
ኢትዮጵያ በኬንያ ለሚገነባው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለድርሻ ለመሆን ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ።

አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ አካባቢ ለመገንባት ላቀዱትና በቀን 700,000 በርመል ነዳጅ የማጣራት አቅም ለሚኖረው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከቀረበው የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ላይ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቷ ተገልጿል።

ይህንን የገለጹት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ ዴቪድ ንዲ በናይሮቢ በተካሄደ የካፒታል ማርኬት መድረክ ላይ እንደሆነ ነው ብሉምበርግ የዘገበው።

አማካሪው ከዚህ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መቅረቡን ነው የገለጹት።

አክለውም፥ ኬንያ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የ10 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷንና ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳም በፕሮጀክቱ ላይ የባለቤትነት ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን በመድረኩ ተናግረዋል።

እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል ተብሎ የሚገመተው ይህ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ አጠቃላይ ወጪው 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።

የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐግብሩ መስከረም ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣207👍6👌1
ነገ ቅዳሜ በመቀሌ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሽንዳ ዓመታዊ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሠረዘ።

የአሸንዳ በዓል ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት የተሠረዘው፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄደው የድሮን ጥቃት ሳቢያ መኾኑን የትግራይ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጧል።

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አንቂዎች፣ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸመሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመቃወም ሴቶች በዓሉን ጥቁር በመልበስና "ጥቁር አሸንዳ" በሚል መሪ ቃል እንዲያከብሩት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር።

ይህንኑ ተከትሎ፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ከመደበኛው ባሕላዊ ስነ ሥርዓት ውጪ ሌላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ሲል ሰሞኑን ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5🤣3🤔1😢1
ኢትዮጵያ ግብፅ የጀመረችዉን ዘመቻ አጥብቃ ተቃወመች

ኢትዮጵያ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በዓባይ ወንዝ ልማት ላይ ያላትን አቋም ለማዛባት ግብፅ በድጋሚ የጀመረችውን ዘመቻ አጥብቃ መቃወሟን የተለያዩ የዉጭ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

መገናኛ ብዙሃኑ ይፋእንዳደረጉት ኢትዮጵያ  የዓባይ ወንዝን የመጠቀም መብቷ፤ በሉዓላዊ የልማት መብት እና ለክልሉ የጋራ ተጠቃሚነት ባላት ዓላማ ላይ የተመሰረተ መሆኑን መንግስት አስታውቋል። በአፍሪቃ ረጅሙ ወንዝ  ዓባይ፣ በ 11 ሀገራትን አቋርጦ በግብፅ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር የሚቀላቀል ነው።

በዚህ ወንዝ ላይ በሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል  አለመግባባት በመፍጠር ውዝግቡ ከአስር ዓመታት በላይ ዘልቋል።

የኢትዮጵያዉ የሕዳሴ ግድብ  የሚገኘው የግድቡ ግንባታ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ  2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ በይፋ የተመረቀው ደግሞ በጎርጎሪያኑ መስከረም 2025 መሆኑ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8😡2
የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፣ በተለያዩ የሙያ መደቦች ለሚቀጠሩ የውጭ ዜጎች ዝቅተኛው ወርሃዊ ደመወዝ አራት ሺሕ ድርሃም ወይም 1 ሺሕ 80 ዶላር ገደማ እንዲኾን ወሠነች።

የአገሪቱ መንግሥት የውጭ ዜጎች የሚሠማሩባቸውን ሁሉንም የሙያ መስኮች በዘጠኝ መደቦች ደልድሏቸዋል።

የውጭ ዜጎች የሚቀጠሩባቸው የሙያ ዘርፎች በዘጠኝ መደቦች የተከፈሉት፣ የዓለም የሥራ ድርጅትን የሙያ ደረጃ መስፈርቶች መሠረት በማድረግ መሆኑን የአገሪቱ መንግሥት ገልጧል።

ከዘጠኙ የሙያ መደቦች መካከል፣ ከድርጅት ማናጀርነት፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከግብርና፣ ከአገልግሎትና ሽያጭ እና ከማዕድን ዘርፍ ጋር የተያያዙ ምድቦች ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ ከቤት ሠራተኞች በተጨማሪ በቅርቡ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የሠለጠኑ ባለሙያዎችን ወደ ኢምሬቶች መላክ መጀመሯ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍3🌚1
የትራምፕ ቪዛ እገዳ በፍርድ ቤት ተሻረ

የኒውዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ75 ሀገራት በሚመጡ ዜጎች ላይ ጥሎት የነበረውን የኢሚግሬሽን ቪዛ እገዳ ውድቅ አደረገ።
​የፍርድ ቤቱ ዳኛ ጄኔት ቫርጋስ በሰጡት ውሳኔ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሳለፈው ይህ እገዳ "በግልጽ ህገ-ወጥ" እና ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ስልጣን ውጭ ነው ብለዋል።

