አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ቀን 15/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
7👍2
የኢትዮጵያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የመመንዘር አቅሙ በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱና ሀገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገለፀ።

ብሉምበርግ የዜና ምንጭ ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገበያ ለማረጋጋትና የብርን እሴት ለመደገፍ ብሔራዊ ባንኩ ከፍተኛ መጠን ያለው የዶላር ክምችት ስራ ላይ ያዋለ ቢሆንም የብር የመግዛት አቅም ግን ታሪካዊ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ወርዷል።

ይህ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የታየው ተጽዕኖ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትና በዜጎች የእለት ተእለት የኑሮ ውድነት ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል የሚል ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔና በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የሚወሰዱ ቀጣይ እርምጃዎች የአለምአቀፉን የፋይናንስ ማህበረሰብ ትኩረት ስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢176👍1👀1
አሜሪካ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን ለኳታር ልትሸጥ መሆኑን አጸደቀች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ አራት የሚደርሱ «KC-46A» የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን እና ተዛማጅ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በ4.5 ቢሊዮን ዶላር ለኳታር ለመሸጥ የቀረበውን እቅድ ማፅደቁን አስታወቀ።

ሽያጩ ስምንት «PW4062» ተርቦፋን ሞተሮችን  የሬዳር ማስጠንቀቂያ ተቀባዮችን  የሌዘር አስተላላፊዎችን  እና ሌሎች አቪዬሽን ነክ መሳሪያዎችን ያካትታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ይህ ሽያጭ ኳታር በቀጠናው ደህንነት መጠበቅ ላይ የምታደርገውን ሚና የሚያጠናክር ሲሆን «በቀጠናው ያለውን መሰረታዊ የወታደራዊ ኃይል ሚዛን  አይቀይረውም» ብሏል።

የ«KC-46A» አውሮፕላኖች የኳታር አየር ኃይል የጦር ጄቶቹ በአየር ላይ እያሉ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የረጅም ርቀት ወታደራዊ ስምሪት የማድረግ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉለት ተጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8🤪43
«ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አያስፈልጋትም!»

ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን የመጠቀም እና የማልማት ሉዓላዊ መብት ስላላት ከማንም አካል ፈቃድ መጠየቅ እንደማያስፈልጋት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኃይል ማመንጨት ብቻ የተገነባና ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ግብይትን በማስፋት ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ሀብት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ባላት ግምት ከግድቡ በታች ሊለሙ የሚችሉ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ የመስኖ መሬቶችን ከመስኖ ልማት ውጪ ማድረጓንም አክለው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ሕዳሴ ግድብን በጋራ ለማስተዳደር የሚቀርቡ ጥሪዎችን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ የተገነባውንና የብሔራዊ ክብር ምልክት የሆነውን ግድብ ግንባታውን ሲቃወም የነበረ አካል መጥቶ «በጋራ እናስተዳድር» ማለቱ ፈጽሞ የማይቻል እና ሊታሰብ የማይችል መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት የኢትዮጵያን የልማት መብት ለመገደብ ከመጣር ይልቅ በውይይት እና በጋራ ትብብር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የቤት ኪራይ
በሐዋሳ የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉ ተገለጸ ።

በሐዋሳ ከተማ በቅርብ ጊዜ የታየው ያልተጠበቀ የቤት ኪራይ ዋጋ ንረት በነዋሪዎች ላይ የከፋ የኑሮ ጫና እና እንግልት እየፈጠረ ይገኛል። በርካታ አከራዮች ቀደም ሲል ይጠይቁት ከነበረው ዋጋ በእጥፍ እና ከዚያም በላይ በመጨመራቸው፣ በተለይም በወር ደመወዝ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፈተና ተዳርገዋል።

