አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.2K photos
422 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
6👍2
በአንድ ጊዜ 5ሺህ የኒት ደም የሚያቀዘቅዘው ክፍል በባህርዳር ስራ ጀመረ
 
በአማራ ክልል የባሕር ዳር ደም ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ደም ባንኮች አንዱ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
 
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የባሕር ዳር ደም ባንክ ሁሌም የተሻለ አፈጻጸም የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ደም ባንኩ አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል  ስርአት በማዘመን በክልሉ የመጀመሪያው ደም ባንክ ነው።
 
ህብረተሰቡ  ደም የመለገስ ባህሉ ዝቅተኛ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በቀጣይ በክልሉ ደም መለገስ ባህል እንዲሆን የግንዛቤ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ   አስረድተዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍3
ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 ዶላር እንደሚያስፈልገው የሚደነግግ መመሪያን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አወጣ።

አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት ለመሆን የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።በመመሪያው መሠረት የውጭ አገር ዜጋ ማለት፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም ሰው ማለት ነው።

የውጭ አገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሠራር ለመወሰን የወጣው መመሪያ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው ሐምሌ ወር የጸደቀ ነው።በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተዘርዝሯል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በሸገር ከተማ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልገዋል።ሸገር ከተማን ሳይጨምር በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ ክልል፣ በሐረሪ ክልል ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ደግሞ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን 120000 የአሜሪካ ዶላር ማቅረብ ነው።

ከሌሎቹ ክልሎች የውጭ አገር ዜጋ የቤት ባለቤት ለመሆን ዝቅተኛ ገንዘብ የሚጠየቀው በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልል ሲሆን የገንዘቡ መጠን ደግሞ 100000 ዶላር እንደሆነ ተደንግጓል።

አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው የቤት መጠን አንድ ብቻ ነው።በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፈቃድ ወስዶ እያለማ ያለ ባለሀብት ግን ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ሳይገድበው የአንድ ቤት ባለቤት መሆን ይችላል።

በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የተጠቀሰውን ለአንድ ቤት የሚያስፈልግ ገንዘብ የሚያስቀምጥበት የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትለትና ገንዘቡን በውጭ ምንዛሬ እንዲያስቀምጥ የሚፈቅድ ደብዳቤ ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት በማጻፍ በመረጠው ባንክ ገቢ ማድረግ አለበት።

አንድ የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ፈቃድ የሚያገኘው፤ የጸና ፓስፖርት ካለው፣ የወንጀል ታሪክ የሌለው ስለመሆኑ ከሚኖርበት አገር ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ነው።

በተጨማሪም ከሀገር ሰላም፣ ደህንነት፣ ጸጥታ፣ የሕዝብ ጥቅም፣ የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃም ማቅረብ አለባቸው ይላል መመሪያው።

ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በመንግሥት ቀጥተኛ ድጎማ ለዜጎች በሚሠሩ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን አይችልም፤ ይህም የቤት ባለቤት በሚሆኑ የውጭ ዜጎች ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ በወጣ አዋጅ የተጣለ ገደብ ነው።

በአዋጁ መሠረት የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋም ወይም ምንጭ ገንዘብ መበደር ወይም ካፒታል ማሰባሰብ አይችልም።

በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት የሆኑ የውጭ ዜጎችን መብት በተመለከተ ደግሞ መመሪያው ሲዘረዝር ለኢትዮጵያውያን የተሰጡ የንብረት መብቶች ይኖራቸዋል፤ ለግለሰቦች ማከራየት ይችላሉ፣ ለንግድ ዓላማ ማከራየት ግን አይቻልም።

ለራሱ እና ለቤተሰቡ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የመግቢያ ቪዛና ኢትዮጵያ መመላለስ እንዲችሉ የሚያደርግ አግባብነት ባለው አካል የሚሰጥ እስከ አምስት ዓመት የሚያገለግል የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ የማግኘት መብት አላቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ እና አሠራር መሠረት ከመኖሪያ ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የሚያገኘውን የኪራይ ወይም የሽያጭ ገቢ በወቅቱ ተመን በውጭ ምንዛሪ ወደ ውጭ አገር የማስተላለፍ መብት አለው ይላል አዋጁ።

