አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
18.1K photos
443 videos
23 files
3.08K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በባዶ እግር የመሄድ የጤና ጥቅሞችና የሚያስፈልገው ጥንቃቄ

በባዶ እግር መሄድ ወይም የእግርን አወቃቀር እና የነርቭ ሥርዓትን ለማጠናከር ተፈጥሯዊ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት የህክምና ጥናቶች እና የዘመኑ ሳይንሳዊ ግኝቶች ያመለክታሉ።

ሆኖም ይህን ልምድ ያለ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ ለአካባቢያዊ ጉዳቶች እና ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ሊያጋልጥ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ያሳስባሉ።

በባዶ እግር መሄድ የእግርን ተፈጥሯዊ ቅስት (Arch) እና ትንንሽ ጡንቻዎችን፣ ጅማቶችን እና እጥፎችን በማንቃት ያጠናክራል።

በተጨማሪም በእግር ስር ካሉ ነርቮች ወደ አእምሮ የሚላኩ መልዕክቶችን በማፋጠን የሰውነትን ሚዛን የመጠበቅ አቅም ይጨምራል።

ተፈጥሯዊ እርምጃዎችን በማስመዝገብ በወገብ፣ በወገብ መገጣጠሚያ እና በጉልበት ላይ የሚፈጠርን ጫና የሚቀርፍ ሲሆን፣ ጥብቅ ያሉ ጫማዎችን በማውለቅ በእግር ጣቶች ላይ የሚፈጠርን ውጥረት በመቀነስ የጣቶች መታጠፍን እና ህመምን ይቀንሳል።

በሌላ በኩል፣ በህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ወይም በቆሻሻ መሬት ላይ በባዶ እግር መሄድ ለፈንገስ፣ ለኪንታሮት መሰል የእግር እብጠቶችና ለጥፍር ፈንገስ ያጋልጣል።

እንደ ኮንክሪት ባሉ ጠንካራ መሬቶች ላይ በባዶ እግር መሄድ የእግርን ጅማት በመወጠር ለከፍተኛ የእግር ጅማት እብጠት ህመም የሚዳርግ ሲሆን፣ ስለታም ነገሮች፣ የመስታወት ስብርባሪዎች፣ እሾሆች እና በሞቃት መሬት የመቃጠል አደጋም ሊያጋጥም ይችላል።

በአጠቃላይ በባዶ እግር መሄድ በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ተፈጥሯዊ ልምድ ቢሆንም፤ የአካባቢውን ሁኔታ በማየት እና ተስማሚ ቦታዎችን በመምረጥ በደህንነት ማድረግ እንደሚገባ የህክምና ባለሙያዎች ያሳስባሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤21👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ያገኘው የጉልበተኝነት ክስተትይህ ቪድዮ ብዙዎችን አሳዝኗል

በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጨ የሚገኝ አጭር ቪዲዮ፣ በወጣቶች መካከል ስለሚከሰት ጉልበተኝነት እና አካላዊ ትንኮሳ የሚያስነሳ ጉዳይ ሆኗል።

በተሰራጨው ምስል ላይ አንዲት ወጣት በተቀመጠችበት ወቅት ከአንዳንድ ወጣቶች የሚመጣ ያልተገባ አካላዊ ትንኮሳ ሲደርስባት የሚመስል ሁኔታ ይታያል። ቪዲዮው በአጭር ጊዜ በተለያዩ ገጾች መሰራጨቱም ብዙ ሰዎች ስለጉዳዩ እንዲወያዩ አድርጓል።

ክስተቱ በተለይም በወጣቶች መካከል ስለሚፈጠር ጉልበተኝነት፣ የአካል እና የስነ-ልቦና ትንኮሳ የሚያስተምረን አንድ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

