Update‼️
በዛሬው ዕለት ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም በመቀሌ ዳዕሮ ልዩ ስሙ ሰረዋት በሚባል አካባቢ ከጠዋቱ 5:05 የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በዋናነት ህወሓት ባስቀመጠው ቻይና ሰራሽ ፀረ ድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ላይ ኢላማ ያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
👉የተረጋገጠ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል።
ከጥቃቱ በኋላ ከባድ ፍንዳታዎች በተደጋጋሚ ተሰምተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ አካባቢ አመራሮች ስብሰባ እንደነበራቸው ምንጮች ጠቁመዋል። ሶስት ሰዎች (አንድ ወንድ ሁለት ሴት) ላይ ጉዳት ደርሶ ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።
በትግራይ ክልል የአሰሳ ድሮኖች 24 ሰዓት እየበረሩ ይገኛሉ።
@Addis_Reporter

👍18❤10😢10🕊2💔1
የ13 ዓመቷን ታዳጊ ሴት በመጠጥ አስክሮ የደፈረው ግለሰብ በ15 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ 26 ብልባላ ቀበሌ በአስገድዶ መድፈር የተጠረጠረው ወንጀለኛ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ።
የላስታ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፈንታ ሱሊማን እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ ይኸነው ፍቃዴ ከይምርሀ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ለመምጣት ብልባላ ቀበሌ ላይ አጎትሽ ነኝ አብረን እንሄዳለን በሚል ታዳጊዋ ለቤተሰብ ሞባይል ካርድ ገዝታ ልትልክ የነበረውን 4 ሺህ ብር በመቀበል አስክሮ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል።
ፖሊስም የወንጀል መዝገቡን በማደራጀት ለወረዳው ፍርድቤት አቅርቧል። ፍርድቤቱም ነሃሴ 25 ቀን 2018 ዓ. ም በ13 አመት ታዳጊ ህፃን ላይ የደረሰውን ወንጀል በቀበሌው በተመደቡ ፖሊሶች እና በህብረተሰቡ ድጋፍ ምርመራ አድርጎል። የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት መዝገቡን ወደ ፍርድ ቤት ልኳል።
ለወንጀሉ ተባባሪ ናቸው ተብለው በ15 አመት ጽኑ እስራት የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ የወንጀል ምርመራ ሲካሂድ ቆይቷል።በዚህም መሰረት 2ኛ ተከሳሽ እመየ አጋዥ ቤቷ ውስጥ ድርጊቱ እንዲፈፀም በመተባበሯ በ11 አመት ፅኑ እስራት ፣ በ3ኛ ተከሳሽ ታደስ ደማሙ ላይ ደግሞ አጎትሽነው በማለት ልጅቷን በማዘናጋቱ በ10 አመት ፅኑ እስራት ተወስኖባቸዋል።
ዋና ሃላፊው አክለውም የሴት ልጅ መደፈር በማህበረሰብ ዘንድ የጤና፣ የሞራል እና እራስን የመምራት ተጽእኖን ስለሚያስከትል እንደዚህ አይነቱን ወንጀል እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች በማውገዝ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ እራሱን እንዲጠብቅና የሀይማኖት አባቶች ትምህርት እንዲሰጡ ጠቁመው ወንጀል የሆኑ ድርጊቶች ሲፈፀሙ መረጃዎችን ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