መመሪያው ታትሞ በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ ከተጫነበት ቀን ጀምሮ ሥራ ላይ ይውላል ይላል።በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ የተጫነው ባለፈው እሁድ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።Via Sheger

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤣14👍2🤯1
ከራያ በጦርነት ስጋት የሚሰደዱ ሕጻናትና ወጣቶች የአጋቾች ሰለባ እየሆኑ ነው ተባለ

ከራያ አካባቢ በጦርነት ስጋት የሚሰደዱ ወጣቶችና ሕጻናት፣ ወደ የመን በሚያደርሱ ደላሎች አማካይነት የአጋቾች ሰለባ እየሆኑ መሆኑ ተገለጸ።

በቆቦ ከተማ ከራያ አላማጣ፣ ኮረም፣ ኦፍላ፣ ዛታና አካባቢዎቻቸው በጦርነት ምክንያት ከ100 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ተብሏል።

አብዛኞቹ ወጣቶች የሆኑት ተፈናቃዮች የምግብና የመጠለያ እጥረት በመጋፈጣቸው ወደ ውጭ ለመሰደድ እየተገደዱ መሆኑ ተመላክቷል።

ይህንን ሁኔታ የሚጠቀሙ ደላሎችም ጉዞውን በነጻ እንደሚያስጀምሩ በመናገር ወጣቶችን እንደሚያግባቡ ተገልጿል።

የመን ከደረሱ በኋላ ግን በአጋቾች እጅ በመውደቅ ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተነግሯል።

የጀርመን ድምጽ ያነጋገራቸው ወጣቶች፣ በስደት ጉዞ ላይ ችግር እንደሚገጥማቸው ቢያውቁም፣ በቆቦ ከተማ ካለው ኑሮ የተሻለ እንደሚሆን በማሰብ ስደትን እንደመረጡ ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በአብዛኛው አዋቂዎች ይሰደዱ እንደነበር የገለጹት ወጣቶቹ፣ አሁን ግን ሕጻናትና ሴቶችም በስደቱ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

ወጣቶቹ በቆቦ ከተማ ተረጋግተው ከመቀመጥ ይልቅ በሕገወጥ መንገድ ወደ ዓረብ ሀገራት መጓዝን እንደሚመርጡም ዘገባው አመልክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10😢5👍3
በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው
 
በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ።
 
ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል።
 
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል።
 
በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ  ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል።
 
በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።
 
የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
 
ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😡17🤣96👍3🤔2😢1💔1
በኮሎምቢያ በተከሰተ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 132 ሰዎች ሲሞቱ 480 ተጎዱ።

በበርካታ ሕንጻዎች ፍርስራሽ ሥር ሰዎች ተቀብረዋል የሚል ስጋት በመኖሩ የሟቾች ብዛት ከ132 ሊጨምር እንደሚችልም ተገልጿል።

በኮሎምቢያ ከባድ መሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፣ ይህም በሬክተር ስኬል 7.4 ሆኖ ተመዝግቧል። በቾኮ ግዛት የተከሰተው አደጋው ከመሬት በ103 ኪሎሜትር በታች የተከሰተ እንደሆነ የአገሪቱ የጂኦሎጂካል አገልግሎት አሳውቋል።

በመሬት መንቀጥቀጥ ከ480 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ከመሬት መንቀጥቀጥ መነሻ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፒሬራ ከተማ የከፋው ጉዳት ተመዝግቧል።

ቢቢሲ ትክክለኛነቱን አረጋገጥኩት ያለው አንድ ቪዲዮ፣ 'ፕላዛ ቦሊቫር' በተባለው የከተማው ዋና አደባባይ የሚገኝ አንድ ሕንፃ ሲደርመስ አሳይቷል። በርካታ ሰዎች ተሰብስበውበት የነበረ ስፍራ በፍርስራሽ እና አቧራ ሲሞላም ይታያል።

