አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዜጎች መካከል እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አወጣ::

በሳዑዲ አረቢያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ (ሪያድ) ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ሲደባደቡና ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በተመለከተ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን እና አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመሆን የምርመራ ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

* በዚህ ኢሰብአዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች መደበኛ ባልሆነ (በህገ-ወጥ) መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ናቸው። እነዚህ አካላት በበረሃና ገጠራማ አካባቢዎች በመሸሸግ፣ ምክንያታቸው በግልጽ ባልታወቀ ጉዳይ ቡድን (ጎራ) በመፍጠር እርስ በርሳቸው ግጭት ሲፈጥሩ እንደነበር ተደርሶበታል።

* እስካሁን በተደረገው ክትትልና ጥረት አንድ ተጠራጣሪ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ኤምባሲው ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅና በዚህ ወንጀል የተሳተፉትን ሁሉ ለህግ ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል።

ኤምባሲው እነዚህን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል ማንኛውንም ተዛማጅ መረጃ ወይም ጥቆማ ያለው ወገን በአስቸኳይ ለኤምባሲው እንዲያቀርብ በአክብሮት ጥሪ አስተላልፏል።

Via፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ - ሪያድ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍3🌚2
የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ

የቀድሞው የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ሚካይሎ ፌዶሮቭ የጦርነት ጊዜ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም ሩሲያ ሙሉ በሙሉ ወረራ ካካሄደችበት ከሶስት ዓመታት ወዲህ በዜለንስኪ ፕሬዝዳንትነት ላይ የተደቀነ ትልቁ ፉክክር ተደርጎ ተወስዱዋል።

ፌዶሮቭ ባለፈው ማክሰኞ በዩቲዩብ ላይ ባሰራጩት መልእክት ‹‹ዲሞክራሲ በሩሲያ ታግቶ ሊያዝ አይገባም ›› ብለዋል አክለውም ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው “በእርግጥም ነፃ የአውሮፓ ሀገር ሆና ለመቀጠል ስለምትፈልግ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

እ.ኤ.አ በ2022 ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ዩክሬን በወታደራዊ አዋጅ ስር የምትገኝ ትገኛለች ይህም ማለት ምርጫዎች ታግደዋል ማለት ነው።

ፌዶሮቭ ከተሾሙ ከስድስት ወራት በኋላ ባለፈው ወር ሳይታሰብ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸው መባረራቸው የሚታወስ ሲሆን ፤ መባረራቸው በመላው በሀገሪቱ ተቃውሞዎችን ቀስቅሷል፡፡

ፌዶሮቭ የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ሚኒስቴሩን በማንቃት፣ ሙስናን በመታገል እና መረጃዎችን በመጠቀም በግንባር ላይ ያለውን አፈፃፀም ለማሻሻል በመስራት ምስጋና ተቸሯቸዋል።

የእሳቸው ከኃላፊነት መነሳት እና በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አሌክሳንደር ሲርስኪ መካከል ከተፈጠረው ውጥረት ጋር የተያያ እንደሆነም ይታመናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍6
በሶማሊያ የባህር ዳርቻ አዲስ የመርከብ ጠለፋ ተፈጸመ

በሶማሊያ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ ስሙ ያልተጠቀሰ አዲስ የጭነት መርከብ በባህር ላይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈጸመው ይህ ድርጊት አባል አገራት አዲስ የደህንነት ግብረ ሃይል እንዲያቋቁሙ አነሳስቷል።

የመርከቡ የጸጥታ ሃላፊ ቢያንስ ስምንት ታጣቂዎች መርከቡን መቆጣጠራቸውን ያሳወቁ ሲሆን፣ አውሮፓ ህብረት የባህር ሃይልም ሁኔታውን በመከታተል ላይ ይገኛል።

ይህ አዲስ ጥቃት የተፈጸመው አራት ሌሎች መርከቦች ከወራት በፊት ተጠልፈው በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ነው። ፓኪስታን እና ግብጽ መርከቦቹን እና ሰራተኞቹን ለማስለቀቅ ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋር ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረጉ ቢሆንም፣ በዘራፊ ቡድኖች መካከል ያለው አለመግባባት ድርድሩን አስቸጋሪ አድርጎታል።

