አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.3K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ግብጽ እና ኢትዮጵያን ለማደራደር‼️
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ከሰሞኑ ግብፅን በጎበኙበት ወቅት 'ዶናልድ ትራምፕ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል የውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት፣ ካይሮ እና አዲስ አበባን እንደገና ለማደራደር ያላቸውን ዝግጁነት መግለጻቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡15🤪8👍74🤔2🤣2👀1🙊1
ቀን 13/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
11👍3
ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታ አቆጣጠር መመሪያውን ቀየረ

ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታዎች የሚቆጠሩበትን መመሪያ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ መቀየሩን ይፋ አድርጓል። እስከዛሬ ድረስ አንድ ቪዲዮ «ታየ» ተብሎ እይታው የሚቆጠረው ተመልካቹ ቢያንስ ለ30 ሰከንዶች ያህል ሲመለከት ነበር።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት ግን ቪዲዮው መጫወት እንደጀመረ በቀጥታ እንደ አንድ እይታ ተቆጥሮ የሚደመር ይሆናል ብሏል።

ይህ አዲስ አሰራር ዩቲዩብ አጫጭር ቪዲዮዎች ከሚቀርቡበት "Shorts" መድረክ ጋር አቆጣጠሩን አንድ ዓይነት ለማድረግና ወጥ አሰራር ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ ለውጥ ይዘት አዘጋጆች የሚያገኙትን የቪዲዮ እይታ ቁጥር በጥቅሉ ሊጨምረው ቢችልም፣ የዩቲዩብ የገቢ ክፍያ እና ስፖንሰርሺፕ ግን አሁንም ተመልካቹ ቪዲዮውን ምን ያህል ሰዓት ተመለከተው (Watch Time) በሚለው መስፈርት ላይ ተመስርቶ እንደሚቀጥል ተብራርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1612
6 ሰዎች ወደአልታወቀ ቦታ ተወሰዱ‼️
በትናንትው ዕለት ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም በትግራይ ክልል ከመቀሌ 12 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በእንደርታ ወረዳ በዴንደራ መንደር ተደጋጋሚ የድንገተኛ ድሮን ጥቃቶችን ተከትሎ በአስተኳሽነት (OP) የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ወደማይታወቅ ቦታ መወሰዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ከስድስቱ ሰዎች ውስጥ አራቱ የታወቁ ሲሆን:-
1.ወይዘሮ ምሂራ ገ/መስቀል
2. አቶ ጸጋዬ ፍጹም
3. አቶ ደብሊው. በርሃን ኪንግ
4. አቶ ሃንስ አዲስ ናቸው።
ምስል:- በጥቃቱ ወቅት የተነሳ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍8🤔3🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአገራዊ ምክክሩ አራት አጀንዳዎች ከስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣይ ዙር ተሻገሩ

በአገራዊ ምክክሩ የመንግሥት አደረጃጀትን ጨምሮ አራት አከራካሪ ጉዳዮች በ120 አባላት ያለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣዩ የምክክር ሂደት መሻገራቸው ተገለጸ።

በአጀንዳው 500 ተሳታፊዎች ባሉበት የሥራ ቡድን 53 ጉዳዮች ቀርበው፣ 50 ላይ ስምምነት ሲደረስ ሦስቱ ግን ሳይስማሙ እንደቀሩ ቀደም ሲል ተገልጿል። የሐሳብ አዘጋጅ ቡድኑ እነዚህን ጉዳዮች በማጣጣም 62 ምክረ ሐሳቦች አድርጎ ሲያቀርብ፣ አራቱ ላይ የጋራ ስምምነት ሊደረስ እንዳልቻለ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል ዋነኛው የመንግሥት አወቃቀር ጉዳይ ሲሆን፣ አንደኛው አማራጭ ፓርላሜንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ እንዲመረጥ የሚደግፍ ሲሆን፣ ሌላኛው ፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ቀጥታ እንዲመረጥ የሚል ነው።

