አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

Via : አንዳፍታ ሚዲያ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢287👍3🤯3
የአነስተኛ ገንዘብ ኖቶች እጥረት‼️
የአነስተኛ የገንዘብ ኖቶች እጥረት የችርቻሮ ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን እየፈተነ ይገኛል።
​በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ አነስተኛ የገንዘብ ኖቶች በተለይም የ 10 ብር ኖት እጥረት በዕለታዊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው። በርካታ የሱቅ ባለቤቶች መልስ በማጣታቸው ምክንያት ደንበኞችን ለመመለስ ወይም እቃዎችን በዕዳ ለመስጠት ተገደዋል።

​የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 13.9% እንዲሁም የምግብ ዋጋ ንረት 15.1% በመድረሱ፣ አነስተኛ ኖቶች በእጅ የመዘዋወር ፍጥነታቸው ጨምሮ በፍጥነት እንዲያልቁና እንዲቀደዱ አድርጓል። እ.ኤ.አ በ 2020 ከተደረገው የብር ቅያሬ ወዲህ አዲስ የ 10 ብር ኖት ያልታተመ በመሆኑም በገበያው ላይ ያለው መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል።

​በተጨማሪም ከ 350 ቢሊዮን ብር በላይ ከባንክ ሥርዓት ውጭ በህዝብ እጅ ስለሚገኝ፣ ብሔራዊ ባንክ ያረጁ ኖቶችን ሰብስቦ ለመተካትና ለማስወገድ ተቸግሯል። እስከ እ.ኤ.አ 2030 ሙሉ በሙሉ ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የመሆን ግብ ቢኖርም፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መቆራረጥ እንዲሁም የዲጂታል መሣሪያዎች ውድነት ሽግግሩን እያዘገየው ይገኛል።

​"የአነስተኛ ኖቶች እጥረት የዘወትር ራስ ምታት ሆኖብናል። አንዳንድ ጊዜ ደንበኞችን መልሰን እንልካለን፤ ወይም ዕቃዎችን በብድር ለመስጠት እንገደዳለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍3
በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር ተነገረ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምቹ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።

ከእነዚህም መካከል አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት  አገልግሎት በኤምባሲዎችና በቆንስላዎች በኩል በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጿል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ እንደገለጹት፥ለዲያስፖራው የሚሰጠው አገልግሎት እንዲቀላጠፍ አዲስ ድረ-ገጽ ተዘጋጅቷል።

ይህ ድረ-ገጽ ተገልጋዮች ባሉበት ሀገር ሳይገደቡ የፓስፖርት እድሳትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በቀላሉ እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የቢጫ ካርድ ባለቤቶች ቀደም ሲልም በሀገር ውስጥ ኢንቨስት የማድረግና የመንቀሳቀስ መብት ያላቸው በመሆኑ፤አዲሱ የጎልደን ቪዛ የግድ አስፈላጊ ላይሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

እነዚህ ቅርንጫፎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው፣ ተገልጋዮች ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ከፓስፖርት ባለፈም፣ የነዋሪነት ፈቃድና የቪዛ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
በሳዑዲ 220 ኪሎ ግራም ጫት በኮንትሮባንድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተያዙ

​በሳዑዲ አረቢያ የጃዛን ክልል አል-ዳየር ዘርፍ የድንበር ጥበቃ አባላት 220 ኪሎ ግራም ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።

ተጠርጣሪዎቹ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት መመሪያ በመጣስ አደንዛዥ ዕፅ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ሲሆን፣ አስፈላጊው ህጋዊ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከተያዘው እቃ ጋር ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልከዋል ሲል ሳዑዱ ጋዜት ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢64👍3
በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ቁጥር 329 ደረሰ አለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
 
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 አዳዲስ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
 
ባለሥልጣኑ ከተሰጡት ፈቃዶች መካከል፦
 
·         ለ14 የበየነ መረብ ወይም ኦንላይን ሚዲያዎች፣
·         ለ5 የማህበረሰብ ብሮድካስቶች፣
·         ለ19 የሚዲያ ፕሮግራም አዘጋጆች፣
·         እንዲሁም ለ9 የማስታወቂያ አዘጋጆች የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጿል።
 
