አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.2K photos
421 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የስኬት ባንክ የተከፈለ ካፒታል 7.9 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ የካፒታል መጠን ደግሞ 10.3 ቢሊዮን ብር ደረሰ

ስኬት ባንክ በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 10.3 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንና ፣ የተከፈለ ካፒታሉንም ደግሞ ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር ማሳደጉን አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ በተከናወነ የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ 14.7 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት 1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን አመልክቷል።

የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 የትኩረት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባኤው ላይ በቀረበው ሪፖርት፤ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን በ51 በመቶ በማሳደግ ወደ 29 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ፣ የበጀት ዓመቱ በስኬትì መጠናቀቁን ገልጸው፤ አዲስ በተጀመረው የ2019 በጀት ዓመት የባንኩን ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማሳደግ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለደንበኞች የሚሰጡ የአገልግሎት አማራጮችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3🤔3
ኢንሳ አዲስ የወጣውን ወሳኝ የመሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ ይፋ አደረገ

የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) የሀገሪቱን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማጠናከር ያለመ አዲስ ወሳኝ የመሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ አስተዋወቀ። በዋና ዳይሬክተር ንግስት ሃሚድ ይፋ በተደረገው በዚህ አዋጅ መሠረት 12 ቁልፍ ዘርፎች እንደ ወሳኝ መሠረተ ልማት ተለይተዋል።

አዋጁ ዘላቂ ፋይናንስ ለማግኘት የሳይበር ደህንነት ፈንድ ማቋቋሙን የሚመለከት ሲሆን፣ ገንዘቡም ከድርጅቶች ወርሃዊ አስተዋጽኦ፣ ከቅጣት እና ከድጋፍ ይሰበሰባል። የፋይናንስ፣ የትራንስፖርት፣ የኢነርጂ፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ አጠቃላይ ዘርፎቹ የጸጥታ ማዕከላትን የማቋቋም፣ የአደጋ ግምገማዎችን የማካሄድ እና የደህንነት ኦዲት የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ተቋማት ማንኛውንም የሳይበር ጥቃት በ48 ሰዓታት ውስጥ ለብሔራዊ ድንገተኛ አደጋ ምላሽ ቡድን ሪፖርት ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን፣ ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ የአንድ ዓመት የጸጋ ጊዜ ተሰጥቷል። ትእዛዙን በማያከብሩ አካላት ላይም ከ1.5 ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር የሚደርስ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚጣል ይሆናል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9😡4👍2🤣1
"ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ‼️
👉እኛ ከእስር የለቀቅናቸው ወደ አሰራቸው ቡድን የተገለበጡም አሉ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )  በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ገለጹ።
ታጣቂዎቹ ኤርትራን እና ሱዳንን ጨምሮ ከውጭ ተዋናዮች ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በጥንቃቄ ሊረዳው እንደሚገባ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሀገሪቱን በብቸኝነት ይመራ የነበረው ቡድን ያጣውን ሥልጣን በኃይል ለመመለስ ማሰቡ ለሀገሪቱ ግጭቶች መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል።
ሆኖም እኛ እውነት ስለያዝን እናሸንፋለን ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2625👍3🤪2
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
7👍3
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ "ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም" በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል።

"በቃ!" በማለት ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳይሬክተሩ የፌዴራል መንግሥቱም ሆነ የክልል መሪዎች ከጦር መሣሪያ ይልቅ ለውይይት ቅድሚያ እንዲሰጡና እውነተኛ ፖለቲካዊ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አሳስበዋል። ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያስከትለውን ሰብዓዊ ቀውስ የገለጹት ዶክተር ቴዎድሮስ ግጭት የሞት ፣ የውድመት ፣ የመፈናቀል እና የከፋ እጦት ምንጭ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም "ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል" ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
40👍9🥰5🤔2
ትራምፕ የ“ወሊድ ቱሪዝምን” ለማገድ አዲስ ትዕዛዝ ፈረሙ፤ “የትውልድ ዜግነት መብትን ቀልድ አድርገውታል” ሲሉ ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንዳንድ የውጭ ሀገር ዜጎች በቱሪስት ቪዛ ተጠቅመው ወደ አሜሪካ በመግባት ልጅ በመውለድ አውቶማቲክ የዜግነት መብት የሚያገኙበትን የ“ወሊድ ቱሪዝም” (Birth Tourism) አሰራር ለማገድ የሚያስችል አዲስ የፕሬዝዳንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈረሙ።