ቪዲዮውን ያዩ በርካታ ሰዎች ስለተስተዋለው ሁኔታ ሀሳባቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ ጉልበተኝነት በማንኛውም ሁኔታ መታገስ እንደሌለበት እና ወጣቶች እርስ በርሳቸው በክብርና በኃላፊነት መኖር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ጉልበተኝነት በቀላሉ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ አይደለም። በአካል ወይም በቃል የሚደርስ ትንኮሳ በተጎጂው ላይ የስነ-ልቦና ጫና ሊያሳድር ስለሚችል፣ ሁላችንም እንደ ማህበረሰብ ጉዳዩን በኃላፊነት መመልከት ይገባናል።

በተለይም እንደዚህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም ከመቅረጽና በማህበራዊ ሚዲያ ከማሰራጨት ይልቅ ሁኔታውን በኃላፊነት ማስቆም እና ተጎጂው ሰው እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ የበለጠ ተገቢ ነው።

ቦታው አለም ባንክ አካባቢ ነው እያሉ ሲሆን እንደዚህ አይነት ነገር ለትውልድ ከባድ ነውና የሚመለከተው አካል አሰፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን::

ጉልበተኝነትን እንቃወም፤ እርስ በርሳችን በክብር እንከባበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤18😢14👍8😡7💔5😱1👀1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍2❤1
የሶማሊ ብሔራዊ አየር መንገድ  ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ ሊመለስ ነው

ከሰላሳ ዓመታት በላይ አገልግሎት አቋርጦ የቆየው የሶማሊያ ብሔራዊ አየር መንገድ በቀጣዩ ወር በድጋሚ ሥራ ሊጀምር መዘጋጀቱ ተዘግቧል ።
 
ካፒታል ጋዜጣ እንዳስነበበው አየር መንገዱ በ 1991 በሀገሪቱ ከተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ መሥራት አቆመው ነበር።
 
አሁን ላይ በሁለት አዲስ የኤርባስ A320 አውሮፕላኖች አገልግሎቱን ለመጀመር እቅድ ተይዟል።

ይህ ድጋሚ መጀመር የሶማሊያን የአቪዬሽን ዘርፍ እንደገና ለመገንባት እና ከቀጠናዊ እንዲሁም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር ያለውን የአየር ትስስር ለማሻሻል ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ አካል መሆኑ ታውቋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍5❤4🌚2👌1
ከእናቶችና ህፃናት በጀት ተቀንሶ ለባለስልጣናት ስልክ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም ስነ-ምግብ ፕሮግራም ከተመደበው በጀት ላይ ተቀንሶ ለሁለት ዘመናዊ ስልኮች ግዢ መዋሉን የሚያሳይ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በርካቶች ለምን ሲሉ ቅሬታቸው እየገለፁ ነው።

በወጣው የቢሮው ደብዳቤና ደረሰኝ መሰረት፣ iPhone 17 Pro Max ስልኮች ግዢ በአጠቃላይ 796 ሺህ ብር  ወጪ ሆኗል ድርጊቱ ለተጋላጭ ወገኖች ከተመደበ የህክምናና የምግብ በጀት ላይ ገንዘብ ማዞር ነው በሚል በርካታ ዜጎች በድርጊቱ ተቃውሟቸውንና ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢33❤5👍2🤔2😱2🥱1
በጥቃቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ!

በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሲሰራጭ በነበረው አሳዛኝ የጥቃት ቪዲዮ ውስጥ ተሳትፋለች የተባለችው “ፈርደውስ” እና አባሪዎቿ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣንና የተቀናጀ ኦፕሬሽን በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ተደርገዋል።

ህብረተሰቡ መረጃዎችን ለህግ አካላት ብቻ እንዲያደርስ ቀደም ሲል የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ፣ የህግ አስከባሪዎቻችን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በመወጣት እውነታውን አጣርተው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር፣ ጥፋተኞችን ለፍትህ ለማቅረብ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ላሳየው ፈጣን ምላሽ ከፍተኛ ምስጋና እየቀረበለት ይገኛል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤58🫡18👍9🤯1🎉1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
❤6👍4
ኢትዮ-ኤርትራ‼️
የኤርትራ ሉዓላዊነት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም-የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር‼️
አሁን ባለው የኤርትራ-ኢትዮጵያ ውጥረት የኤርትራ ሉዓላዊነት ለድርድር የማይቀርብ መሰረታዊ ጥያቄ ነው' ሲሉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።
የንግድ ወደብ መዳረሻ መፈለግ ሌላ ጉዳይ ነው፤ የሌላ ሀገር ግዛትን ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ሌላ ጉዳይ ነው።" ብሏል።