ከዚህ በተጨማሪም ለ5 ቋሚ የውጭ ዜና ወኪሎችና ለአጭር ጊዜ የፊልም ቀረፃና ዘገባ ወደ አገር ውስጥ ለገቡ 78 የውጭ ጋዜጠኞች ፈቃድ ተሰጥቷል።
 
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ሁለንተናዊ የሪፎርም፣ የክትትልና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
 
አክለውም፤ ሚዲያዎች ለአገር ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጉልህ እንዲያሳይ ባለሥልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ስለ ተማሪዎችና መምህራን ዝውውር የተወራውን አስተባበለ!

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ተማሪዎቹና መምህራኑ የዝውውር ጥያቄ አቅርበዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ "ከእውነት የራቀ እና ምንም አይነት መነሻ የሌለው ፈጠራ ነው" ሲል አስተባበለ። ተማሪዎችና መምህራን ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳይሸበሩ ያሳሰበው ዩኒቨርሲቲው፣ የተወራው ወሬ መሠረት የሌለው መሆኑን አረጋግጧል።

ሰሞኑን በመቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ አቅርበዋል የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸው አይዘነጋም፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍4🤪2🤔1
በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️

በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ  እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ  አሳስበዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል።

የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍2🤣2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
#እንድታውቁት

በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን ተከትሎ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆኖ በሚቆይበት የክረምት ወራት በተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች አሳውቋል።

ፍርድ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳመለከተው፣ አገልግሎቱ የሚሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት ነው።

ይህም መሰረታዊ የመብት ጥሰት እንዳይከሰት እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት በክረምቱ የተረኛ ችሎት የሚታዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዝርዝር፦

• አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች እና የልጅ ቀለብ ጥያቄዎች፣
• አካል ነጻ ለማውጣት እና እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀረቡ አቤቱታዎች፣
• የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም ጉዳዮች፣
• ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች፣
• እንዲሁም ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ ጉዳዮች በዳኛው ውሳኔ የሚስተናገዱ ይሆናል።

በወንጀል ጉዳዮች በኩል ደግሞ የሚከተሉት ነጥቦች ተለይተዋል፦

• የዋስትና እና የአምክሮ ጥያቄዎች፣
• እስረኛ ያለባቸው የክስ መዛግብት፣
• የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች (በአራዳ ምድብ ችሎት)፣
• በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ለመሰየም የሚቀርቡ ጥያቄዎች፣
• ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ የወንጀል ጉዳዮች ይስተናገዳሉ።

ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሆነባቸው በእነዚህ ሁለት ወራት፣ ለዳኞች ተራ ወጥቶ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፤ የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብም ሆነ ተገልጋዩ ለሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍3
የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናን 81 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም ተባለ
 
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ክልላዊ ፈተና 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጿል።ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ 48 እና ከዛ በላይ ማለፊያ ነጥብ ተቆርጦለታል።የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመውሰድ የተመዘገቡ ተማሪዎች 86 ሺህ 502 እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን 78 ሺህ 203 የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል።
 
ከእነዚህ ውስጥ ወደ ቀጣይ ክፍል ያለፋት 47 ሺህ 307 ተማሪዎች መሆናቸውን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት  ዳይሬክተር አቶ የሱፍ አህመድ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በዚህም መሠረት ክልላዊ ውጤት ከመቶ አንፃር ሲታይ 60 ነጥብ 4 መሆኑ ተገልጿል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ ተፈታኞች 126 ሺህ 224 ናቸው። ፈተና የወሰዱት ደግሞ 110 ሺህ 566  ከእነዚህ ደግሞ ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበው ወደ ቀጣይ 7ኛ ክፍል የተዛወሩ 70 ሺህ 584 መሆናቸውን አቶ የሱፍ ነግረውናል።
 