በከተማው 40 ሰዎች መሞታቸውን እና 65 ሕንፃዎች መፍረሳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በ15ቱ ሕንፃዎች ፍርስራሽ ስር ሰዎች ተቀብረው ሊሆን እንደሚችልም ይታመናል።

ከመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ካሊ ከተማ ውስጥ ደግሞ 32 ሕንፃዎች ፈርሰዋል።

በቾኮ እና ቫሌ ዴል ካውካ ግዛቶች በሚገኙት ማኒዛሌስ፣ ኪብዶ እና ሜዴሊን ከተሞችም የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘግቧል። ንዝረቱ በጎረቤት አገራት ቬንዙዌላ፣ ኢኳዶር እና ፓናማም ደርሶባቸዋል።

የአሁኑ አደጋ የተከሰተበት ኮሎምቢያ አጎራባች በሆነችው ቬንዙዌላ ከ6 ሺሕ በላይ ሰዎች በተመሳሳይ አደጋ መሞታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። #Bbc

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔86👍3
ግልገል በለስ‼️
በጋራ ግልገል በለስ ከተማን ለመቆጣጠር ሞክረዋል - የመተከል ዞን አስተዳደር‼️
የመተከል ዞን አስተዳደር የፋኖ ሀይሎችና የጉሙዝ ሀይሎች ግልገል በለስ ከተማን ዛሬ ማለትም ነሐሴ 5/2018 ከንጋቱ 12:00 ሰዓት አካባቢ ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበረ ገለፀ።

የዞኑ አስተዳደር ይሄ ኦፕሬሽን እንዳልተሳካና ከተማውም ወደ ቀድሞ ሰላሙ መመለሱን አስታውቋል።

በከተማዋ ዋና መንገድ መድፍ ጭምር ሲንቀሳቀስ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ የገለፁ ሲሆን ጠዋት አካባቢ በከተማ መናኸሪያ ውስጥ ፈንጂ በማፈንዳት በርካታ ተሳፋሪዎች እንደተጎዱ እና እንዲሁም 10 ሰዎች እንደሞቱ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። ተጎጂዎች ፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀውልናል።
ምስል:- ከግልገል በለስ ከተማ(የመድፍ እንቅስቃሴ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16💔3👍2🤪2
ባለቤቱን በመግደል የተከሰሰው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በአዲግራት ከተማ ቀበሌ 06 ዞን 6 ነዋሪ የሆነው አቶ ሳምሶም ሓጎስ አብርሃ የተባለው ተከሳሽ የሁለት ልጆቹ እናት የሆነችውን የ22 ዓመቷን ባለቤቱን ወይዘሮ ቅሳነት ተሾመን መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፈፀመው አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው በ21 አመት ከ 3 ወር ፅኑ እስራት የተቀጣው።

የምስራቅ ትግራይ ዞን ዓቃቤ ሕግ አቶ መሓሪ እንደገለፁት ተከሳሹ በከባድ የነፍስ ግድያ ወንጀል ተከሰሶ ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሞ የማያውቅ  እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበረ መሆኑን እንደ ማቅለያ እንዲሁም ሁለት የማክበጃ ነጥቦችን በመያዝ ሕግን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ሰጥቷል ብለዋል።

በአዲግራት ከተማ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበር እና የሴቶች ጉዳይ ፅህፈት ቤት በበኩሉ በአሁኑ ወቅት በሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እና ነፍስ ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ገልጾ የሕግ ባለሙያዎች ግንዛቤ እንዲፈጥሩ እና ማህበራትም ተጎጂዎች ፈጣን ፍትህ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል የተበዳይ ቤተሰቦች ፍትህ ለማግኘት ረጅም ጊዜ እንደወሰደባቸው በመግለፅ የፍርድ ቤቱን የቅጣት ውሳኔ እንዳልተቀበሉትና ደስተኛ እንዳልሆኑ መግለፃቸውን ብስራት ከአዲግራት ከተማ የኮሚኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🤯4👍3
በደቡብ ትግራይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ባለሥልጣናት መካከል ያለው ውጥረት ዳግም አገረሸ