ኤርትራ ከኢትዮጵያ የጠየቀችው የግዛት ጥያቄ የላትም፣ የኢትዮጵያን መሬት ወይም ሀብት አትጠይቅም እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘችውን ድንበሮች መለወጥ አትፈልግም። ኢትዮጵያ በቀጠናው የሚገኙ ወደቦችን በድርድር ለንግድ እንዳትጠቀም ኤርትራ ተቃውማ አታውቅም። በዓለም ላይ የባህር ዳርቻ የሌላቸው አገሮች የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት ሳይጥሱ የአጎራባች ሀገራት የባህር ዳርቻዎችን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ንግድ ያካሂዳሉ።
ኤርትራ የሌላ ሀገር ግዛት አትጠይቅም፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያ እና ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላማዊና ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ትሻለች።
ድርድር የማይደረግባቸው ጉዳዮች ግን የኤርትራ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ናቸው'ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍18🤣16❤12👀1
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
❤4👍2🥰1👌1
ሰበር
አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ!

ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ የምኅረት መጠየቂያ ሠነድ መፈረማቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርሰቲያን ታደለን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይንን ጨምሮ በርካታ እስረኞች የምኅረት መጠየቂያውን በመሙላት ስምምነታቸውን እንደገለጡ ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። አምስት ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ጨምሮ 30 ያህል እስረኞች ግን ሠነዱን 'አንፈርምም' ማለታቸው ታውቋል።