በዚህም ክልላዊ ውጤት በመቶ ሲገለፅ 63 ነጥብ 8 እንደሆነ ተገልጿል። 540 ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ አሳልፈዋል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ 81 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ አላሳለፉም።
 
በአጠቃላይ ክልላዊ ውጤቱ ከአምና የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ8ኛ ክፍል በ3 በመቶ ያነሰ አፈፃፀምን አስመዝግቧል ።  አምና በነበረው ክልላዊ ውጤት  63 በመቶ  የሆነ ውጤት ተመዝግቦበት እንደነበር ተገልጿል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል የአምና ክልላዊ ውጤትን በተመለከተ 56 በመቶ አፈፃፀም የታየበት እንደነበር የተነገረ ሲሆን በ2018 በጀት አመት ደግሞ 63 ነጥብ 84 በመቶ መሆኑን  አቶ የሱፍ አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍4
የጦርነት ዝግጅቱ ቀጥሏል‼️
ህወሓት በራያ ግንባር በተለይ በትምህርት ቤቶች ውስጥ መድፎችን እና ዙ-23 መሳሪያዎችን እያስጠጋ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በመሆኒ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 28 ተጨማሪ ሰራዊት ማራገፉን እና የጦርነት ዝግጅቱ መቀጠሉን ገልፀዋል።
በተያያዘ ዜና ወታደራዊ አመራሩ በጦር ኃይሎች እና ግንባሮች ውስጥ የሞባይል ስልኮችን እና የሳተላይት ስልኮችን አጠቃቀም በጥብቅ ለመቆጣጠር መመሪያዎችን አውጥቷል።
🔴በስልክ (ሞባይል ስልክ) የሚደረጉ የተለያዩ ግንኙነቶች የሰራዊቱን እና የወታደራዊ መረጃዎችን ሚስጥሮች አሳልፈው በመስጠት አደጋን  ስለሚፈጥሩ የሞባይል ስልክ ሙሉ ለሙሉ መከልከሉን ለአመራሮች በደብዳቤ አሳውቋል።
📍ከተፈቀደላቸው የጦር ሀይሎች በስተቀር ማንም ሰው የሳተላይት ስልክ ግንኙነቶች ማድረግ አይፈቀድለትም ተብሏል።
📍ይህንን መመሪያ የማያከብር ማንኛውም ወታደራዊ አካል ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ቅጣት ይጣልበታል ተብሏል።
👉የአውሮፓ ህብረት አሁን ላይ በትግራይ ክልል የተከሰተው ውጥረት እንዳሳሰበው ገልፆ ሁለቱ አካላት ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22🤪11👍4🤯1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል - ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ‼️
ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ኃይሎችን ድባቅ የሚመታ ጀግና አየር ኃይል ተገንብቷል አሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡፡

የአየር ኃይሉ የ3ኛ አየር ምድብ ላስመዘገበው የላቀ የግዳጅና የሥራ አፈጻጸም ስኬት በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው የምድቡ ጠቅላይ መምሪያ የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መከላከያ ሠራዊት በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ከፍተኛ ለውጥ እያደረገ ይገኛል፡፡

አሁን የምንገኝበት ዘመን የውጊያ አካሄድና ስልት ለመገመት በሚያዳግት መልኩ በፍጥነት እየተቀያየረ ነው ያሉት አዛዡ፥ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ቀጣናም ያለው የኃይል አሰላለፍ ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይልም ይህንን ታሳቢ በማድረግ የዘመኑን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችል የሰው ኃይል በማብቃት፣ በርካታ ፓይለቶችን፣ ቴክኒሽያኖችንና የአስተዳደር ባለሙያዎች  እያፈራ መሆኑንና የዘመኑን የውጊያ ቴክኖሎጂዎች እየታጠቀ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

3ኛ አየር ምድብም የሪፎርሙ አካል በመሆን በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ልዩ ታሪክ ያለው መሆኑንም አንስተዋል።

