አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
421 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ወንዶች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው  በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !   

ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው...

በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።

ይሄንን መሰል አፀያፊ ተግባር እንዳይከሰት መፍትሔ ግን ምን ይሆን ? በጣም አስደንጋጭ ነው ።

Via፦ የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ኮምኒኬሽን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34🤣28😢17💔10🤔8🙉4👍3🙈2👀1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟ህልምዎን እውን ያርጉ!! ከአይሩሳሌም እና እህቷ ልምድ ይውሰዱ!!!🌟

ከሁለት ዓመት በፊት አይሩሳሌም የአላቡጋ ስታርት ዓለም አቀፍ ፕሮግራምን ተቀላቀለች፣ እዚያም የሩሲያ ቋንቋን ተምራ፣ ስኬታማ የባሪስታ ባለሙያ ከመሆኗም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የራሷን ሬስቶራንት ለመክፈት አቅዳለች። ​​በዚህ ስኬቷ በመነሳሳት እህቷም ፕሮግራሙን በመጠቀም በሩሲያ ውስጥ ስልጠና እና ሥራ ማግኘት ችላለች። እህትማማቾቹ ልምዳቸውን ሲያጋሩ እንደሚገልጹት ፕሮግራሙ ታላቅ የእድገት እድሎችን የሚሰጥና እንደ የጊዜ አያያዝ እና አመራር ያሉ እና ሌሎችም የግል እድገት ክህሎቶችን ለማዳበር እድል የሚፈጥር ነው።

የራስዎን ሰራ ለመጀመር ዝግጁ ነዎት?

ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣት ኢትዮጵያዊ ሴቶች ለዚህ ህይወትን የሚቀይር ፕሮግራም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

ሙሉ የጥቅማጥቅም ፓኬጁ ጥሩ ደሞዝ፣ ነፃ የአየር ትኬቶች፣ የህክምና መድን እና ልዩ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን የሚያካትት ሲሆን በስምንት የተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ማመልከት ይቻላል።

ጊዜ ሳያጠፉ ዛሬውኑ በአላቡጋ ስታርት ማመልከቻ ፖርታል https://start-alabuga.com ላይ ያመልክቱ።
8👍2🥰1🎉1
ጦርነት ከተጀመረ የኤርትራ መንግስት አይኖርም፤ ይቀየራል - ባጫ ደበሌ‼️
አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ጦርነት ከተቀሰቀሰ የኤርትራ መንግስት ፋፃሜ ይሆናል ሲሉ አስጠነቀቁ።

ባጫ በቀጠናው መንግስት ይቀየራል ጂኦግራፊ ይቀየራል ሲሉ የጦርነቱን ውጤት ተንብየዋል።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተወሰነ ድንበር የለም ያሉት ባጫ፣ እሱም ራሱ ችግር ይፈጥራል ነው ያሉት።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጦርነት ከተጀመረ ግንባር እና ደጀን አይኖርም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ባጫ ይህን አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረት በተነገሰበት ወቅት መሆኑ አነጋጋሪ ሁኗል።

የቀድሞው የጦር አመራር የአሁኑ ዲፕሎማት ይህን ሁሉ ዛቻ መሰል አስተያየት ከሰጡ በኋላ ግን አያስፈልግም ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3617🥱7👍4
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ  በተደራጀ የኢኮኖሚ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 91 ግለሰቦች መሀል ይገኙበታል ተባለ

​በጉዳዩ ላይ ከተካሄደው ምርመራ ከተገኙ ግኝቶች መካከል፡-

👉​በገቢዎች እና ጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ የተደራጀ ህገ-ወጥ መረብ መኖሩ ተጠቁሟል።

👉​የታክስ ምዘናዎችን ማሻሻጥ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞችን ማስተናገድ እና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን መሰረዝ እንደ ዘዴ ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል።

👉​ድርጊቶቹ የመንግስት ገቢ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ተመልክቷል።

​በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ አስከባሪ አካላት ተይዞ ምርመራው በዝርዝር እየተካሄደ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣149😡4👍3
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚደርስ መሆኑን እና አየር ኃይሉም ይህን ለማስጠበቅ አቅሙን እየገነባ እንደሚገኝ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን እጅግ ሰፊና እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታወቀ። የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት ጌታቸው እንዳሉት፣ ተቋሙ ይህንን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚመጥን ጠንካራ አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን በትጋት እየሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት ጌታቸው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እጅግ በጣም ሰፊና እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚዘልቅ ነው። አየር ኃይሉም ለዚህ አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅም የሚመጥን የላቀ የመከላከል አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን እየሠራ ይገኛል።

ምክትል አዛዡ አክለውም ባላጋራ ኃይሎች የቱንም ያህል ፍላጎትና ዛቻ ቢኖራቸውም፣ የአየር ኃይሉ የመከላከል አቅም በየቀኑ እየጨመረ መምጣቱን በሚገባ ስለሚረዱት ጥቃት ከመሰንዘር መቆጠባቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ የአየር ኃይሉ ከአፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር አሁን ላይ ያለበት ደረጃ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት፤ በተለይም በቴክኖሎጂ፣ በእውቀት እና ራስን ችሎ በመሥራት በኩል ኢትዮጵያ ከፍተኛውን ድርሻ እንደምትይዝ አስረድተዋል።

እንደ ምክትል አዛዡ ገለጻ፣ ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ተቋሙን ለመጎብኘት የሚመጡ የልዑካን ቡድኖች በአየር ኃይሉ ውስጥ ያለውን ዘመናዊ አሠራር ሲመለከቱ ከጠበቁት በላይ ይሆንባቸዋል። በዚህም ምክንያት ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ጋር “በጋራ እንሥራ” የሚሉ ጥያቄዎችን በስፋት የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከሦስት በላይ ከሚሆኑ የአፍሪካ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸውን ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2515👍4🤔1🤩1
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ አስታወቀ

የደንበኞቹ ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን አገልግሎቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው  በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት በበጀት አመቱ  በከተማና በገጠር የኤሌለክትሪክ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ተሰርቷል።

አዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወነው ስራም ከዋናው ግሪድ (የኤሌክትሪክ መረብ) 179 ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል  ከዋናው ግሪድ የራቁ 26 የገጠር ቀበሌዎችና ከተሞችን በኦፍ ግሪድ (በፀሃይ ኃይል) አማራጭ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከዋናው ግሪድና በኦፍ ግሪድ በጠቅላላው 205  የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ አስታውቀዋል።

በበጀት አመቱ 664 ሺህ 505 አዲስ ደንበኞች  የአገልግሎት እንዳገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህም አዲስ ቆጣሪ ያገኙትን ጨምሮ አጠቃላይ የአገልግሎቱ ደንበኞች ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ በ2018 በጀት ዓመት ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 118 ነጥብ 91 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘ  ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታውቀዋል።

የተገኘው ገቢም  ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 88.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢14🌚95👍4🙊1
በአዲግራት ከተማ ደረጃውን ያልጠበቀ የአልኮል መጠጥ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

የዓዲግራት ከተማ ፍርድ ቤት ደረጃውን ያልጠበቀና ፈቃድ ሳይኖረው የታሸገ የአልኮል መጠጥ (አረቄ) ለህብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በ25 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ብስራት ከአዲግራት ከተማ የኮሚኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው ግለሰቦች የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት አንደኛ ተከሳሽ ኢንጂነር ዑቅባይ በርሀ ይፍጠር፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ፅዱቅ በርሀ ይፍጠር እና ሦስተኛ ተከሳሽ ሊቀ ሁሩያን ጋይም አስገለ አለማየሁ ናቸው። ተከሳሾቹ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤት ውስጥ አረቄ በማዘጋጀትና የተለያዩ ስቲከሮችን በመጠቀም አሽገው ለህብረተሰቡ ሲያሰራጩ መቆየታቸው በምስክርነት እና በቤተ-ሙከራ በተረጋገጠ ማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጊቱ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መነሻነት በዓዲግራት ከተማ የጤና ቁጥጥር መስሪያ ቤት የስራ ሃላፊ አቶ ወለገብርኤል ገብሩ እና በከተማዋ ፖሊስ ጥረት አደገኛነቱ ተረጋግጦ ወደ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

የዓዲግራት ከተማ ዓቃቤ ህግ የተጣለውን የፅኑ እስራት ውሳኔ የተቀበለው ቢሆንም በገንዘብ መቀጮው መጠን ላይ ግን ይግባኝ ማለቱን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ የነበሩ የጤና ቁጥጥር አካላት ህብረተሰቡ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን እንዲሁም በህገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ መድኃኒቶችን፣ ሳሙናዎችን፣ ቅቤ፣ ማርና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ ምርቶችን ሲገዛ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ተመሳሳይ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
11👍4👌1
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለተጨማሪ ዉጊያ እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተነገረ‼️

የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ።የአዉሮጳ የሰላም ተቋም መገናኛ ዘዴዎችንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የመቀሌና የአዲስ አበባ ግንኙነት ይበልጥ እየተበላሸ ነዉ።ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉት የጦር ኃይል ንቅናቄም ሌላ ጦርነት ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት አንሮታል።ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታችና ገንቢ በሆነ ዉይይት እንዲፈቱ ተቋሙ ጠይቋል።

የአይን ምሥክሮች በበኩላቸዉ የትግራይ ኃይል የሚባለዉ የታጣቂዎች ስብስብ በርካታ ተዋጊዎችን ወደ ምዕራብ ትግራይ እያዘመተ ነዉ።እንደሚሉት የትግራይ ተዋጊዎች ትግራይ ክልልን ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢም ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባንፃሩ አማራና አፋር ክልሎች ከፍተኛ የወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑን የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል።

ከአፋር ክልል በደረሰን መረጃ መሠረት  በክልሉ የዞን አራት ተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተጨማሪ ወታደሮች ሠፍረዋል።ነዋሪዎቹ በሥም በዘረዘሯቸዉ ወረዳና ቀበሌዎች  ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀሱና ተጨማሪ ኃይል ማስሩ እስከ ትናንት ማታ ድረስ ቀጥሎ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍5
በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ ከሰሞኑ የወጣቶች አፈሳ በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈፀመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።
በዚህ የተነሳ ወጥቶ መግባት አስቸጋሪ ሆኗል ያሉ ሲሆን የተወሰኑ ወጣቶች ገንዘብ እየከፈሉ እየተለቀቁ ነው ብለዋል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍6🤪5😢3💯2
ሲፒጄ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ገለልተኛ የዜና ክፍሎችን “ለመበተን ዘመቻ” እያካሄዱ ነው ሲል ከሰሰ!

ጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድኑ በሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ እነዚህ ተከታታይ ክስተቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግንባር ቀደም ነጻ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት መካከል በአንዱ ላይ የሚደረገውን ጫና በከፍተኛ ሁኔታ ማባበሳቸውን ገልጻል።

የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “በአዲስ ስታንዳርድ እና በዮናስ ከድር ላይ የተፈጸሙት እነዚህ ጥቃቶች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የአገሪቱን ነጻ የዜና ድርጅቶች ለመበተን የሚያካሂዱት ዘመቻ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያሉ” ብለዋል።

አስተባባሪዋ ባለሥልጣናቱ “የተቋሙን ቁሳቁሶች በአፋጣኝ እንዲመልሱ፣ ከቢሮው በግዳጅ የማስወጣት ሂደትን እንዲያስቆሙ፣ ማንኛውንም ተጨማሪ ትንኮሳ እንዲያቆሙ እና ለዮናስ እስርና ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ  እንዲያደርጉ” አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
6👍2
የከባድ መሳሪያ ተኩስ‼️
በራያ ግንባር የሚንቀሳቀሰውና ከሰሞኑ ከባድ መሳሪያዎችን እና ተጨማሪ ታጣቂዎችን ሲያጠጋ የነበረው የህወሃት አርሚ 33 እና 44  ዓዲጉደም ➡️ ደቡብ ወጀራት ➡️ኮንካ ➡️ጎነቕ ➡️ቶንሳ ➡️ንፋሮ መጋለ መስመር በዓዲቀይሕ ወደ ገራርሳ እና ቶንሳ አሁን ዛሬ ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ላይ በትግራይ ሰላም ሰራዊት ላይ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መጀመሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል።

እራሱን 'የትግራይ ሰላም ሰራዊት' በሚል የተደራጀው ታጣቂ ሀይል ወደ መቀሌ ለመግባት ዝግጁ መሆኑን ከሳምንት በፊት አሳውቆ ነበር።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍157👀6🕊2🥱1🤪1
በአርባምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት የመብራት ምሰሶ ላይ ጉዳት ያደረሰው አሽከርካሪ 1 ሚሊዮን ብር ተቀጣ

በአርባምንጭ ከተማ በኮሪደር ልማት ሥራ የተተከለ ዘመናዊ የመንገድ ዳር መብራት ምሰሶ (ፖል) በመግጨት ውድመት ያደረሰ አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ 1 ሚሊዮን ብር እንዲቀጣና የወደመውን ሀብት በራሱ ወጪ ወደ ነበረበት እንዲመልስ ተወሰነ።

በከተማዋ ሲቀላ ክፍለ ከተማ አሽከርካሪው ተሽከርካሪ ለማንቀሳቀስ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ በማሽከርከር በከፍተኛ ወጪ የተተከለውን ስማርት የመብራት ምሰሶ በመግጨት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ የአርባምንጭ ከተማ ደንብ አስከባሪ ጽሕፈት ቤት ከከተማው ትራፊክ ፖሊስ ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ጥፋተኛውን አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል።

የከተማው ደንብ አስከባሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰራዊት ገዛኸኝ እንዳስታወቁት፣ በቸልተኝነት በሚፈጸሙ ጥፋቶች የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት እንዳይባክን እና አስተማሪ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ሲባል የተሰበረውንና የወደመውን ስማርት የመብራት ምሰሶ በራሱ ወጪ ወደ ነበረበት እንዲመልስ።

ጥፋተኛውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከነዋሪዎች የተገኘው የጥቆማ ትብብር ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የገለጹት አቶ ሰራዊት፣ ለኅብረተሰቡ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኃላፊው አክለውም ለከተማዋ እድገትና ለነዋሪዎች ምቾት በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ሥራዎችንና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በሚያበላሹ ወይም ሕግ በሚተላለፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣16🤯1410😢5👍3🙉2🥰1🤪1
አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን በእስር ላይ ሆነው እንዲከታተሉ አቃቢ ህግ አቅርቦት የነበረው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ እና በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ብይን ተሰጠ።

አቃቢ ህግ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾች እና ጠበቃቸው፣ የተከሰሱበት የክስ መዝገቡ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ እና በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት ሆኖ እያለ በሚዲያ ላይ በመቅረብ ከክሱ አውድ ውጪ የሆነ ማብራሪያ በመስጠታቸው የፍትሕ ሂደቱን ተጽዕኖ ውስጥ ለመክተት እና ምስክሮችን ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ሞክረዋል በሚል የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ከማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር።

በተጨማሪም ዘገባው የተጫነበት ሚዲያ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ቪዲዮውን እንዲያወርድ ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 457 ስር በቀጥታ እንዲቀጡ እንዲወሰን የሚሉ አቤቱታዎችንም አቃቢ ህግ አካቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ማስጠንቀቂያ ፦ ይህ ቪዲዮ አስደንጋጭ እና ለአንዳንድ ተመልካቾች ሊረብሽ የሚችል ምስል ይዟል። ከመመልከትዎ በፊት ጥንቃቄ ያድርጉ።

በታይላንድ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ግዛት እየተካሄደ በነበረ የእግር ኳስ ውድድር ላይ አንድ እግር ኳስ ተጫዋች በመብረቅ ተመትቶ ህይወቱን አጥቷል።

ጨዋታው በከባድ ዝናብ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው መብረቅ በሜዳው ላይ በመውረድ ተጫዋቹን የመታው።

ከአደጋው በኋላ ተመልካቾች እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እርዳታ ቢያደርጉም፣ ወደ ሆስፒታል ቢወስዱም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።

ባለሥልጣናት በአደጋው ተጨማሪ 12 ሰዎች በቃጠሎ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3212👍2🤯1
ብዙ ስፍራዎች ኤርትራ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ ይጠራሉ- ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኦቢኤን።
📌በ1512 ዓ.ም የባሕረ ነጋሽ (የዛሬዋ ኤርትራ) ንጉሥ የነበረው 'ዶሪ' ኦሮሞ እንደነበር፣ በተጨማሪም 'ባሬንቱ' የተሰኘው ትልቅ ከተማ እና እንደ አምባ ሶይራና አምባ ደብራ ያሉ ተራራዎች ስያሜያቸው የኦሮሞ ሥረ-መሠረት እንዳለው አስረድተዋል።
📌በ1499 ዘርፀድንግል የኦሮሞ ሰራዊትን ይዞ እስከ ምፅዋ ታግሏል ብለዋል።
📌ኦሮሞ ደሙን ያላፈሰሰበት አጥንቱን ያልከሰከሰበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም ብለዋል።
📌ኦሮሞ በታሪኩ የተቃወመው የተበላሸ አስተዳደርን እንጂ ኢትዮጵያን አይደለም ብለዋል።
📌ኦሮሞ ነፃ ወጥቷል፤ ግራ፣ ቀኝ፣ ኋላ፣ ፊት ማየት አያስፈልግም። ኦሮሞን ነፃ ለማውጣት ዛሬ መታገል ሞኝነት ነው"ሲሉ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🥱33🙉18🤪1510👍8🤣4😱1👀1🙊1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟ህልምዎን እውን ያርጉ!! ከአይሩሳሌም እና እህቷ ልምድ ይውሰዱ!!!🌟

ከሁለት ዓመት በፊት አይሩሳሌም የአላቡጋ ስታርት ዓለም አቀፍ ፕሮግራምን ተቀላቀለች፣ እዚያም የሩሲያ ቋንቋን ተምራ፣ ስኬታማ የባሪስታ ባለሙያ ከመሆኗም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የራሷን ሬስቶራንት ለመክፈት አቅዳለች። ​​በዚህ ስኬቷ በመነሳሳት እህቷም ፕሮግራሙን በመጠቀም በሩሲያ ውስጥ ስልጠና እና ሥራ ማግኘት ችላለች። እህትማማቾቹ ልምዳቸውን ሲያጋሩ እንደሚገልጹት ፕሮግራሙ ታላቅ የእድገት እድሎችን የሚሰጥና እንደ የጊዜ አያያዝ እና አመራር ያሉ እና ሌሎችም የግል እድገት ክህሎቶችን ለማዳበር እድል የሚፈጥር ነው።

የራስዎን ሰራ ለመጀመር ዝግጁ ነዎት?

ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣት ኢትዮጵያዊ ሴቶች ለዚህ ህይወትን የሚቀይር ፕሮግራም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

ሙሉ የጥቅማጥቅም ፓኬጁ ጥሩ ደሞዝ፣ ነፃ የአየር ትኬቶች፣ የህክምና መድን እና ልዩ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን የሚያካትት ሲሆን በስምንት የተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ማመልከት ይቻላል።

ጊዜ ሳያጠፉ ዛሬውኑ በአላቡጋ ስታርት ማመልከቻ ፖርታል https://start-alabuga.com ላይ ያመልክቱ።
7