❤26😱8👍4😢1💔1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአዲስ አበባ ጉዳይ❗❗
በዛሬው ዕለት ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ምክረ ሃሳቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዲስ አበባን በሚመለከተው ምክረ ሃሳብ ላይ ቅሬታ በማቀረባቸው ምክረ ሃሳቦቹ ሳይጸድቁ ቀርተዋል።
የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በዓምስት መቶ (500) ደረጃ በተነበበው ሰነድ ላይ በሬዲዮ
ው መሠረት ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በሕገ መንግሥቱ ላይ አዲስ አበባ ዋና መቀመጫ መሆኗ ይደንግግ የሚል ቅሬታ ለኮሚሽኑ በማቅረባቸው ምክረ ሃሳቡ ዳግም እንዲታይ ምክንያት መሆኑን ተሳታፊዎች ነግረውናል።
ጉዳዩ ዳግም መታየት የለበትም፤ በ500 ቡድን ደረጃ ተስማምተናል ያሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።
በትናንትናው ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለርዕሰ ቡድን ተመካካሪዎች በንባብ የቀረበው ሰነድ ግን "አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር" በሚለው ላይ ሁሉም ከስምምነት መድረሱን ያስረዳል፤ ክልሉ ከከተማው አስተዳደር ልዩ ጥቅም ማግኘት ስላለበት የሚደንግገው የሕገ መንግሥቱ ክፍልም "የጋራ ጥቅም" በሚል እንዲሻሻል ከስምምነት መደረሱን ያክላል።
አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ ትሁን ከሚለው ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ምክረ ሃሳቦች ቀርበው ነበር። እነሱም፦ ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ መወሰን እንዲችሉ በሕገ መንግሥቱ ይካተት የሚለው አንደኛው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 (ወይም አግባብ ያለው አንቀጽ) ላይ የሰፈረው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ከተማዋን እና ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሕግ ይወሰኑ የሚል ድንጋጌ ይካተት የሚሉት ናቸው።
ይሁንና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ መሆኗ በሕገ መንግሥቱ መካተት አለበት" የሚል ቅሬታ ለ500 ቡድን ከተነበበ በኋላ ዳግም በማንሳታቸው፣ ዛሬ ምክረ ሃሳቦችን ያጸድቃል ተብሎ የነበረው ጉባኤተኛ በምክክር ስፍራው ውሎ ተመልሷል።
በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ዳግም የሚመለከት ኮሚቴ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ተመርጧል።
ኮሚሽኑ ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረበለትን ቅሬታ ለመመልከት የክልል ምክር ቤት ጉባኤ ጠርቶ ምክረ ሃሳቡን ከ10 ወይም ገና ከጀመሩት የተሰጡ የቡድን ምክረ ሃሳቦችን ዳግም እንዲመለከቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከክልል፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከሽማግሌዎች እና ከሌሎች ቡድኖች ተወካዮች ተመርጠው እስከ ዛሬ ማታ ድረስ ጉዳዩን እንዲያጠናቅቁ ከኮሚሽኑ እንደተነገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልል ጉባኤ አባል ነግረውናል።
በሌላ በኩል የሂደቱን ወደ ኋላ መመለስ የተቹ እና ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ወገኖች መኖራቸውን ሰምተናል፤ ተመካካሪዎቹ "በትናንትናው ዕለት በ500 ቡድን ደረጃ በንባብ በቀረበልን ምክረ ሃሳብ ላይ ተስማምተን ሳለ እንደገና ወደ ጉዳዩ አድሮ እንደ አዲስ መታየቱ አግባብ አይደለም፤ የኮሚሽኑ የአሰራር ስርዓትም አይፈቅድም" ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
እስካሁን ባለው ሂደት ከአዲስ አበባ አጀንዳ ውጪ በሁሉም ምክረ ሃሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ከተመካካሪዎች ሰምተናል።
የምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳቦች በተመካካሪዎች ይጸድቃሉ ብሎ የነበረው ነሃሴ 12 ቀን ነበር።
ይሁናን በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ ደግሞ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።
ይሁንና በሁለቱም ቀን በተበላይ ቀነ ገደብ ምክረ ሀሳቦች አ4ሺ ጉባዔተኛ አልቀረበም።

❤15🤪7👍5
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 14 አመት ሆኗቸዋል
ከ 14 አመታት በፊት ነሃሴ 14 ቀን የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር እና የህወሓት ሊቀመንበር የነበሩት መለስ ዜናዊ አስረስ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት እለት ነዉ።
ጠ/ሚኒስትር መለስ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አይነት አመለካከት ያላቸዉ ሲሆን ግማሾች ባለራዕይ ፣ ቆራጥ እና ጀግና መሪ ሲሏቸዉ ግማሾች ኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ ዉስጥ የከተቱ ፣ ከፋፋይ መሪ ይሏቸዋል።
በጠ/ሚኒስትር መለስ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችበት ፣ የአባይ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት እንዲሁም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የተከፈቱበት እና ከቀደመዉ አገዛዝ ለዉጥ የታየበት ነዉ ሲሉ በርካቶች ግን ኢትዮጵያዊ ዛሬ ላይ ጭምር ላለችበት የብሔር ግጭት መሰረት የጣሉ ሰዉ ናቸዉ ይሏቸዋል።
ጠ/ሚኒስትር መለስ በ 2002 ዓ.ም ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። ጠ/ሚኒስትሩ ለ 2 ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ህይወታቸው ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ጠ/ሚኒሰትሩ በሌሊት በቤልጂየም ነሃሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር በ 57 አመታቸዉ ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።