ህወሓት የፌደራል መንግሥት ኃይሎች ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በደቡብ ትግራይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል ሲል መክሰሱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ውጥረት ዳግም ማገረሹ ተገለጸ።

በጥቃቱ በደረሰው የጉዳት መጠን እና በኢላማዎቹ ላይ የተለያዩ ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ጥቃቱ የተፈጸመው በአማራ ክልል አዋሳኝ አቅራቢያ በራያ አላማጣ ወረዳ መረዋ ቀበሌ ውስጥ መሆኑ ተዘግቧል።

ኤኤፍፒ (AFP) የትግራይ ባለሥልጣናትን እና የሕክምና ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በጥቃቱ አንዲት ሴት እና ሶስት ወንዶችን ጨምሮ ሶስት የትግራይ ኃይል አባላት ቆስለዋል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ መንበር አማኑኤል አሰፋ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በመረዋ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል ሲሉ ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

ጥቃቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መታቱን የተናገሩ ሲሆን፣ ኤኤፍፒ ግን ይህንን መረጃ በተናጠል ማረጋገጥ አለመቻሉን ገልጻል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍3👀1
ሶስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ!

🔴 ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም

🔴 የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ብቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት)

በአሜሪካ ኦሪገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል።

ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጓዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል።

ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ፖሬትላንድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጧል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን በአሁን ሠዓት ከፖርትላንድ ተነስቶ ወደ ቺካጎ አየር ማረፊያ እየተጓዘ ሲሆን እነዚሁ ሰባቱ የቡድኑ አባላት ከልዑኳን ቡድኑ ተለይተው መቅረታቸውን ነው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ያረጋገጠችው።

እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ከሄዱት አራት አሠልጣኞች ሶስቱ ከቡድኑ ጋር ባለመመለሳቸው በአሁን ሠዓት ወደ ኢትዮጵያ በመገስገስ ላይ በሚገኘው አውሮፕላን ውስጥ አንድ አሠልጣኝ ማለትም አሠልጣኝ መሠረት  ብቻ እንደሚገኝ ነው ምንጮቻችን የገለፁልን።

አትሌቶቻችን በተመለከተ አራት አትሌቶች እንደኮበለሉ የገለፁልን የመረጃ ምንጮቻችን በወኪንግ፣በ800፣በ5ሺ እና በ3ሺ መሠናክል ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ከቡድኑ ጋር አብረው እንዳልተመለሱና እንደኮበለሉ ነው የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው የገለፁልን።

የአትሌቶቹና የአሠልጣኞቹ ሙሉ ስም የደረሳት ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ለቤተሠቦቻቸውና ለደህንነታቸው ስትል የሁሉንም ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች።

የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካታ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና  አመራሮች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21👌18🤣14👍6🏆2👀1🙊1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
በአዲስ አበባ ከተማ የ26 ዓመቷ እናት አራት ህፃናትን በአንድ ጊዜ በሰላም ተገላገለች

በአዲስ አበባ በሚገኘው ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የ26 ዓመቷ እናት አራት ህፃናትን በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏ ተሰምቷል።
 
እናትየዋ አራት ፅንሶችን መፀነሷ በእርግዝና ክትትል ወቅት መለየቱን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር እሸቱ ታደለ ገልጸዋል።

አራት ፅንሶችን የያዘ እርግዝና ለእናቲቱም ሆነ ለሚወለዱት ህፃናት ከፍተኛ ክትትልና ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ የወሊድ ቀኗ ከመድረሱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በሆስፒታሉ ዋርድ እንድትቆይ ተደርጎ የሌት ተቀን ክትትል ሲደረግላት ቆይታለች።

በወሊድ ወቅትም ለአራቱ ጨቅላ ህፃናት የሚያስፈልጉ ማረፊያዎችና የድጋፍ መሳሪያዎች አስቀድመው መዘጋጀታቸውን ዶ/ር እሸቱ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ ከጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በዶ/ር እሸቱ ታደለና በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ናትናኤል የተመራው የህክምና ቡድን የቀዶ ጥገና ሂደቱን በስኬት ማጠናቀቁን ሆስፒታሉ አስታውቋል።እናትየው እና አራቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በሆስፒታሉ ከሦስት ዓመት በፊት የ24 ዓመቷ እናት በሪፈር ከጤና ጣቢያ መጥታ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተገልጿል።