የኢንተርናሽናል ማሪታይም ድርጅት የጂቡቲ የባህር ላይ ንግድ ስምምነት አባል አገራት የባህር ላይ ጠላፊዎችን ለመከላከል አዲስ ጥምር ግብረ ሃይል ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍2😢1
ከ750 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች መቁሰላቸውን ፔንታጎን የተጎጂዎችን ቁጥር አሻሽሎ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ

የፔንታጎን የጦርነት ተጎጂዎች መረጃ ቋት እንደሚያሳየው፣ ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ከ750 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች የቆሰሉ ሲሆን፣ ከየካቲት 21 ጀምሮ 18 ወታደሮች ተገድለዋል፡፡

የፔንታጎን ይፋዊ ግምት ቀጥተኛ የወታደራዊ ወጪውን 37.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ቢያሳይም፤ አንዳንድ ተንታኞች ግን በአሜሪካውያን አባወራዎች ላይ የሚደርሰው ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ  ወደ 1,000 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይገልጻሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቐለ‼️
በመቀሌ ከተማ ዳዕሮ አካባቢ ዛሬ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:05 የተፈፀመው የአየር ጥቃት ምስል። ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1410💔6😢3🤔2🎉2👌1
Update‼️
በዛሬው ዕለት ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም በመቀሌ ዳዕሮ ልዩ ስሙ ሰረዋት በሚባል አካባቢ ከጠዋቱ 5:05 የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በዋናነት ህወሓት ባስቀመጠው ቻይና ሰራሽ ፀረ ድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ላይ ኢላማ ያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
👉የተረጋገጠ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል።
ከጥቃቱ በኋላ ከባድ ፍንዳታዎች በተደጋጋሚ ተሰምተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ አካባቢ አመራሮች ስብሰባ እንደነበራቸው ምንጮች ጠቁመዋል። ሶስት ሰዎች (አንድ ወንድ ሁለት ሴት) ላይ ጉዳት ደርሶ ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።
በትግራይ ክልል የአሰሳ ድሮኖች 24 ሰዓት እየበረሩ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1810😢10🕊2💔1
የ13 ዓመቷን ታዳጊ ሴት በመጠጥ አስክሮ  የደፈረው ግለሰብ በ15 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ 26 ብልባላ ቀበሌ በአስገድዶ መድፈር የተጠረጠረው ወንጀለኛ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ።

የላስታ ወረዳ   ፖሊስ ፅ/ቤት  የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ  ምክትል ኢንስፔክተር ፈንታ ሱሊማን እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ  ይኸነው ፍቃዴ  ከይምርሀ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ለመምጣት ብልባላ ቀበሌ ላይ አጎትሽ ነኝ አብረን እንሄዳለን በሚል ታዳጊዋ ለቤተሰብ ሞባይል ካርድ ገዝታ ልትልክ የነበረውን 4 ሺህ ብር በመቀበል አስክሮ  የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል።

ፖሊስም የወንጀል መዝገቡን በማደራጀት ለወረዳው ፍርድቤት አቅርቧል። ፍርድቤቱም  ነሃሴ 25 ቀን 2018 ዓ. ም  በ13 አመት ታዳጊ ህፃን ላይ የደረሰውን ወንጀል በቀበሌው በተመደቡ ፖሊሶች እና በህብረተሰቡ ድጋፍ ምርመራ አድርጎል። የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት መዝገቡን  ወደ ፍርድ ቤት ልኳል።

ለወንጀሉ ተባባሪ ናቸው ተብለው በ15 አመት ጽኑ እስራት የተጠረጠሩ  ሁለት ግለሰቦች ላይ  የወንጀል ምርመራ ሲካሂድ ቆይቷል።በዚህም መሰረት  2ኛ ተከሳሽ እመየ አጋዥ ቤቷ ውስጥ ድርጊቱ እንዲፈፀም በመተባበሯ  በ11 አመት ፅኑ እስራት ፣  በ3ኛ ተከሳሽ ታደስ ደማሙ ላይ ደግሞ አጎትሽነው በማለት ልጅቷን በማዘናጋቱ   በ10 አመት  ፅኑ እስራት  ተወስኖባቸዋል።