ሠነዱን አንፈርምም ካሉት መካከል፤ የአማራ ክልል ምክር አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፤ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደወሠን አሠፋ፣ መስከረም አበራ እና ጎበዜ ሲሳይ ይገኙበታል ተብሏል። የምኅረት ሠነዱን እንዲፈርሙ የቀረበላቸው እስረኞች 300 ገደማ እንደሚጠጉ ታውቋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍19❤13🤪6😢2🥰1🤣1
ቀን 12/12/18 የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
📞09 07 36 23 85
📞09 09 17 48 53
🇪🇹የስራ አይነት👉NGO phone opretor&reseption
    ✨ደመወዝ===350_400dollar
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===ድግ&ዲፕ
🇪🇹የስራ አይነት👉NGOበሁሉም ግማሽ ቀን/ሙሉ ቀን/አዳር/
    ✨ደመወዝ===200-600 dollar
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
   ✨ ልምድ===0-5አመት
    ✨የት/ት ደረጃ= ከ12 ጀምሮ
🇪🇹position👉፡ቡና አሻጊ ለexport
     ✨ደመወዝ===13500+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የ/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ውሀ ሽያጭ መኪና ላይ
    ✨ደመወዝ===13000+
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ብስኩት ፋብሪካ
    ✨ደመወዝ===14500
    ✨ዖታ===ወ/ሴት
   ✨ልምድ===0አመት
   ✨የት/ት=== ደረጃ-10+
🇪🇹positionትኬት ቆራጭ/ለባስ/ለባቡር/
     ✨ደመወዝ===15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===አይጠይቅም
     ✨የት/ደረጃ===6-12
🇪🇹position👉ስልክ ኦፕሬተር/ለድርጅት/NGO/ኤጀንሲ/
     ✨ደመወዝ-15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ሞዴል አሰልጥኖ
      ✨ደመወዝ===15000+
      ✨ፆታ===ወ/ሴት
      ✨ልምድ===0አመት
      ✨የት/ት ደረጃ===10
🇪🇹position👉ፕላስቲክ ፋብሪካ
     ✨ደመወዝ===12500+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹potition👉ጉዳይ አስፈፃሚ ለድርጅቶች
     ✨ደመወዝ===15000+
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ0===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ለስላሳ ፋብሪካ ውስጥ
     ✨ደመወዝ===14000
     ✨ፆታ===ወ/ሴት
     ✨ልምድ===0አመት
     ✨የት/ት ደረጃ===8ኛ-12
🇪🇹position👉እንግዳ ተቀባይ/reseption/
✨ደመወዝ===12000+
✨ፆታ===ወ/ሴት
✨ልምድ===0-1አመት
✨የት/ትደረጃ ==8-12
🇪🇹position👉አምፖል ማምረት
   ✨ደመወዝ===13,000
   ✨ፆታ===ወ/ሴት
   ✨ልምድ===0አመት
   ✨የት/ት ደረጃ===8+
🇪🇹position👉ሹፌር
    ✨ደመወዝ 14-22000
    ✨ፆታ===ወ
    ✨ልምድ=2አመት
    ✨የት/ት ደረጃ===ህዝብ1/ደረቅ/2/3/
🇪🇹position👉አካውንታት
   ✨ደመወዝ=14500+
   ✨ፆታ===ወ
   ✨ልምድ===0-5አመት
   ✨የት/ት ደረጃ===digree
🇪🇹position👉ሆስተስ
   ✨ደመወዝ===25000
   ✨ፆታ=/ሴት
   ✨ልምድ===0-አመት
   ✨የት/ት ደረጃ10-12
🇪🇹position👉ቴሌ ማርኬተር ሽያጭ
    ✨ደመወዝ===13500
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0-1አመት
    ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position👉ቀለም ፍብሪካ
    ✨ደመወዝ===16000
    ✨ዖታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===አይጠይቅም
    ✨የት/ት ደረጃ===አይጠይቅም
🇪🇹position👉 ጫኝ አውራጅ
     ✨ደመወዝ===10000+
     ✨ዖታ===ወ/
     ✨ልምድ===0-አመት
     ✨የት/ት ደረጃ==8-12
🇪🇹position===ማናጀር ለሆቴል
    🔶ደመወዝ===18,000
    ✨ፆታ===ወ/ሴት
    ✨ልምድ===0-2
    ✨የት/ት ደረጃ===digree
ማሳሰቢያ ስራው አ/አ ነዋሪ ለሆናቹ ብቻ ነው
☎️ 📞09 09 17 48 53
     📞 09 07 36 23 85
     አድራሻ መገናኛ ደራርቱ ህፃ
    ወደ 24 በሚወስደው መንገድ
  መብራቱን ተሻግሮ ሰኒ ህንፃ 3 ፎቅ
      ቢሮ ቁጥር 305
   
❤19👍3
የዴሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ፡
በአገሪቱ ታሪክ የከፋው ሆኖ ተመዘገበ

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቱ ታሪክ እጅግ የከፋው ሆኖ መመዝገቡን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ። ቫይረሱ ግንቦት ላይ መከሰቱ ከተወጀ ወዲህ ከ4,900 በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2,325 ደርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወረርሽኙን የስርጭት ፍጥነት "በየ30 ደቂቃው ሰው እየገደለ ነው" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በሽታው ከኮንጎ ውጪ በዩጋንዳ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ በትንሹም ቢሆን መታየቱ ተገልጿል።

ይህ አሁን የተከሰተው የቡንዲቡግዮ የተባለው የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ እጅግ ያልተለመደና እስካሁን የተረጋገጠ ክትባት የሌለው በመሆኑ ሁኔታውን የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታል። በአገሪቱ ለዓመታት የዘለቀው ግጭትና የሰዎች እንቅስቃሴ ስርጭቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ ያደረገው ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን ስርጭት በሦስት ወር ውስጥ ለመቀልበስ አልሞ እየሰራ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2😢2🙏1
ላሚን ያማል (Lamine Yamal) በአዲስ አበባ ‼

ተወዳጁ ቲክቶከር አዶናይ ባጋራው አስገራሚ ቪዲዮ መላው የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚ አስገርሟል።

የስፔንና የባርሴሎናውን የዓለም እግር ኳስ ድንቅ ኮከብ ላሚን ያማልን አናትና ጆሮ ሳይቀር Exactly የሚመስለውን ኢትዮጵያዊ ወጣት ይፋ አድርጎልናል።

የሁለቱ መመሳሰል እስከ አሁን ከተዩት ሁሉ በጣም አስገራሚው "Look-alike" ሆኗል! ብዙዎች “ኧረ የጠፋ ወንድሙ ነው የሚመስለው!”፣ “ፊቱ ብቻ ሳይሆን የፀጉር ስታይሉና ፈገግታው ሳይቀር ያማል ነው!” እያሉ ጉድ ብለዋል።

እስቲ እናንተስ ምን ትላላችሁ? በእውነት የላሚን ያማል ታላቅ/ታናሽ ወንድም ይመስላል ወይስ የአዶናይ ካሜራ ማጂክ ነው?

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤26🙉8👍3🤔1
የጤና ሚኒስቴር በፎርሙላ ወተት አጠቃቀም እና ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው

በህጻናት ፎርሙላ ወተት አጠቃቀም፣ ስርጭት እና ማስታወቂያዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና ክትትል ከዚህ ቀደሙ የበለጠ ጥብቅ ሆኖ እንደሚተገበር ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ጤና ሚኒስቴር እንዳለው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት ከሆኑ ምክንያቱች መካከል ምርቶቹ ከውጭ የሚገቡ በመሆኑ በቤተሰብ እና በሀገር ደረጃ ከፍተኛ የወጪ ጫና ማሳደራቸው፣ ያለአግባብ ፎርሙላ ወተት የሚወስዱ ህጻናት ለተለያዩ የጤና እክሎች እና ለተጨማሪ የሕክምና ወጪ መጋለጣቸው፣
እናቶች የተፈጥሮ ጡት ማጥባትን እንዲተው የሚያደፋፍሩ የተጋነኑ የማስታወቂያ ዘመቻዎችን መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብሏል።

በመሆኑም የፎርሙላ ወተት ስርጭትና አጠቃቀም በህጻናት ምግብ ቁጥጥር መመሪያ መሠረት በትክክል በሚያስፈልግባቸው አጋጣሚዎች ብቻ እንዲውል ይደረጋል ሲል አሳውቋል።

የሕግ ማዕቀፎችን በመጣስ የሚደረጉ የስርጭትና የማስታወቂያ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤14👍4😱1
አሁናዊ መረጃ❗❗
ነሐሴ 12/2018❗
በደቡብ ወሎ በምዕራብ ቀጠና ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ።

በምዕራብ ወሎ ቀጠና በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከዛሬ ማለዳ 11 ሰዓት ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ገለፁ።

ውጊያው እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ በሚባሉት በዋናነት በመቅደላ ወረዳ፣ በተንታ እንዲሁም በደላንታ ቀጠናዎች በሚገኙ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሰባት የተለያዩ ንኡስ ግንባሮች ተከፍሎ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢13👍7❤3🥰3🕊2🤪1
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ

​በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ የሆነና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ህገ-ወጥ የሀበሻ አረቄ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲደፋ ተደረገ።

​የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለጤና ጉዳትና ለወንጀል መበራከት መንስኤ በመሆኑ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢32👍15❤8🍾3
ሰበር-መረጃ‼️
በትግራይ ክልል የድሮን ጥቃት‼️
በትግራይ ክልል በአንደርታ ወረዳ ልዩ ስሙ ቀዳማይ ወያኔ በሚባል አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል።
ምንጮች ለአዩዘሀበሻ እንደገለጹት ጥቃቱ ዛሬ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተፈፅሟል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ምሽት በዚሁ ቦታ ላይ ተራግፎ በነበረ ከባድ መሳሪያ፣ተተኳሽ እና ተሽከርካሪዎች ላይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17😢5🤔2❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍3❤2