ተቋሙ በዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂና መሳሪያዎች የተደራጀ ሲሆን በየህክምናው ዘርፍ የተሰማሩ ስፔሻሊስቶችና ቁርጠኛ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸው ለተሳካው የህክምና ሂደት አስተዋፅዖ አድርጓል ተብሏል።

ሆስፒታሉ በተለይም ለእናቶችና ህፃናት ጤና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ እና  እንደዚህ ያሉ ከፍተኛ ጥንቃቄና ልዩ ክትትል የሚፈልጉ እርግዝናዎችን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ የ“እናት ጤና፣ ልጅም ደህና” የሚለውን የጤና መርህ በተግባር ማዋል አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
33👍12🙉9🤔3🥰1
"የኢትዮጵያ ወጣቶች የሉዓላዊነታችን ፅኑ ማገር ናቸው" አሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
 
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት እንደማይቻል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ ወጣቱ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ድርሻ የሚይዝ እና የሁለንተናዊ እድገት መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በሚከበረው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፦ "የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው" ብለዋል። አክለውም የአሁኑ ትውልድ የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
 
አሁን ያለው ወጣት ሀገርን ወደኋላ የሚያስቀሩ አጓጉል ልማዶችን፣ አላስፈላጊ ንትርኮችን እና ግጭቶችን በመራቅ ትኩረቱን በልማት ላይ ማድረጉንና ድህነትን የተጸየፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
 
በመጨረሻም ሀገራዊ ርዕይን ዕውን ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በንቃት እየተጋ በፍቅር እና በአንድነት እንዲመላለስ ጥሪ አቅርበዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣6812👍2🥱1👀1🤪1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 በአላቡጋ ስታርት አማካኝነት በሩሲያ ውስጥ ስራዎን ይጀምሩ! 🌟

ትምህርት አጠናቀዋል? እንግዲያውስ አሁን የወደፊት ሕይወትዎን የመምረጥ ጊዜ ነው። የአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣት ኢትዮጲያውያን ሴቶችን ኦፊሴላዊ የሙያ ሥልጠና እና በሩሲያ ውስጥ ስኬታማ የሥራ ጅምር የመገንባት ታላቅ ዕድል ይሰጣል።

ይህ ሁሉን አቀፍ ፕሮግራም በእያንዳንዱ እርምጃዎ ላይ እንዲደግፉዎ የተነደፈ ሲሆን ጥሩ ደሞዝ፣ ነፃ የአየር ቲኬት፣ አጠቃላይ የሕክምና መድን እና የተሟላ ምቹ መኖርያ ቤት በድጎማ ይሰጣል። በተጨማሪም ስራዎን ለማስተካከል እና ለማሳደግ የሚረዱዎትን ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ።

በፕሮግራሙ በምርት ኦፕሬተር፣ የምግብ አገልግሎት፣ የምግብ አቅርቦት እና የእንግዳ ተቀባይነት አገልግሎቶችን ጨምሮ ስምንት የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ማመልከት ይችላሉ።

አሁኑኑ በማመልከት እና የእድሉ ተጠቃሚ በመሆን ህልሞችዎን ዛሬውኑ መገንባት ይጀምሩ። ለበለጠ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት ማመልከቻ ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
3👍1
መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር

መንግስት ያቀረበውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም ያሉ ተከሳሾች እነማን እንደሆኑ የሚያመላክት የስም ዝርዝር አዲስ ማለዳ የደረሳት ሲሆን በዚህ መዘርዝር ውስጥ በዋናነት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ወንደወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጎበዜ ሲሳይ፣ ገነት አስማማው ይገኙበታል፡፡

