አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ ከ2 ሺህ በላይ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ህጋዊ እውቅና እንደተሰጣቸው ተገለጸ

በከተማዋ በባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገው ለውጥ ህጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት በከተማዋ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ህገ-ወጥ እና ሰሌዳቸው እውቅና ያልነበረው በመሆኑ ለወንጀልና ለፀጥታ ስጋት ተዳርገው እንደነበር የሚናገሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው፣ ይህንን ችግር ለመፍታት በተዘረጋው አሰራር የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ እንዲደራጁ መደረጉን እና 2 ሺህ 800 ባጃጆች በማህበር ተደራጅተው እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ህጋዊ እውቅና ያገኙ ባጃጆች ከዋና ዋና መንገዶች ውጭ ባሉ እና የህዝብ ትራንስፖርት ባልደራሰባቸው አካባቢዎች ተሰማርተው በቀን እስከ 250 ሺህ ሰዎችን እያጓጓዙ እንደሚገኙ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል።

ባጃጆቹ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የስርቆትና ህገ-ወጥነት ስራዎችን በመከላከል ረገድ የሰላም አጋዥ ሃይል ሆነው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

አዲስ አበባ የባጃጅ ከተማ ባለመሆኗ በሂደት እነዚህ አነስተኛ የትራንስፖርት አማራጮች በአውቶቡሶች፣ በትላልቅ ተሽከርካሪዎች እና በሜትር ታክሲዎች እየተተኩ እንደሚሄዱ አቶ ዳኛቸው ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅት ዋና ዋና መንገዶችን ከመኖሪያ አካባቢዎች ጋር በማያያዝ ረገድ ባጃጆች ከፍተኛ ሚና በመጫወታቸው የተጀመረው ህጋዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በተሻሻለው የባጃጅ አሰራር ህብረተሰቡ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም ፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ ቂሊንጦ ላይ ሰፈር፣ ቂሊንጦ ሚካኤል፣ ሌስ ፍራንስ ት/ቤት፣ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ ኮዬ አደባባይ ፣ ዋሊያ ቢራ እና አካባቢው፣  

👉ዊንጌት ት/ቤት፣ ድሬ ቆዳ ፣ ጊዮን በረኪና ፣ መከላከያ መኖሪያ ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ሚኒሊየም ሰፈር ፣ ሸጎሌ ጨፌ ፣ ጉለሌ እጽዋት ማዕከል እና አካባቢው ፣

👉አለምባንክ ፣ ኢንዲያና ት/ቤት ፣ ታፍ ማደያ ፣ አቃቂ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት ፣ ኮፊ ሲቲ ድረስ፣ ፊሪ ፤ ኖክ ፤ ዋልያ ብረታ ብረት ፤ ካፒታል ሲሚንቶ ጀርባ እና አካባቢው ፣

👉ፓርሞ ሳይት፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ቼራሊያ ፣ ቃሊቲ ገብር ኤል 40/60 ፣ ቼራሊያ ኮንዶሚየም፣ ቃሊቲ መናኸሪያ ፣ ግራር ኮንዶሚኒየም ፣ አለም ባንክ ፣ ትሮፒካል ፣ አየር ጤና ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው ፣

👉ኪዳነ ምህርት ፣ ሸጎሌ መንደር 7 ፣ ዊንጌት ጤና ጣቢያ ፣አበራ ሆቴል ፣ እምነበረድ ፣ አጠና ተራ ፣ ኢትዮ ጠቢብ ፣ ደጉ ሆቴል ፣ ሰፈረ ሰላም እና አካባቢው ፣

👉ካራ ፣ ናትራን ፣ ለማ ነጎ ት/ቤት ፣ አየር ጤና ፣ አየር ጤና ኪዳነምህረት ፣ አየር ጤና ሞቢል ፣ ፉሪ ፣ ሰይድ ያሲን ጀርባ ፣ ኡራኤል እና አካባቢው ፣