ዋና ሃላፊው አክለውም የሴት ልጅ መደፈር በማህበረሰብ ዘንድ የጤና፣ የሞራል እና እራስን የመምራት ተጽእኖን ስለሚያስከትል እንደዚህ አይነቱን ወንጀል እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች  በማውገዝ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ እራሱን እንዲጠብቅና የሀይማኖት አባቶች ትምህርት እንዲሰጡ ጠቁመው ወንጀል የሆኑ ድርጊቶች ሲፈፀሙ መረጃዎችን ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ  መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26😱8👍4😢1💔1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአዲስ አበባ ጉዳይ
በዛሬው ዕለት ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ምክረ ሃሳቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዲስ አበባን በሚመለከተው ምክረ ሃሳብ ላይ ቅሬታ በማቀረባቸው ምክረ ሃሳቦቹ ሳይጸድቁ ቀርተዋል።

የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በዓምስት መቶ (500) ደረጃ በተነበበው ሰነድ ላይ በሬዲዮ

ው መሠረት ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በሕገ መንግሥቱ ላይ አዲስ አበባ ዋና መቀመጫ መሆኗ ይደንግግ የሚል ቅሬታ ለኮሚሽኑ በማቅረባቸው ምክረ ሃሳቡ ዳግም እንዲታይ ምክንያት መሆኑን ተሳታፊዎች ነግረውናል።

ጉዳዩ ዳግም መታየት የለበትም፤ በ500 ቡድን ደረጃ ተስማምተናል ያሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።

በትናንትናው ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለርዕሰ ቡድን ተመካካሪዎች በንባብ የቀረበው ሰነድ ግን "አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር" በሚለው ላይ ሁሉም ከስምምነት መድረሱን ያስረዳል፤ ክልሉ ከከተማው አስተዳደር ልዩ ጥቅም ማግኘት ስላለበት የሚደንግገው የሕገ መንግሥቱ ክፍልም "የጋራ ጥቅም" በሚል እንዲሻሻል ከስምምነት መደረሱን ያክላል።

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ ትሁን ከሚለው ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ምክረ ሃሳቦች ቀርበው ነበር። እነሱም፦ ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ መወሰን እንዲችሉ በሕገ መንግሥቱ ይካተት የሚለው አንደኛው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 (ወይም አግባብ ያለው አንቀጽ) ላይ የሰፈረው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ከተማዋን እና ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሕግ ይወሰኑ የሚል ድንጋጌ ይካተት የሚሉት ናቸው።

ይሁንና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ መሆኗ በሕገ መንግሥቱ መካተት አለበት" የሚል ቅሬታ ለ500 ቡድን ከተነበበ በኋላ ዳግም በማንሳታቸው፣ ዛሬ ምክረ ሃሳቦችን ያጸድቃል ተብሎ የነበረው ጉባኤተኛ በምክክር ስፍራው ውሎ ተመልሷል።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ዳግም የሚመለከት ኮሚቴ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ተመርጧል።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረበለትን ቅሬታ ለመመልከት የክልል ምክር ቤት ጉባኤ ጠርቶ ምክረ ሃሳቡን ከ10 ወይም ገና ከጀመሩት የተሰጡ የቡድን ምክረ ሃሳቦችን ዳግም እንዲመለከቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከክልል፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከሽማግሌዎች እና ከሌሎች ቡድኖች ተወካዮች ተመርጠው እስከ ዛሬ ማታ ድረስ ጉዳዩን እንዲያጠናቅቁ ከኮሚሽኑ እንደተነገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልል ጉባኤ አባል ነግረውናል።

በሌላ በኩል የሂደቱን ወደ ኋላ መመለስ የተቹ እና ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ወገኖች መኖራቸውን ሰምተናል፤ ተመካካሪዎቹ "በትናንትናው ዕለት በ500 ቡድን ደረጃ በንባብ በቀረበልን ምክረ ሃሳብ ላይ ተስማምተን ሳለ እንደገና ወደ ጉዳዩ አድሮ እንደ አዲስ መታየቱ አግባብ አይደለም፤ የኮሚሽኑ የአሰራር ስርዓትም አይፈቅድም" ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት ከአዲስ አበባ አጀንዳ ውጪ በሁሉም ምክረ ሃሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ከተመካካሪዎች ሰምተናል።

የምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳቦች በተመካካሪዎች ይጸድቃሉ ብሎ የነበረው ነሃሴ 12 ቀን ነበር።