ይህ የኪራይ ዋጋ ንረት ዋነኛ ምክንያት ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከቤት ንብረታቸው የተነሱ በርካታ ዜጎች በአንድ ጊዜ ወደ ኪራይ ገበያው መግባታቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ አከራዮችም ይህንን የመኖሪያ ቤት እጥረት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ዋጋውን እንዲሰቅሉት አድርጎታል። በዚህም ምክንያት ቤት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ማግኘት ሲቸገሩ፣ ያገኙትም ቢሆኑ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ክፍያ ለመክፈል ተገደዋል።

ከዚሁ ከልማት ተነሾች ጋር ተያይዞ መንግሥት በተለይ ከመንግሥት ቤት ለሚነሱ ነዋሪዎች ቀድሞ ምትክና ማረፊያ አዘጋጅቶ ማንሳት ሲገባው፣ በቂ ዝግጅት ሳያደርግ ሰዎችን ከቤት በማስወጣቱ ለተጨማሪ እንግልት ዳርጓቸዋል። የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ከተጀመረ አሁኑ አንድ ዓመት ገደማ እየሆነው ቢሆንም፣ እስከ ዛሬ ድረስ ከቤታቸው ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ምትክ ቤት ተሠርቶ አልተረከበም።

በተጨማሪም ምትክ ማቅረብ በማይቻልበት ሁኔታ ለቤት ኪራይ የሚከፈለው ክፍያ የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው ተብሏል። ለአነስተኛ ቤተሰብ በሐዋሳ የሚከፈለው የቤት ኪራይ ድጎማ በወር ከ4,000 እስከ 7,000 ብር ብቻ በመሆኑ ከወቅቱ የኪራይ ገበያ ጋር በፍጹም የማይመጣጠን ሲሆን፣ በአንፃሩ እንደ ይርጋለም ባሉ አቅራቢያ ከተሞች ለተነሾች ከ10,000 ብር በላይ ክፍያ እየተፈጸመ ማቆየት መቻሉ በሐዋሳ ያለውን ክፍተት አጉልቶ አሳይቷል።

በመሆኑም ነዋሪዎቹ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደርና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በጉዳዩ ላይ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። ችግሩ የግል አከራይና ተከራይ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኑሮ ውድነትን የሚያባብስ በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ተተግሮ እንደነበረው ሁሉ አከራይና ተከራይን በሕጋዊ ውል የሚያስተዳድርና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን የሚያስቀር ሕጋዊ የአሠራር ማዕቀፍ በሐዋሳም እንዲዘረጋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13😢4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
5👍2
ወለጋ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ከትላንት በስተያ ረቡዕ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ኦዲተርን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። በጥቃቱ የአዋሽ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ኦዲተር ለሚ መንግሥቱ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ማሙሽ ማሩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በወረዳው ቱሉ ሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ "መቀ ለሊ" በተባለ ሥፍራ ጸጥታ ኃይሎች ከባንኮቹ የተሠበሠበ ጥሬ ብር በተሽከርካሪ አጅበው በመጓዝ ላይ ሳሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ሰሞኑን በዞኑ አንገር ጉቴ ከተማ ተፈጽሞ የነበረውን ጥቃት በመሸሽ ነቀምት ከተማ ቆይተው ወደ ቀያቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ነዋሪዎችን ጭምር ከመኪና በማስውረድ  መግደላቸውንና ቀሪዎችን አፍነው መውሠዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢2418👍12🤪3🙉3🕊1
የአዲስ አበባ ጉዳይ‼️
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው 300 ያህል የኦሮሚያ ክልል ተመካካሪዎች፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ መኾኗን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ በሕገመንግሥቱ ይካተት የሚለው ጥያቄያችን አማራጭ የሌለው ምክረ ሀሳብ ኾኖ ካልተያዘ ከጉባኤው እንወጣለን በማለት ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል። የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንም፣ የጋራ ማረጋገጫ ቡድኑ ያመሳከራቸውን ምክረ ሀሳቦች ከማቅረቡ በፊት ስብሰባ ያልጠራውን የክልል ተወካዮች ጉባኤ ትናንት ሰብስቦ የኦሮሚያ ተመካካሪዎችን ቅሬታ አቅርቧል። የክልል ተወካዮች ጉባኤ፣ ቅሬታውን መርምሮ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ የ11 ክልሎች ፕሬዝዳንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ሦስት የትግራይ ተወካዮች፣ አምስት የሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት የወጣቶች ተወካዮች የተካተቱበት ኮሚቴ አቋቁሟል።