💔22😢17❤7👍6🥰1👀1
ከውኃ ውጭ መኖር የማይችለው ታዳጊ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ!
በህንድ ዌስት ቤንጋል የሚኖረው የ16 ዓመቱ ታዳጊ ኢቅባል ሼክ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ ህይወቱን ኩሬ ውኃ ውስጥ ለማሳለፍ ተገዷል።
ኢቅባል:-
1. ከውኃ በሚወጣበት ጊዜ በሰውነቱና በቆዳው ላይ ሊቋቋሙት የማይችሉት የሚያቃጥል ከፍተኛ ሕመም ይሰማዋል።
2. ከ11 ዓመቱ ጀምሮ የሚበላው፣ የሚተኛው እና ሙሉ ውሎውን የሚያሳልፈው በኩሬ ውኃ ውስጥ ተዘፍቆ ነው።
3. ቤተሰቦቹ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች እና ሀገር በቀል ሕክምና ቦታዎች ቢወስዱትም የሕመሙን መንስኤ ማወቅ አልተቻለም ነበር።
ነገር ግን ኢቅባል ውኃ ውስጥ ሆኖ ምግብ ሲመገብ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ፣ ታዋቂው ባለሀብት አናንት አምባኒ የሕክምና ወጪውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል።
በአሁኑ ወቅት ኢቅባል በልዩ አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ከተማ ተወስዶ በከፍተኛ ሆስፒታል ልዩ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
ይህ አስገራሚ ታሪክ የሚያስተምረን ትልቁ እውነት ጤና ከምንም በላይ አስፈላጊ እና ትልቅ ሀብት መሆኑን ነው!
በሰላም መተንፈስ፣ ያለ ሕመም መኖር እና በምቾት በየአካባቢው መንቀሳቀስ መቻል እጅግ ታላቅ ጸጋ በመሆኑ ሁልጊዜ "ተመሰግን" ልንል ይገባል።
ጤናችሁን ጠብቁ፣ ላላችሁ መልካም ጤንነትም ሁልጊዜ ምስጋና አቅርቡ!

❤63🙏21👍5👀2
በአቶ ታዬ ደንደአ ላይ ተጥሎ የነበረው የአራት ዓመት የጽኑ እስራት ውሳኔ በሰበር ሰሚ ችሎት ጸደቀ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ የታዘዘውን የአራት ዓመታት የእስር ቅጣት ሙሉ በሙሉ ማጸናቱን አስታወቀ።
ችሎቱ በአዲስ አበባ በዋለው ሰበር ችሎት በአቶ ታዬ ደንደአ በኩል የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በታችኛው ፍርድ ቤት ተበይኖ የነበረውን ውሳኔ አጽንቶታል።
አቶ ታዬ በመጀመሪያ ደረጃ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት በሚል በተመሠረተባቸው ክስ የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ቅጣቱ ወደ አራት ዓመት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።
ይሁን እንጂ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ የነበራቸው አቶ ታዬ አምስት የመከራከሪያ ነጥቦችን በማንሳት ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ችሎቱ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃል ባለቤታቸው የመሣሪያውን መገኘት ባያስተባብሉም ከሌሎች ዜጎች እኩል የመዳኘት መብት እንደተከለከሉ እና ካቀረቧቸው አምስት ተከላካይ ምስክሮች መካከል የሁለቱ ብቻ ቃል ተሰምቶ ውሳኔ መሰጠቱን በቅሬታነት ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ይግባኝ ባሰማበት ተጓዳኝ የክስ ነጥብ ላይ ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጣይ ቀጠሮ ሰጥቷል።