ምድቡ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እና ኮሎኔል ባጫ ሁንዴን የመሳሰሉ በርካታ ጀግኖችን ያፈራ መሆኑን አስታውሰው፥ አሁንም ያንን የጀግንነት ታሪክ እያደሰ በርካታ ተተኪ ወጣት በራሪዎችን በአጭር ጊዜ፣ በጥራትና በብዛት እያፈራ ይገኛል ነው ያሉት።

የሚለወጠውን የውጊያ አውድና የኃይል አሰላለፍ በመገንዘብ አመራሩና ሠራዊቱ ራሱን ከጊዜው ጋር ማዘመን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን ሊፈታተኑ የሚሞክሩ ጠላቶችን መመከትና ድባቅ መምታት የሚያስችል ጀግና ተቋም መገንባቱን ገልጸው፥ የምድቡ አመራሮችና የሠራዊት አባላት ግዳጃቸውን በጀግንነትና በስኬት በመወጣታቸው ሊኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ታላላቅ ተልዕኮዎች እንደሚጠበቁ በመረዳት በሁሉም ረገድ ዝግጁነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
32🤣29👍5💯2🤩1🤪1
የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል በዩክሬን ላይ ጥቃት ሰነዘረ‼️
የሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች ከሰሜን ኮሪያ ያገኙትን አጭር ርቀት ተኳሽ ባሊስቲክ ሚሳይል በዩክሬን ላይ እንደገና መተኮስ መጀመራቸውን የዩክሬን የመከላከያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በጥቃቱ በዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልል ራዱሽኔ መንደር የሚገኝ የቮሮኖቭ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት በሙሉ ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን የበርካታ ሲቪሎች ሕይወት አልፏል።

የዩክሬን ራዳር ሥርዓቶች እንደመዘገቡት ጥቃቱ በሰሜን ኮሪያ ሰራሹ KN-23 ወይም KN-24 ሚሳይል አማካኝነት ከሩሲያ ብሪያንስክ ክልል የተተኮሰ ነው።ይህ ጥቃት ሩሲያ ከፒዮንግያንግ አዲስ የጦር መሣሪያ አቅርቦት ማግኘቷንና ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብራቸውን ማጠናከራቸውን ያሳያል።

እነዚህ ሚሳይሎች ከሩሲያው 'እስካንደር' ጋር ተመሳሳይ ዝቅተኛ የጉዞ መስመር ያላቸው በመሆናቸው ለመምታት የላቀ የፓትሪዮት አየር መከላከያ ይፈልጋሉ።

ይህም ለሰሜን ኮሪያ የጦር መሣሪያዎቿን በእውነተኛ የውጊያ ሜዳ ላይ እንድትፈትሽ እድል ሲሰጥ፣ ለሩሲያ ደግሞ የዩክሬንን የጦር መሣሪያ እጥረት በመጠቀም ከፍተኛ ጥቃት ለመሰንዘር ያስችላታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18👍6🤯1
የታጠቁ ኃይሎች አራት ኪሎ ባዶ ሁኖ "ኑና ቤተመንግሥት ግቡ" ቢባሉ ወደ አዲስ አበባ አይመጡም‼️

👉 የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጀነራል አምባሳደር #ባጫ_ደበሌ ከቢቢሲ አማርኛ (BBC News Amharic) ጋር ያደረጉት ሰፊ ቃለ-መጠይቅ በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ የተገለፀ ሲሆን፤ ቢቢሲ ከቃለ-መጠይቁ አጠር አድርጎ ያወጣው አነስተኛ የቪዲዮ ምስል ቀጣዩን አቅጣጫ ጠቋሚ በመሆኑ በድጋሚ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