ሌሎቹ ሁለት ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አመራረጥና በምክር ቤቱ የብሔረሰቦች ውክልና አሠራርን የሚመለከቱ ናቸው። በአባላት አመራረጥ ላይ አንዱ ሐሳብ አባላት በክልሎች ምክር ቤቶች እንዲመረጡ ሲደግፍ፣ ሌላው ሕዝቡ በቀጥታ እንዲመርጣቸው የሚል ነው።

በብሔረሰቦች ውክልና ላይም አንድ ሐሳብ በሕዝብ ብዛት መሠረት ተጨማሪ ውክልና እንዲኖር ሲደግፍ፣ ሌላው ሁሉም ብሔረሰቦች በእኩል መልኩ እንዲወከሉ የሚል ሐሳብ ቀርቧል።

አራተኛው አከራካሪ ጉዳይ “ውህድ ማንነት” የሚለው ሐሳብ ሲሆን፣ የሥራ ቡድኑ ቀደም ሲል በስምምነት አልፎ የነበረው ሐሳብ በ120 አባላት ባለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ዳግም የአለመስማማት ጉዳይ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መቅረቡንና ከስምምነት ይልቅ አለመስማማት በሚል ወደ ቀጣዩ ዙር መተላለፉን ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በመሆኑም አራቱ ጉዳዮች በቀጣዩ የምክክር ዙር የበለጠ ውይይትና የመግባባት ሥራ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሆነው መቀጠላቸው ታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5🤪2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስደንጋጭ ነው‼️
በራያ አዘቦ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
አዝመራም አልተዘራም ብለዋል።
አሁን የክረምቱ መውጫ ሰዓት እየደረሰ ነው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔20😢7👍42😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
4👍3
የክልል "ልዩ ኃይል" መፍረሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲፈተሽ ተጠየቀ።

"በሀገራዊ ምክክሩ የተቋማት ግንባታ ቡድን ባደረገው ስብሰባ፣ የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲረጋገጥ ወይም ኦዲት እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ኦዲቱን የሚያደርጉት ደግሞ መከላከያ እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ማንኛውም የክልል የጸጥታ መዋቅር ከመከላከያ እና ከፌደራል ፖሊስ በላይ መሆን እንደሌለበት ተጠቁሟል ።

ክልሎች የሚኖሯቸው የሚሊሻ አባላትም በወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠኑ እንዲሆኑ ስምምነት ተደርጓል።

ይህ አሰራር የሀገሪቱን ሰላም በዘላቂነት ያስከብራል ትላላችሁ? ኮመንታችሁን አስቀምጡ!"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤪7👍2💔2🤔1🤣1
አዲስ አበባ የኦሮሚያ መቀመጫ ሁና በህገ መንግስቱ እውቅና ሳይሆን መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር የውጡ ግቡ ስጋቱ እንዳይኖር ለመቀነስ ዋስትና ይሰጠን ሲሉ ተመካካሪዎች ሃሳባቸውን አቀረቡ

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ሁና በህገ መንግስቱ እውቅና ይሰጥ የሚለው በልዩነት የተያዘውን ምክረ ሃሳብ የሚያስማሙት የ120 ቡድኖች፣ ለሥራ ቡድኑ ካቀረቡ በኋላ “እውቅና ይሰጥ ሳይሆን መንግስት ሲቀያየር ውጡ ግቡ” የሚለው ስጋት እንዳይኖር በህገ መንግስቱ “ዋስትና ይሰጠን” በሚል  እንዲስተካከል የሚል ምክረ ሃሳብ መቅረቡን አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች ሰምታለች።  
 
ይህ ሃሳብ የመጨረሻው ሰነድ ሲነበብ የተሰማ መሆኑንና የቃል ማስተካከያ እንዲደረግበት እንደተጠየቀም አዲስ ማለዳ ተገንዝባለች፡፡

በሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ በተሳተፉ ተወካዮች እና ተመካካሪዎች ዘንድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደራዊ ሁኔታ፣ በዋስትና እና እውቅና የሚሉ በርካታ አከራካሪ ምክረ ሃሳቦች የቀረቡበት ነው። በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ጉባኤ የክልል ጉባኤተኞች ይመካካራሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስከ ትናንት አመሻሽ ግን ኮሚሽኑ ያለው ነገር የለም።

