ተጨማሪ መረጃ‼️
ዛሬ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በራያ አላማጣ ወረዳ በመረዋ ንዑስ ወረዳ የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በአራት ዙር መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል።
እንደ የአካባቢው ምንጮች ገለጻ፣ ጥቃቱ:-
📌በመረዋ 2ኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
▪️📌በችግኝ ጣቢያው አካባቢ በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
▪📌ከቤተ-ክርስቲያን አለፍ ብሎ ባለው ዋርካ (ዳዕሮ) ዛፍ ስር በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
📌ሚይ ሓርማዝ በሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተፈፀመው።
ጥቃቱ በአራት ዙር የተፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታጣቂዎች ተሰውተዋል።
የተጎዱ ታጣቂዎች ደግሞ ወደ አላማጣ ለህክምና ተወስደዋል። መረዋ አካባቢ በሚገኝ በአንድ የቤተክርስቲያን ዋሻ ውስጥ የህክምና አገልግሎት መስጫ አዘጋጅተው ነበር ተብሏል።
Via : አዩዘሀበሻ
@Addis_Reporter

❤13👍8
ውጊያውን አናንዛዛውም:-ጄኔራል ባጫ ደበሌ‼️
'ሱዳኖች ጦርነት እጀምራለሁ ብለው ካሰቡ አናንዛዛውም‼️
የሱዳን መንግስት በራሱ ጦርነት ነው ያለው። የሱዳን መንግስት የራሱን ጦርነት ሳይጨርስ ወደ ኢትዮጵያ የሚያልፍ ከሆነ እድሜው አጭር ነው፣ይጠፋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን ሙሉ አቅምና ሃይሉን ተጠቅሞ መጨረስ ነው የሚፈልገው።እንደ በፊቱ የሚንዛዛበት ምክንያት የለም። ጀመርክ በአጭር ግዜ መጨረስ ነው፣ እንደበፊቱ ምሽግ ይዘህ ደጀን ይዘህ፣እረፍት አድርገህ እንደገና ላደራጅ...ወዘተ በሚል የምትሮጥበት አይደለም። ውጊያው በቴክኔሎጂ ነው'ሲሉ ተደምጠዋል።

🤪37👍22❤12🫡2
የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ለአውሮፓ ትልቁ የጄት ነዳጅ አቅራቢ መሆን ቻለ
የናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ብቻ ለአውሮፓ ከገባው አጠቃላይ የጄት ነዳጅ ውስጥ አምስተኛውን ድርሻ በመያዝ (ከ2.06 ሚሊዮን ቶን ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ ቶን በማቅረብ) ለአሁኑ ወርም ከአሜሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ቀድሞ የአውሮፓ ትልቁ የውጭ አቅራቢ መሆን መቻሉ ተገለፀ።
ይህ አፈጻጸም የተመዘገበው በፋብሪካው ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የጥገና ሥራዎች ተከናውነው የነዳጅ ማጣሪያ አቅሙ ከነበረበት በቀን ከ600 ሺህ በላይ ወደ 350 ሺህ ቀንሶ በነበረበት ወቅት ጭምር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የአውሮፓ አገራት የኃይል አቅርቦታቸውን ለማብዛት ያላቸው ፍላጎት ለዚህ ስኬት መሠረት ሆኗል።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ በርድ እንዳሉት ተቋሙ የናፍጣ እና ቤንዚን ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ ጀምሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፋብሪካው በጥቅምት ወር 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

❤16
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-
✅ከጠዋቱ 2፡00-11፡00
👉 ጎፋ መብራት ኮንዶሚኒየም፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ናሰው ሪልስቴት፣ ጎፋ ካምፕ ፣ ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን እና አካባቢው፣
👉መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ ቆሬ አደባባይ ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም በከፊል፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው፣
✅ከረፋዱ 4፡00-11፡00
👉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋራጅ አካባቢ፣ ማዕድን ሚኒስቴር ፣ ላምበረት መናሀሪያ እና አካባቢው፣
👉ጉርድ ሾላ ቴሌ ፣ የካ ሞሰብ ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ፣ ጃክሮስ አደባባይ ፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡30-11፡30
👉ባህርዳር ቀበሌ11፣ ማራኪ ቴሌ፣ ማራኪ ቀበሌ ቢሮ፣ ቀበሌ16፣ ሕዳሴ፣ መኮድ ኮንዶሚኒየም ፣ ጭሮ፣ ጨለንቆ፣ ቀርሳ፣ ቁልቢ፣ ኮሮሚ፣ ላንጌ እና አካባቢው
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን ።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