❤9👍4🤔3😢1
ቀን 15/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
✨ደመወዝ===350_400dollar
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
✨ደመወዝ===200-600 dollar
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ ልምድ===0-5አመት
✨የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
✨ደመወዝ===13500+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
✨ደመወዝ===13000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
✨ደመወዝ===14500
✨ዖታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===አይጠይቅም
✨የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
✨ደመወዝ-15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
✨ደመወዝ===12500+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ0===0አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
✨ደመወዝ===14000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
✨ደመወዝ===12000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
✨ደመወዝ===13,000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
✨ደመወዝ 14-22000
✨ፆታ===ወ
✨ልምድ=2አመት
✨የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
✨ደመወዝ=14500+
✨ፆታ===ወ
✨ልምድ===0-5አመት
✨የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
✨ደመወዝ===25000
✨ፆታ=/ሴት
✨ልምድ===0-አመት
✨የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
✨ደመወዝ===13500
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
✨ደመወዝ===16000
✨ዖታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===አይጠይቅም
✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
✨ደመወዝ===10000+
✨ዖታ===ወ/
✨ልምድ===0-አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
🔶ደመወዝ===18,000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-2
✨የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
📞 0907362385
አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
ቢሮ ቁጥር 305
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
✨ደመወዝ===350_400dollar
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
✨ደመወዝ===200-600 dollar
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ ልምድ===0-5አመት
✨የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
✨ደመወዝ===13500+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
✨ደመወዝ===13000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
✨ደመወዝ===14500
✨ዖታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===አይጠይቅም
✨የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
✨ደመወዝ-15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
✨ደመወዝ===12500+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
✨ደመወዝ===15000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ0===0አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
✨ደመወዝ===14000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
✨ደመወዝ===12000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
✨ደመወዝ===13,000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0አመት
✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
✨ደመወዝ 14-22000
✨ፆታ===ወ
✨ልምድ=2አመት
✨የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
✨ደመወዝ=14500+
✨ፆታ===ወ
✨ልምድ===0-5አመት
✨የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
✨ደመወዝ===25000
✨ፆታ=/ሴት
✨ልምድ===0-አመት
✨የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
✨ደመወዝ===13500
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
✨ደመወዝ===16000
✨ዖታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===አይጠይቅም
✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
✨ደመወዝ===10000+
✨ዖታ===ወ/
✨ልምድ===0-አመት
✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
🔶ደመወዝ===18,000
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-2
✨የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
📞 0907362385
አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
ቢሮ ቁጥር 305
❤7👍2
የኢትዮጵያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የመመንዘር አቅሙ በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱና ሀገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገለፀ።
ብሉምበርግ የዜና ምንጭ ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገበያ ለማረጋጋትና የብርን እሴት ለመደገፍ ብሔራዊ ባንኩ ከፍተኛ መጠን ያለው የዶላር ክምችት ስራ ላይ ያዋለ ቢሆንም የብር የመግዛት አቅም ግን ታሪካዊ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ወርዷል።
ይህ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የታየው ተጽዕኖ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትና በዜጎች የእለት ተእለት የኑሮ ውድነት ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል የሚል ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔና በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የሚወሰዱ ቀጣይ እርምጃዎች የአለምአቀፉን የፋይናንስ ማህበረሰብ ትኩረት ስበዋል።

😢17❤6👍1👀1
አሜሪካ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን ለኳታር ልትሸጥ መሆኑን አጸደቀች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ አራት የሚደርሱ «KC-46A» የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን እና ተዛማጅ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በ4.5 ቢሊዮን ዶላር ለኳታር ለመሸጥ የቀረበውን እቅድ ማፅደቁን አስታወቀ።
ሽያጩ ስምንት «PW4062» ተርቦፋን ሞተሮችን የሬዳር ማስጠንቀቂያ ተቀባዮችን የሌዘር አስተላላፊዎችን እና ሌሎች አቪዬሽን ነክ መሳሪያዎችን ያካትታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ይህ ሽያጭ ኳታር በቀጠናው ደህንነት መጠበቅ ላይ የምታደርገውን ሚና የሚያጠናክር ሲሆን «በቀጠናው ያለውን መሰረታዊ የወታደራዊ ኃይል ሚዛን አይቀይረውም» ብሏል።
የ«KC-46A» አውሮፕላኖች የኳታር አየር ኃይል የጦር ጄቶቹ በአየር ላይ እያሉ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የረጅም ርቀት ወታደራዊ ስምሪት የማድረግ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉለት ተጠቅሷል።

👍8🤪4❤3
«ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አያስፈልጋትም!»
ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን የመጠቀም እና የማልማት ሉዓላዊ መብት ስላላት ከማንም አካል ፈቃድ መጠየቅ እንደማያስፈልጋት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኃይል ማመንጨት ብቻ የተገነባና ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ግብይትን በማስፋት ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ሀብት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ባላት ግምት ከግድቡ በታች ሊለሙ የሚችሉ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ የመስኖ መሬቶችን ከመስኖ ልማት ውጪ ማድረጓንም አክለው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ሕዳሴ ግድብን በጋራ ለማስተዳደር የሚቀርቡ ጥሪዎችን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ የተገነባውንና የብሔራዊ ክብር ምልክት የሆነውን ግድብ ግንባታውን ሲቃወም የነበረ አካል መጥቶ «በጋራ እናስተዳድር» ማለቱ ፈጽሞ የማይቻል እና ሊታሰብ የማይችል መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት የኢትዮጵያን የልማት መብት ለመገደብ ከመጣር ይልቅ በውይይት እና በጋራ ትብብር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