በሀገራዊ የምክክር መድረኩ በፌደራል አጀንዳ ከተሞች ስር የሚመክሩ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ በፌደራል ተጠሪነት ስር ያለች ከተማ እንድትሆን በሚል ሁሉም በሚባል ደረጃ ስምምነት ተደርስበታል ተብሏል። ነዋሪዎች የራሳቸውን መሪ፣ ማለትም ከንቲባ የመምረጥ መብት እንዲጠበቅ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል።
 
በአንጻሩ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫነት እና የመውጣትና የመግባት ስጋት መፍትሔን በተመለከተ “ህገ መንግስቱ ላይ የኦሮሚያ ርዕሰ መዲና ተብሎ ይፃፍ” እና “ክልሎች መቀመጫቸውን የመምረጥ ስልጣን ክፍት ሁኖ፣ ለራሳቸው ክልሎች ሆኖ ይተው” በሚሉ ሁለት አማራጮች በልዩነት ተይዘዋል።

በ120 አባላት ባሉት አካል ሲጣጣም የቆየው ምክረ ሃሳብ ለሥራ ቡድኑ ማለትም ለ500ው ከቀረበ በኋላ ከኦሮሚያ ተሳታፊዎች ዘንድ በልዩነት ተይዞ የነበረው በህገ መንግስቱ የኦሮሚያ መቀመጫ እንደሆነች እውቅና ይሰጥ  የሚለው  የ"እውቅና" ሳይሆን የ"ዋስትና" ይሰጥ በሚል ይስተካከል ብለዋል ሲሉ ተመካካሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። 

አዲስ አበባን ወክለው በፌደራል ከተሞች አጀንዳ ላይ እየመከሩ ያሉ አንድ ተሳታፊ ለሥራ ቡድኑ ከቀረበ በኋላ “እውቅና ሳይሆን ዋስትና ይሰጥ ነው ያልነው። ማለትም የመውጣት፣ የመግባት፣ የመቀመጫ፣ ዋና ከተማ እውቅና ሳይሆን ዋስትና ነው። አሁን እውቅና እና ዋስትና አይለያይም? ልዩነት አለው አለው። ስለዚህ እኛ እውቅና አላለንም ዋስትና ይሰጠን ነው ያልነው” የሚል ሀሳብ ከኦሮሚያ ተመካካሪዎች ዘንድ ተነስቷል። ይህም ማለት መንግስት በተቀያየረ ቁጥር  ክልሉ መቀመጫውን እንዳያጣ እና ልቀቁ የሚል እንዳይመጣ እንደሆነ አንስተዋል።

ተሳታፊው አክለውም ከኦሮሚያ በኩል ተነስቷል ያሉት ሃሳብ፣ ከአዲስ አበባ  ውጡና ግቡ የሚባል ነገር እንዳይመጣ በሚል ይሄን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል ብለዋል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ጊዜ የኦሮሚያ መስተዳድር አዲስ አበባ ወጥቶ፣ ከዛ ደግሞ አዲስ አበባ የወጣበት አጋጣሚ ነበረ እና ለዛም ዋስትና (ጋራንቲ) እንዲሆን "የሆነ ነገር ይፃፍልን" የሚል ጥያቄ ነበራቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ የተያዘው አማራጭ ህገ-መንግስቱ ላይ አይጻፍ የሚል እንደሆነ ተሳታፊው አንስተዋል።
“ርእሰ መዲናነቱ ህገ-መንግስቱ ላይ መፃፍ የለበትም። ምክንያቱም የራሳቸውን መቀመጫ መምረጥ የሚችሉት ክልሎች በመሆናቸው፣ ህገ-መንግስት ላይ መፃፉ ራሱ የክልሉን ምክር ቤት አሳሪ ሊሆን ይችላል።” በሚል የተነሳ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሁሉም ክልል መቀመጫ በህገ-መንግስት ስለማይፃፍ  “የኦሮሚያ ብቻ ተለይቶ መፃፍ የለበትም። ይልቁንም ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ የመምረጥ መብት እንዲኖራቸው ክፍት ይደረግ” በሚል በልዩነት ሃሳብ ተነስቷል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
 