ውሳኔው በዜግነት ላይ የተመሰረተ መድልዎ በመሆኑ ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ህግ ጋር እንደሚጋጭም ገልጸዋል።
​እገዳው ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ የመጡ የቪዛ አመልካቾችን የጎዳ ሲሆን፣ የትራምፕ አስተዳደር አመልካቾቹ "በመንግስት ላይ ጥገኛ የመሆን ስጋት አለባቸው" የሚል ምክንያት አቅርቦ ነበር።

​ክሱን የመሰረቱት የኢሚግሬሽን መብት ተሟጋች ድርጅቶች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መደሰታቸውን ሲገልጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍189🤯2🙏1👌1
የኢሚግሬሽን አገልግሎት "በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር" ማህተም ያልተረጋገጡ ሰነዶችን እንደማይቀበል አስታወቀ‼️

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት፤ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከትግራይ ክልል የሚመጡ ዜጎች የሚያቀርቡት ሰነድ በክልሉ "ጊዜያዊ አስተዳደር" የተረጋገጠ ካልሆነ አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

📌 የውሳኔው ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች፦ የልደት ካርድ፣ የመታወቂያ እና ሌሎችም ለፓስፖርት ማውጫነት የሚያገለግሉ ሰነዶች በሙሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ማህተም እና 'ሄዲንግ' (Heading) ያረፈባቸው መሆን አለባቸው።

ውድቅ የተደረጉ ሰነዶች፦ "የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት" በሚል ሄዲንግ እና ማህተም የተሰጡ ማንኛቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

የውሳኔው ምክንያት፦ የፌደራል መንግስቱ "የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት" የሚለውን አጠራር ስለማይቀበለው እና እውቅና ስለማይሰጠው፤ እነዚህን ህገወጥ ማህተሞች የያዙ ሰነዶችን ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች ተቋሙ አገልግሎት መስጠት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢65👍3
ከሀገሬ መቼም አልሸሽም-ኮሚሽነሩ‼️
ከሀገሬ አለሸሸሁም፣መቼም አልሸሽም፣ወደ አሜሪካ የሄድኩት በሀዘን ምክንያት ለቀብር ስነስርዓት ነው-የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ።
በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች ኮሚሽነሩ ከአገር እንደሸሹ ሲወራ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤣8🙉7👍4
ውጤት ዛሬ ይለቀቃል‼️
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን ፈተናውን ወስደዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች ተሰጥቷል።

ከዘንድሮ ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 257 ሺህ 45 ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ውጤቱን በተመለከትም ትምህርት ሚኒስቴር በ9 ሰዓት መግለጫ ይሰጣል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21😱4👍3🤔2🙏1👌1🤪1
#MoE : ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪96👍41🙏1
#የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️

ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።

ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍64🤪3😢2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
#የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️ ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው። ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው። በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።…
የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና ዋና መረጃዎች‼️

📊 የማለፊያ ውጤት
• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።
• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።
• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

🏫 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88
➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።

💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ
• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።

🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ
🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2%
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።

🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ
• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት
• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት
• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት

📌 በአጠቃላይ፦ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል። በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍5🤣5💔2
ውጤት መቼ ይታያል

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
የውጤት ማሳያ ሊንኮችን በዚሁ ቻናል የምናጋራ ይሆናል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪6👍3🙏2😢1🤡1😡1
ጄኔራል ባጫ ደበሌ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው‼️
በኬኒያ አምባሳደር በመሆን የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁት አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ የክብር ሽኝት ሥነ-ሥርዓት በናይሮቢ ተካሂዷል።
ጄኔራሉ በፌደራል መንግስቱ ለአንድ ከፍተኛ ስልጣን እንደታጩ ታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2113👍3🤪3🤔2🎉2🤷‍♂1
ተጠናቀቀ‼️ደሴጅማደብረ ማርቆስ
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ የፍጥነት መንገዶች የአዋጭነት ጥናት ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ የመንገድ መረብ ባለፉት 8 ዓመታት በ53,000 ኪ.ሜ ማደጉን እና በቀጣይ 5 ዓመታት 245,000 ኪ.ሜ ለማድረስ ዕቅድ መያዙን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሀገሪቱን የፍጥነት መንገዶች ርዝመት ወደ 1,600 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ ታቅዶ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶች የአዋጭነት ጥናት መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቁልፍ መረጃዎች፦

🛣 የመንገድ እድገት፦ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 126,773 ኪ.ሜ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180,232 ኪ.ሜ አድጓል፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት +53,000 ኪ.ሜ አዲስ መንገድ ተገንብቷል።

🚗 የፍጥነት መንገዶች፦ ከ2010 ዓ.ም በፊት የነበረው ሽፋን 84.7 ኪ.ሜ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ እና ድሬዳዋ-ደዋሌ አዳዲስ የፍጥነት መንገዶች (+450 ኪ.ሜ.) ተገንብተዋል፡፡

🏗 የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፦ ባለፉት 8 ዓመታት 182 ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ የገቡ ሲሆን 71 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🌚7👍61👌1🤪1🙉1