👉ጎላጎል ህንጻ ፣ፋንዲሻ ሆቴል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ፣ ወርቁ ህንጻ ፣ ቃል ፔኒሲዮን ፣ ዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ፣ ሻላ መናፈሻ፣ ለማ ስጋ ቤት ፣ ቺቺንያ ጫፍ ድረስ እና አካባቢው ፣

👉ድሬ ከአስፋልት በላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ ፣ ኬላ ፣BM ሳይት ሲሼር ፣ ዘጸአት ፣ መናገሻ አበባ ልማት እና አካባቢው ፣

ከጠዋቱ 2፡00-12፡00

👉አዳማ፣ ጎሮ ቀበሌ፣ ዳቢ ቀበሌ፣ ቀበሌ 18፣ ጋምቤላ፣ ኢላ መውጫ፣ ኒግናንጊ፣ ጋምቤላ ቤተመንግስት፣ 1ኛ ኮብልስቶን፣ አየርጤና፣ ሰላም ሰፈር  እና አካባቢው ፣

ከጠዋቱ 2፡30-7፡30

👉ለቡ መብራት ፣ቫርኔሮ አደባባይ ፣ ለቡ መድሀኒያለም ፣ ለቡ ላቢያጆ ፣ ጀሞ 1 ፣ ካሳ ሳይት ፣ አፍሪካ ህንጻ ድረስ ፣ ጀሞ ሚካኤል እና አካባቢው ፣

👉ገላን ኮንዶሚኒየም (ልደታ ቤተ- ክርስቲያን አካባቢ) ፣ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ፣ አቃቂ ቴሌ ዌር ሀውስ፣ አንበሳ ጫማ ፣ አለምባንክ ፣ ከተማ ልማት ፣ ፊታውራሪ ት/ቤት ፣ አባ ቦራ እና አካባቢው ፣

👉ሐዋሳ፣ ተግባረ ዕድ፣ ሌዊ፣ ቅድስት ሥላሴ ኮንዶሚኒየም፣ ሚሽን መቃብር፣ ቲቲሲ፣ ብሌን እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍4
በኬኒያ የሚደረግ ድርድር የለም-TPLF‼️
ቀጣይ ሳምንት ህወሃትና የፌዴራል መንግሥቱ በኬኒያ ሊደራደሩ ነው በሚል በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ ውሸት መሆኑን የህወሓት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብረሃም ሐጎስ ዛሬ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ላይ ገልፀዋል።
አላማችን አራት ኪሎን መቆጣጠር ነው ብለዋል።
የፌደራል መንግሥቱ ምዕራብ ትግራይን ልስጣችሁ፣ተፈናቃዮች ይመለሱ ቢል እንኳን ጊዜው አልፏል ብለዋል።
መንግሥት አሁን ላይ በድሮን እና በአንቶኖቭ ሙሉ ጦርነት ከፍቶብናል ብሏል።
የፌደራል መንግስቱን ለመጣል ከተለያዩ ሀይሎች ጋር የተፈጠረው ስምምነት ወደመጨረሻው ምዕራፍ መድረሱን እና መግለጫ እንደማሰጥ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26🤣14👍12🌚3🤪1
የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር የሚል ምክረ-ሐሳብ ከስምምነት ላይ ተደረሰበት

እየተገባደደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የስራ ቅጥርን በተመለከተ «የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር» የሚል ምክረ-ሐሳብ አቅርበው ከስምምነት መድረሳቸው ተገለፀ።

በተጨማሪም በጉባዔው ውይይት ወቅት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ እንዲያቀርቡ የሚል አዎንታዊ ምክረ-ሐሳብ ተነስቶ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል።

በአሁኑ ወቅት 500 አባላት ባሏቸው 8 ቡድኖች ተከፋፍለው ውይይታቸውን በማጠቃለል ላይ የሚገኙት ተወካዮች፣ በአብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ወደ መስማማት መምጣታቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ እስካሁን መስማማት ያልተቻለባቸው እና በይደር እንዲቆዩ የተደረጉ አጀንዳዎች የትኞቹ እንደሆኑ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተወካዮቹ በምክክሩ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ የቀረቡትን ምክረ-ሐሳቦች በማጠናከር አጠቃላይ ወጥ የሆነ ሰነድ የማዘጋጀት ሥራ ጀምረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙉2212👍3🤪3🤔2👀2
😢8💔71👍1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በድርቅ 16 ሰው😥‼️
በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ገለፁ‼️‼️
👉ከ17000 በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል።
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡

በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል።

ችግሩን በተመለከተ እስከ ክልል ድረስ አቤቱታ መቅረቡን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ከየቀበሌው የተመደቡ አካላት የሞቱ ሰዎችን፣ የተሰደዱ አባወራዎችን እና ያለቁ እንስሳትን ቁጥር መዝግበው ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቁም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከመንግሥት የተደረገው ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች ብቻ የተሰጠ የሴፍቲኔት እርዳታ እንደነበርም አክለው ጠቁመዋል።

እየከፋ የመጣውን የረሃብ አደጋ ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የድንገተኛ እርዳታ ጥያቄ በማንሳት ሰልፍ መውጣታቸውን የገለጹት ጥላሁን፤ አሁንም አስቸኳይ ድጋፍ ካልቀረበ የአካባቢው ሕዝብ በረሃብ የሚያልቅበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲደርሱላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሼር አድርጉት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢33💔129👍4🥰1🤯1
የቻይና ኩባንያዎች በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በሚገነባው የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡ ድርጅቶች ውስጥ የበላይነቱን ያዙ

በኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ በሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡት ድርጅቶች ውስጥ አብዛኞቹ የቻይና ኩባንያዎች ወይም ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የተመሰረቱ ድጅቶች መሆናቸውን የአቪዬሽን መረጃ አቅራቢ እና የዜና ፖርታል የሆነው ‘ch-aviation’ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ የተደረገው የእጩዎች ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ የቻይና ኩባንያዎች በከፍተኛ ልዩነት ትልቁን ቁጥር የያዙ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ላይ የቻይና ኢንጂነሪንግ እና ግንባታ ድርጅቶች ያላቸውን የጎላ ሚና የሚያሳይ ነው።

በተወዳዳሪነት የተመረጡት የቻይና ኩባንያዎች ቻይና ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ፣ ቻይና ኮንስትራክሽን ኤይትዝ ኢንጂነሪንግ ዲቪዥን፣ ቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን፣ ቤጂንግ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ቤጂንግ እርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ፣ ቻይና ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ፣ ቻይና ናሽናል ኤሮ-ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ ቻይና ሬይልዌይ ቤጂንግ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ሻንዶንግ ሉቂያኦ ግሩፕ ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍7🤔3
ቀን 14/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
10👍2
በ216 ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በብልሹ አሰራር የተሳተፉ በ216 ሠራተኞች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል የ6 ሠራተኞች የቅጥር ውል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ነው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የገለጸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍3🙏2
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዜጎች መካከል እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አወጣ::

በሳዑዲ አረቢያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ (ሪያድ) ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ሲደባደቡና ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በተመለከተ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን እና አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመሆን የምርመራ ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

* በዚህ ኢሰብአዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች መደበኛ ባልሆነ (በህገ-ወጥ) መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ናቸው። እነዚህ አካላት በበረሃና ገጠራማ አካባቢዎች በመሸሸግ፣ ምክንያታቸው በግልጽ ባልታወቀ ጉዳይ ቡድን (ጎራ) በመፍጠር እርስ በርሳቸው ግጭት ሲፈጥሩ እንደነበር ተደርሶበታል።

* እስካሁን በተደረገው ክትትልና ጥረት አንድ ተጠራጣሪ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ኤምባሲው ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅና በዚህ ወንጀል የተሳተፉትን ሁሉ ለህግ ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል።

ኤምባሲው እነዚህን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል ማንኛውንም ተዛማጅ መረጃ ወይም ጥቆማ ያለው ወገን በአስቸኳይ ለኤምባሲው እንዲያቀርብ በአክብሮት ጥሪ አስተላልፏል።

Via፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ - ሪያድ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍3🌚2
የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ

የቀድሞው የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ሚካይሎ ፌዶሮቭ የጦርነት ጊዜ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም ሩሲያ ሙሉ በሙሉ ወረራ ካካሄደችበት ከሶስት ዓመታት ወዲህ በዜለንስኪ ፕሬዝዳንትነት ላይ የተደቀነ ትልቁ ፉክክር ተደርጎ ተወስዱዋል።

ፌዶሮቭ ባለፈው ማክሰኞ በዩቲዩብ ላይ ባሰራጩት መልእክት ‹‹ዲሞክራሲ በሩሲያ ታግቶ ሊያዝ አይገባም ›› ብለዋል አክለውም ዩክሬን እየተዋጋች ያለችው “በእርግጥም ነፃ የአውሮፓ ሀገር ሆና ለመቀጠል ስለምትፈልግ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

እ.ኤ.አ በ2022 ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ዩክሬን በወታደራዊ አዋጅ ስር የምትገኝ ትገኛለች ይህም ማለት ምርጫዎች ታግደዋል ማለት ነው።

ፌዶሮቭ ከተሾሙ ከስድስት ወራት በኋላ ባለፈው ወር ሳይታሰብ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸው መባረራቸው የሚታወስ ሲሆን ፤ መባረራቸው በመላው በሀገሪቱ ተቃውሞዎችን ቀስቅሷል፡፡

ፌዶሮቭ የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ሚኒስቴሩን በማንቃት፣ ሙስናን በመታገል እና መረጃዎችን በመጠቀም በግንባር ላይ ያለውን አፈፃፀም ለማሻሻል በመስራት ምስጋና ተቸሯቸዋል።

የእሳቸው ከኃላፊነት መነሳት እና በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አሌክሳንደር ሲርስኪ መካከል ከተፈጠረው ውጥረት ጋር የተያያ እንደሆነም ይታመናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍6
በሶማሊያ የባህር ዳርቻ አዲስ የመርከብ ጠለፋ ተፈጸመ

በሶማሊያ የባህር ጠረፍ አቅራቢያ ስሙ ያልተጠቀሰ አዲስ የጭነት መርከብ በባህር ላይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈጸመው ይህ ድርጊት አባል አገራት አዲስ የደህንነት ግብረ ሃይል እንዲያቋቁሙ አነሳስቷል።

የመርከቡ የጸጥታ ሃላፊ ቢያንስ ስምንት ታጣቂዎች መርከቡን መቆጣጠራቸውን ያሳወቁ ሲሆን፣ አውሮፓ ህብረት የባህር ሃይልም ሁኔታውን በመከታተል ላይ ይገኛል።

ይህ አዲስ ጥቃት የተፈጸመው አራት ሌሎች መርከቦች ከወራት በፊት ተጠልፈው በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ነው። ፓኪስታን እና ግብጽ መርከቦቹን እና ሰራተኞቹን ለማስለቀቅ ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋር ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እያደረጉ ቢሆንም፣ በዘራፊ ቡድኖች መካከል ያለው አለመግባባት ድርድሩን አስቸጋሪ አድርጎታል።

የኢንተርናሽናል ማሪታይም ድርጅት የጂቡቲ የባህር ላይ ንግድ ስምምነት አባል አገራት የባህር ላይ ጠላፊዎችን ለመከላከል አዲስ ጥምር ግብረ ሃይል ማቋቋማቸውን አስታውቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4👍2😢1
ከ750 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች መቁሰላቸውን ፔንታጎን የተጎጂዎችን ቁጥር አሻሽሎ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ

የፔንታጎን የጦርነት ተጎጂዎች መረጃ ቋት እንደሚያሳየው፣ ከኢራን ጋር በተደረገው ጦርነት ከ750 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች የቆሰሉ ሲሆን፣ ከየካቲት 21 ጀምሮ 18 ወታደሮች ተገድለዋል፡፡

