አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.2K photos
421 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ሸረሪና‼️
ባሳለፍነው ሳምንት ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11:45 ጀምሮ በሱዳን ድንበር ሸረሪና አካባቢ የሚንቀሳቀሰው የህወሓት አርሚ 70 (በዋናነት ኮር 131) ሁመራን ለመቆጣጠር በመከላከያ ሠራዊት ላይ ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው የአፀፋ ምላሽ አንድ ሙሉ የተከማቸ የመሳሪያ ዲፖን በቁጥጥር ሥር አውሏል፣በርካታ ታጣቂዎች ተማርከዋል፣በርካታ ታጣቂዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣በርካታ ሎጀስቲክ ወድሟል።
ሸረሪና እና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ውሏል።
አሁን ላይ በአካባቢው ከፍተኛ አሰሳ እየተካሄደ ሲሆን በተለይ የመሳሪያ ማከማቻዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛሉ።
ከላይ የሚታዩት ምስሎች ከስፍራው የደረሱን ምስሎች ሲሆኑ በመከላከያ ሠራዊት የተማረኩ የአርሚ 70 ታጣቂዎችን፣ መሳሪያዎችን እንዲሁም ተሽከርካሪዎችን የሚሳይ ነው።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
28👍12😢2🤣2🤔1👀1🤪1💊1🙊1
አሜሪካ የኤምባሲዎቿን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ልትቀንስ ነው

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የቪዛ ማመልከቻዎችን የሚያስተናግዱ ኤምባሲዎቹንና ቆንስላዎቹን ቁጥር ከ50 ወደ 20 ዝቅ ለማድረግ ማቀዱ ተሰምቷል።

ይህ የተቋማት ውህደትና ቅነሳ ውሳኔ በተለይም በትራምፕ አስተዳደር እየተተገበረ ያለው ጥብቅ የኢሚግሬሽን ቁጥጥር አካል ሲሆን፣ በመጪዎቹ ሳምንታት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍4
በኮሬ ዞን የገዛ ባሏን የገደለችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
 
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማለ ወረዳ ደርባ ማናና ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ወካለ ወይም ወይዶ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል።ተከሳሽ  ተስፋይነሽ ዘለቀ የተባለች ሲሆን  ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ  ድርጊቱን ፈጽማለች።
 
ተከሳሽ ከትዳር አጋሯ  ሳሪያ ጋር በተነሳ አለመግባባት ምክንያት ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ እንደተሰወረች ተገልጿል።የትዳር አጋሯም ተከሳሽን  ለመፈለግ ወደ ጎረቤት ቤት ሲሄድ  ወደዚያ አልመጣችም የሚል ምላሽ ያገኛል። በመቀጠልም ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ በጓሮ በኩል ባትሪ እያበራ ሲፈልጋት ተከሳሽ ተደብቃ በነበረችበት ቦታ አጠገቧ እያለፈ እያለ ይዛዉ በነበረው ቆጮ መቁረጫ የቀኝ አንገቱን  አንድ ጊዜ በመቁረጥ  ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
ፖሊስም ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል የክስ መዝገቧን ለአቃቤ ህግ ያቀርባል።አቃቤ ህግም ተከሳሽ በፈፀመችው ከባድ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶ ለፍርድ ቤት ያቀርባል።
 
ፍርድ ቤቱም ተከሻሽ ጥፋተኛ መሆኗን በቀረበለት የክስ መዝገብ በማጣራት   በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ  ወስኖባታል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11😢10👍2
የመጸዳጃ ቤት እና ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ የሚለቁ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እስከ 3 መቶ ሺህ ብር ድረስ እየተቀጡ መሆኑ ተነገረ
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከመኖሪያ ቤት የመጸዳጃ ቤት ወይም ማንኛውንም ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ወይም መስመሩን አገናኝተው ወንዙን የበከሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ከ150 ሺህ እስከ 3 መቶ ሺህ ብር እየቀጣ ይገኛል።
 
የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ወቅቱ የክረምት ወቅት በመሆኑ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ከግለሰቦች መኖሪያ እንዲሁም ከድርጅቶች የመጸዳጃ ቤት ወይም ማንኛውም ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝ የሚለቁ እንዲሁም አካባቢን የሚበክሉ ግለሰቦች በባለስልጣኑ ደንቡ መሠረት እስከ 300 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይጣልባቸዋል።
 
ይህንን ህግ ጥሰው የተገኙ አካላት አሁን ላይ እየተቀጡ እንደሚገኙ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ አቶ የምስራች ጨምረው ገልፀዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23🙉5👍2😢1🤣1
ያልተጠናቀቁ ሕንፃዎችን ማከራየት የ100ሺ ብር ቅጣት ያስከትላል፡፡

የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባወጣው አዲስ የአደጋ ሥጋት ደኅንነት መመሪያ መሠረት፤ ግንባታቸው ሳይጠናቀቅና የደኅንነት ማረጋገጫ ሳያገኙ ሕንፃዎችን ለአገልግሎት የሚያከራዩ አከራዮች የ100 ሺሕ ብር ቅጣትና የወንጀል ተጠያቂነት ይጠብቃቸዋል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው ሕንፃዎች በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ የሚያደርሱትን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል ነው።

በተጨማሪም መመሪያው በግንባታ ወቅት የሠራተኞች ደኅንነት መጠበቂያዎችን አለማሟላት፣ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን አለመከለልና ምልክት አለማድረግ፣ ጠንካራ ያልሆኑ የማደላደያ ቁሳቁሶችን መጠቀም፣ እንዲሁም በቀላሉ ሊደረመሱ የሚችሉ አፈርና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማከማቸት በጥብቅ ይከለክላል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍5🤪2👌1
ያልተጠናቀቀ ህንፃ ማከራየት‼️
በአዲስ አበባ ያልተጠናቀቁ ሕንፃዎችን የሚያከራዩ አከራዮች የ100 ሺሕ ብር ቅጣት እና የወንጀል ተጠያቂነትይጠብቃቸዋል

📄 የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ያዘጋጀው አዲስ የአደጋ ሥጋት ደኅንነት መመሪያ ወደ ሥራ ገብቷል።
 
በመመሪያው የተካተቱ ክልከላዎች፦
 
⚡️ በሕንፃ ግንባታ ወቅት የሠራተኞች ደኅንነት መጠበቂያ መስፈርቶችን አለማሟላት፣
⚡️ ለአደጋ የሚያጋልጡ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን አለመከለልና ምልክት አለማድረግ፣
⚡️ ለአደጋ የሚያጋልጡ ጠንካራ ያልሆኑ የማደላደያ ቁሳቁሶችን መጠቀም፣
⚡️ በቀላሉ ሊደረመስ የሚችል አፈርና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማከማቸት።
 
👉 እርምጃው ግንባታቸው ሳይጠናቀቅና የደኅንነት ማረጋገጫ ሳያገኙ ለአገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎች በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ ከመደቀናቸው ጋር ተያይዞ የመጣ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍4🤪2👌1🙊1
5ቱ ለሙስና በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ የመንግሥት ተቋማት ተለዩ

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው አዲስ የዳሰሳ ጥናት፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ይፋ አደረገ።

በጥናቱ መሠረት:-

1.የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣

2. የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣

3. የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣

4. የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ እንዲሁም

5. የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና የተጋለጡ ተቋማት ተብለው ተለይተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34👍16🤣5🙏2👌2🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዝንጀሮውም አረንጓዴ አሻራውን አኖረ

🐒🌱 በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ከተተከሉት 805.3 ሚሊዮን ችግኞች መካከል፤ ይህ ዝንጀሮ የተወሰኑትን ተክሏል(ስፑትኒክ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣55🤪2219👍4🥱4😎2👀1🙈1
የሙቀት ማዕበል በሰሜን ኮሪያ፡ መንግሥት ዜጎች የውሻ ሥጋ ሾርባ እንዲመገቡ መከረ

​በሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ የሙቀት ማዕበል በመከሰቱ መንግሥት ዜጎች አካላቸውን ለማቀዝቀዝ የውሻ ሥጋ ሾርባ እንዲመገቡ መከረ።

​በሀገሪቱ የሙቀት መጠን ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ የማያውቅ 36.7 ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ የአየር ሁኔታ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። 'ሳምቦክ' በተሰኘው በዚህ የከፋ የሙቀት ወቅት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደ የውሻ ሥጋ ሾርባ፣ የዓሣ ገንፎ፣ ሀብሐብ እና ዱባ ያሉ ምግቦች የሰውነትን ጥንካሬ ለመጠበቅና ሙቀቱን ለመቋቋም ይረዳሉ ብለዋል።

​የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና ኤጀንሲ (KCNA) እንደገለጸው፣ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ የሚገኙ ምግብ ቤቶች እነዚህን ባህላዊ ምግቦች ለሚፈልጉ ደንበኞች አስተናጋጅነት እየሰጡ ይገኛሉ።

​ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ከሙቀት ማዕበሉ ጋር በተያያዘ ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ብታረጋግጥም፣ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን የሞት መረጃ አላወጣችም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤩9🤔6🙈5🤯3🤣3👍2😱1👀1
የህወሓት አመራር ከኤርትራና ከሌሎች ኃይሎች ጋር ፈጠርነው ያሉት ጥምረት "የጥፋት ቀመር ነው" - ጌታቸው ረዳ‼️

​የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የህወሓት አመራሮች ከኤርትራው የኢሳይያስ አፈወርቂ ሥርዓትና ከሌሎች የፌደራል መንግሥቱን በሚቃወሙ ኃይሎች ጋር የፈጠሩት ጥምረት በትግራይና በመላው አገሪቱ ላይ ታላቅ ጥፋት የሚያመጣ «የጥፋት ቀመር» ነው ሲሉ ኮነኑ።

​አቶ ጌታቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት እንዳመለከቱት፣ የህወሓት አመራር ቀደም ሲል የፌደራል መንግሥቱን ለማፍረስ ከውስጥና ከውጭ ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሲክድ ቢቆይም፣ አሁን ላይ ግን «የማይመለሱበትን ወሳኝ እርምጃ መውሰዱን» እና ወደ ኃይል አማራጭ መሸጋገሩን በአደባባይ እያወጀ ይገኛል።

​ የጥምረቱ ዋና ዓላማ፦ የህወሓት አመራር ዓላማ የምዕራብ ትግራይን ቦታዎች በሰላማዊ መንገድ ማስመለስ ወይም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ማስፈጸም ሳይሆን፣ አዲስ አበባ ያለውን የፌደራል መንግሥት በኃይል መገልበጥ ነው ብለዋል።

​የኢሳይያስ አፈወርቂ ሚና፦ በቅርቡ በሸረሪና የተከሰተውን ግጭትና የተማረከውን በርካታ የጦር መሣሪያ እንደ ማሳያ በማቅረብ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ትግራይን ከለላ ለማድረግ «ጠቃሚ ሞኞች»ን በመመልመል በትግራይና በአማራ እናቶችና ሕፃናት ላይ ቁማር እየተጫወቱ ነው ሲሉ ከሰውታል።

​ለትግራይ ሰራዊት የቀረበ ጥሪ፦ ሰራዊቱ ሊገድደው የሚገባው የሕዝቡ ህልውና እንጂ ጦርነትን እንደ ጡረታ ማውጫቸው ያደረጉ ጥቂት አካላት አለመሆናቸውን በመገንዘብ «በቃ» ሊላቸው እንደሚገባና የተደቀነውን ስጋት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንደሚቻል አሳስበዋል።

​ለፌደራል መንግሥቱ፦ የፌደራል መንግሥቱ ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሙሉ ትግበራ ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥልና ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች ቢኖሩም ትዕግሥቱን አጠናክሮ የሰላም አማራጮችን ክፍት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

⨳ በድንበር አካባቢ የሚደረጉ የጦር እንቅስቃሴዎችን ለማረጋገጥ የሳተላይትና የመሬት ላይ ክትትል እንዲደረግ፤
⨳ ግጭት የሚቀሰቅሱ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤
⨳ የሲቪሎችን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ከሁሉም ወታደራዊ ኃይሎች ሙሉ ወታደራዊ ግልጽነት እንዲጠየቅ።

​"በጦርነት ዝግጅት ፊት ዝምታን መምረጥ የጥፋቱ ተባባሪ መሆን ነው" ሲሉ አቶ ጌታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🤪9👍21
ኢራን አሜሪካን መምታት የሚችሉ ሚሳኤሎችን እያዘጋጀች መሆኗን ገለጸች

አንድ ከፍተኛ የኢራን የሃይማኖት መሪ አገራቸው የሜሳይሎቿን የመምታት አቅም እስከ 15 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራች መሆኑንና ይህም አሜሪካን ቀጥታ ለመምታት ያስችላታል ሲሉ በይፋ ተናግረዋል።

የአህቫዝ ከተማ የጁምአ ሶላት መሪ አብዶልነቢ ሙሳቪፋርድ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ አሜሪካውያንም በሚሳኤል መመታት እና በደም እንዲሁም በውድመት ውስጥ መወደቅ ምን እንደሚመስል እንዲረዱትና እንዲቀምሱት በሚል ኢራን ይህንን ረጅም ርቀት ተኳሽ ሚሳኤል እያዘጋጀች መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህ መግለጫ በአይራን ኢንተርናሽናል የተዘገበ ሲሆን፣ የኢራን ባለስልጣናት ቀደም ሲል የነበራቸውን የ2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሳኤል ርቀት ገደብ ለማንሳት እና አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ለማልማት እያደረጉት ያለውን ዝግጅት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ሆኖም ግን የወታደራዊና የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፣ ይህ የኢራን ባለስልጣን የተናገሩት ቃል የፖለቲካ ማስፈራሪያ እንጂ አገሪቱ በአሁኑ ወቅት አሜሪካን መሬት ድረስ መምታት የሚችል 15 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሚሳኤል የላትም።

የኢራን የጦር መሳሪያዎች በአሁኑ ወቅት የሚደርሱት ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ኪሎ ሜትር ብቻ በመሆኑ፣ አቅሟ በመካከለኛው ምስራቅ እና በከፊል አውሮፓ ክልሎች ላይ ብቻ የተገደበ ነው።

ምንም እንኳን ኢራን ለሳተላይት ማሰወንጨፊያ የምትጠቀምበት ቴክኖሎጂ ለወደፊት አህጉር አቋራጭ ሚሳኤሎችን ለመስራት ሊረዳት ቢችልም፣ በአሁኑ ወቅት ግን አሜሪካን የመምታት ዝግጅቱም ሆነ የቴክኖሎጂ ብቃቱ የላትም ነው የተባለው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤣8👍3🥰2🤡1🤪1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ለወደፊት ህይወትዎ አሁን ይወስኑ፡ ወጣት ሴቶች የአላቡጋ ስታርትን ለምን ይመርጣሉ?🌟

የአላቡጋ ስታርት ግልጽ እና ከወጪ ነፃ የሆነየሥራ ስምሪት ፕሮግራም በመሆኑ በብዙዎች ተመራጭ ሆኗል። የፋይናንስ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የተረጋጋ ሥራ፣ የተረጋገጠ ገቢ እና ምቹ ማረፊያ በማቅረብ፣ ይህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ የወደፊት ሕይወታቸውን በመገንባት እና ጠቃሚ ዓለም አቀፍ ልምድ በማግኘት ላይ እንዲያተኩሩ ይረዳል። ለዚህም ነው ብዙ ወጣት ሴቶች በሩሲያ ውስጥ የአላቡጋ ስታርት ፕሮግራምን የሚመርጡት - ሁሉም አስፈላጊ ነገሮች በዜሮ ዋጋ ስለሚሸፈኑ።

በአላቡጋ ስታርት ኢንተርናሽናል ፕሮግራም ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጥራት ላለው ስልጠና እና ስታርት አፕ እድሎች ማመልከት ይችላሉ። ተሳታፊዎች ጥሩ ደመወዝ፣ ነፃ የአየር ዋጋ፣ የህክምና መድን፣ የተደገፈ መኖሪያ ቤት እና ነፃ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን ያገኛሉ። ፕሮግራሙ ምርትን፣ የምግብ አገልግሎትን፣ አቅርቦትን እና መስተንግዶን ጨምሮ ስምንት የስራ ስምሪት ዘርፎችን ይሸፍናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለማመልከት የአላቡጋ ስታርት የስፖርት ፖርታልን ይጎብኙ፡ https://start-alabuga.com
👍54🤣2
😆አውስትራሊያ ለሥራ አጥ ዜጎቿ በየሁለት ሳምንቱ ከ91,000 ብር በላይ ትከፍላለች 🇦🇺
# ይህን ግን ያውቁ ኖሯል

አውስትራሊያ ለሥራ አጥ ዜጎቿ የምታደርገው የገንዘብ ድጋፍ
#አውስትራሊያ "JobSeeker Payment" በተሰኘው የመንግሥት የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራም አማካኝነት፣ ሥራ አጥ ለሆኑና መስፈርቱን ለሚያሟሉ ዜጎቿ በየሁለት ሳምንቱ የፋይናንስ ድጋፍ ታደርጋለች።

* እንደ እ.ኤ.አ 2026 መረጃ መስረት ልጅ የሌለው/ላት አንድ ነጠላ ግለሰብ በየሁለት ሳምንቱ እስከ 808.70 የአውስትራሊያ ዶላር (A$808.70) ማግኘት ይችላል/ትችላለች።

ወደ ብር ስንመነዝረው በየሁለት ሳምንቱ 91 ሺህ 335 ብር ከ87 ሳንቲም ይሆናል፤ ማለትም በወር 182 ሺህ 671 ብር ከ74 ሳንቲም ይደርሳል።

* የሚከፈለው የገንዘብ መጠን እንደ ግለሰቡ የኑሮ ሁኔታ (ልጅ መኖር፣ የትዳር አጋር መኖር ወይም ሌላ የገቢ ምንጭ መኖር) ይወሰናል።

ሥራ አጥ የሆነ ሰው ሁሉ ክፍያው በቀጥታ አይሰጠውም። አመልካቾች የነዋሪነት ሁኔታን፣ የገቢና የንብረት መጠን ምርመራን ማለፍ እንዲሁም በንቃት ሥራ የመፈለግ ግዴታ አለባቸው።

በዓለም ዙሪያ ያሉ አገራት ሥራ አጥ ዜጎቻቸውን ለመደገፍ የተለያዩ አሰራሮችን የሚከተሉ ሲሆን፣ የአውስትራሊያ "JobSeeker" ፕሮግራም የመንግሥት የማህበራዊ ዋስትና (Social Safety Net) አንዱ ማሳያ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍185🤔3👌3🥰1🙏1
የስኬት ባንክ የተከፈለ ካፒታል 7.9 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ የካፒታል መጠን ደግሞ 10.3 ቢሊዮን ብር ደረሰ

ስኬት ባንክ በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 10.3 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንና ፣ የተከፈለ ካፒታሉንም ደግሞ ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር ማሳደጉን አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ በተከናወነ የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ 14.7 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት 1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን አመልክቷል።

የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 የትኩረት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባኤው ላይ በቀረበው ሪፖርት፤ የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠኑን በ51 በመቶ በማሳደግ ወደ 29 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉ ተገልጿል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ፣ የበጀት ዓመቱ በስኬትì መጠናቀቁን ገልጸው፤ አዲስ በተጀመረው የ2019 በጀት ዓመት የባንኩን ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማሳደግ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለደንበኞች የሚሰጡ የአገልግሎት አማራጮችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3🤔3
ኢንሳ አዲስ የወጣውን ወሳኝ የመሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ ይፋ አደረገ

የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) የሀገሪቱን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማጠናከር ያለመ አዲስ ወሳኝ የመሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ አስተዋወቀ። በዋና ዳይሬክተር ንግስት ሃሚድ ይፋ በተደረገው በዚህ አዋጅ መሠረት 12 ቁልፍ ዘርፎች እንደ ወሳኝ መሠረተ ልማት ተለይተዋል።

አዋጁ ዘላቂ ፋይናንስ ለማግኘት የሳይበር ደህንነት ፈንድ ማቋቋሙን የሚመለከት ሲሆን፣ ገንዘቡም ከድርጅቶች ወርሃዊ አስተዋጽኦ፣ ከቅጣት እና ከድጋፍ ይሰበሰባል። የፋይናንስ፣ የትራንስፖርት፣ የኢነርጂ፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ አጠቃላይ ዘርፎቹ የጸጥታ ማዕከላትን የማቋቋም፣ የአደጋ ግምገማዎችን የማካሄድ እና የደህንነት ኦዲት የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ተቋማት ማንኛውንም የሳይበር ጥቃት በ48 ሰዓታት ውስጥ ለብሔራዊ ድንገተኛ አደጋ ምላሽ ቡድን ሪፖርት ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን፣ ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ የአንድ ዓመት የጸጋ ጊዜ ተሰጥቷል። ትእዛዙን በማያከብሩ አካላት ላይም ከ1.5 ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን ብር የሚደርስ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚጣል ይሆናል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9😡4👍2🤣1
"ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ‼️
👉እኛ ከእስር የለቀቅናቸው ወደ አሰራቸው ቡድን የተገለበጡም አሉ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )  በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ገለጹ።
ታጣቂዎቹ ኤርትራን እና ሱዳንን ጨምሮ ከውጭ ተዋናዮች ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በጥንቃቄ ሊረዳው እንደሚገባ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሀገሪቱን በብቸኝነት ይመራ የነበረው ቡድን ያጣውን ሥልጣን በኃይል ለመመለስ ማሰቡ ለሀገሪቱ ግጭቶች መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል።
ሆኖም እኛ እውነት ስለያዝን እናሸንፋለን ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2625👍3🤪2
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
7👍3
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረኢየሱስ በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ "ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም" በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል።

"በቃ!" በማለት ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳይሬክተሩ የፌዴራል መንግሥቱም ሆነ የክልል መሪዎች ከጦር መሣሪያ ይልቅ ለውይይት ቅድሚያ እንዲሰጡና እውነተኛ ፖለቲካዊ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አሳስበዋል። ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያስከትለውን ሰብዓዊ ቀውስ የገለጹት ዶክተር ቴዎድሮስ ግጭት የሞት ፣ የውድመት ፣ የመፈናቀል እና የከፋ እጦት ምንጭ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም "ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል" ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
40👍9🥰5🤔2
ትራምፕ የ“ወሊድ ቱሪዝምን” ለማገድ አዲስ ትዕዛዝ ፈረሙ፤ “የትውልድ ዜግነት መብትን ቀልድ አድርገውታል” ሲሉ ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አንዳንድ የውጭ ሀገር ዜጎች በቱሪስት ቪዛ ተጠቅመው ወደ አሜሪካ በመግባት ልጅ በመውለድ አውቶማቲክ የዜግነት መብት የሚያገኙበትን የ“ወሊድ ቱሪዝም” (Birth Tourism) አሰራር ለማገድ የሚያስችል አዲስ የፕሬዝዳንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ ፈረሙ።

ፕሬዝዳንቱ አዲሱን መመሪያ በኦቫል ኦፊስ (Oval Office) ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ደግፈው ሲናገሩ፦ “የትውልድ ዜግነት መብትን መጫወቻና ቀልድ አድርገውታል” ሲሉ አሰራሩን አጥብቀው ኮንነዋል።

ይህ የትራምፕ አዲስ እርምጃ የመጣው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የትውልድ ዜግነት መብትን ለማገድ ያወጡትን ተመሳሳይ መመሪያ ውድቅ ማድረጉን ተከተሎ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ “በጣም አሳዛኝ ውሳኔ” ሲሉ ገልጸውታል።

የአሜሪካ ሕገ-መንግስት በሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ለሚወለድ ማንኛውም ህጻን (ከዲፕሎማቶች ልጆች በስተቀር) አውቶማቲክ የአሜሪካ ዜግነት መብት ይሰጣል። ይሁን እንጂ የትራምፕ አስተዳደር በስደተኞች እና በዜግነት ፖሊሲው ላይ የሚወስዳቸው ጠንካራ እርምጃዎች እንደቀጠሉ ሲሆን፣ አዲሱ አስፈጻሚ ትዕዛዝም በድጋሚ ከፍተኛ የሕግ ክሶች እና ተቃውሞዎች እንደሚገጥሙት ይጠበቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16🙊4👍2🤣1
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ "ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም" በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። 

ዶክተር ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። 

በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል።

"ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል" ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍9🤔6