በሌላ በኩል ደግሞ ሁለተኛው አማራጭ የኦሮሚያ መቀመጫ ሁና በህገ-መንግስቱ ላይ ይጻፍ የሚል መሆኑን አንስተዋል። 

“የኦሮሚያ ርዕሰ መዲና ተብሎ ይፃፍ” የሚል አማራጭም ቀርቧል። ምክንያቱም ይሄ በግልጽ ካልተቀመጠ ነገ ሌሎች ክልሎችም መቀመጫችንን አዲስ አበባ እናደርጋለን ቢሉ ቀውስ ይፈጠራል። ይህ ምክረ ሃሳብ የመጀመሪያውን የሚቃወም እንደሆነ የሚያነሱት ተሳታፊው አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኗ ለኦሮሚያ ልዩ እውቅና በመስጠት “የኦሮሚያ ርእሰ መዲና” ተብላ በህገ-መንግስቱ መፃፍ አለባት ተብሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ “የኦሮሚያ ርዕሰ መዲና” ተብሎ ከተፃፈ ደግሞ፣ ክልሉ የሌላ አካል ስልጣን ውስጥ እንዳይገባ የህግ ወሰን ሊበጅለት ይገባል። ይህ አባባል ከተማዋን እንደ ዋና መዲና የመጠቀም ስጋትን ለመቀነስ ብቻ ታስቦ የተደረገ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ስልጣን ለመስጠት እንዳልሆነ በግልጽ እንዲቀመጥ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል ተብሏል።

መጀመሪያ አካባቢ ራስ ገዝ ወይንም ነጻ ከተማ የሚል ሃሳብ ተነስቶ እንደነበረ እና ይህም ብዙም ያልተገፋበት መሆኑን ተሳታፊው ተናግረዋል። ነገር ግን ምክረ ሃሳብ አጣጣሚዎቹ ነፃ ከተማ የሚል ስላነበቡ ለምን ገባ የሚል ተነስቷል ብለዋል። አክለውም ነጻ የሚለው ይነሳ የሚል ሃሳብ ቀርቧል ያሉ ሲሆን “እንደኔ ግን የሚነሳ አይመስለኝም” ብለዋል።

ተሳታፊው ይቀጥሉ እና “ነፃ ከተማ” ማለት ነዋሪው የራሱን መሪ የሚመርጥበት ሁኔታ፣ ሙሉ ኃላፊነት ያለው እንደሆነ በማንሳት  ከሌልች ማለትም ከፌደራል ወይም ማንኛውም አካል ነፃ ሁኖ የሚል በመሆኑ ይነሳ ያሉ መኖራቸውን ጠቅሰዋል። አክለውም “ምክንያቱም ከሌሎች ነፃ ከተማ ሆኖ የሚል ነበረ የተነበበው” ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ አንዳንዶች እንዳልተስማሙበት አውስተዋል።

የከተማዋ የሥራ ቋንቋን በተመለከተ ደግሞ ወደ ሌላ አጀንዳ ማለትም በቋንቋ ላይ ወደተመከረበት አጀንዳ እንዲሄድ መሸጋሸጉን አንስተዋል። ይህም በሌላው አጀንዳ ላይ 13 የሥራ ቋንቋ ተብሎ እንደነበር እና አዲስ አበባ ላይ ያነሱት ስድስት ቋንቋዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል። 

ተሳታፊው አክለውም የፌደራል ከተሞች አጀንዳ ከሁሉም አጀንዳዎች የተሻለ እና በደንብ የተጠቃለለ ተደርጎ  የተጠናቀቀ አጀንዳ ነው ተብሏል ብለዋል። 