ሙሉ ዝርዝራቸው ተከታዩ ነው፡-

1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ
5. ዶ/ር መሠረት ቀለመወርቅ
6. ዶ/ር ዘሪሁን ባህሪው
7. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ
8. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
9. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
10. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ
11. ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ
12. አቶ አለልኝ ምህረት
13. አቶ መንበር አለሙ
14. አቶ ማይክ መላክ
15. አቶ አሳምነው ታደሠ
16. አቶ ደሳለኝ እጅጉ
17. አቶ እሱባለው በለጠ
18. አቶ እስክንድር ሽፈራው
19. አቶ መሰለ ቸሩ
20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ
21. አቶ ጫኔ ዘየደ
22. ወ/ት ሃሊማ አህመድ
23. ወ/ት ህይወት አለማየሁ
24. አቶ ሲሳይ መልካሙ
25. አቶ ታደሰ ወዳይነው
26. አቶ በላይ ሲሳይ
27. አቶ ያሬድ ግርማ
28. አቶ ማረው ስለሺ
29. አቶ ሠለሞን ተፈሪ
30. አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ

ለአዲስ ማለዳ የደረሳት ደብዳቤ እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ከመንግስት ጋር በጀመረው ውይይት በመጨረሻ ፈርሙ የተባሉት ተከታዮቹን ጉዳዮች ያካትታል፡-

“በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት ውሰዱ፤ በአማራ ክልል በተፈጠረው ቀውስ ለሞቱ ሰዎች፣ ለቆሰሉ  ሰዎች (በየመዝገብ ቁጥሩ ይለያያል) ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤ ለወደመው በበሊዮን የሚገመት ንብረት ፈጽመናል ብላችሁ እመኑ፤  ሀገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እና እሳቤ ካልተመራች ማለታችሁን ወንጀል ነው በሉ፤ ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ”  በቅድመ ሁኔታ እንደቀረበላቸው አዲስ ማለዳ የተመለከተችው  ያመላክታል፡፡

ይህንን ተከትሎ ተከሳሾቹ በሰጡት ምላሽ “እኛ ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ በህግም፣ በሞራልም፣ በታሪክም ተቀባይነት የለውም ብለን አንፈርምም” ብለዋል፡፡ 

አክለውም፤ “የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችም ህጋዊ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ በመግለጽ የ60 ሚሊዮን ህዝብን መልካም እሴት ወንጀል ነው ብለን አውቀን አንሰጥም ወንጀልም አይደለም፤ በህገመንግስት እና በዓለምአቀፍ ህጎች ነፃ ሆኖ የመኖር መብታችንን ፈቅደን አንተውም፤ በህግ የተከለከለውን ራስን መከላከል እና ራሳችንን ወንጀለኛ አናደርግም” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውን መመልከት ተችሏል፡፡

Via Addis Maleda

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
44👍10🫡1
ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ‼️
ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ።
እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር ፦

በመደበኛ/ ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው።

በአጭር ቪዲዮዎች /Shorts / በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።

የ1,000 ተከታዮች መስፈርት አልተለወጠም።

ይህ ለውጥ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍3🤔3😱2😎2😢1
በአማራ ክልል ግጭት የተከሰሱ ከ300 በላይ ግለሰቦች የይቅርታ ሂደት ላይ ናቸው

📌በይቅርታ ሂደቱ ላይ ምን ተፈጠረ?

በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ክስ በእስር ላይ የሚገኙ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጣኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ የመደራደር ሂደት እየተካሄደ ይገኛል። ሂደቱን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ አደራዳሪነት የተመራ እንደሆነ ተገልጿል።

ለተከሳሾቹ የቀረበው የይቅርታ ሰነድ በክልሉ ለተፈጸሙ ግድያዎች እና ጉዳቶች ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ ቅድመ ሁኔታ ያካተተ ነው። አብዛኞቹ ተከሳሾች ሰነዱን የፈረሙ ቢሆንም፣ ፖለቲከኞችን እና የሜዲያ ባለሙያዎችን ጨምሮ ቢያንስ 30 ያህሉ ግን «ቅድመ ሁኔታውን አንቀበልም» በማለት ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም።