❤20👍5
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የቤት ኪራይ❗❗❗
በሐዋሳ የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉ ተገለጸ ።
በሐዋሳ ከተማ በቅርብ ጊዜ የታየው ያልተጠበቀ የቤት ኪራይ ዋጋ ንረት በነዋሪዎች ላይ የከፋ የኑሮ ጫና እና እንግልት እየፈጠረ ይገኛል። በርካታ አከራዮች ቀደም ሲል ይጠይቁት ከነበረው ዋጋ በእጥፍ እና ከዚያም በላይ በመጨመራቸው፣ በተለይም በወር ደመወዝ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፈተና ተዳርገዋል።
ይህ የኪራይ ዋጋ ንረት ዋነኛ ምክንያት ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ከቤት ንብረታቸው የተነሱ በርካታ ዜጎች በአንድ ጊዜ ወደ ኪራይ ገበያው መግባታቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ አከራዮችም ይህንን የመኖሪያ ቤት እጥረት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ዋጋውን እንዲሰቅሉት አድርጎታል። በዚህም ምክንያት ቤት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ማግኘት ሲቸገሩ፣ ያገኙትም ቢሆኑ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ክፍያ ለመክፈል ተገደዋል።
ከዚሁ ከልማት ተነሾች ጋር ተያይዞ መንግሥት በተለይ ከመንግሥት ቤት ለሚነሱ ነዋሪዎች ቀድሞ ምትክና ማረፊያ አዘጋጅቶ ማንሳት ሲገባው፣ በቂ ዝግጅት ሳያደርግ ሰዎችን ከቤት በማስወጣቱ ለተጨማሪ እንግልት ዳርጓቸዋል። የሐዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ከተጀመረ አሁኑ አንድ ዓመት ገደማ እየሆነው ቢሆንም፣ እስከ ዛሬ ድረስ ከቤታቸው ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች ምትክ ቤት ተሠርቶ አልተረከበም።
በተጨማሪም ምትክ ማቅረብ በማይቻልበት ሁኔታ ለቤት ኪራይ የሚከፈለው ክፍያ የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ነው ተብሏል። ለአነስተኛ ቤተሰብ በሐዋሳ የሚከፈለው የቤት ኪራይ ድጎማ በወር ከ4,000 እስከ 7,000 ብር ብቻ በመሆኑ ከወቅቱ የኪራይ ገበያ ጋር በፍጹም የማይመጣጠን ሲሆን፣ በአንፃሩ እንደ ይርጋለም ባሉ አቅራቢያ ከተሞች ለተነሾች ከ10,000 ብር በላይ ክፍያ እየተፈጸመ ማቆየት መቻሉ በሐዋሳ ያለውን ክፍተት አጉልቶ አሳይቷል።
በመሆኑም ነዋሪዎቹ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደርና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በጉዳዩ ላይ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። ችግሩ የግል አከራይና ተከራይ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኑሮ ውድነትን የሚያባብስ በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ተተግሮ እንደነበረው ሁሉ አከራይና ተከራይን በሕጋዊ ውል የሚያስተዳድርና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን የሚያስቀር ሕጋዊ የአሠራር ማዕቀፍ በሐዋሳም እንዲዘረጋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

❤13😢4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟
የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።
በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።
ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com

❤5👍2
ወለጋ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ከትላንት በስተያ ረቡዕ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ኦዲተርን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። በጥቃቱ የአዋሽ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ኦዲተር ለሚ መንግሥቱ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ማሙሽ ማሩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በወረዳው ቱሉ ሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ "መቀ ለሊ" በተባለ ሥፍራ ጸጥታ ኃይሎች ከባንኮቹ የተሠበሠበ ጥሬ ብር በተሽከርካሪ አጅበው በመጓዝ ላይ ሳሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ሰሞኑን በዞኑ አንገር ጉቴ ከተማ ተፈጽሞ የነበረውን ጥቃት በመሸሽ ነቀምት ከተማ ቆይተው ወደ ቀያቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ነዋሪዎችን ጭምር ከመኪና በማስውረድ መግደላቸውንና ቀሪዎችን አፍነው መውሠዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