ኾኖም በርካታ ተመካካሪዎች፣ የኦሮሚያ ተመካካሪዎች ቅሬታ ከምክክር ሂደቱ የወጣና ሂደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ነው የሚል ተቃውሞ አሠምተዋል ተብሏል። ለሥራ ቡድኖች ከቀረቡት 476 ምክረ ሀሳቦች ውጭ አዲስ የሚጨመር ወይም የሚቀነስ ምክረ ሀሳብ ካለ፣ ራሳቸውን ከጉባኤው ለማግለል የወሠኑ ተመካካሪዎች መኖራቸውም ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የምክክር ጉባኤው በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የተጠናቀሩትን የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች በማዳመጥ ላይ መኾኑን ዛሬ ነሐሴ 15 ማምሻውን ገልጧል። የምክክር ጉባኤው የተጠራው፣ የኦሮሚያ ተወካዮችን ቅሬታ ይመረምራል የተባለው የክልል ተወካዮች ገባኤ ምን መፍትሄ አቅርቦ እንደኾነ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2623😢4👍3
ከቤተሰብ 850 ሺህ ብር ለማግኘት ሳትታገት ታግቻለሁ ያለችው ተጠርጣሪና ተባባሪዋ ተያዙ

ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ራሄል መለሰ የተባለች ወጣት ከቤት ወጥታ ባለመመለሷ ቤተሰቦቿ ለፖሊስ ያመለክታሉ። 

ፖሊስ ፍለጋ እያደረገ ባለበት ሰዓት ለአባቷ ስልክ ተደውሎ «ልጅቷን  አግተናል፤ እንድትለቀቅ 850 ሺህ ብር ላኩ» የሚል ማስፈራሪያ ደረሰ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል የታገተችው የተባለችው ወጣት በባህር ዳር ከተማ ስማዳ አካባቢ ከሰለሞን ቁምላቸው ከተባለ ወንድ ጋር ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር ውላለች። 

በምርመራውም ግለሰቦቹ የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው፣ ከሀገር ለመውጣት አስበው 850 ሺህ ብር ከቤተሰቦቿ ለመቀበል ሲሉ የሠሩት የእገታ ድራማ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ የምርመራ ስራውን መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች እየታዩ በመምጣታቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ  አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🙉8🤔5👍4
አለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታውን ይስበር-ህወሓት‼️
'ህወሃት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዝምታ ወጥቶ የፌደራል መንግሥቱ የሚፈፅመውን የድሮን ጥቃት እንዲያወግዝ እና እንዲያደራደር ጥሪ አቀረበ።
ህወሃት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን የድሮን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ያለ ሲሆን ነገር ግን ሁኔታውን ላለማባባስና ቀጠናውን ወደ ሌላ ጦርነት ላለመውሰድ ለጥቃቱ ወታደራዊ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበናል ብሏል።
ህወሃት አሁንም ቢሆን ለሰላም እና ድርድር ያለው አቋም አልተለወጠም፣ነገር ግን ትዕግስትም ልክ አለው፣ትዕግስት እንደፍርሃት መቆጠር የለበትም፣ትግራይን ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን' ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3611👍5🤪3🤔1🤡1👀1🙈1
ከንቲባው በሳይክል ስለተገጩ ሳይክል ከለከሉ‼️
በኤሌክትሪክ የሚሰራ ሳይክል የተገጩት የጣልያኗ ኮሞ ከተማ ከንቲባ ከእንግዲህ በከተማዋ ሳይክል እንዳይነዳ ማገዳቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ከንቲባ አሌሳንድሮ ራፒንስ ጅምላ እገዳው የተጣለው የከተማዋና ሕዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል። በከንቲባው ውሳኔ መሰረት ከቀናት በኋላ በአነስተኛ ከተማዋ 30 ጐዳናዎች ላይ ሳይክል ጋላቢዎች ዝር እንዲሉ አይፈቀድላቸውም።