ምክረ ሃሳቡ ሲያጠናቅር የቆየው ቡድን በንባብ ካቀረበ በኋላ  ስምምነቱ ላይ ማስተካከያዎች እንዲወሰዱ ተመካካሪዎች የጠየቁ ሲሆን የመጀመሪያው “የፌደራል” ትሁን በሚለው ላይ ሁሉም ሰው ተስማምቷል የሚለውን ሃሳብ  “አይ፣ እሱም ሙሉ በሙሉ የተስማማንበት የሚለውም ምናልባት ባይሆን” እና በዚህ ምትክ “እንደ ሀሳብ እንደ አማራጭ የቀረበ ነው በሚለው ቢቀመጥ" ተብሎ ይስተካከልልን  ያሉ ተመካካሪዎች አሉ ተብሏል። 

የምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎችን ሰብስቦ ቦታው ላይ የተገኙት ከመጡበት ይዘው የመጡትን አቋም አስጠብቀው ሊሄዱ ሳይሆን እንደሀገር የሚያስቀጥልን ሃሳብ በማንሳት በዚያ ላይ ሁሉንም በሚያስማማ ጉዳይ ላይ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

 @Addis_Reporter
@Addis_Reporter
27🤪5👍3🤔3😡3👌1🤣1
በአዲስ አበባ ከተማ ከ2 ሺህ በላይ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ህጋዊ እውቅና እንደተሰጣቸው ተገለጸ

በከተማዋ በባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገው ለውጥ ህጋዊ እውቅና እንዲኖራቸው መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት በከተማዋ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ህገ-ወጥ እና ሰሌዳቸው እውቅና ያልነበረው በመሆኑ ለወንጀልና ለፀጥታ ስጋት ተዳርገው እንደነበር የሚናገሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው፣ ይህንን ችግር ለመፍታት በተዘረጋው አሰራር የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ እንዲደራጁ መደረጉን እና 2 ሺህ 800 ባጃጆች በማህበር ተደራጅተው እውቅና ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ህጋዊ እውቅና ያገኙ ባጃጆች ከዋና ዋና መንገዶች ውጭ ባሉ እና የህዝብ ትራንስፖርት ባልደራሰባቸው አካባቢዎች ተሰማርተው በቀን እስከ 250 ሺህ ሰዎችን እያጓጓዙ እንደሚገኙ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል።

ባጃጆቹ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የስርቆትና ህገ-ወጥነት ስራዎችን በመከላከል ረገድ የሰላም አጋዥ ሃይል ሆነው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

አዲስ አበባ የባጃጅ ከተማ ባለመሆኗ በሂደት እነዚህ አነስተኛ የትራንስፖርት አማራጮች በአውቶቡሶች፣ በትላልቅ ተሽከርካሪዎች እና በሜትር ታክሲዎች እየተተኩ እንደሚሄዱ አቶ ዳኛቸው ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅት ዋና ዋና መንገዶችን ከመኖሪያ አካባቢዎች ጋር በማያያዝ ረገድ ባጃጆች ከፍተኛ ሚና በመጫወታቸው የተጀመረው ህጋዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በተሻሻለው የባጃጅ አሰራር ህብረተሰቡ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም ፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ ቂሊንጦ ላይ ሰፈር፣ ቂሊንጦ ሚካኤል፣ ሌስ ፍራንስ ት/ቤት፣ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ ኮዬ አደባባይ ፣ ዋሊያ ቢራ እና አካባቢው፣  

👉ዊንጌት ት/ቤት፣ ድሬ ቆዳ ፣ ጊዮን በረኪና ፣ መከላከያ መኖሪያ ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ሚኒሊየም ሰፈር ፣ ሸጎሌ ጨፌ ፣ ጉለሌ እጽዋት ማዕከል እና አካባቢው ፣

👉አለምባንክ ፣ ኢንዲያና ት/ቤት ፣ ታፍ ማደያ ፣ አቃቂ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት ፣ ኮፊ ሲቲ ድረስ፣ ፊሪ ፤ ኖክ ፤ ዋልያ ብረታ ብረት ፤ ካፒታል ሲሚንቶ ጀርባ እና አካባቢው ፣

👉ፓርሞ ሳይት፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ቼራሊያ ፣ ቃሊቲ ገብር ኤል 40/60 ፣ ቼራሊያ ኮንዶሚየም፣ ቃሊቲ መናኸሪያ ፣ ግራር ኮንዶሚኒየም ፣ አለም ባንክ ፣ ትሮፒካል ፣ አየር ጤና ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው ፣

👉ኪዳነ ምህርት ፣ ሸጎሌ መንደር 7 ፣ ዊንጌት ጤና ጣቢያ ፣አበራ ሆቴል ፣ እምነበረድ ፣ አጠና ተራ ፣ ኢትዮ ጠቢብ ፣ ደጉ ሆቴል ፣ ሰፈረ ሰላም እና አካባቢው ፣

👉ካራ ፣ ናትራን ፣ ለማ ነጎ ት/ቤት ፣ አየር ጤና ፣ አየር ጤና ኪዳነምህረት ፣ አየር ጤና ሞቢል ፣ ፉሪ ፣ ሰይድ ያሲን ጀርባ ፣ ኡራኤል እና አካባቢው ፣

👉ጎላጎል ህንጻ ፣ፋንዲሻ ሆቴል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ፣ ወርቁ ህንጻ ፣ ቃል ፔኒሲዮን ፣ ዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ፣ ሻላ መናፈሻ፣ ለማ ስጋ ቤት ፣ ቺቺንያ ጫፍ ድረስ እና አካባቢው ፣

👉ድሬ ከአስፋልት በላይ፣ ገፈርሳ ውሀ ግድብ፣ ሲሊ፣ ከረላ፣ መናገሻ ፣ ኬላ ፣BM ሳይት ሲሼር ፣ ዘጸአት ፣ መናገሻ አበባ ልማት እና አካባቢው ፣

ከጠዋቱ 2፡00-12፡00

👉አዳማ፣ ጎሮ ቀበሌ፣ ዳቢ ቀበሌ፣ ቀበሌ 18፣ ጋምቤላ፣ ኢላ መውጫ፣ ኒግናንጊ፣ ጋምቤላ ቤተመንግስት፣ 1ኛ ኮብልስቶን፣ አየርጤና፣ ሰላም ሰፈር  እና አካባቢው ፣

ከጠዋቱ 2፡30-7፡30

👉ለቡ መብራት ፣ቫርኔሮ አደባባይ ፣ ለቡ መድሀኒያለም ፣ ለቡ ላቢያጆ ፣ ጀሞ 1 ፣ ካሳ ሳይት ፣ አፍሪካ ህንጻ ድረስ ፣ ጀሞ ሚካኤል እና አካባቢው ፣

👉ገላን ኮንዶሚኒየም (ልደታ ቤተ- ክርስቲያን አካባቢ) ፣ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ፣ አቃቂ ቴሌ ዌር ሀውስ፣ አንበሳ ጫማ ፣ አለምባንክ ፣ ከተማ ልማት ፣ ፊታውራሪ ት/ቤት ፣ አባ ቦራ እና አካባቢው ፣

👉ሐዋሳ፣ ተግባረ ዕድ፣ ሌዊ፣ ቅድስት ሥላሴ ኮንዶሚኒየም፣ ሚሽን መቃብር፣ ቲቲሲ፣ ብሌን እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍4
በኬኒያ የሚደረግ ድርድር የለም-TPLF‼️
ቀጣይ ሳምንት ህወሃትና የፌዴራል መንግሥቱ በኬኒያ ሊደራደሩ ነው በሚል በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ ውሸት መሆኑን የህወሓት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብረሃም ሐጎስ ዛሬ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ላይ ገልፀዋል።
አላማችን አራት ኪሎን መቆጣጠር ነው ብለዋል።
የፌደራል መንግሥቱ ምዕራብ ትግራይን ልስጣችሁ፣ተፈናቃዮች ይመለሱ ቢል እንኳን ጊዜው አልፏል ብለዋል።
መንግሥት አሁን ላይ በድሮን እና በአንቶኖቭ ሙሉ ጦርነት ከፍቶብናል ብሏል።
የፌደራል መንግስቱን ለመጣል ከተለያዩ ሀይሎች ጋር የተፈጠረው ስምምነት ወደመጨረሻው ምዕራፍ መድረሱን እና መግለጫ እንደማሰጥ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26🤣14👍12🌚3🤪1
የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር የሚል ምክረ-ሐሳብ ከስምምነት ላይ ተደረሰበት

እየተገባደደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች የስራ ቅጥርን በተመለከተ «የዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ቅጥር እንዲቀር» የሚል ምክረ-ሐሳብ አቅርበው ከስምምነት መድረሳቸው ተገለፀ።

በተጨማሪም በጉባዔው ውይይት ወቅት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ እንዲያቀርቡ የሚል አዎንታዊ ምክረ-ሐሳብ ተነስቶ ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል።

በአሁኑ ወቅት 500 አባላት ባሏቸው 8 ቡድኖች ተከፋፍለው ውይይታቸውን በማጠቃለል ላይ የሚገኙት ተወካዮች፣ በአብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ወደ መስማማት መምጣታቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ እስካሁን መስማማት ያልተቻለባቸው እና በይደር እንዲቆዩ የተደረጉ አጀንዳዎች የትኞቹ እንደሆኑ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ተወካዮቹ በምክክሩ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ የቀረቡትን ምክረ-ሐሳቦች በማጠናከር አጠቃላይ ወጥ የሆነ ሰነድ የማዘጋጀት ሥራ ጀምረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🙉2212👍3🤪3🤔2👀2
😢8💔71👍1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በድርቅ 16 ሰው😥‼️
በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ገለፁ‼️‼️
👉ከ17000 በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል።
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡

በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል።

ችግሩን በተመለከተ እስከ ክልል ድረስ አቤቱታ መቅረቡን የጠቆሙት አስተዳዳሪው፣ ከየቀበሌው የተመደቡ አካላት የሞቱ ሰዎችን፣ የተሰደዱ አባወራዎችን እና ያለቁ እንስሳትን ቁጥር መዝግበው ለሚመለከተው አካል ቢያሳውቁም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከመንግሥት የተደረገው ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች ብቻ የተሰጠ የሴፍቲኔት እርዳታ እንደነበርም አክለው ጠቁመዋል።

እየከፋ የመጣውን የረሃብ አደጋ ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የድንገተኛ እርዳታ ጥያቄ በማንሳት ሰልፍ መውጣታቸውን የገለጹት ጥላሁን፤ አሁንም አስቸኳይ ድጋፍ ካልቀረበ የአካባቢው ሕዝብ በረሃብ የሚያልቅበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲደርሱላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሼር አድርጉት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢33💔129👍4🥰1🤯1
የቻይና ኩባንያዎች በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በሚገነባው የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡ ድርጅቶች ውስጥ የበላይነቱን ያዙ

በኢትዮጵያ በ12.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ በሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ለመሳተፍ ከቀረቡት ድርጅቶች ውስጥ አብዛኞቹ የቻይና ኩባንያዎች ወይም ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የተመሰረቱ ድጅቶች መሆናቸውን የአቪዬሽን መረጃ አቅራቢ እና የዜና ፖርታል የሆነው ‘ch-aviation’ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ የተደረገው የእጩዎች ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ የቻይና ኩባንያዎች በከፍተኛ ልዩነት ትልቁን ቁጥር የያዙ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ላይ የቻይና ኢንጂነሪንግ እና ግንባታ ድርጅቶች ያላቸውን የጎላ ሚና የሚያሳይ ነው።

በተወዳዳሪነት የተመረጡት የቻይና ኩባንያዎች ቻይና ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ፣ ቻይና ኮንስትራክሽን ኤይትዝ ኢንጂነሪንግ ዲቪዥን፣ ቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን፣ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን፣ ቤጂንግ ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ቤጂንግ እርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ፣ ቻይና ፈርስት ሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ፣ ቻይና ናሽናል ኤሮ-ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ ቻይና ሬይልዌይ ቤጂንግ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ሻንዶንግ ሉቂያኦ ግሩፕ ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍7🤔3
ቀን 14/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
10👍2
በ216 ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በብልሹ አሰራር የተሳተፉ በ216 ሠራተኞች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል።

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል የ6 ሠራተኞች የቅጥር ውል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ነው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የገለጸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5👍3🙏2