በዚህ አጭር መግለጫቸው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ የታጠቁ ግጭቶች ከመጨራረስ ውጭ ምንም ዓይነት ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ያስገነዘቡት ጀነራል አምባሳደሩ፤ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ አካላትን አቅም አስመልከተው ሲናገሩም "አራት ኪሎ ክፍት ሆኖ ኑና ግቡ ቢባሉም እንኳን #ፋኖም ሆነ #ኦላ (ጃል መሮ) አይመጡም፤ መጥተውም የሚያደርጉት ነገር የለም" ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም፤ "እንደ #ዘመነ_ካሴ ያሉ የውጊያ መሪዎች መጥተው አራት ኪሎ የመግባትና ሀገር የመምራት አቅም የላቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በጦርነት ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ የሚባል ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ጀነራል አምባሳደሩ፣ "የታጠቁ ኃይሎች ገንዘብ ከፈለጉ ከመንግስት ይውሰዱና ህዝቡን ይተውት" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ካልሆነ ግን የትግሉ መጨረሻ የህዝብና የሀገር መጨራረስ ብቻ ሆኖ እንደሚቀርና ማንኛውም ወገን የፖለቲካ ማተርፊያ እንደማያገኝበት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪39🤣2322👍8👀2
የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ) ፦የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ መልዕክት የደረሳቸው የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ክፍያቸውን በመፈጸም የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ በሰጡት መግለጫ፣ቢሮው የግብር ስርዓቱን በማዘመን እና ፍትሃዊ አሰባሰብን በመዘርጋት ገቢን በጥራት እየሰበሰበ ይገኛል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከሚሰበስበው ገቢ 72 በመቶውን ለዘላቂ ልማት፣ ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እና ለኮሪደር ልማት በማዋል የመዲናዋን ገጽታና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እያጎለበተ ይገኛልም ብለዋል።

በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ከ456 ሺህ በላይ የደረጃ «ለ» ግብር ከፋዮች አዲስ በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ መሰረት ግዴታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

ከደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በዘንድሮ በጀት ዓመት 9.2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍2😡2😢1
የኤቦላ ቫይረስ በአሳሳቢ ሁኔታ እየተሰራጨ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አሳወቀ

የዛሬ ሁለት ወራት ተኩል ገደማ በኮንጎ የተከሰተው የኤቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በአሳሳቢና ባልተጠበቀ ሁኔታ በሀገሪቱ እየተሰራጨ ነው ሲል ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በምህፃሩ MSF አስታወቀ።

ድርጅቱ እንደሚለው በሽታውን ለመከላከል የህክምና ባለሞያዎች ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ወረርሽኙ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአሳሳቢ ሁኔታ እየተሰራጨ ይገኛል።

እስካሁን ከ3 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በላቦራቶሪ ተረጋገጧል፤ ቁጥራቸው 1 ሺህ 500 የሚጠጋ ሰዎችም ሞተዋል።

በአሁኑ ጊዜ ዋናው ተግዳሮት ባለሥልጣናት በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎች መለየት እንደተሳናቸው መሆኑ ነው።

ቡንያ በተባለው አካባቢ የሚገኝ የህክምና ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት በሽተኞች ውስጥ 90 በመቶው ከዚህ ቀደም በኤቦላ ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው የሚታወቅ ነገር የለም።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከመንግሥት ኃላፊዎችና ከሰብአዊ ድርጅቶች ጋር ለመነጋገር ዛሬ ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ ሄደዋል።

ዶክተር ቴዎድሮስ የኤቦላ ወረርሽኝ ከተሰከሰተ ወዲህ ወደ ኮንጎ ሲጓዙ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍2😱1
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ10 ዓመታት በላይ በመሪነት በማገልገል ተቋሙን ወደ አፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት አቶ ተወልደ፣ አሁን የሕንድ ሁለተኛው ትልቁ አየር መንገድ የሆነውን ኤር ኢንዲያን ይመራሉ።

ኤር ኢንዲያ በቅርብ ጊዜ ከደረሰበት የአውሮፕላን አደጋ እና ከሌሎች የሥራ ተግዳሮቶች በኋላ አዲስ አመራር እየፈለገ ሲሆን፣ አቶ ተወልደ በቀድሞ የአመራር ልምዳቸው እና በአቪዬሽን ዘርፍ ባላቸው ስኬት ተመርጠዋል።

አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ከ20 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም በጤና ምክንያት ከዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለቀው የነበሩት።

tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26👍11👌2🤪1