ፕሬዝዳንቱ አዲሱን መመሪያ በኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደግፈው ሲናገሩ፦ “የትውልድ ዜግነት መብትን መጫወቻና ቀልድ አድርገውታል” ሲሉ አሰራሩን አጥብቀው ኮንነዋል።

ይህ የትራምፕ አዲስ እርምጃ የመጣው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የትውልድ ዜግነት መብትን ለማገድ ያወጡትን ተመሳሳይ መመሪያ ውድቅ ማድረጉን ተከተሎ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ “በጣም አሳዛኝ ውሳኔ” ሲሉ ገልጸውታል።

የአሜሪካ ሕገ-መንግስት በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ለሚወለድ ማንኛውም ህጻን (ከዲፕሎማቶች ልጆች በስተቀር) አውቶማቲክ የአሜሪካ ዜግነት መብት ይሰጣል። ይሁን እንጂ የትራምፕ አስተዳደር በስደተኞች እና በዜግነት ፖሊሲው ላይ የሚወስዳቸው ጠንካራ እርምጃዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፣ አዲሱ አስፈጻሚ ትዕዛዝም በድጋሚ ከፍተኛ የሕግ ክሶች እና ተቃውሞዎች እንደሚገጥሙት ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙊4👍2🤣1
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ "ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም" በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። 

ዶክተር ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። 

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል።

"ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል" ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍9🤔6
የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
በዛሬዉ እለት በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

በዛሬዉ እለት ምሽት 2 ሰዓት ከ 11 ደቂቃ ላይ በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.6 የተለካ መሆኑን ቮልካኖ ዲስከቨሪ የተሰኘዉ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተገሞራ ፍንዳታዎችን የሚከታተል ተቋም በገጹ አሳዉቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስአበባም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13😢8👍3
ለጥንቃቄ!!!!

ትናንት ይሁን ከትናንት ወዲያ ይህንን መረጃ  የሰይፉ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ ብዙዎች ተምረውበታል። ጉዳዩን ላልሰማችሁ ለጥንቃቄ እነሆ ብሎ ዳዊት እርገጤ እንዲህ ከትቦታል።

የዕድሜ ልክ ጥረቱን የተበላው የፌድራል ፖሊስ አመራሩ ባለቤት ታማ ፀበል ገባች!

በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት ሽመልስ እና ቤተሰቦቻቸው፣ በዘመናዊ የዲጂታል ቀማኞች ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ ተዘርፈዋል።

ጉዳዩ የተጀመረው "ቤት ቁጭ ብሎ በወር ከ70 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር መሥራት ይቻላል" በሚል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚወጣ አታላይ ማስታወቂያ ነው።

የቤት እመቤት የሆነችው ባለቤታቸው ነገሩን አምና አፕሊኬሽኑን ስትሞክረው፤ ወደ ቴሌግራም እና ዋትስአፕ ግሩፖች በመግባት "አሊባባ ኦንላይን ንግድ" በሚባል አደገኛ መዋቅር ውስጥ ትገባለች።

አጭበርባሪዎቹ ሰዎችን ለማጥመድ የተካኑ ስለሆኑ፣ እምነት ለማግኘት ሲሉ በመጀመሪያ 800 ብር ልከው 1,500 ብር ይመልሱላቸዋል። ቤተሰቡም "ነገሩ እውነት ነው" ብሎ እንዲያምን ያደርጉታል።ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ትክክለኛው ሰቆቃ የሚጀምረው።

የገንዘቡ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲመጣ፣ የራሳቸውን ቁጠባ ጨምሮ ከውጭ ሀገር ከምትኖር የባለቤታቸው እህት ጭምር 600,000 ብር ተበድረው ገቢ ያደርጋሉ።

አጭበርባሪዎቹ ጨካኝነታቸውን አሳይተው "አንደኛ ደረጃ ነጋዴ ስለሆናችሁ ከፍተኛ ግብር መክፈል አለባችሁ" በማለት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስገቡ አድርገው በድምሩ 1.3 ሚሊየን ብር እንዲዘረፉ አድርገዋቸዋል።

በሐሰተኛው መተግበሪያ ላይ 3 ሚሊየን ብር አትርፈዋል ተብሎ ይታይባቸውም ነበር፤ ነገር ግን ገንዘቡን ማውጣት ሳይችሉ ቀርተው አካውንታቸው ላይ የቀረው 59 ብር ብቻ ነው! ይህ ሁሉ አሰቃቂ ድርጊት ሲፈጸም ረዳት ኢንስፔክተር አንድነት በሥራ ስምሪት (ፊልድ) ላይ ነበሩ።