ይሁናን በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ ደግሞ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።

ይሁንና በሁለቱም ቀን በተበላይ ቀነ ገደብ ምክረ ሀሳቦች አ4ሺ ጉባዔተኛ አልቀረበም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤪7👍5
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 14 አመት ሆኗቸዋል

ከ 14 አመታት በፊት ነሃሴ 14 ቀን የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር እና የህወሓት ሊቀመንበር የነበሩት መለስ ዜናዊ አስረስ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት እለት ነዉ።

ጠ/ሚኒስትር መለስ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አይነት አመለካከት ያላቸዉ ሲሆን ግማሾች ባለራዕይ ፣ ቆራጥ እና ጀግና መሪ ሲሏቸዉ ግማሾች ኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ ዉስጥ የከተቱ ፣ ከፋፋይ መሪ ይሏቸዋል።

በጠ/ሚኒስትር መለስ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችበት ፣ የአባይ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት እንዲሁም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የተከፈቱበት እና ከቀደመዉ አገዛዝ ለዉጥ የታየበት ነዉ ሲሉ በርካቶች ግን ኢትዮጵያዊ ዛሬ ላይ ጭምር ላለችበት የብሔር ግጭት መሰረት የጣሉ ሰዉ ናቸዉ ይሏቸዋል።

ጠ/ሚኒስትር መለስ በ 2002 ዓ.ም ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። ጠ/ሚኒስትሩ ለ 2 ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ  ህይወታቸው ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ጠ/ሚኒሰትሩ በሌሊት በቤልጂየም ነሃሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር በ 57 አመታቸዉ ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔22😢177👍6🥰1👀1
ከውኃ ውጭ መኖር የማይችለው ታዳጊ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ!

በህንድ ዌስት ቤንጋል የሚኖረው የ16 ዓመቱ ታዳጊ ኢቅባል ሼክ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ ህይወቱን ኩሬ ውኃ ውስጥ ለማሳለፍ ተገዷል።

ኢቅባል:-

1. ከውኃ በሚወጣበት ጊዜ በሰውነቱና በቆዳው ላይ ሊቋቋሙት የማይችሉት የሚያቃጥል ከፍተኛ ሕመም ይሰማዋል።

2. ከ11 ዓመቱ ጀምሮ የሚበላው፣ የሚተኛው እና ሙሉ ውሎውን የሚያሳልፈው በኩሬ ውኃ ውስጥ ተዘፍቆ ነው።

3. ቤተሰቦቹ ወደ ተለያዩ ሆስፒታሎች እና ሀገር በቀል ሕክምና ቦታዎች ቢወስዱትም የሕመሙን መንስኤ ማወቅ አልተቻለም ነበር።

ነገር ግን ኢቅባል ውኃ ውስጥ ሆኖ ምግብ ሲመገብ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ፣ ታዋቂው ባለሀብት አናንት አምባኒ የሕክምና ወጪውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል።

በአሁኑ ወቅት ኢቅባል በልዩ አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ከተማ ተወስዶ በከፍተኛ ሆስፒታል ልዩ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

ይህ አስገራሚ ታሪክ የሚያስተምረን ትልቁ እውነት ጤና ከምንም በላይ አስፈላጊ እና ትልቅ ሀብት መሆኑን ነው!
በሰላም መተንፈስ፣ ያለ ሕመም መኖር እና በምቾት በየአካባቢው መንቀሳቀስ መቻል እጅግ ታላቅ ጸጋ በመሆኑ ሁልጊዜ "ተመሰግን" ልንል ይገባል።

ጤናችሁን ጠብቁ፣ ላላችሁ መልካም ጤንነትም ሁልጊዜ ምስጋና አቅርቡ!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
64🙏21👍5👀2
በአቶ ታዬ ደንደአ ላይ ተጥሎ የነበረው የአራት ዓመት የጽኑ እስራት ውሳኔ በሰበር ሰሚ ችሎት ጸደቀ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ የታዘዘውን የአራት ዓመታት የእስር ቅጣት ሙሉ በሙሉ ማጸናቱን አስታወቀ።

ችሎቱ በአዲስ አበባ በዋለው ሰበር ችሎት በአቶ ታዬ ደንደአ በኩል የቀረበውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በታችኛው ፍርድ ቤት ተበይኖ የነበረውን ውሳኔ አጽንቶታል።

