አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
421 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑ ተነገረ‼️
"የዘመሙ አካሄዶች ሲታዩ በጊዜውና በወቅቱ ዕርምት ይደረግባቸዋል"
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
- 250ው ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል
የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ገለጹ
በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ  አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል።
ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው  የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል።
በተለይ የተቋማት ግንባታን በተመለከተ፣ “ስለ ተቋም ግንባታ ለእኛ አትነግሩንም፣ የተቋም ግንባታ ምን መሆን እንዳለበት እናውቃለን፣ ተቋሙን የምንመራው እኛ ነን፣ ሪፎርም አድርገናል” ተቋማትን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ተቆጥተው ውይይት ጥለው የወጡ ተመካካሪዎች እንደነበሩም አክለዋል።
አመካካሪዎች በሙስናና መልካም አስተዳደር አጀንዳ ሥር፣ ንዑስ አጀንዳ በሆነው የሙስና ጉዳዮች፣ በአንዳንድ ቡድኖች ከስምምነት እንዳይደረስና ለውይይት በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ
ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት ሐሳብ ተንዛዝቶ ከመግባባት ለመድረስ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን ድረስ ውይይት እንዲቀጥል ማስገደዱን አስረድተዋል።
የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን በተመለከተ የፅንሰ ሐሳብ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ በኮሚሽኑ የተመደቡ ምሁራን (Panel of Experts)፣ በተለይ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል ትሁን
በሚለው የአጀንዳ ሐሳብ ፅንፍ በያዘ ሁኔታ መከራከራቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
ሆኖም ይህን አካሄድ የተከተሉ ምሁራን ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ይቅርታ መጠየቀታቸውን ተመካካሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።
በቃለ ጉባዔ ያዥነት የተመደቡ አንዳንድ ባለሙያዎችም የቀረቡ ሐሳቦችን በሙሉ ያለማጠናከርና በፈለጉት መንገድ ብቻ የመሰነድ ችግር እንደተስተዋለባቸው ተናግረዋል። እነዚህ ቃለ ጉባዔ ያዦች የአንዱን ሐሳብ ይዘው የሌላውን የመተው አካሄድ መከተላቸው ተነግሯል።
በመሆኑም እንዲህ ያሉ ድርጊቶች አስፈላጊ እንዳልሆኑ፣ የምክክሩም ዓላማ ይህ እንዳልሆነ የገለጹት የመረጃ ምንጮቹ አሁን ያሉ ተቋማት ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የማይሰሩና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመፍታት ከፍተኛ ችግሮች ስላሉባቸው፣ ውሃው እንዳይደርቅና አሳውም እንዳይሞት መታረምና መስተካከል እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።
ኮሚሽኑም እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን ጣልቃ ገብቶ በጊዜ እንዲታረሙ ማድረግ እንዳለበትም
አስገንዝበዋል።
በዚሁ ረገድ የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይ ትልቁ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደነበር፣ በዚህም አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት አካልና ዋና መቀመጫ ከተማ እንድትሆን ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል።
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሌሎች የፌዴራል ከተሞች እንዲኖሩ ሰፊ ምክረሐሳብ መቅረቡን፣ ለዚህም ደቡብ አፍሪካ እንደ ምሳሌ መቅረቧን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ከተማ የራሷ የሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የተጠናከረ የፖሊስ ኮሚሽን እንዲኖራትና በከተማዋ ውስጥ የሚሰየሙ የሰፈር ስሞች የአገር አንድነትንና የሁሉንም ማኅበረሰብ ውክልና እንዲኖራቸው ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል የሥራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ የአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እንዲቀጥል ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል። ሆኖም አማርኛ፣ ኦሮሚኛና፣ ትግርኛ፣ አፋርኛና ሶማሊያ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች ከሆኑ የአዲስ አበባም እንዲሆኑ ሐሳብ መኖሩን ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24👍7🤔4😢1👀1🫡1
በፑንትላንድ እና በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት መካከል በተካሄደ ግጭት የፑንትላንድ ኃይሎች የፌዴራል መንግሥቱን  የጦር ካምፕ መቆጣጠራቸውን ገለጹ!

የሶማሊያ ከፊል ራስ-ገዝ አስተዳደር በሆነችው ፑንትላንድ እና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል ያለው ውጥረት እንደገና ባነሰራበት በዚህ ወቅት፣ የፑንትላንድ ታጣቂ ኃይሎች ትላንት በጋልካዮ በሚገኘው የፌዴራል መንግሥት ጦር ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በቦሳሶ የሚገኘውን በፌዴራል መንግሥቱ የተቋቋመ “የፑንትላንድ ደህንነት ኃይል” (PSF) የጦር ካምፕ መቆጣጠራቸውን ገለጹ።

የፑንትላንድ ፕሬዚዳንት ሳይድ አብዱላሂ ደኒ ረቡዕ ዕለት በክልሉ መዲና ጋሮዌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በጋልካዮ የተካሄደው ጥቃት “በፑንትላንድ መንግሥት ላይ ተቃውሞ በሚያነሱ አካላት ላይ ግልጽ መልእክት ለማስተላለፍ” ታስቦ የተካሄደ “የታቀደ የደህንነት እርምጃ” ነው ብለዋል።ረቡዕ ዕለት የተካሄደው ይህ ግጭት በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ የተኩስ ልውውጥ የተደረገበት ሲሆን፣ የሲቪሎችን መፈናቀል እና የሰው ህይወት ጉዳት ማድረሱ ተዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍74💯1🤣1
የሚስቱን ጓደኛ ክብረ ንጽህና አታሎ የደፈረው በእስራት ተቀጣ!

የ19 ዓመት ወጣት የሆነችውን የሚስቱን ጓደኛ "ሚስቴ ቤት ትፈልግሻለች፣ ቡና አፍልታ እየጠበቀችሽ ነው፤"በማለት አታሎ ግብረ ስጋ ግንኘነት በማድረግ ክብረ ንጽህና የገረሰሰው ግለሰብ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ አንተነህ ተዘራ የተባለው ግለሰብ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3 00ሰአት ላይ በሐረር ከተማ አቦከር ወረዳ ልዩ ስፍራው ወርዋሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ19 አመት ወጣት የሆነችውን አስገድዶ በመድፈሩ በእስራት መቀጣቱን የሴቶችና ህፃናት መርማሪ የሆኑት ሣጅን አዚዛ አህመድ ገልፀዋል ።

መርማሪዋ እንደገለፁት ተከሳሹ የ19 አመት እድሜ ያላትን  ወጣት የሚስቱን ጓደኛ ሚስቴ የምሰራበት ቦታ ልትጠይቀኝ መታለችና ነይ አንቺም ቡና ተፈልቷል ትጠጭያለሽ እኛጋር ታድሪያለሽ በማለት አታሎ በመውሰድ ሀይል በመጠቀም የግብረስጋ ግንኙነት የፈፀመባት ክብረ ንጽሕና የገረሰሳ በመሆኑ በፈፀመው አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድቤት ሀምሌ 27 28/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አንተነህ ተዘራ በ 5 አመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲሉ የህፃናትና ሴቶች ወንጀል መርማሪ የሆኑት ሳጅን አዚዛ አህመድ ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2320😢8👍2🤔2👀2🤯1💔1🙈1
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2018 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ የሱባዔ መልእክት አስተላለፉ
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ለ2018 ዓ.ም ጾመ ማርያም (ፍልሰታ) ባስተላለፉት የቡራኬና የሱባዔ መልእክት፣ ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅና ፍቅርን በመተግበር ሱባዔውን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቀረቡ።
 
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው እግዚአብሔርን መውደድ በምናባዊ ነገር ሳይሆን ትእዛዙን በመጠበቅና ባልንጀራን ፤ መላውን የሰው ወገን እንደ ራስ አድርጎ በመውደድ የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ድንግል ማርያም ከአእላፋት መላእክት በላይ የምትበልጥ የአምላክ ማደሪያ በመሆኗ፣ ምእመናን በጾሙ ወቅት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ እመቤታችንን ሊያከብሯትና በጸሎቷም ሊታመኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
በ15ቱ የሱባዔ ወቅት የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ እንዲሁም በንሥሐና በቅዱስ ቁርባን ማለፍ እንደሚገባ አዝዘዋል።
 
በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ሥጋት የሆነውንና ፍጥረትን የሚያወድመውን ጦርነት እግዚአብሔር በኃይሉ እንዲያስቆም ምእመናን በሱባዔው ወቅት በትሑት ሰብእናና በቅን ልቦና እንዲጸልዩ አባታዊ አደራቸውን አስተላልፈዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
59🥰5🙏4👍2
የመብራት ምሰሶዎችን ከገጩ አሽከርካሪዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የጉዳት ካሳ ተሰበሰበ
 
በአዲስ አበባ ከተማ በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የመብራት ምሰሶዎችን ከገጩ አሽከርካሪዎች 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የጉዳት ካሳ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።
 
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን እንደገለፁት ባለስልጣኑ ከተቋቋመ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የከተማዋን የመብራት አገልግሎት ዘመናዊ ለማድረግ የተለያዩ የልማትና የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል።
 
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ 41 ሺህ 283 የመብራት ምሰሶዎች በጂኦግራፊያዊ የመረጃ ሥርዓት  እንዲመዘገቡ መደረጉ ተገልጿል። ይህ ሥርዓት የመብራት ምሰሶዎችን በዲጂታል መንገድ ለመከታተል፣ ቁጥጥርን ለማጠናከር እና የጥገና ሥራዎችን በፍጥነትና በብቃት ለማከናወን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
 
ባለስልጣኑ ለብስራት ሬዲዮ የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው  የከተማዋን የመብራት መሠረተ ልማት ይበልጥ ለማዘመን፣ የህዝብ ንብረትን ከጉዳት ለመጠበቅ እና ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመቀነስ የቁጥጥርና የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9😢9👍3🤔2👀2
ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል‼️
የተቋማት ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ።
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ፡፡
የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡
በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡
በጥናቱ ጉቦ ለመስጠት የሚገደዱ ሰዎች ለድርጊታቸው የሚያቀርቡት አንዱ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ግለሰቦች ጉቦ የሚሰጡት የሚፈልጉት አገልግሎት እንዲፈጸምላቸውና የሚጠበቅባቸውን ባለማድረጋቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለማስቀረት መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡

የሙስና ድርጊትን ለመጠቆም የሚፈልጉ ግለሰቦች ሊደርስባቸው የሚችል የበቀል ዕርምጃና የማስፈራራት ሥጋት በመኖሩ፣ አስተማማኝ የጠቋሚዎች ጥበቃ ሥርዓት ማነስ፣ እንዲሁም የጥቆማ አሰጣጥ ሒደቱ ረዥምና ውስብስብ መሆን ኅብረተሰቡ ሙስና ለመጠቆም ሥጋት እንዳለበት በጥናቱ መገለጹ ተነግሯል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍11🤪6🥰1🤣1
የትግራይ ሚዲያዎች ከምድር በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ተሸጋግረዋል‼️
"ጥምረቱና ትብብሩ ወደ ከፍተኛ የትግል ደረጃ ተሸጋግሯል" ሲሉ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የሆኑት ገብረ ገብረፃድቃን(ዓዴት) በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።
ህወሓት የፌደራል መንግስቱን በጦርነት ለመጣል ወደ ራያ እና አፋር ድንበር መካናይዝድ ጦሩን ጨምሮ እያስጠጋ የሚገኝ ሲሆን መንግስትም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
የትግራይ ሚዲያዎች ከመሬት በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ውስጥ መግባታቸውን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣17👍145🙊2🕊1🤡1🤪1
በመዲናዋ ሆቴሎችን ጨምሮ የምሽት መዝናኛዎች የድምፅ ብክለት መጨመሩ ተገለፀ

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለቁጥጥር  የሚያመች የድምፅ ብክለት መመሪያ እያዘጋጀሁ እገኛለሁ ብሏል።

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን  በበጀት አመቱ በ12 ሺህ 3መቶ 76 ተቋማት ላይ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል።

በመዲናዋ ሆቴሎች፣ ግሮሰሪዎች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች በስፋት መኖራቸዉን ተከትሎ ህብረተሰቡ መረበሹን ቅሬታ እየቀረበ መገኘቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና አማካሪ አቶ አዱኛ ወንድሙ በመዲናዋ የሆቴሎችና የምሽት መዝናኛ ተቋማት መስፋፋትን ተከትሎ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት መኖሩን ተናግረዋል።

በአገልግሎት ዘርፍ ባሉ ተቋማት ላይ ክትትል ብቻ ሳይሆን እርምጃ እየወሰድኩ ነዉ ያለዉ ባለስልጣኑ ሆቴሎች እና ግሮሰሪዎችን ጨምሮ 3 ሺህ 1መቶ 16 በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

አቶ አዱኛ ከተሰጡት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷቸዉ ያላስተካከሉ ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

በዚህም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ 28ቱ ላይ የማሸግ እርምጃ እንደተወሰደ ተገልጿል።

የድምፅ ብክለት ላይ ችግሮች እንዳሉ የሚናገሩት የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና አማካሪ አቶ አዱኛ ወንድሙ፤የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸዉ አስረድተዋል።

የድምፅ ብክለት መመሪያን በማዘጋጀት ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን አማካሪዉ የገለፁ ሲሆን፤ አሁን ያለዉን ብክለት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ ያግዛል ተብሎ እንደታመነበት አንስተዋል።

የአዲስ አበባ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተጠናቀቀው 2018 የበጀት አመት የአካባቢ ብክለትንና የአየር ንብረት ለዉጥ ስራዎችን አስመልክቶ በዛሬዉ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9🥱2
የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️
በሱዳን የሚንቀሳቀሰው የህወሓት አርሚ 70 በሸረሪና ግንባር አከማችቶት የነበረው የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️
ከሸረሪና ካምፕ ወጣ ብሎ 'ግዴማ' በተባለች ቦታ መጋዘን ውስጥ እንዲሁም ከመሬት በታች በኮንክሪት በተሰራ ግዙፍ ምሽግ ተጠራቅሞ የነበረ ተተኳሽ፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ ሮኬት፣ የአጭር እና መካከለኛ ርቀት ሚሳይሎች፣ RPG-7፣ የሳተላይት ስልኮች፣ የሬዲዮ መገናኛ፣ የቅኝት ድሮኖች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ለጊዜው ምንነታቸውን ለመለየት ያልተቻሉ የጦር መሳሪያዎች ገቢ መደረጋቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል።

እንደ ወታደራዊ ምንጮቹ ገለፃ ከሆነ፤ በትናንትናው እለት ብቻ ከሸረሪና እና ግዴማ ካምፕ 31 ከባድ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ከአርሚ 70 የተማረኩ የተለያዩ ትጥቆችን ወደ ሁመራ እና ዳንሻ ከተማ ተጓጉዘዋል።
ለዚህ ዲፖ መገኘት የተማረኩ የአርሚ 70 ታጣቂዎች አስተዋጽኦ አድርገዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
42🤣22👍9👌3🤪3😢1👀1🙊1
ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ወንዶች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው  በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !   

ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው...

በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።

ይሄንን መሰል አፀያፊ ተግባር እንዳይከሰት መፍትሔ ግን ምን ይሆን ? በጣም አስደንጋጭ ነው ።

Via፦ የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ኮምኒኬሽን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
34🤣28😢17💔10🤔8🙉4👍3🙈2👀1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌟ህልምዎን እውን ያርጉ!! ከአይሩሳሌም እና እህቷ ልምድ ይውሰዱ!!!🌟

ከሁለት ዓመት በፊት አይሩሳሌም የአላቡጋ ስታርት ዓለም አቀፍ ፕሮግራምን ተቀላቀለች፣ እዚያም የሩሲያ ቋንቋን ተምራ፣ ስኬታማ የባሪስታ ባለሙያ ከመሆኗም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የራሷን ሬስቶራንት ለመክፈት አቅዳለች። ​​በዚህ ስኬቷ በመነሳሳት እህቷም ፕሮግራሙን በመጠቀም በሩሲያ ውስጥ ስልጠና እና ሥራ ማግኘት ችላለች። እህትማማቾቹ ልምዳቸውን ሲያጋሩ እንደሚገልጹት ፕሮግራሙ ታላቅ የእድገት እድሎችን የሚሰጥና እንደ የጊዜ አያያዝ እና አመራር ያሉ እና ሌሎችም የግል እድገት ክህሎቶችን ለማዳበር እድል የሚፈጥር ነው።

የራስዎን ሰራ ለመጀመር ዝግጁ ነዎት?

ከ18 እስከ 22 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወጣት ኢትዮጵያዊ ሴቶች ለዚህ ህይወትን የሚቀይር ፕሮግራም ለማመልከት ብቁ ናቸው።

ሙሉ የጥቅማጥቅም ፓኬጁ ጥሩ ደሞዝ፣ ነፃ የአየር ትኬቶች፣ የህክምና መድን እና ልዩ የሩሲያ ቋንቋ ኮርሶችን የሚያካትት ሲሆን በስምንት የተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ማመልከት ይቻላል።

ጊዜ ሳያጠፉ ዛሬውኑ በአላቡጋ ስታርት ማመልከቻ ፖርታል https://start-alabuga.com ላይ ያመልክቱ።
8👍2🥰1🎉1
ጦርነት ከተጀመረ የኤርትራ መንግስት አይኖርም፤ ይቀየራል - ባጫ ደበሌ‼️
አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ጦርነት ከተቀሰቀሰ የኤርትራ መንግስት ፋፃሜ ይሆናል ሲሉ አስጠነቀቁ።

ባጫ በቀጠናው መንግስት ይቀየራል ጂኦግራፊ ይቀየራል ሲሉ የጦርነቱን ውጤት ተንብየዋል።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተወሰነ ድንበር የለም ያሉት ባጫ፣ እሱም ራሱ ችግር ይፈጥራል ነው ያሉት።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጦርነት ከተጀመረ ግንባር እና ደጀን አይኖርም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ባጫ ይህን አስተያየት የሰጡት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረት በተነገሰበት ወቅት መሆኑ አነጋጋሪ ሁኗል።

የቀድሞው የጦር አመራር የአሁኑ ዲፕሎማት ይህን ሁሉ ዛቻ መሰል አስተያየት ከሰጡ በኋላ ግን አያስፈልግም ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3617🥱7👍4
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ  በተደራጀ የኢኮኖሚ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 91 ግለሰቦች መሀል ይገኙበታል ተባለ

​በጉዳዩ ላይ ከተካሄደው ምርመራ ከተገኙ ግኝቶች መካከል፡-

👉​በገቢዎች እና ጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ የተደራጀ ህገ-ወጥ መረብ መኖሩ ተጠቁሟል።

👉​የታክስ ምዘናዎችን ማሻሻጥ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞችን ማስተናገድ እና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን መሰረዝ እንደ ዘዴ ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል።

👉​ድርጊቶቹ የመንግስት ገቢ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ተመልክቷል።

​በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ አስከባሪ አካላት ተይዞ ምርመራው በዝርዝር እየተካሄደ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣149😡4👍3
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚደርስ መሆኑን እና አየር ኃይሉም ይህን ለማስጠበቅ አቅሙን እየገነባ እንደሚገኝ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን እጅግ ሰፊና እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታወቀ። የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት ጌታቸው እንዳሉት፣ ተቋሙ ይህንን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚመጥን ጠንካራ አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን በትጋት እየሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት ጌታቸው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እጅግ በጣም ሰፊና እስከ ሕንድ ውቅያኖስ የሚዘልቅ ነው። አየር ኃይሉም ለዚህ አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅም የሚመጥን የላቀ የመከላከል አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን እየሠራ ይገኛል።

ምክትል አዛዡ አክለውም ባላጋራ ኃይሎች የቱንም ያህል ፍላጎትና ዛቻ ቢኖራቸውም፣ የአየር ኃይሉ የመከላከል አቅም በየቀኑ እየጨመረ መምጣቱን በሚገባ ስለሚረዱት ጥቃት ከመሰንዘር መቆጠባቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል፣ የአየር ኃይሉ ከአፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር አሁን ላይ ያለበት ደረጃ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት ብርጋዴር ጄኔራል መሠረት፤ በተለይም በቴክኖሎጂ፣ በእውቀት እና ራስን ችሎ በመሥራት በኩል ኢትዮጵያ ከፍተኛውን ድርሻ እንደምትይዝ አስረድተዋል።

እንደ ምክትል አዛዡ ገለጻ፣ ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ተቋሙን ለመጎብኘት የሚመጡ የልዑካን ቡድኖች በአየር ኃይሉ ውስጥ ያለውን ዘመናዊ አሠራር ሲመለከቱ ከጠበቁት በላይ ይሆንባቸዋል። በዚህም ምክንያት ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ጋር “በጋራ እንሥራ” የሚሉ ጥያቄዎችን በስፋት የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከሦስት በላይ ከሚሆኑ የአፍሪካ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸውን ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪2515👍4🤔1🤩1
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ አስታወቀ

የደንበኞቹ ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን አገልግሎቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው  በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት በበጀት አመቱ  በከተማና በገጠር የኤሌለክትሪክ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ተሰርቷል።

አዲስ የገጠር ቀበሌዎችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወነው ስራም ከዋናው ግሪድ (የኤሌክትሪክ መረብ) 179 ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል  ከዋናው ግሪድ የራቁ 26 የገጠር ቀበሌዎችና ከተሞችን በኦፍ ግሪድ (በፀሃይ ኃይል) አማራጭ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከዋናው ግሪድና በኦፍ ግሪድ በጠቅላላው 205  የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ አስታውቀዋል።

በበጀት አመቱ 664 ሺህ 505 አዲስ ደንበኞች  የአገልግሎት እንዳገኙ ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህም አዲስ ቆጣሪ ያገኙትን ጨምሮ አጠቃላይ የአገልግሎቱ ደንበኞች ቁጥር 5 ነጥብ 88 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ በ2018 በጀት ዓመት ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 118 ነጥብ 91 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘ  ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታውቀዋል።

የተገኘው ገቢም  ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 88.4 በመቶ ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢14🌚95👍4🙊1
በአዲግራት ከተማ ደረጃውን ያልጠበቀ የአልኮል መጠጥ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

የዓዲግራት ከተማ ፍርድ ቤት ደረጃውን ያልጠበቀና ፈቃድ ሳይኖረው የታሸገ የአልኮል መጠጥ (አረቄ) ለህብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በ25 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑን ብስራት ከአዲግራት ከተማ የኮሚኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው ግለሰቦች የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት አንደኛ ተከሳሽ ኢንጂነር ዑቅባይ በርሀ ይፍጠር፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ፅዱቅ በርሀ ይፍጠር እና ሦስተኛ ተከሳሽ ሊቀ ሁሩያን ጋይም አስገለ አለማየሁ ናቸው። ተከሳሾቹ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤት ውስጥ አረቄ በማዘጋጀትና የተለያዩ ስቲከሮችን በመጠቀም አሽገው ለህብረተሰቡ ሲያሰራጩ መቆየታቸው በምስክርነት እና በቤተ-ሙከራ በተረጋገጠ ማስረጃ ተረጋግጧል።

ድርጊቱ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መነሻነት በዓዲግራት ከተማ የጤና ቁጥጥር መስሪያ ቤት የስራ ሃላፊ አቶ ወለገብርኤል ገብሩ እና በከተማዋ ፖሊስ ጥረት አደገኛነቱ ተረጋግጦ ወደ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

የዓዲግራት ከተማ ዓቃቤ ህግ የተጣለውን የፅኑ እስራት ውሳኔ የተቀበለው ቢሆንም በገንዘብ መቀጮው መጠን ላይ ግን ይግባኝ ማለቱን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ የነበሩ የጤና ቁጥጥር አካላት ህብረተሰቡ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን እንዲሁም በህገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ መድኃኒቶችን፣ ሳሙናዎችን፣ ቅቤ፣ ማርና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ ምርቶችን ሲገዛ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ተመሳሳይ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

@Addis_Reporter
11👍4👌1