አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17K photos
415 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
አሁናዊ መረጃ
ነሐሴ 12/2018
በደቡብ ወሎ በምዕራብ ቀጠና ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ።

በምዕራብ ወሎ ቀጠና በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከዛሬ ማለዳ 11 ሰዓት ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ገለፁ።

ውጊያው እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ በሚባሉት በዋናነት በመቅደላ ወረዳ፣ በተንታ እንዲሁም በደላንታ ቀጠናዎች በሚገኙ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሰባት የተለያዩ ንኡስ ግንባሮች ተከፍሎ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢13👍73🥰3🕊2🤪1
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ

​በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ የሆነና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ህገ-ወጥ የሀበሻ አረቄ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲደፋ ተደረገ።

​የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለጤና ጉዳትና ለወንጀል መበራከት መንስኤ በመሆኑ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢32👍158🍾3
ሰበር-መረጃ‼️
በትግራይ ክልል የድሮን ጥቃት‼️
በትግራይ ክልል በአንደርታ ወረዳ ልዩ ስሙ ቀዳማይ ወያኔ በሚባል አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል።
ምንጮች ለአዩዘሀበሻ እንደገለጹት ጥቃቱ ዛሬ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተፈፅሟል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ምሽት በዚሁ ቦታ ላይ ተራግፎ በነበረ ከባድ መሳሪያ፣ተተኳሽ እና ተሽከርካሪዎች ላይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17😢5🤔21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍31
ኢትዮጵያ የኤልኒኖ ክስተት በኃይል ማመንጨት አቅሟ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አስጠነቀቀች

የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚጠበቀው የኤልኒኖ ክስተት በውሃ ኃይል ላይ በተመሠረተው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል በማሳሰብ፣ ቅድመ ጥንቃቄዎችና ዝግጅቶች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ከውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች የሚመነጭ መሆኑን በመጠቆም፣ የኤልኒኖ ክስተት ከባድ የአየር ንብረት መዛባትንና በግብርናው ዘርፍ ላይ እንቅፋት ከመፍጠር ባሻገር በሀገራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ መዋቅር ላይ ስጋት እንደሚፈጥር አስታውቋል።

ተቋሙ አክሎ እንደገለጸው፣ በኤልኒኖ ምክንያት የሚመጣው የሙቀት መጨመር የዓለም አቀፍ የነፋስና የዝናብ ስርጭትን በማዛባት ከፍተኛ ድርቅና የውሃ እጥረት ያስከትላል። ይህም በውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን በመቀነስ በኃይል አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ መስተጎደል እንደሚፈጥር አስጠነቅቋል።

የዝናብ እጥረት ወደ ግድቦች የሚገባውን የውሃ መጠን በእጅጉ እንደሚቀንሰው የጠቆመው ተቋሙ፣ የውሃው መጠን ከዝቅተኛው የኃይል ማመንጫ ወሰን በታች በሚወርድበት ጊዜ ታርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ማመንጨት እንደማይችሉ አብራርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍5🤪2🤔1
መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲል ሕወሃት ከሰሰ።

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲሉ ሕወሃት መራሹ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከሰዋል።

የባለስልጣናቱ ክስ የተሰማው በሁለቱ ኃይላት መካከል ከዛሬ ነገ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለው ውጥረት እያየለ በመጣበት ወቅት ነው።

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉን ከላሊ ሃጋዚን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው የፌደራል ኃይሎች ከክልሉ መዲና መቀሌ በግምት 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳንደራ በተባለች መንደር ውስጥ ባለ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማእከል ላይ ጠዋት 4:00 ገደማ "የድሮን ጥቃት ፈፅመዋል" ብለዋል።

ደረሰ በተባለው የድሮን ጥቃት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት ባለስልጣኑ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዳልሰጡ ዘገባው አመልክቷል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ካህን ግን በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ተናግረዋል።

በድሮን ጥቃቱ የተወነጨፈው ሚሳኤል በአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ መውደቁን መመልከታቸውን የተናገሩት ካህኑ ለዜና ወኪሉ "በጥቃቱ የተገደለ አንድ ታጣቂ በቁስለኛ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ሲወሰድ አይቻለሁ" ብለዋል።

በህወሃት እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል ዳግም ጦርነት ቀስቃሽ ውጥረት ከተከሰተ ወዲህ የድሮን ጥቃት ሲፈጸም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህ ሁለተኛው ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍5😢3🤡3🕊1
የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር ገባ

የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1388/2017 መሰረት የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደውን አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል።

በዚሁ መሰረት መመሪያ ተዘጋጅቶ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚያስችለው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው፡፡

በመመሪያው መሰረት አንድ የውጭ ዜጋ ቢያንስ 150 ሺህ ዶላር ካፒታል ሊኖረው እንደሚገባ ተመላክቷል።

በተጨማሪም በመንግሥት ድጎማ የተገነቡ ቤቶችን መግዛት እንደማይችሉም ነው የተገለጸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3😢2
በድጋሚ የድሮን ጥቃት‼️
ከትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና ከመቀሌ 12 ኪሎሜትር እርቀት በምትገኘው እንደርታ ወረዳ፣ ኩሃ ቀዳማይ ወያኔ አካባቢ ዳንዴራ በተባለች መንደር ዛሬ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም በድጋሚ ከቀኑ 10:10 አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።
በዚሁ ቦታ ጠዋት 3:30 አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፣ ሌላ አንድ ታጣቂ ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ የዓይን እማኞችን እና የአካባቢውን አስተዳደር ጠቅሶ ዘግቧል።
ህወሃት በበኩሉ የፌዴራል መንግስቱ የድሮን ጥቃት ፈፅሞብናል ሲል የክስ መግለጫ አውጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍86🤪3🕊2🤝2
#USA🇺🇸

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ሰጥታው የነበረው ከለላ (TPS) መቋረጥን ለጊዜው እንዳይተገበር የከለከለው የፍርድ ቤት እገዳ መነሳቱን ኤቢሲ ኒውስ ዘገበ።

በአሜሪካ፣ ቦስተን የሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን የተሰጠው ጊዜያዊ የጥበቃ ከለላ (TPS) እንዲያቋርጥ መንገድ ከፍቷል።

በቦስተን የፌዴራል ዳኛ ብራያን መርፊ ዛሬ የጊዜያዊ ከለላ (TPS) መቋረጥን ለጊዜው ያገደውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አንስተዋል።

በዚህም የአሜሪካ የሆምላንድ ሴኪዩሪቲ (DHS) የኢትዮጵያውያን የTPS ጥበቃን ለማቋረጥ ሊወስድ የነበረውን እርምጃ ማስቀጠል ይችላል።

ውሳኔው በአሜሪካ ከ5,000 በላይ ኢትዮጵያውያንን የሚነካ ሲሆን TPS በአሜሪካ በሕጋዊ መንገድ እንዲኖሩና እንዲሰሩ እንዲሁም ከአገር መባረር ጥበቃ ይሰጣቸው ነበር።

ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያውያን የተሰጠው ጊዜያዊ የህግ ከለላ (TPS) " በኢትዮጵያ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ አይደለም " በሚል ነበር ፍርድ ቤት ከለላው እንዳይነሳ በጊዜያዊነት ያገደው።

አሁን በአሜሪካ ቦስተን የሚገኘው የፌዴራል ፍርድ ቤት ይህንን ከለላ አንስቷል። ከውሳኔው ጋር ተያይዞ አንዳንድ የሕግ ክርክሮች አሁንም በፍርድ ቤት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍7😢2🥰1
ግብጽ እና ኢትዮጵያን ለማደራደር‼️
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ከሰሞኑ ግብፅን በጎበኙበት ወቅት 'ዶናልድ ትራምፕ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል የውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት፣ ካይሮ እና አዲስ አበባን እንደገና ለማደራደር ያላቸውን ዝግጁነት መግለጻቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡15🤪8👍74🤔2🤣2👀1🙊1
ቀን 13/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ደመወዝ===350_400dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ደመወዝ===200-600 dollar
    ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0-5አመት
    የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ደመወዝ===13500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ደመወዝ===13000+
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0አመት
    የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ደመወዝ===14500
    ዖታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===አይጠይቅም
     የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ደመወዝ-15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ደመወዝ===15000+
      ፆታ===ወ/ሴት
      ልምድ===0አመት
      የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ደመወዝ===12500+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ደመወዝ===15000+
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ0===0አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ደመወዝ===14000
     ፆታ===ወ/ሴት
     ልምድ===0አመት
     የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
ደመወዝ===12000+
ፆታ===ወ/ሴት
ልምድ===0-1አመት
የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ደመወዝ===13,000
   ፆታ===ወ/ሴት
   ልምድ===0አመት
   የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ደመወዝ 14-22000
    ፆታ===ወ
    ልምድ=2አመት
    የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ደመወዝ=14500+
   ፆታ===ወ
   ልምድ===0-5አመት
   የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ደመወዝ===25000
   ፆታ=/ሴት
   ልምድ===0-አመት
   የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ደመወዝ===13500
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-1አመት
    የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ደመወዝ===16000
    ዖታ===ወ/ሴት
    ልምድ===አይጠይቅም
    የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ደመወዝ===10000+
     ዖታ===ወ/
     ልምድ===0-አመት
     የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ፆታ===ወ/ሴት
    ልምድ===0-2
    የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞0909174853
     📞 0907362385
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
11👍3
ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታ አቆጣጠር መመሪያውን ቀየረ

ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታዎች የሚቆጠሩበትን መመሪያ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ መቀየሩን ይፋ አድርጓል። እስከዛሬ ድረስ አንድ ቪዲዮ «ታየ» ተብሎ እይታው የሚቆጠረው ተመልካቹ ቢያንስ ለ30 ሰከንዶች ያህል ሲመለከት ነበር።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት ግን ቪዲዮው መጫወት እንደጀመረ በቀጥታ እንደ አንድ እይታ ተቆጥሮ የሚደመር ይሆናል ብሏል።

ይህ አዲስ አሰራር ዩቲዩብ አጫጭር ቪዲዮዎች ከሚቀርቡበት "Shorts" መድረክ ጋር አቆጣጠሩን አንድ ዓይነት ለማድረግና ወጥ አሰራር ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልጿል።

ይህ ለውጥ ይዘት አዘጋጆች የሚያገኙትን የቪዲዮ እይታ ቁጥር በጥቅሉ ሊጨምረው ቢችልም፣ የዩቲዩብ የገቢ ክፍያ እና ስፖንሰርሺፕ ግን አሁንም ተመልካቹ ቪዲዮውን ምን ያህል ሰዓት ተመለከተው (Watch Time) በሚለው መስፈርት ላይ ተመስርቶ እንደሚቀጥል ተብራርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1612
6 ሰዎች ወደአልታወቀ ቦታ ተወሰዱ‼️
በትናንትው ዕለት ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም በትግራይ ክልል ከመቀሌ 12 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በእንደርታ ወረዳ በዴንደራ መንደር ተደጋጋሚ የድንገተኛ ድሮን ጥቃቶችን ተከትሎ በአስተኳሽነት (OP) የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ወደማይታወቅ ቦታ መወሰዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ከስድስቱ ሰዎች ውስጥ አራቱ የታወቁ ሲሆን:-
1.ወይዘሮ ምሂራ ገ/መስቀል
2. አቶ ጸጋዬ ፍጹም
3. አቶ ደብሊው. በርሃን ኪንግ
4. አቶ ሃንስ አዲስ ናቸው።
ምስል:- በጥቃቱ ወቅት የተነሳ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍8🤔3🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የአገራዊ ምክክሩ አራት አጀንዳዎች ከስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣይ ዙር ተሻገሩ

በአገራዊ ምክክሩ የመንግሥት አደረጃጀትን ጨምሮ አራት አከራካሪ ጉዳዮች በ120 አባላት ያለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ስምምነት ሳይደረስባቸው ወደ ቀጣዩ የምክክር ሂደት መሻገራቸው ተገለጸ።

በአጀንዳው 500 ተሳታፊዎች ባሉበት የሥራ ቡድን 53 ጉዳዮች ቀርበው፣ 50 ላይ ስምምነት ሲደረስ ሦስቱ ግን ሳይስማሙ እንደቀሩ ቀደም ሲል ተገልጿል። የሐሳብ አዘጋጅ ቡድኑ እነዚህን ጉዳዮች በማጣጣም 62 ምክረ ሐሳቦች አድርጎ ሲያቀርብ፣ አራቱ ላይ የጋራ ስምምነት ሊደረስ እንዳልቻለ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል ዋነኛው የመንግሥት አወቃቀር ጉዳይ ሲሆን፣ አንደኛው አማራጭ ፓርላሜንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ እንዲመረጥ የሚደግፍ ሲሆን፣ ሌላኛው ፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት እንዲኖርና ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ቀጥታ እንዲመረጥ የሚል ነው።

ሌሎቹ ሁለት ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አመራረጥና በምክር ቤቱ የብሔረሰቦች ውክልና አሠራርን የሚመለከቱ ናቸው። በአባላት አመራረጥ ላይ አንዱ ሐሳብ አባላት በክልሎች ምክር ቤቶች እንዲመረጡ ሲደግፍ፣ ሌላው ሕዝቡ በቀጥታ እንዲመርጣቸው የሚል ነው።

በብሔረሰቦች ውክልና ላይም አንድ ሐሳብ በሕዝብ ብዛት መሠረት ተጨማሪ ውክልና እንዲኖር ሲደግፍ፣ ሌላው ሁሉም ብሔረሰቦች በእኩል መልኩ እንዲወከሉ የሚል ሐሳብ ቀርቧል።

አራተኛው አከራካሪ ጉዳይ “ውህድ ማንነት” የሚለው ሐሳብ ሲሆን፣ የሥራ ቡድኑ ቀደም ሲል በስምምነት አልፎ የነበረው ሐሳብ በ120 አባላት ባለው የሐሳብ አዘጋጅ ቡድን ዳግም የአለመስማማት ጉዳይ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መቅረቡንና ከስምምነት ይልቅ አለመስማማት በሚል ወደ ቀጣዩ ዙር መተላለፉን ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

በመሆኑም አራቱ ጉዳዮች በቀጣዩ የምክክር ዙር የበለጠ ውይይትና የመግባባት ሥራ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሆነው መቀጠላቸው ታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍5🤪2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አስደንጋጭ ነው‼️
በራያ አዘቦ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
አዝመራም አልተዘራም ብለዋል።
አሁን የክረምቱ መውጫ ሰዓት እየደረሰ ነው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔20😢7👍43😱1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
4👍3
የክልል "ልዩ ኃይል" መፍረሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲፈተሽ ተጠየቀ።

"በሀገራዊ ምክክሩ የተቋማት ግንባታ ቡድን ባደረገው ስብሰባ፣ የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲረጋገጥ ወይም ኦዲት እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ኦዲቱን የሚያደርጉት ደግሞ መከላከያ እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ማንኛውም የክልል የጸጥታ መዋቅር ከመከላከያ እና ከፌደራል ፖሊስ በላይ መሆን እንደሌለበት ተጠቁሟል ።

ክልሎች የሚኖሯቸው የሚሊሻ አባላትም በወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠኑ እንዲሆኑ ስምምነት ተደርጓል።

ይህ አሰራር የሀገሪቱን ሰላም በዘላቂነት ያስከብራል ትላላችሁ? ኮመንታችሁን አስቀምጡ!"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤪7👍2💔2🤔1🤣1