ከንቲባ ራፒንስ ለጣልያን ዜና አገልግሎት እንደነገሩት ሰዎች ከልምዳቸው ተነስተው ነው ውሳኔ የሚሰጡት እኔም በእነዚህ አውሬ ሳይክሎች የደረሰብኝን አውቀዋለሁ ብለዋል።

በሌላ በኩል በርካታ የአውሮፓ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሳይክሎች የትና እንዴት እንደሚጋለቡ የሚወስን ድንጋጌ ያወጡ ሲሆን በሌላ በኩል ሰዎች በእግራቸው የሚያሽከረክሯቸው ሳይክሎች ግን እገዳ አልተጣለባቸውም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣276👍3
ኢትዮጵያ በኬንያ ለሚገነባው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለድርሻ ለመሆን ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ።

አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ አካባቢ ለመገንባት ላቀዱትና በቀን 700,000 በርመል ነዳጅ የማጣራት አቅም ለሚኖረው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከቀረበው የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ላይ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቷ ተገልጿል።

ይህንን የገለጹት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ ዴቪድ ንዲ በናይሮቢ በተካሄደ የካፒታል ማርኬት መድረክ ላይ እንደሆነ ነው ብሉምበርግ የዘገበው።

አማካሪው ከዚህ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መቅረቡን ነው የገለጹት።

አክለውም፥ ኬንያ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የ10 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷንና ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳም በፕሮጀክቱ ላይ የባለቤትነት ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን በመድረኩ ተናግረዋል።

እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል ተብሎ የሚገመተው ይህ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ አጠቃላይ ወጪው 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።

የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐግብሩ መስከረም ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣207👍6👌1
ነገ ቅዳሜ በመቀሌ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የአሽንዳ ዓመታዊ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሠረዘ።

የአሸንዳ በዓል ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት የተሠረዘው፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄደው የድሮን ጥቃት ሳቢያ መኾኑን የትግራይ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጧል።

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አንቂዎች፣ በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸመሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመቃወም ሴቶች በዓሉን ጥቁር በመልበስና "ጥቁር አሸንዳ" በሚል መሪ ቃል እንዲያከብሩት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር።

ይህንኑ ተከትሎ፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ከመደበኛው ባሕላዊ ስነ ሥርዓት ውጪ ሌላ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም ሲል ሰሞኑን ማስጠንቀቂያ አውጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5🤣3🤔1😢1
ኢትዮጵያ ግብፅ የጀመረችዉን ዘመቻ አጥብቃ ተቃወመች

ኢትዮጵያ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በዓባይ ወንዝ ልማት ላይ ያላትን አቋም ለማዛባት ግብፅ በድጋሚ የጀመረችውን ዘመቻ አጥብቃ መቃወሟን የተለያዩ የዉጭ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።

መገናኛ ብዙሃኑ ይፋእንዳደረጉት ኢትዮጵያ  የዓባይ ወንዝን የመጠቀም መብቷ፤ በሉዓላዊ የልማት መብት እና ለክልሉ የጋራ ተጠቃሚነት ባላት ዓላማ ላይ የተመሰረተ መሆኑን መንግስት አስታውቋል። በአፍሪቃ ረጅሙ ወንዝ  ዓባይ፣ በ 11 ሀገራትን አቋርጦ በግብፅ በኩል ወደ ሜዲትራኒያን ባህር የሚቀላቀል ነው።

በዚህ ወንዝ ላይ በሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል  አለመግባባት በመፍጠር ውዝግቡ ከአስር ዓመታት በላይ ዘልቋል።

የኢትዮጵያዉ የሕዳሴ ግድብ  የሚገኘው የግድቡ ግንባታ በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ  2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ በይፋ የተመረቀው ደግሞ በጎርጎሪያኑ መስከረም 2025 መሆኑ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8😡2
የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፣ በተለያዩ የሙያ መደቦች ለሚቀጠሩ የውጭ ዜጎች ዝቅተኛው ወርሃዊ ደመወዝ አራት ሺሕ ድርሃም ወይም 1 ሺሕ 80 ዶላር ገደማ እንዲኾን ወሠነች።

የአገሪቱ መንግሥት የውጭ ዜጎች የሚሠማሩባቸውን ሁሉንም የሙያ መስኮች በዘጠኝ መደቦች ደልድሏቸዋል።

የውጭ ዜጎች የሚቀጠሩባቸው የሙያ ዘርፎች በዘጠኝ መደቦች የተከፈሉት፣ የዓለም የሥራ ድርጅትን የሙያ ደረጃ መስፈርቶች መሠረት በማድረግ መሆኑን የአገሪቱ መንግሥት ገልጧል።

ከዘጠኙ የሙያ መደቦች መካከል፣ ከድርጅት ማናጀርነት፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከግብርና፣ ከአገልግሎትና ሽያጭ እና ከማዕድን ዘርፍ ጋር የተያያዙ ምድቦች ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ ከቤት ሠራተኞች በተጨማሪ በቅርቡ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የሠለጠኑ ባለሙያዎችን ወደ ኢምሬቶች መላክ መጀመሯ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👍3🌚1
የትራምፕ ቪዛ እገዳ በፍርድ ቤት ተሻረ

የኒውዮርክ የፌደራል ፍርድ ቤት፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ75 ሀገራት በሚመጡ ዜጎች ላይ ጥሎት የነበረውን የኢሚግሬሽን ቪዛ እገዳ ውድቅ አደረገ።
​የፍርድ ቤቱ ዳኛ ጄኔት ቫርጋስ በሰጡት ውሳኔ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያሳለፈው ይህ እገዳ "በግልጽ ህገ-ወጥ" እና ከሚኒስቴሩ ህጋዊ ስልጣን ውጭ ነው ብለዋል።

ውሳኔው በዜግነት ላይ የተመሰረተ መድልዎ በመሆኑ ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ህግ ጋር እንደሚጋጭም ገልጸዋል።
​እገዳው ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ እና ከአውሮፓ የመጡ የቪዛ አመልካቾችን የጎዳ ሲሆን፣ የትራምፕ አስተዳደር አመልካቾቹ "በመንግስት ላይ ጥገኛ የመሆን ስጋት አለባቸው" የሚል ምክንያት አቅርቦ ነበር።

​ክሱን የመሰረቱት የኢሚግሬሽን መብት ተሟጋች ድርጅቶች በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መደሰታቸውን ሲገልጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍199🤯2🙏1👌1
የኢሚግሬሽን አገልግሎት "በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር" ማህተም ያልተረጋገጡ ሰነዶችን እንደማይቀበል አስታወቀ‼️

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት፤ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከትግራይ ክልል የሚመጡ ዜጎች የሚያቀርቡት ሰነድ በክልሉ "ጊዜያዊ አስተዳደር" የተረጋገጠ ካልሆነ አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

📌 የውሳኔው ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች፦ የልደት ካርድ፣ የመታወቂያ እና ሌሎችም ለፓስፖርት ማውጫነት የሚያገለግሉ ሰነዶች በሙሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ማህተም እና 'ሄዲንግ' (Heading) ያረፈባቸው መሆን አለባቸው።

ውድቅ የተደረጉ ሰነዶች፦ "የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት" በሚል ሄዲንግ እና ማህተም የተሰጡ ማንኛቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

የውሳኔው ምክንያት፦ የፌደራል መንግስቱ "የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት" የሚለውን አጠራር ስለማይቀበለው እና እውቅና ስለማይሰጠው፤ እነዚህን ህገወጥ ማህተሞች የያዙ ሰነዶችን ይዘው ለሚመጡ ተገልጋዮች ተቋሙ አገልግሎት መስጠት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢65👍3