😢24❤18👍12🤪3🙉3🕊1
የአዲስ አበባ ጉዳይ‼️
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው 300 ያህል የኦሮሚያ ክልል ተመካካሪዎች፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ መኾኗን የሚያረጋግጥ ድንጋጌ በሕገመንግሥቱ ይካተት የሚለው ጥያቄያችን አማራጭ የሌለው ምክረ ሀሳብ ኾኖ ካልተያዘ ከጉባኤው እንወጣለን በማለት ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል። የአገራዊ ምክክር ኮሚሽንም፣ የጋራ ማረጋገጫ ቡድኑ ያመሳከራቸውን ምክረ ሀሳቦች ከማቅረቡ በፊት ስብሰባ ያልጠራውን የክልል ተወካዮች ጉባኤ ትናንት ሰብስቦ የኦሮሚያ ተመካካሪዎችን ቅሬታ አቅርቧል። የክልል ተወካዮች ጉባኤ፣ ቅሬታውን መርምሮ የመፍትሄ ሀሳብ የሚያቀርብ የ11 ክልሎች ፕሬዝዳንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ሦስት የትግራይ ተወካዮች፣ አምስት የሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት የወጣቶች ተወካዮች የተካተቱበት ኮሚቴ አቋቁሟል።
ኾኖም በርካታ ተመካካሪዎች፣ የኦሮሚያ ተመካካሪዎች ቅሬታ ከምክክር ሂደቱ የወጣና ሂደቱን ወደ ኋላ የሚመልስ ነው የሚል ተቃውሞ አሠምተዋል ተብሏል። ለሥራ ቡድኖች ከቀረቡት 476 ምክረ ሀሳቦች ውጭ አዲስ የሚጨመር ወይም የሚቀነስ ምክረ ሀሳብ ካለ፣ ራሳቸውን ከጉባኤው ለማግለል የወሠኑ ተመካካሪዎች መኖራቸውም ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የምክክር ጉባኤው በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የተጠናቀሩትን የመጨረሻ ምክረ ሀሳቦች በማዳመጥ ላይ መኾኑን ዛሬ ነሐሴ 15 ማምሻውን ገልጧል። የምክክር ጉባኤው የተጠራው፣ የኦሮሚያ ተወካዮችን ቅሬታ ይመረምራል የተባለው የክልል ተወካዮች ገባኤ ምን መፍትሄ አቅርቦ እንደኾነ ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም።

🤪26❤23😢4👍3
ከቤተሰብ 850 ሺህ ብር ለማግኘት ሳትታገት ታግቻለሁ ያለችው ተጠርጣሪና ተባባሪዋ ተያዙ
ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አያት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ራሄል መለሰ የተባለች ወጣት ከቤት ወጥታ ባለመመለሷ ቤተሰቦቿ ለፖሊስ ያመለክታሉ።
ፖሊስ ፍለጋ እያደረገ ባለበት ሰዓት ለአባቷ ስልክ ተደውሎ «ልጅቷን አግተናል፤ እንድትለቀቅ 850 ሺህ ብር ላኩ» የሚል ማስፈራሪያ ደረሰ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ፈጣን ክትትል የታገተችው የተባለችው ወጣት በባህር ዳር ከተማ ስማዳ አካባቢ ከሰለሞን ቁምላቸው ከተባለ ወንድ ጋር ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር ውላለች።
በምርመራውም ግለሰቦቹ የፍቅር ግንኙነት እንዳላቸው፣ ከሀገር ለመውጣት አስበው 850 ሺህ ብር ከቤተሰቦቿ ለመቀበል ሲሉ የሠሩት የእገታ ድራማ መሆኑ ተረጋግጧል።
በተጠርጣሪዎቹ ላይ የምርመራ ስራውን መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚገቡ ግለሰቦች እየታዩ በመምጣታቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

❤10🙉8🤔5👍4
አለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታውን ይስበር-ህወሓት‼️
'ህወሃት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዝምታ ወጥቶ የፌደራል መንግሥቱ የሚፈፅመውን የድሮን ጥቃት እንዲያወግዝ እና እንዲያደራደር ጥሪ አቀረበ።
ህወሃት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን የድሮን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ያለ ሲሆን ነገር ግን ሁኔታውን ላለማባባስና ቀጠናውን ወደ ሌላ ጦርነት ላለመውሰድ ለጥቃቱ ወታደራዊ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበናል ብሏል።
ህወሃት አሁንም ቢሆን ለሰላም እና ድርድር ያለው አቋም አልተለወጠም፣ነገር ግን ትዕግስትም ልክ አለው፣ትዕግስት እንደፍርሃት መቆጠር የለበትም፣ትግራይን ከጥቃት ለመከላከል እንገደዳለን' ብሏል።

🤣36❤11👍5🤪3🤔1🤡1👀1🙈1