በሌላ በኩል የሕግ ባለሙያዎች እንደሚረዱት፣ ይቅርታ የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ ለቀረበባቸው ሰዎች በመሆኑ፣ ገና በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ ተከሳሾች ከእስር ሊፈቱ የሚችሉት በይቅርታ ሳይሆን ክሳቸው ተቋርጦ በምህረት መሆን አለበት ሲሉ ያስረዳሉ።(መረጃው የቢቢሲ አማርኛ ነው)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍2🙉2🕊1
❗️“ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውን ትርክት የፈጠረው ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ነው ሲሉ ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ

​ ​በኬኒያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ትናንት ምሽት ከአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ፣ በግል ህይወታቸው እና በወታደራዊ አገልግሎታቸው ዙሪያ ለሚነሱ ትችቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

​አምባሳደሩ በዚሁ ቆይታቸው “ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውና በሰፊው የሚናፈሰው ትርክት ያለምንም ማስረጃ በሟቹ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የተቀናበረ መሆኑን ተናግረዋል። “ጄነራልነት የሰጠኝ ብሄራዊ ቲያትር አይደለም” ያሉት ጄነራል ባጫ፣ ምርኮኛም ሆነ ዳንሰኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ “የማረከኝ አካል ካለም ይውጣና ይናገር” ሲሉ የቀረቡባቸውን ወቀሳዎች አስተባብለዋል።

​አክለውም ይህ አይነቱ ትችት በግል እሳቸው ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን፣ ከወጡበት የብሄር ማንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ስልታዊ ስም ማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣5313👍2🤔2👀1
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ  የኃይል አቅርቦት

ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ትግሬ ሰፈር፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ እና አካባቢው ፣

👉 ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ፣ መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ ፣ ቆሬ አደባባይ፣አሚጎ ኮንዶሚንየም ፣ ፋና ት/ቤት ፣አርሴማ ቤ/ክ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ ጀርመን አደባባይ እና አካባቢው ፣

👉ባህርዳር ቀበሌ11፣ቴሌ፣ምድረገነት፣ አዲሱ  አስፓልት፣ ቀበሌ14፣ ልደታ፣ ይባብ፣ ባታ፣100ካሬ፣ ኮቲና፣ሙሉጌታ ሪልስቴት፣ አቡነሃራ፣ ዱዱ፣ ጨለንቆ፣ ቀርሳ፣ ቆሎሚ፣ ቁልቢ እና አካባቢው ፣

👉ድሬ ከአስፋልት በታች፣ ጉዳ፣ ኬላ፣ ጉዮ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ቶልቻ ፣ ሰሪፊ ፣ ጉጄ ፣ ቶልቻ ፣ ታጠቅ ኢንዱስትሪ ፣ ፌስቱላ ማዕከል እና አካባቢው፣

👉ኮተቤ ኮሌጅ  ፣ መሳለሚያ ፣ ኮተቤ አማኑኤል ሆስፒታል ፣ ዘርፌ ቦኖ ፣ ፍናን ዶቦ ፣ ቀርሳ ሚካኤል እና አካባቢው፣

👉ጥሩ መናፈሻ፣ አባዶ ኮንዶሚኒየም በከፊል፣ጣፎ አያት ኮንዶሚንየም ፣ ሳራ አምፓል ፣ኮተቤ ካራ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉ቀራንዮ መድህንዓለም ቤ/ክ ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ ፣ መስኪድ ፣ ቤተል ፓስታ ቤት ፣ኮልፌ ወ.8  እና አካባቢው

👉ሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦርሀይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ፣ ቻይና ኢንባሲ፣ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስኪድ እና አካባቢው፣ 

👉ግራር ኮንዶሚኒየም ፣ አለምባንክ ፣ ትሮፒካል ፣ አየር ጤና ኪዳነ ምህረት ፣ ጣፎ ገብርኤል ፣ ገመናይ ማርያም እና አካባቢው፣

👉ካራ ፣ ናትራን ፣ ለማ ነጎ ት/ቤት ፣ አየር ጤና ፣ አየር ጤና ኪዳነምሕረት ፣ አየር ጤና ሞቢል ፤ ፉሪ ፣ ሰይድ ያሲን ጀርባ፣ ኡራኤል  እና አካባቢው ፣

ስለሆነም በአካቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍3🆒1