❤9😢1
ለታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ዘመናዊ ህንጻ ሊገነባለት ነው
አዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ የሚገኘው አንጋፋው የኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርርስ መሆኑ ተሰማ። ከዚህ ቀደም የሆቴሉ ጀርባ ያለው የስብሰባ አዳራሽ መፍረስ የጀመረ ሲሆን፣ ዋናው ሕንፃም በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተገልጿል። በቅጥር ግቢው ውስጥ የነበሩ ሰባት የንግድ ሱቆችም አስቀድመው ተነስተዋል።
ይህንን ባለ አምስት ፎቅ ሆቴል ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በ2002 ዓ.ም በ94 ሚሊዮን ብር ገዝተውት ነበር። አሁን ላይ በቦታው ላይ ዘመናዊ ሕንፃ ለመገንባት ታቅዷል። ሆቴሉ ሲፈርስ 140 ሠራተኞች ሥራቸውን እንደማያጡና በባለቤቱ ሌሎች ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚዛወሩ ተነግሯል።

❤20🤯8👍2😢1🎉1🤪1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምዝገባ ተጀመረ!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ እና የአውሮፕላን ጥገና ቦታዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።
እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ በኦንላይን ምዝገባ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እና መታወቂያቸውን በተለዩ ሁለት የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎች አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የምዝገባ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚከናወን ቢሆንም የጽሁፍ ፈተና እና የኢንተርቪው ሂደቶች በአዲስ አበባ ብቻ የሚሰጡ በመሆናቸው የክፍለ ሀገር አመልካቾች ይህንን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው።
የፋይል መጠኑም ከ1 ሜጋባይት መብለጥ የሌለበት ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን እና የአመዘጋገብ ቅደም ተከተሎችን በኩባንያው ይፋዊ ድረ-ገጽ ይከታተሉ።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ!

❤25
በኩርሙክ የጅምላ መቃብር ተገኘ‼️
በኢትዮጵያ ድንበር በሱዳን ብሉ ናይል ክልል በምትገኘው ኩርሙክ ከተማ የ25 ሰላማዊ ሰዎችን አስከሬን የያዘ የጅምላ መቃብር መገኘቱን የከተማዋ ባለሥልጣን አስታወቁ።
በመቃብሩ የተገኙት አስከሬኖች የሴቶች፣ የሕፃናት እና የሆስፒታል ሠራተኞች መሆናቸው ተገልጿል። የኩርሙክ ከተማ ኮሚሽነር አብደል አቲ ሞሐመድ አል-ፋኪ እንዳሉት፣ የሱዳን ሠራዊት ከተማዋን ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ነፃ ካወጣ ከአንድ ወር በኋላ በተካሄደ የማጽዳት ሥራ ወቅት በከተማዋ ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል መቃብሩ ተገኝቷል።
ባለሥልጣኑ እንደገለጹት፣ ተጎጂዎቹ በከተማዋ ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት RSF የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን ለማስወንጨፍ ይጠቀምበት ከነበረው ጄበል ፋንካት ኮረብታ አቅራቢያ መገኘታቸውን ተናግረዋል።
የጅምላ መቃብሩ መገኘቱ በሱዳን በቀጠለው ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ከባድ ጥሰቶች እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እየተጋለጡ መሆናቸውን ያሳያል። በኩርሙክ የተገኘው መቃብር ከዚህ ቀደም በካርቱምና በጌዚራ ግዛቶች ከተገኙ ተመሳሳይ የጅምላ መቃብሮች ጋር ተያይዞ በሱዳን ጦርነት የሚደርሰውን የሰላማዊ ሰዎች ሰቆቃ እንደገና አጉልቶ አሳይቷል።

❤13😢8💔7👍2
የጦርነት ዝግጅቱ‼️
ህወሃት በራያ የጦርነት ዝግጁትን ወደ መጨረሻ ምዕራፍ እያደረሰ ይገኛል።
በዚህም በሁሉም አካባቢዎች የሚደረጉ ስብሰባዎች ከቀትር ወደ ማታ እንዲሸጋገሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለራያ አዘቦ 1,000 ሊትር ነዳጅ እና ለመኮኒ ከተማ 3,000 ሊትር ነዳጅ እንዲከፋፈል ገልጿል።
እንስሳትን ጨምሮ የስንቅ አቅርቦት፣ውሃ የሚያቀርቡ ቦቢዎች እንዲሁም ለቀብር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እስከ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም እንዲዘጋጅ ለሁሉም አመራሮቹ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል።
ጦርነት ይብቃ፣ ችግሮች በውይይት ይፈቱ።

❤26🤔5👍2😢2
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የተፈፀመ‼️
ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል።
ግለሰቦቹ የተለያዩ ወንጀሎችን እንደፈፀሙና የተያዙትም ከአካባቢው ለማምለጥ በሚሞክሩበት ጊዜ መሆኑንና ከተያዙ በኋላ እንዲረሸኑ መደረጉን የአካባቢው ምንጮች ይገልፃሉ።
Via:- መሰረት ሚዲያ

😡50😢14❤11💔5🙉4✍1👍1🍾1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪዲዮ በምዕራብ ኮሎምቢያ 7.4 በMagnitude የተለካ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰበት ቅጽበት የአንድ ቤተክርስቲያን የፊት ለፊት ገጽታ በ ከፊል ሲናድ ያሳያል።
በ ሀገሪቱ በደረሰው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 20 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
የ ነብስ አድን ስራዎች ለማገዝ ወታደሮች እየተሰማሩ ይገኛሉ ሲል CNN ዘግቧል::

😢15❤4👍1
ድንጋይ የሚያክል በረዶ‼️
ዛሬ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ የጣለው በረዶ ነዋሪዎቹን አስደንግጧል። በከተማዋ የሚኖሩ ቤተሰቦች የላኩልን ምስል ከላይ ተያይዟል።

😢36❤5👍4🤯1
ሳዑዲ በአንድ ሳምንት ውስጥ 940 ኢትዮጵያውያንን
በሕገወጥ ድንበር ጥሰት በቁጥጥር ሥር አዋለች
በሳዑዲ ዓረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት፤ ሀገሪቱ በቅርቡ ባካሄደችው የድንበር ቁጥጥር ዘመቻ በሕገወጥ መንገድ ድንበር ለማቋረጥ የሞከሩ 940 ኢትዮጵያውያንን በአንድ ሳምንት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውላለች። ሚኒስቴሩ ከጁላይ 30 እስከ ኦገስት 5 ባለው ጊዜ ውስጥ ባካሄደው በዚህ ዘመቻ በጠቅላላው 1,593 ሕገወጥ ድንበር አቋራጮችን የያዘ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 59 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን እና 40 በመቶ ያህሉ ደግሞ የየመን ዜጎች ናቸው። በዚሁ ሳምንት የመኖሪያና የሥራ ሕግ የጣሱ 14,440 ሰዎች የተያዙ ሲሆን፣ 10,827 ሕገወጥ ነዋሪዎች ደግሞ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ተደርገዋል።
የሳዑዲ ዓረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አክሎ እንዳስታወቀው፤ ሕገወጥ ድንበር አቋራጮችን ሲያጓጉዙ፣ ሲሸሽጉ ወይም ሥራ ሲሰጡ የተገኙ 25 ግለሰቦችም ተይዘዋል። ሚኒስቴሩ በሰጠው ማስጠንቀቂያ፤ ሕገወጥ መግቢያን የሚያመቻቹ ወይም ጥሰተኞችን የሚያስጠጉ ሰዎች እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ የፅኑ እስራት፣ እስከ 1 ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል (260 ሺህ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንዲሁም የተጠቀሙባቸው ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች መወረስ እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል።

❤9👍1
የትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ትምህርት ዓይነቶችን ይፋ አደረገ
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር የሚተገበሩ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ መመሪያ አስተላለፈ።
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ «የሙያና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜ ጋር በተመጣጠነ መልኩ ይሰጣል» በሚለው አቅጣጫ መሠረት፣ በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል።
በተጨማሪም በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በ12 የሙያ ዓይነቶች ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሚተገበሩት 11 ተጨማሪ የሙያ ዓይነቶች የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ-ትምህርቶችን፣ እንዲሁም የ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችንና የመምህራን መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ለዚሁ ትግበራ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፦
👉ዝርዝር ዕቅድና በጀት በመያዝ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤትና በተማሪዎች ደረጃ እንዲያስመርጡ፣
👉የሙያ መምህራንን እንዲቀጥሩና እንዲያሰለጥኑ፣
👉የመማሪያና ማስተማሪያ ግብዓቶችን እንዲያሟሉ፣
የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠንና የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የአዲሶቹ 11 የሙያ ዓይነቶች ዝርዝር፦
👉ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ
👉አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
👉አልባሳት ቴክኖሎጂ
👉ሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
ቧንቧ ሥራ
👉ሶፍትዌር ማበልጸግ
👉ሰብል አመራረት
👉ጤና ክብካቤ አገልግሎት
👉ሆቴል አገልግሎት
👉ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
👉ምግብ ዝግጅት

❤39👍3🥰2🤪2
"ኢራን ለገደለቻቸውና ለጎዳቻቸው ሰዎች ካሳ መክፈል አለባት" — ዶናልድ ትራምፕ
ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በተከሰተው ግጭት የደረሰብኝ ውድመት ይካስ ስትል ለጠየቀችው ቴህራን፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ በራሳቸው 'ትሩዝ ሶሻል' (Truth Social) የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ባስተላለፉት መልእክት፣ ኢራን ካሳ ለመጠየቅ ያቀረበችው ሀሳብ "አስደናቂ" ነው ካሉ በኋላ፣ ይልቁንም ቴህራን በተለያዩ ግጭቶች እና በመንገድ ዳር ቦምቦች ለገደለቻቸው እና ለጎዳቻቸው ሰዎች በሙሉ ካሳ መክፈል እንዳለባት ገልጸዋል።
ቴህራን የሆርሙዝ ሰርጥን (Strait of Hormuz) ለመክፈት እና የተጣሉባትን ማዕቀቦች ለማንሳት በሚደረጉ ውይይቶች ወቅት፣ ባለፉት ወራት በደረሰባት የጦርነት ውድመት አሜሪካ ካሳ እንድትከፍላት ጠይቃ ነበር።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአንጻሩ በአሜሪካ ተደራዳሪዎች በኩል ኢራን በውጊያ ላይ ለተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮች፣ ለተጎዱ ቤተሰቦች (እ.ኤ.አ. በ2000 በዩኤስኤስ ኮል ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀምሮ) እና በሃገር ውስጥ በነበሩ ተቃውሞዎች ለተገደሉ የኢራን ዜጎች ጭምር ካሳ እንድትከፍል ጥያቄው በድርድር ወቅት እንዲቀርብ አዘዋል።
የሁለቱ ወገኖች የካሳ ጥያቄ መወራወር የነገሰበትን ቀጣናዊ ድርድር እና የሆርሙዝ ሰርጥን የመክፈት ሂደት ይበልጥ ያወሳስበዋል ተብሎ ተጠብቋል።

❤17🤣16🫡3👍1
በትግራይ የኤርትራ እንቅስቃሴ‼️
ኤርትራ ከሕወሓት ጋር በመሆን በሉዓላዊነታችን ላይ ግልጽ ጥሰት እየፈጸመች ነው - አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ‼️
👉የኤርትራ መድፎች በዛላንበሳ በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉሎምከዳ ወረዳ ገብተዋል።
በሆርን ሪቪው ላይ ጽሁፋቸው ያሰፈሩት አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ የኤርትራ መንግሥት ከሕወሓት አክራሪዎች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ግልጽ ጥሰት መፈጸሙን አጋለጡ። በተለይም ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የኤርትራ ወታደራዊ ባለሥልጣናት የሀገራቸውን ባንዲራ ይዘው ወደ ዘላንበሳ መግባታቸውና ታንኮችን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ማዘዋወራቸው ሁኔታውን እጅግ አደገኛ እንዳደረገው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ ለቀጠናዊ ሰላም ስትል ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ትዕግስት ማሳየቷን አምባሳደሩ አስታውሰዋል። ሆኖም የኤርትራ መንግሥት ለቀረበላት የሰላም ጥሪ ጆሮ በመስጠት ፈንታ፣ ኢትዮጵያን የማዳከምና የማተራመስ የቆየ ዓላማውን አጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ የሕወሓት አክራሪዎች የትግራይን ወጣቶች በግድ በመመልመልና ለሱዳን ጦርነት በመሰልፍ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያዋሏቸው መሆኑ ተመላክቷል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያደረጋቸው ውስን ማዕቀቦች የኤርትራን አካሄድ መቀየር እንዳልቻሉ የገለጹት ጄኔራል ባጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አሳስበዋል። ኤርትራ ይህንን የጥፋት እርምጃ ካልገታች፣ የሚመጣው ቀውስ በራሷ በኤርትራ ላይ የሀገር መፍረስ አደጋን ጨምሮ ለአጠቃላይ ቀጠናው ሰላም ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር በማስጠንቀቅ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

❤17🤣7🤷♂3👍1
Forwarded from አዲስ ሪፖርተር - NEWS
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟
የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።
በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።
ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com

❤6👍2
በአንድ ጊዜ 5ሺህ የኒት ደም የሚያቀዘቅዘው ክፍል በባህርዳር ስራ ጀመረ
በአማራ ክልል የባሕር ዳር ደም ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ከሚያስመዘግቡ ደም ባንኮች አንዱ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የባሕር ዳር ደም ባንክ ሁሌም የተሻለ አፈጻጸም የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ደም ባንኩ አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል ስርአት በማዘመን በክልሉ የመጀመሪያው ደም ባንክ ነው።
ህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉ ዝቅተኛ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በቀጣይ በክልሉ ደም መለገስ ባህል እንዲሆን የግንዛቤ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

❤16👍3
ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 ዶላር እንደሚያስፈልገው የሚደነግግ መመሪያን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አወጣ።
አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት ለመሆን የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።በመመሪያው መሠረት የውጭ አገር ዜጋ ማለት፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም ሰው ማለት ነው።
የውጭ አገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሠራር ለመወሰን የወጣው መመሪያ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው ሐምሌ ወር የጸደቀ ነው።በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተዘርዝሯል።
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በሸገር ከተማ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልገዋል።ሸገር ከተማን ሳይጨምር በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ ክልል፣ በሐረሪ ክልል ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ደግሞ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን 120000 የአሜሪካ ዶላር ማቅረብ ነው።
ከሌሎቹ ክልሎች የውጭ አገር ዜጋ የቤት ባለቤት ለመሆን ዝቅተኛ ገንዘብ የሚጠየቀው በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልል ሲሆን የገንዘቡ መጠን ደግሞ 100000 ዶላር እንደሆነ ተደንግጓል።
አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው የቤት መጠን አንድ ብቻ ነው።በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፈቃድ ወስዶ እያለማ ያለ ባለሀብት ግን ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ሳይገድበው የአንድ ቤት ባለቤት መሆን ይችላል።
በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የተጠቀሰውን ለአንድ ቤት የሚያስፈልግ ገንዘብ የሚያስቀምጥበት የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትለትና ገንዘቡን በውጭ ምንዛሬ እንዲያስቀምጥ የሚፈቅድ ደብዳቤ ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት በማጻፍ በመረጠው ባንክ ገቢ ማድረግ አለበት።
አንድ የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ፈቃድ የሚያገኘው፤ የጸና ፓስፖርት ካለው፣ የወንጀል ታሪክ የሌለው ስለመሆኑ ከሚኖርበት አገር ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ነው።
በተጨማሪም ከሀገር ሰላም፣ ደህንነት፣ ጸጥታ፣ የሕዝብ ጥቅም፣ የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃም ማቅረብ አለባቸው ይላል መመሪያው።
ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በመንግሥት ቀጥተኛ ድጎማ ለዜጎች በሚሠሩ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን አይችልም፤ ይህም የቤት ባለቤት በሚሆኑ የውጭ ዜጎች ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ በወጣ አዋጅ የተጣለ ገደብ ነው።
በአዋጁ መሠረት የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋም ወይም ምንጭ ገንዘብ መበደር ወይም ካፒታል ማሰባሰብ አይችልም።
በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት የሆኑ የውጭ ዜጎችን መብት በተመለከተ ደግሞ መመሪያው ሲዘረዝር ለኢትዮጵያውያን የተሰጡ የንብረት መብቶች ይኖራቸዋል፤ ለግለሰቦች ማከራየት ይችላሉ፣ ለንግድ ዓላማ ማከራየት ግን አይቻልም።
ለራሱ እና ለቤተሰቡ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የመግቢያ ቪዛና ኢትዮጵያ መመላለስ እንዲችሉ የሚያደርግ አግባብነት ባለው አካል የሚሰጥ እስከ አምስት ዓመት የሚያገለግል የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ የማግኘት መብት አላቸው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ እና አሠራር መሠረት ከመኖሪያ ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የሚያገኘውን የኪራይ ወይም የሽያጭ ገቢ በወቅቱ ተመን በውጭ ምንዛሪ ወደ ውጭ አገር የማስተላለፍ መብት አለው ይላል አዋጁ።
መመሪያው ታትሞ በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ ከተጫነበት ቀን ጀምሮ ሥራ ላይ ይውላል ይላል።በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ የተጫነው ባለፈው እሁድ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።Via Sheger

❤16🤣14👍2🤯1