የገንዘቡን መበላት ስትሰማ የባለቤታቸው ልብ ድንጋጤን መቋቋም አቅቶት ዛሬ ላይ በጽኑ ታማ በጸበል ቦታ መንፈሳዊ ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል። የዕድሜ ልክ ድካማቸው በአንድ ቀን ባዕድ ኃይል መናጋቱ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከቷቸዋል። Via_ጉርሻ page

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
27😢21👍3🙉1
ኢዜማ ከሀገራዊ ምክክሩ ምን ይፈልጋል?

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ፓርቲያቸው ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረክ የገባው ለአጭር ጊዜ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ሳይሆን መሠረታዊና ሥርዓታዊ ለውጥ ለማምጣት ታግሎ ለመለወጥ መሆኑን አሳሰቡ።

መሪው አክለውም ኢዜማ እስከ ምክክሩ መዝጊያ ቀን ድረስ በማይበገር አቋም የዜግነት ፖለቲካን፣ የነፃና ገለልተኛ መንግሥታዊ ተቋማትን ግንባታ እንዲሁም በብቃት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት መዘርጋትን እንደ ዋና መሠረታዊ ምሰሶዎች አድርጎ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

  ትውልዱን ከግጭትና ከመከፋፈል አዙሪት ነፃ ለማውጣትና ጠንካራ ሀገራዊ ሥርዓት ለመገንባት እነዚህን መርሆዎች እውን ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ እዮብ፣ የዜጋ ክብር ፍጹምና የማይደፈር የሆነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በጋራ እውን እስከሚደረግ ድረስ ፓርቲያቸው ያለማቋረጥ እንደሚታገል አጽንኦት ሰጥተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤣5👍4
ከ2010 በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው በተደጋጋሚ እንዲሸሻሉ መደረጋቸው በጥናት ተመላከተ

ከ2010 ዓ.ም. በኋላ የወጡ አብዛኛዎቹ አዋጆች በችኮላ የተዘጋጁ በመሆናቸው ለተደጋጋሚ ማሻሻያ መጋለጣቸውንና ከአዋጆቹ ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጩ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲወጡ ምክንያት መሆናቸውን የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጥናት አመላከተ።

ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ባካሄዳቸው አምስት ጥናቶች ላይ ባደረገው የማጽደቂያ ዓውደ ጥናት ግኝቶቹን አቅርቧል።

ጥናቱ ከ2010 እስከ 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጡ ሁሉንም አዋጆች የሸፈነ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የሕግ አወጣጥ ሥርዓት መረጋጋትን የሚመለከት የተለየ ፖሊሲ እንደሌለ ጠቁሟል።

ለአብነትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በተመሳሳይ ዓመት በሌላ አዋጅ መሻሻሉንና ከሁለት ዓመት በኋላም በ2015 ዓ.ም. እንደገና መሻሻሉን ጥናቱ አመላክቷል።

በተጨማሪም አንዳንድ አዋጆች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጩ ድንጋጌዎች እንዳሏቸው ጥናቱ ጠቁሟል።

በሕገ መንግሥቱ ውስጥም አሻሚ ቃላት፣ ግልጽነት የጎደላቸው አንቀጾችና አንዳንድ የሚጋጩ መርሆዎች መኖራቸውን ጥናቱ አመላክቶ፣ የሕገ መንግሥቱ ትርጓሜ ጉዳይ በጥናት እንዲታይ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

ደንቦችና መመሪያዎች በየጊዜው ሲሻሻሉም በቂ ጥናትና ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጥናቱ አሳስቧል።ዘገባው የሪፖርተር ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍4
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ‼️

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።

ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር።

አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል።

ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
5
693 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌደራልና ከክልል ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን ከሀምሌ 23 እስከ ሀምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል የተያዙት 648 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የገቢ እንዲሁም 44 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ የግብርና ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባከናወነው ክትትል ህብረተሰቡ ከፍተኛ ትብብር ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፥ በፍተሻ፣ በጥቆማና በበረራ ከተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተጨማሪ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 30 ተጠርጣሪዎችና 17 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍4
ተጨማሪ መረጃ‼️
ዛሬ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በራያ አላማጣ ወረዳ በመረዋ ንዑስ ወረዳ የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በአራት ዙር መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል።
እንደ የአካባቢው ምንጮች ገለጻ፣ ጥቃቱ:-
📌በመረዋ 2ኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
▪️📌በችግኝ ጣቢያው አካባቢ በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
📌ከቤተ-ክርስቲያን አለፍ ብሎ ባለው ዋርካ (ዳዕሮ) ዛፍ ስር በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
📌ሚይ ሓርማዝ በሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተፈፀመው።
ጥቃቱ በአራት ዙር የተፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታጣቂዎች ተሰውተዋል።
የተጎዱ ታጣቂዎች ደግሞ ወደ አላማጣ ለህክምና ተወስደዋል። መረዋ አካባቢ በሚገኝ በአንድ የቤተክርስቲያን ዋሻ ውስጥ የህክምና አገልግሎት መስጫ አዘጋጅተው ነበር ተብሏል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍8
ውጊያውን አናንዛዛውም:-ጄኔራል ባጫ ደበሌ‼️
'ሱዳኖች  ጦርነት እጀምራለሁ ብለው ካሰቡ አናንዛዛውም‼️
የሱዳን መንግስት በራሱ ጦርነት ነው ያለው። የሱዳን መንግስት  የራሱን ጦርነት ሳይጨርስ ወደ ኢትዮጵያ  የሚያልፍ ከሆነ እድሜው አጭር ነው፣ይጠፋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ያለውን ሙሉ  አቅምና ሃይሉን ተጠቅሞ መጨረስ ነው የሚፈልገው።እንደ በፊቱ የሚንዛዛበት ምክንያት የለም። ጀመርክ በአጭር ግዜ መጨረስ ነው፣ እንደበፊቱ ምሽግ ይዘህ ደጀን ይዘህ፣እረፍት አድርገህ እንደገና ላደራጅ...ወዘተ በሚል የምትሮጥበት አይደለም። ውጊያው በቴክኔሎጂ ነው'ሲሉ ተደምጠዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪37👍2212🫡2
የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ለአውሮፓ ትልቁ የጄት ነዳጅ አቅራቢ መሆን ቻለ

የናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ብቻ ለአውሮፓ ከገባው አጠቃላይ የጄት ነዳጅ ውስጥ አምስተኛውን ድርሻ በመያዝ (ከ2.06 ሚሊዮን ቶን ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ ቶን በማቅረብ) ለአሁኑ ወርም ከአሜሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ቀድሞ የአውሮፓ ትልቁ የውጭ አቅራቢ መሆን መቻሉ ተገለፀ።


ይህ አፈጻጸም የተመዘገበው በፋብሪካው ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የጥገና ሥራዎች ተከናውነው የነዳጅ ማጣሪያ አቅሙ ከነበረበት በቀን ከ600 ሺህ በላይ ወደ 350 ሺህ ቀንሶ በነበረበት ወቅት ጭምር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የአውሮፓ አገራት የኃይል አቅርቦታቸውን ለማብዛት ያላቸው ፍላጎት ለዚህ ስኬት መሠረት ሆኗል።

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ በርድ እንዳሉት ተቋሙ የናፍጣ እና ቤንዚን ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ ጀምሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፋብሪካው በጥቅምት ወር 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
 
ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-

ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉  ጎፋ መብራት ኮንዶሚኒየም፣ ጉራጌ ሰፈር፣ ናሰው ሪልስቴት፣ ጎፋ ካምፕ ፣ ሀዋርያው ቸርች ፣ ኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን እና አካባቢው፣

👉መካኒሳ አረቄ ፋብሪካ ቆሬ አደባባይ ፣ አሚጎ ኮንዶሚንየም በከፊል፣ ፋና ት/ቤት እና አካባቢው፣

ከረፋዱ 4፡00-11፡00

👉የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋራጅ አካባቢ፣ ማዕድን ሚኒስቴር ፣ ላምበረት መናሀሪያ እና አካባቢው፣

👉ጉርድ  ሾላ ቴሌ ፣ የካ ሞሰብ ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ፣ ጃክሮስ አደባባይ ፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡30-11፡30

👉ባህርዳር ቀበሌ11፣ ማራኪ ቴሌ፣ ማራኪ ቀበሌ ቢሮ፣ ቀበሌ16፣ ሕዳሴ፣ መኮድ ኮንዶሚኒየም ፣ ጭሮ፣ ጨለንቆ፣ ቀርሳ፣ ቁልቢ፣ ኮሮሚ፣ ላንጌ እና አካባቢው

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን ።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9😢1