አቶ ታዬ በመጀመሪያ ደረጃ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት በሚል በተመሠረተባቸው ክስ የሰባት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ቅጣቱ ወደ አራት ዓመት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር።

ይሁን እንጂ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ የነበራቸው አቶ ታዬ አምስት የመከራከሪያ ነጥቦችን በማንሳት ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ችሎቱ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል።

የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃል ባለቤታቸው የመሣሪያውን መገኘት ባያስተባብሉም ከሌሎች ዜጎች እኩል የመዳኘት መብት እንደተከለከሉ እና ካቀረቧቸው አምስት ተከላካይ ምስክሮች መካከል የሁለቱ ብቻ ቃል ተሰምቶ ውሳኔ መሰጠቱን በቅሬታነት ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ይግባኝ ባሰማበት ተጓዳኝ የክስ ነጥብ ላይ ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ቀጣይ ቀጠሮ ሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍4🤔3😢1
ቀን 15/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
7👍2
የኢትዮጵያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የመመንዘር አቅሙ በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱና ሀገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማረጋጋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉ ተገለፀ።

ብሉምበርግ የዜና ምንጭ ባወጣው ዘገባ መሰረት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገበያ ለማረጋጋትና የብርን እሴት ለመደገፍ ብሔራዊ ባንኩ ከፍተኛ መጠን ያለው የዶላር ክምችት ስራ ላይ ያዋለ ቢሆንም የብር የመግዛት አቅም ግን ታሪካዊ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ወርዷል።

ይህ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የታየው ተጽዕኖ በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትና በዜጎች የእለት ተእለት የኑሮ ውድነት ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል የሚል ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔና በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ የሚወሰዱ ቀጣይ እርምጃዎች የአለምአቀፉን የፋይናንስ ማህበረሰብ ትኩረት ስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢176👍1👀1
አሜሪካ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን ለኳታር ልትሸጥ መሆኑን አጸደቀች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ አራት የሚደርሱ «KC-46A» የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን እና ተዛማጅ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በ4.5 ቢሊዮን ዶላር ለኳታር ለመሸጥ የቀረበውን እቅድ ማፅደቁን አስታወቀ።

ሽያጩ ስምንት «PW4062» ተርቦፋን ሞተሮችን  የሬዳር ማስጠንቀቂያ ተቀባዮችን  የሌዘር አስተላላፊዎችን  እና ሌሎች አቪዬሽን ነክ መሳሪያዎችን ያካትታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ይህ ሽያጭ ኳታር በቀጠናው ደህንነት መጠበቅ ላይ የምታደርገውን ሚና የሚያጠናክር ሲሆን «በቀጠናው ያለውን መሰረታዊ የወታደራዊ ኃይል ሚዛን  አይቀይረውም» ብሏል።

የ«KC-46A» አውሮፕላኖች የኳታር አየር ኃይል የጦር ጄቶቹ በአየር ላይ እያሉ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የረጅም ርቀት ወታደራዊ ስምሪት የማድረግ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉለት ተጠቅሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍8🤪43
«ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን ለማልማት ከማንም ፈቃድ አያስፈልጋትም!»

ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ ሀብቷን የመጠቀም እና የማልማት ሉዓላዊ መብት ስላላት ከማንም አካል ፈቃድ መጠየቅ እንደማያስፈልጋት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለኃይል ማመንጨት ብቻ የተገነባና ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ግብይትን በማስፋት ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ሀብት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ባላት ግምት ከግድቡ በታች ሊለሙ የሚችሉ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ የመስኖ መሬቶችን ከመስኖ ልማት ውጪ ማድረጓንም አክለው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ሕዳሴ ግድብን በጋራ ለማስተዳደር የሚቀርቡ ጥሪዎችን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ የተገነባውንና የብሔራዊ ክብር ምልክት የሆነውን ግድብ ግንባታውን ሲቃወም የነበረ አካል መጥቶ «በጋራ እናስተዳድር» ማለቱ ፈጽሞ የማይቻል እና ሊታሰብ የማይችል መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት የኢትዮጵያን የልማት መብት ለመገደብ ከመጣር ይልቅ በውይይት እና በጋራ ትብብር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍5