የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል በዩክሬን ላይ ጥቃት ሰነዘረ‼️
የሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ከሰሜን ኮሪያ ያገኙትን አጭር ርቀት ተኳሽ ባሊስቲክ ሚሳይል በዩክሬን ላይ እንደገና መተኮስ መጀመራቸውን የዩክሬን የመከላከያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
በጥቃቱ በዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልል ራዱሽኔ መንደር የሚገኝ የቮሮኖቭ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በሙሉ ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን የበርካታ ሲቪሎች ሕይወት አልፏል።
የዩክሬን ራዳር ሥርዓቶች እንደመዘገቡት ጥቃቱ በሰሜን ኮሪያ ሰራሹ KN-23 ወይም KN-24 ሚሳይል አማካኝነት ከሩሲያ ብሪያንስክ ክልል የተተኮሰ ነው።ይህ ጥቃት ሩሲያ ከፒዮንግያንግ አዲስ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ማግኘቷንና ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብራቸውን ማጠናከራቸውን ያሳያል።
እነዚህ ሚሳይሎች ከሩሲያው 'እስካንደር' ጋር ተመሳሳይ ዝቅተኛ የጉዞ መስመር ያላቸው በመሆናቸው ለመምታት የላቀ የፓትሪዮት አየር መከላከያ ይፈልጋሉ።
ይህም ለሰሜን ኮሪያ የጦር መሣሪያዎቿን በእውነተኛ የውጊያ ሜዳ ላይ እንድትፈትሽ እድል ሲሰጥ፣ ለሩሲያ ደግሞ የዩክሬንን የጦር መሣሪያ እጥረት በመጠቀም ከፍተኛ ጥቃት ለመሰንዘር ያስችላታል።
@Addis_Reporter

❤18👍6🤯1
የታጠቁ ኃይሎች አራት ኪሎ ባዶ ሁኖ "ኑና ቤተመንግሥት ግቡ" ቢባሉ ወደ አዲስ አበባ አይመጡም‼️
👉 የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጀነራል አምባሳደር #ባጫ_ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ (BBC News Amharic) ጋር ያደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ የተገለፀ ሲሆን፤ ቢቢሲ ከቃለ-መጠይቁ አጠር አድርጎ ያወጣው አነስተኛ የቪዲዮ ምስል ቀጣዩን አቅጣጫ ጠቋሚ በመሆኑ በድጋሚ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
በዚህ አጭር መግለጫቸው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ የታጠቁ ግጭቶች ከመጨራረስ ውጭ ምንም ዓይነት ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ያስገነዘቡት ጀነራል አምባሳደሩ፤ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ አካላትን አቅም አስመልከተው ሲናገሩም "አራት ኪሎ ክፍት ሆኖ ኑና ግቡ ቢባሉም እንኳን #ፋኖም ሆነ #ኦላ (ጃል መሮ) አይመጡም፤ መጥተውም የሚያደርጉት ነገር የለም" ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም፤ "እንደ #ዘመነ_ካሴ ያሉ የውጊያ መሪዎች መጥተው አራት ኪሎ የመግባትና ሀገር የመምራት አቅም የላቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በጦርነት ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ የሚባል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጀነራል አምባሳደሩ፣ "የታጠቁ ኃይሎች ገንዘብ ከፈለጉ ከመንግስት ይውሰዱና ህዝቡን ይተውት" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ካልሆነ ግን የትግሉ መጨረሻ የህዝብና የሀገር መጨራረስ ብቻ ሆኖ እንደሚቀርና ማንኛውም ወገን የፖለቲካ ማተርፊያ እንደማያገኝበት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

🤪39🤣23❤22👍8👀2
የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ መልዕክት የደረሳቸው የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያቸውን በመፈጸም የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ በሰጡት መግለጫ፣ቢሮው የግብር ስርዓቱን በማዘመን እና ፍትሃዊ አሰባሰብን በመዘርጋት ገቢን በጥራት እየሰበሰበ ይገኛል ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ከሚሰበስበው ገቢ 72 በመቶውን ለዘላቂ ልማት፣ ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እና ለኮሪደር ልማት በማዋል የመዲናዋን ገጽታና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እያጎለበተ ይገኛልም ብለዋል።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ከ456 ሺህ በላይ የደረጃ «ለ» ግብር ከፋዮች አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ከደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በዘንድሮ በጀት ዓመት 9.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።

❤12👍2😡2😢1
የኤቦላ ቫይረስ በአሳሳቢ ሁኔታ እየተሰራጨ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አሳወቀ
የዛሬ ሁለት ወራት ተኩል ገደማ በኮንጎ የተከሰተው የኤቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በአሳሳቢና ባልተጠበቀ ሁኔታ በሀገሪቱ እየተሰራጨ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በምህፃሩ MSF አስታወቀ።
ድርጅቱ እንደሚለው በሽታውን ለመከላከል የህክምና ባለሞያዎች ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ወረርሽኙ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአሳሳቢ ሁኔታ እየተሰራጨ ይገኛል።
እስካሁን ከ3 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በላቦራቶሪ ተረጋገጧል፤ ቁጥራቸው 1 ሺህ 500 የሚጠጋ ሰዎችም ሞተዋል።
በአሁኑ ጊዜ ዋናው ተግዳሮት ባለሥልጣናት በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች መለየት እንደተሳናቸው መሆኑ ነው።
ቡንያ በተባለው አካባቢ የሚገኝ የህክምና ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት በሽተኞች ውስጥ 90 በመቶው ከዚህ ቀደም በኤቦላ ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው የሚታወቅ ነገር የለም።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከመንግሥት ኃላፊዎችና ከሰብአዊ ድርጅቶች ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ ሄደዋል።
ዶክተር ቴዎድሮስ የኤቦላ ወረርሽኝ ከተሰከሰተ ወዲህ ወደ ኮንጎ ሲጓዙ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

❤10👍2😱1
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 ዓመታት በላይ በመሪነት በማገልገል ተቋሙን ወደ አፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት አቶ ተወልደ፣ አሁን የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ የሆነውን ኤር ኢንዲያን ይመራሉ።
ኤር ኢንዲያ በቅርብ ጊዜ ከደረሰበት የአውሮፕላን አደጋ እና ከሌሎች የሥራ ተግዳሮቶች በኋላ አዲስ አመራር እየፈለገ ሲሆን፣ አቶ ተወልደ በቀድሞ የአመራር ልምዳቸው እና በአቪዬሽን ዘርፍ ባላቸው ስኬት ተመርጠዋል።
አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም በጤና ምክንያት ከዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለቀው የነበሩት።
tikvah

❤26👍11👌2🤪1
መረጃ‼️
ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ አዲስ ግድብ እንድትገነባ ግብጽ አትፈቅድም ሲሉ የአገሪቱ የመስኖ ሚንስትር ሃኒ ስዊላም ትናንት ካይሮ ውስጥ በሠጡት መግለጫ ላይ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ አዳዲስ ግድቦችን የመገንባት ዕቅድ እንዳላት ይታወቃል ያሉት ስዊላም፣ ኾኖም ግብጽ ይህን ትፈቅዳለች ወይ ቢባል፣ 'መልሱ አትፈቅድም' የሚል ነው ማለታቸውን የአገሪቱ ጋዜጦች ጽፈዋል።
ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ምን ያህል ውሃ በየጊዜው እንደምትለቅ አለማሳወቋ ሱዳንን "አስቸጋሪ ኹኔታ" ላይ ጥሏታል በማለት ስዊላም ኢትዮጵያን ወቅሠዋል ተብሏል።

🤣55❤8👍4🤔2🤪2🤯1👀1
አውሮፓ በእሳት እየተቃጠለች ነው፦ የሙቀት መጠኖች አዲስ ሪኮርድ እያሰመዘገቡ ነው፣ ሰደድ እሳቶች እየተስፋፉ ነው፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን እየቀነሱ ነው
እጅግ በጣም ሞቃታማ እና ደረቅ የሆነው የበጋ ወቅት በግብርና ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል
አዲስ የሙቀት ሪኮርድ፦ በአውሮፓ የሙቀት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በኦስትሪያ እስከ 41.2°C ተመዝግቧል።
የኃይል ማመንጫዎች አቅም መቀነስ፦ የዳኑብ እና የሳቫ ወንዞች የውሃ መጠን በመቀነሱ በሃንጋሪ እና በስሎቬንያ የሚገኙ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ምርታቸውን ለመቀነስ ተገደዋል።
የደን እሳት እና መፈናቀል፦ በፈረንሳይ፣ እስፓንያ፣ አልባንያ እና ግሪክ አጥፊ የእሳት አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታር መሬቶች ተቃጥለው በርካቶች ተፈናቅለዋል።
የኢኮኖሚና የግብርና ጉዳት፦ በራይን ወንዝ የውሃ ማነስ ምክንያት የመርከብ ትራፊክ ሲስተጓጎል፣ በታላቋ ብሪታንያ ደግሞ እ.ኤ.አ. ከ1984 ወዲህ እጅግ አነስተኛው የእህል ምርት እንደሚመዘገብ ተገምቷል።
የሕይወት እልቂት፦ በሙቀት ማዕበሉ ምክንያት በአህጉሩ ከ1,300 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

❤11👍3😢2👌1
ዳናዊት መክብብ በፍትሐብሔር ክስ በነፃ ተሰናበተች
የታዋቂዋ የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብ ቀርቦባት የነበረው የፍትሐብሔር ክስ ውድቅ ተደርጎ በነፃ የተሰናበተች ሲሆን፣ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ግን ጥፋተኛ ተብለው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ አምስተኛ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ዳናዊት መክብብ የንግድ ፈቃድ አይታ የማስታወቂያ ሥራ የሰራች በመሆኗ በጉዳዩ ላይ ልትጠየቅ አይገባም በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷታል።
ጉዳዩ የተጀመረው 13 ከሳሾች «ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን» በሚል ከእያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር የተቀበላቸው የኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ፣ አቤል ተስፋዬ እና የዳናዊት መክብብ ክስ በመስረታቸው ነው። ከሳሾቹ የተወሰደብን ገንዘብ እንዲመለስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ተከሳሾቹ ሊመልሱልን አልቻሉም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አብራርተው ነበር።
እንደ ኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ፣ አራቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በነጠላና በአንድነት የተወሰደውን ገንዘብ ለከሳሾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን፣ ዳናዊት መክብብ ግን በነፃ ተሰናብታለች።

❤29👍2
በአገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት ያልተገባ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑ ተነገረ‼️
"የዘመሙ አካሄዶች ሲታዩ በጊዜውና በወቅቱ ዕርምት ይደረግባቸዋል"
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
- 250ው ስልታዊ ቡድን አዲስ አበባና ድሬዳዋ የፌዴራል አካል ሆነው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል
የአገራዊ የምክክር ጉባዔ በአጀንዳ ጭብጦች ላይ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተመደቡ አመካካሪዎች፣ምሁራንና ቃለ ጉባዔ ያዦች፣ ተመካካሪዎች የሚያነሱትን ሃሳብ ባለመቀበልና በተለይ የመጡበትን ተቋም መሠረት ያደረገ አቋም በመያዝ፣ ተመካካሪዎች ሐሳብ እንዲቀይሩና የምክክር ሒደቱ እንዲዘገይ ተፅዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ተመካካሪዎች ገለጹ
በተለይ መንግሥትን ወክለው የመጡ አመካካሪዎች እንደ የመንግሥት አደረጃጀትና አገር ግንባታ ያሉ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከምክክሩ ሒደት ባፈነገጠ መልኩ የራሳቸውን ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
የመንግሥት አደረጃደት አጀንዳን በተመለከተ እንዲያወያዩ በኮሚሽኑ የተመደቡ አመካካሪዎች በዚህ የተነሳ ለቀናቶች ውይይት እንዳይመሩና ማይክ ብቻ እንዲያቀብሉ በማድረግ፣ በእነርሱ ምትክ ደግሞ ከቡድን መሪዎች ተመርጠው ውይይት እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል።
ከዚህ አልፎ የኮሚሽኑ አመካካሪዎች ውይይት እንዲመሩ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ የአጀንዳ ሐሳብ በተለይ የተለያዩ የፓርቲዎችን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች የአመካካሪዎች አካሄድ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ሁኔታው ከላይ በተገለጸው መንገድ እንዲመራ መደረጉን ተመካካሪዎቹ ተናግረዋል።
በተለይ የተቋማት ግንባታን በተመለከተ፣ “ስለ ተቋም ግንባታ ለእኛ አትነግሩንም፣ የተቋም ግንባታ ምን መሆን እንዳለበት እናውቃለን፣ ተቋሙን የምንመራው እኛ ነን፣ ሪፎርም አድርገናል” ተቋማትን ወክለው የተገኙ ተመካካሪዎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት ተቆጥተው ውይይት ጥለው የወጡ ተመካካሪዎች እንደነበሩም አክለዋል።
አመካካሪዎች በሙስናና መልካም አስተዳደር አጀንዳ ሥር፣ ንዑስ አጀንዳ በሆነው የሙስና ጉዳዮች፣ በአንዳንድ ቡድኖች ከስምምነት እንዳይደረስና ለውይይት በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ
ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት ሐሳብ ተንዛዝቶ ከመግባባት ለመድረስ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29 ቀን ድረስ ውይይት እንዲቀጥል ማስገደዱን አስረድተዋል።
የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማን በተመለከተ የፅንሰ ሐሳብ ገለጻና ማብራሪያ እንዲሰጡ በኮሚሽኑ የተመደቡ ምሁራን (Panel of Experts)፣ በተለይ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል አካል ትሁን
በሚለው የአጀንዳ ሐሳብ ፅንፍ በያዘ ሁኔታ መከራከራቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
ሆኖም ይህን አካሄድ የተከተሉ ምሁራን ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ይቅርታ መጠየቀታቸውን ተመካካሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።
በቃለ ጉባዔ ያዥነት የተመደቡ አንዳንድ ባለሙያዎችም የቀረቡ ሐሳቦችን በሙሉ ያለማጠናከርና በፈለጉት መንገድ ብቻ የመሰነድ ችግር እንደተስተዋለባቸው ተናግረዋል። እነዚህ ቃለ ጉባዔ ያዦች የአንዱን ሐሳብ ይዘው የሌላውን የመተው አካሄድ መከተላቸው ተነግሯል።
በመሆኑም እንዲህ ያሉ ድርጊቶች አስፈላጊ እንዳልሆኑ፣ የምክክሩም ዓላማ ይህ እንዳልሆነ የገለጹት የመረጃ ምንጮቹ አሁን ያሉ ተቋማት ብቁ፣ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የማይሰሩና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የመፍታት ከፍተኛ ችግሮች ስላሉባቸው፣ ውሃው እንዳይደርቅና አሳውም እንዳይሞት መታረምና መስተካከል እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።
ኮሚሽኑም እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን ጣልቃ ገብቶ በጊዜ እንዲታረሙ ማድረግ እንዳለበትም
አስገንዝበዋል።
በዚሁ ረገድ የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይ ትልቁ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደነበር፣ በዚህም አዲስ አበባ የፌዴራል መንግሥት አካልና ዋና መቀመጫ ከተማ እንድትሆን ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል።
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሌሎች የፌዴራል ከተሞች እንዲኖሩ ሰፊ ምክረሐሳብ መቅረቡን፣ ለዚህም ደቡብ አፍሪካ እንደ ምሳሌ መቅረቧን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ከተማ የራሷ የሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የተጠናከረ የፖሊስ ኮሚሽን እንዲኖራትና በከተማዋ ውስጥ የሚሰየሙ የሰፈር ስሞች የአገር አንድነትንና የሁሉንም ማኅበረሰብ ውክልና እንዲኖራቸው ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል የሥራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ቋንቋ የአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ ሆኖ እንዲቀጥል ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል። ሆኖም አማርኛ፣ ኦሮሚኛና፣ ትግርኛ፣ አፋርኛና ሶማሊያ የፌዴራል የሥራ ቋንቋዎች ከሆኑ የአዲስ አበባም እንዲሆኑ ሐሳብ መኖሩን ጠቁመዋል።

❤24👍7🤔4😢1👀1🫡1
በፑንትላንድ እና በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት መካከል በተካሄደ ግጭት የፑንትላንድ ኃይሎች የፌዴራል መንግሥቱን የጦር ካምፕ መቆጣጠራቸውን ገለጹ!
የሶማሊያ ከፊል ራስ-ገዝ አስተዳደር በሆነችው ፑንትላንድ እና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል ያለው ውጥረት እንደገና ባነሰራበት በዚህ ወቅት፣ የፑንትላንድ ታጣቂ ኃይሎች ትላንት በጋልካዮ በሚገኘው የፌዴራል መንግሥት ጦር ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በቦሳሶ የሚገኘውን በፌዴራል መንግሥቱ የተቋቋመ “የፑንትላንድ ደህንነት ኃይል” (PSF) የጦር ካምፕ መቆጣጠራቸውን ገለጹ።
የፑንትላንድ ፕሬዚዳንት ሳይድ አብዱላሂ ደኒ ረቡዕ ዕለት በክልሉ መዲና ጋሮዌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በጋልካዮ የተካሄደው ጥቃት “በፑንትላንድ መንግሥት ላይ ተቃውሞ በሚያነሱ አካላት ላይ ግልጽ መልእክት ለማስተላለፍ” ታስቦ የተካሄደ “የታቀደ የደህንነት እርምጃ” ነው ብለዋል።ረቡዕ ዕለት የተካሄደው ይህ ግጭት በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ የተኩስ ልውውጥ የተደረገበት ሲሆን፣ የሲቪሎችን መፈናቀል እና የሰው ህይወት ጉዳት ማድረሱ ተዘግቧል።

👍7❤4💯1🤣1
የሚስቱን ጓደኛ ክብረ ንጽህና አታሎ የደፈረው በእስራት ተቀጣ!
የ19 ዓመት ወጣት የሆነችውን የሚስቱን ጓደኛ "ሚስቴ ቤት ትፈልግሻለች፣ ቡና አፍልታ እየጠበቀችሽ ነው፤"በማለት አታሎ ግብረ ስጋ ግንኘነት በማድረግ ክብረ ንጽህና የገረሰሰው ግለሰብ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ አንተነህ ተዘራ የተባለው ግለሰብ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3 00ሰአት ላይ በሐረር ከተማ አቦከር ወረዳ ልዩ ስፍራው ወርዋሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ19 አመት ወጣት የሆነችውን አስገድዶ በመድፈሩ በእስራት መቀጣቱን የሴቶችና ህፃናት መርማሪ የሆኑት ሣጅን አዚዛ አህመድ ገልፀዋል ።
መርማሪዋ እንደገለፁት ተከሳሹ የ19 አመት እድሜ ያላትን ወጣት የሚስቱን ጓደኛ ሚስቴ የምሰራበት ቦታ ልትጠይቀኝ መታለችና ነይ አንቺም ቡና ተፈልቷል ትጠጭያለሽ እኛጋር ታድሪያለሽ በማለት አታሎ በመውሰድ ሀይል በመጠቀም የግብረስጋ ግንኙነት የፈፀመባት ክብረ ንጽሕና የገረሰሳ በመሆኑ በፈፀመው አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድቤት ሀምሌ 27 28/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ አንተነህ ተዘራ በ 5 አመት እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ሲሉ የህፃናትና ሴቶች ወንጀል መርማሪ የሆኑት ሳጅን አዚዛ አህመድ ገልፀዋል።

🤣23❤20😢8👍2🤔2👀2🤯1💔1🙈1
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2018 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ የሱባዔ መልእክት አስተላለፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ለ2018 ዓ.ም ጾመ ማርያም (ፍልሰታ) ባስተላለፉት የቡራኬና የሱባዔ መልእክት፣ ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅና ፍቅርን በመተግበር ሱባዔውን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቀረቡ።
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው እግዚአብሔርን መውደድ በምናባዊ ነገር ሳይሆን ትእዛዙን በመጠበቅና ባልንጀራን ፤ መላውን የሰው ወገን እንደ ራስ አድርጎ በመውደድ የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል።
ድንግል ማርያም ከአእላፋት መላእክት በላይ የምትበልጥ የአምላክ ማደሪያ በመሆኗ፣ ምእመናን በጾሙ ወቅት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ እመቤታችንን ሊያከብሯትና በጸሎቷም ሊታመኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ15ቱ የሱባዔ ወቅት የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ እንዲሁም በንሥሐና በቅዱስ ቁርባን ማለፍ እንደሚገባ አዝዘዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ሥጋት የሆነውንና ፍጥረትን የሚያወድመውን ጦርነት እግዚአብሔር በኃይሉ እንዲያስቆም ምእመናን በሱባዔው ወቅት በትሑት ሰብእናና በቅን ልቦና እንዲጸልዩ አባታዊ አደራቸውን አስተላልፈዋል።

❤59🥰5🙏4👍2
የመብራት ምሰሶዎችን ከገጩ አሽከርካሪዎች ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የጉዳት ካሳ ተሰበሰበ
በአዲስ አበባ ከተማ በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የመብራት ምሰሶዎችን ከገጩ አሽከርካሪዎች 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የጉዳት ካሳ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን እንደገለፁት ባለስልጣኑ ከተቋቋመ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የከተማዋን የመብራት አገልግሎት ዘመናዊ ለማድረግ የተለያዩ የልማትና የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል።
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ 41 ሺህ 283 የመብራት ምሰሶዎች በጂኦግራፊያዊ የመረጃ ሥርዓት እንዲመዘገቡ መደረጉ ተገልጿል። ይህ ሥርዓት የመብራት ምሰሶዎችን በዲጂታል መንገድ ለመከታተል፣ ቁጥጥርን ለማጠናከር እና የጥገና ሥራዎችን በፍጥነትና በብቃት ለማከናወን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
ባለስልጣኑ ለብስራት ሬዲዮ የላከው መረጃ እንደሚያመላክተው የከተማዋን የመብራት መሠረተ ልማት ይበልጥ ለማዘመን፣ የህዝብ ንብረትን ከጉዳት ለመጠበቅ እና ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመቀነስ የቁጥጥርና የማሻሻያ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው።

❤9😢9👍3🤔2👀2
ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል‼️
የተቋማት ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ።
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ፡፡
የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡
በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡
በጥናቱ ጉቦ ለመስጠት የሚገደዱ ሰዎች ለድርጊታቸው የሚያቀርቡት አንዱ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ግለሰቦች ጉቦ የሚሰጡት የሚፈልጉት አገልግሎት እንዲፈጸምላቸውና የሚጠበቅባቸውን ባለማድረጋቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለማስቀረት መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡
የሙስና ድርጊትን ለመጠቆም የሚፈልጉ ግለሰቦች ሊደርስባቸው የሚችል የበቀል ዕርምጃና የማስፈራራት ሥጋት በመኖሩ፣ አስተማማኝ የጠቋሚዎች ጥበቃ ሥርዓት ማነስ፣ እንዲሁም የጥቆማ አሰጣጥ ሒደቱ ረዥምና ውስብስብ መሆን ኅብረተሰቡ ሙስና ለመጠቆም ሥጋት እንዳለበት በጥናቱ መገለጹ ተነግሯል፡፡

❤18👍11🤪6🥰1🤣1
የትግራይ ሚዲያዎች ከምድር በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ተሸጋግረዋል‼️
"ጥምረቱና ትብብሩ ወደ ከፍተኛ የትግል ደረጃ ተሸጋግሯል" ሲሉ የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር የሆኑት ገብረ ገብረፃድቃን(ዓዴት) በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው ተናግረዋል።
ህወሓት የፌደራል መንግስቱን በጦርነት ለመጣል ወደ ራያ እና አፋር ድንበር መካናይዝድ ጦሩን ጨምሮ እያስጠጋ የሚገኝ ሲሆን መንግስትም ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።
የትግራይ ሚዲያዎች ከመሬት በታች ወደተቆፈረ ስቱዲዮ ውስጥ መግባታቸውን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል።

🤣17👍14❤5🙊2🕊1🤡1🤪1
በመዲናዋ ሆቴሎችን ጨምሮ የምሽት መዝናኛዎች የድምፅ ብክለት መጨመሩ ተገለፀ
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለቁጥጥር የሚያመች የድምፅ ብክለት መመሪያ እያዘጋጀሁ እገኛለሁ ብሏል።
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በበጀት አመቱ በ12 ሺህ 3መቶ 76 ተቋማት ላይ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል።
በመዲናዋ ሆቴሎች፣ ግሮሰሪዎች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች በስፋት መኖራቸዉን ተከትሎ ህብረተሰቡ መረበሹን ቅሬታ እየቀረበ መገኘቱ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና አማካሪ አቶ አዱኛ ወንድሙ በመዲናዋ የሆቴሎችና የምሽት መዝናኛ ተቋማት መስፋፋትን ተከትሎ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት መኖሩን ተናግረዋል።
በአገልግሎት ዘርፍ ባሉ ተቋማት ላይ ክትትል ብቻ ሳይሆን እርምጃ እየወሰድኩ ነዉ ያለዉ ባለስልጣኑ ሆቴሎች እና ግሮሰሪዎችን ጨምሮ 3 ሺህ 1መቶ 16 በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።
አቶ አዱኛ ከተሰጡት የፅሁፍ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷቸዉ ያላስተካከሉ ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
በዚህም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ 28ቱ ላይ የማሸግ እርምጃ እንደተወሰደ ተገልጿል።
የድምፅ ብክለት ላይ ችግሮች እንዳሉ የሚናገሩት የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና አማካሪ አቶ አዱኛ ወንድሙ፤የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎች የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸዉ አስረድተዋል።
የድምፅ ብክለት መመሪያን በማዘጋጀት ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን አማካሪዉ የገለፁ ሲሆን፤ አሁን ያለዉን ብክለት ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ ያግዛል ተብሎ እንደታመነበት አንስተዋል።
የአዲስ አበባ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በተጠናቀቀው 2018 የበጀት አመት የአካባቢ ብክለትንና የአየር ንብረት ለዉጥ ስራዎችን አስመልክቶ በዛሬዉ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

❤13👍9🥱2
የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️
በሱዳን የሚንቀሳቀሰው የህወሓት አርሚ 70 በሸረሪና ግንባር አከማችቶት የነበረው የመሳሪያ ዲፖ ተያዘ‼️
ከሸረሪና ካምፕ ወጣ ብሎ 'ግዴማ' በተባለች ቦታ መጋዘን ውስጥ እንዲሁም ከመሬት በታች በኮንክሪት በተሰራ ግዙፍ ምሽግ ተጠራቅሞ የነበረ ተተኳሽ፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ ሮኬት፣ የአጭር እና መካከለኛ ርቀት ሚሳይሎች፣ RPG-7፣ የሳተላይት ስልኮች፣ የሬዲዮ መገናኛ፣ የቅኝት ድሮኖች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና ለጊዜው ምንነታቸውን ለመለየት ያልተቻሉ የጦር መሳሪያዎች ገቢ መደረጋቸውን ምንጮቹ አረጋግጠዋል።
እንደ ወታደራዊ ምንጮቹ ገለፃ ከሆነ፤ በትናንትናው እለት ብቻ ከሸረሪና እና ግዴማ ካምፕ 31 ከባድ ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ከአርሚ 70 የተማረኩ የተለያዩ ትጥቆችን ወደ ሁመራ እና ዳንሻ ከተማ ተጓጉዘዋል።
ለዚህ ዲፖ መገኘት የተማረኩ የአርሚ 70 ታጣቂዎች አስተዋጽኦ አድርገዋል።

❤42🤣22👍9👌3🤪3😢1👀1🙊1