የፔንታጎን ይፋዊ ግምት ቀጥተኛ የወታደራዊ ወጪውን 37.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ቢያሳይም፤ አንዳንድ ተንታኞች ግን በአሜሪካውያን አባወራዎች ላይ የሚደርሰው ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ  ወደ 1,000 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይገልጻሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መቐለ‼️
በመቀሌ ከተማ ዳዕሮ አካባቢ ዛሬ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:05 የተፈፀመው የአየር ጥቃት ምስል። ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1410💔6😢3🤔2🎉2👌1
Update‼️
በዛሬው ዕለት ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም በመቀሌ ዳዕሮ ልዩ ስሙ ሰረዋት በሚባል አካባቢ ከጠዋቱ 5:05 የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በዋናነት ህወሓት ባስቀመጠው ቻይና ሰራሽ ፀረ ድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ላይ ኢላማ ያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
👉የተረጋገጠ ሶስት ሰዎች ተጎድተዋል።
ከጥቃቱ በኋላ ከባድ ፍንዳታዎች በተደጋጋሚ ተሰምተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ አካባቢ አመራሮች ስብሰባ እንደነበራቸው ምንጮች ጠቁመዋል። ሶስት ሰዎች (አንድ ወንድ ሁለት ሴት) ላይ ጉዳት ደርሶ ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።
በትግራይ ክልል የአሰሳ ድሮኖች 24 ሰዓት እየበረሩ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1810😢10🕊2💔1
የ13 ዓመቷን ታዳጊ ሴት በመጠጥ አስክሮ  የደፈረው ግለሰብ በ15 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ 26 ብልባላ ቀበሌ በአስገድዶ መድፈር የተጠረጠረው ወንጀለኛ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ።

የላስታ ወረዳ   ፖሊስ ፅ/ቤት  የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ  ምክትል ኢንስፔክተር ፈንታ ሱሊማን እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ  ይኸነው ፍቃዴ  ከይምርሀ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ለመምጣት ብልባላ ቀበሌ ላይ አጎትሽ ነኝ አብረን እንሄዳለን በሚል ታዳጊዋ ለቤተሰብ ሞባይል ካርድ ገዝታ ልትልክ የነበረውን 4 ሺህ ብር በመቀበል አስክሮ  የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሟል።

ፖሊስም የወንጀል መዝገቡን በማደራጀት ለወረዳው ፍርድቤት አቅርቧል። ፍርድቤቱም  ነሃሴ 25 ቀን 2018 ዓ. ም  በ13 አመት ታዳጊ ህፃን ላይ የደረሰውን ወንጀል በቀበሌው በተመደቡ ፖሊሶች እና በህብረተሰቡ ድጋፍ ምርመራ አድርጎል። የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት መዝገቡን  ወደ ፍርድ ቤት ልኳል።

ለወንጀሉ ተባባሪ ናቸው ተብለው በ15 አመት ጽኑ እስራት የተጠረጠሩ  ሁለት ግለሰቦች ላይ  የወንጀል ምርመራ ሲካሂድ ቆይቷል።በዚህም መሰረት  2ኛ ተከሳሽ እመየ አጋዥ ቤቷ ውስጥ ድርጊቱ እንዲፈፀም በመተባበሯ  በ11 አመት ፅኑ እስራት ፣  በ3ኛ ተከሳሽ ታደስ ደማሙ ላይ ደግሞ አጎትሽነው በማለት ልጅቷን በማዘናጋቱ   በ10 አመት  ፅኑ እስራት  ተወስኖባቸዋል።

ዋና ሃላፊው አክለውም የሴት ልጅ መደፈር በማህበረሰብ ዘንድ የጤና፣ የሞራል እና እራስን የመምራት ተጽእኖን ስለሚያስከትል እንደዚህ አይነቱን ወንጀል እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች  በማውገዝ ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ እራሱን እንዲጠብቅና የሀይማኖት አባቶች ትምህርት እንዲሰጡ ጠቁመው ወንጀል የሆኑ ድርጊቶች ሲፈፀሙ መረጃዎችን ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ  መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26😱8👍4😢1💔1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአዲስ አበባ ጉዳይ
በዛሬው ዕለት ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ምክረ ሃሳቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዲስ አበባን በሚመለከተው ምክረ ሃሳብ ላይ ቅሬታ በማቀረባቸው ምክረ ሃሳቦቹ ሳይጸድቁ ቀርተዋል።

የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በዓምስት መቶ (500) ደረጃ በተነበበው ሰነድ ላይ በሬዲዮ

ው መሠረት ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በሕገ መንግሥቱ ላይ አዲስ አበባ ዋና መቀመጫ መሆኗ ይደንግግ የሚል ቅሬታ ለኮሚሽኑ በማቅረባቸው ምክረ ሃሳቡ ዳግም እንዲታይ ምክንያት መሆኑን ተሳታፊዎች ነግረውናል።

ጉዳዩ ዳግም መታየት የለበትም፤ በ500 ቡድን ደረጃ ተስማምተናል ያሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።

በትናንትናው ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለርዕሰ ቡድን ተመካካሪዎች በንባብ የቀረበው ሰነድ ግን "አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር" በሚለው ላይ ሁሉም ከስምምነት መድረሱን ያስረዳል፤ ክልሉ ከከተማው አስተዳደር ልዩ ጥቅም ማግኘት ስላለበት የሚደንግገው የሕገ መንግሥቱ ክፍልም "የጋራ ጥቅም" በሚል እንዲሻሻል ከስምምነት መደረሱን ያክላል።

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ ትሁን ከሚለው ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ምክረ ሃሳቦች ቀርበው ነበር። እነሱም፦ ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ መወሰን እንዲችሉ በሕገ መንግሥቱ ይካተት የሚለው አንደኛው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 (ወይም አግባብ ያለው አንቀጽ) ላይ የሰፈረው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ከተማዋን እና ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሕግ ይወሰኑ የሚል ድንጋጌ ይካተት የሚሉት ናቸው።

ይሁንና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች "አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ መሆኗ በሕገ መንግሥቱ መካተት አለበት" የሚል ቅሬታ ለ500 ቡድን ከተነበበ በኋላ ዳግም በማንሳታቸው፣ ዛሬ ምክረ ሃሳቦችን ያጸድቃል ተብሎ የነበረው ጉባኤተኛ በምክክር ስፍራው ውሎ ተመልሷል።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ዳግም የሚመለከት ኮሚቴ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ተመርጧል።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረበለትን ቅሬታ ለመመልከት የክልል ምክር ቤት ጉባኤ ጠርቶ ምክረ ሃሳቡን ከ10 ወይም ገና ከጀመሩት የተሰጡ የቡድን ምክረ ሃሳቦችን ዳግም እንዲመለከቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከክልል፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከሽማግሌዎች እና ከሌሎች ቡድኖች ተወካዮች ተመርጠው እስከ ዛሬ ማታ ድረስ ጉዳዩን እንዲያጠናቅቁ ከኮሚሽኑ እንደተነገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልል ጉባኤ አባል ነግረውናል።

በሌላ በኩል የሂደቱን ወደ ኋላ መመለስ የተቹ እና ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ወገኖች መኖራቸውን ሰምተናል፤ ተመካካሪዎቹ "በትናንትናው ዕለት በ500 ቡድን ደረጃ በንባብ በቀረበልን ምክረ ሃሳብ ላይ ተስማምተን ሳለ እንደገና ወደ ጉዳዩ አድሮ እንደ አዲስ መታየቱ አግባብ አይደለም፤ የኮሚሽኑ የአሰራር ስርዓትም አይፈቅድም" ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት ከአዲስ አበባ አጀንዳ ውጪ በሁሉም ምክረ ሃሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ከተመካካሪዎች ሰምተናል።

የምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳቦች በተመካካሪዎች ይጸድቃሉ ብሎ የነበረው ነሃሴ 12 ቀን ነበር።

ይሁናን በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ ደግሞ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።

ይሁንና በሁለቱም ቀን በተበላይ ቀነ ገደብ ምክረ ሀሳቦች አ4ሺ ጉባዔተኛ አልቀረበም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤪7👍5