በመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው ታላቋ የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬት እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉን የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።
በተከሰተው በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት፣ እንዲሁም በ2 ሰዎች ላይ መለስተኛ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።
የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን መሪር ሐዘን ገልጿል።
አደጋው ከተከሰተበት ቅጽበት ጀምሮ የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በስፍራው በአካል በመገኘት ነፍስ የማዳን ሥራውን በበላይነት ሲያስተባብሩ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ውለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የሕክምና ባለሙያዎች በቅንጅት በተደረገው ብርቱ ትግል፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቦታው ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል።
@Addis_Reporter

😢30❤10💔8🤯1😱1
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!
➠ ሱቆች ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል ➠ ክሊኒኮች
➠ websites ➠ Events
➠ ሆቴሎች ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም
የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።
ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።
👉@Addis_reporter_bot

❤4👍2
ይከፈላል ተብሏል‼️
በምርጫ ቦርድ እና በምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል ያለው የክፍያ ውዝግብ።
በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የተሳተፉ የመስክ አሠልጣኞች፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎችና የቆጠራ አስተባባሪዎች በገቡት ውል መሠረት ሊከፈላቸው የሚገባው የአገልግሎትና የጉዞ አበል ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ገለጹ።
ባለሙያዎቹ ኃላፊነታቸውን በሰዓቱና በውሉ መሠረት ቢያጠናቅቁም ክፍያው በመዘገየቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ጫና እንደደረሰባቸው በመግለጽ የቦርዱን ኃላፊዎች ለጥያቄያቸው ግዴለሽነት አሳይተዋል ሲሉ ከሰዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ምላሽ፣ ክፍያው ከመፈጸሙ በፊት አሠልጣኞቹ በውላቸው መሠረት ሥራቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ መሠራት እንዳለበት አስታውቋል።
ቦርዱ አክሎም ምርጫው የተካሄደው የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ላይ በመሆኑ የነበረው በጀት በማለቁ ተጨማሪ በጀት እንዲለቀቅለት መጠየቁንና በጀቱ ሲፈቀድ ማጣራቱ ተጠናቆ ክፍያው እንደሚፈጸም አብራርቷል።

❤18🤪6👍3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።
🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።
🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።
አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy
@sputnik_ethiopia

❤2👍2
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00
👉ጎጃም በረንዳ ጫፍ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ሰን ሆቴል፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢው፣
👉 ዳውን ታውን ሆቴል፣ አውራሪስ ሆቴል፣ አዲሱ ስታዲየም፣ ካልዲስ ቡና፣ መድሓኒዓለም ቤ/ክ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00 - 10፡00
👉 ጉርድ ሾላ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት፣ ግብርና ምርምር፣ ጃክሮስ አደባባይ በስተጀርባ እና አካባቢው፣
👉 ላምበረት መናኸሪያ ፣ ላመበረት፣ እስራኤል ኤምባሲ፣ አቢሲኒያ ሆቴል፣ ሱሉልታ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 4፡00 - 8፡00
👉 ከደንበሯ ሆስፒታል ፣ በግ ተራ፣ ምስራቅ አጠቃላይ፣ ሾላ ገበያ፣ የካ መንፈሻ፣ ዘፍመሽ ሞል፣ እና አካባቢው፣
👉 አትላስ ሆቴል፣ ሻላ መናፈሻ፣ ኤስኦኤስ፣ ደሳለኝ ሆተል ጀርባ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ፕሬዚደንሺያል ሆቴል፣ሩዋንዳ ኦቨርፓስ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00 - 11፡00
👉በጭሮ ሪጅን ደደር፣ ሜታ ፣ መልካ በሎ ፣ ጎሮ ጉቱ ወረዳዎች እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00 - 11፡00
በበህርዳር ሪጅን ቀበሌ 16 ነጋድራስ በቄ ሰፈር፣ ዶንጎስ መኪና ማሰልጠኛ፣ቤዛ ብዙሃን ት/ቤት እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

❤8👍4
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከ805 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ተከልኩ አለች
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ይፋዊ እቅድ በመያዝ "805.3 ሚሊዮን" ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ እቅድ በላቀ ስኬት ማጠናቀቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በንቃት በተሳተፉበት በዚህ ግዙፍ የንቅናቄ መርሃ ግብር ሀገሪቱ ታላቅ ድምቀት ያለው ድል አስመዝግባለች።
ይህ ታሪካዊ ድል የዕለቱ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የያዘችውን የረጅም ጊዜ እቅድ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

🤣42❤15👍4🤪2🙊2🤡1👀1
ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማረፊያ የሚሆን መሬት ሰጠች
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የትራንስፖርት ኮሪደር ለማዘመን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ ስምምነት በመተግበር በሞጆ ከተማ የመሬት ርክክብ ፈጸሙ።
ላለፉት 25 ዓመታት ዘግይቶ የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ ለጅቡቲ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታ የሚውል መሬት ለጅቡቲ ወገን በመስጠት እውን ሆኗል።
በሞጆ ከተማ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ፣ የጅቡቲ የመሠረተ ልማትና መሳሪያዎች ሚኒስትር ሳይድ ኑህ ሀሰን፣ የሞጆ ከተማ ከንቲባ እና የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።
ዓለሙ ስሜ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በጅቡቲ ባለሥልጣናት መካከል በተደረገው ውይይት ውሳኔ ያገኘ ሲሆን፣ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት የበለጠ ያጠናክራል።
ለባህር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ዋነኛ የንግድ መስመር የሆነው የሞጆ-ጅቡቲ ኮሪደር፣ አዲሱ የከባድ መኪኖች ማቆሚያ ተርሚናል ሲገነባበት በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ይባክን የነበረውን ጊዜና ተጨማሪ ወጪ በእጅጉ ይቀንሰዋል ተብሏል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ጅቡቲን የሚያገናኘውን የባቡር መስመር የጭነት አቅም እስከ እ.ኤ.አ. 2027 ወደ 6.2 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

❤21🤪12🤔4👍3🤣1
በራያ ውጥረት አለ-ነዋሪዎቹ‼️
ከቀናት በፊት በሱዳን አዋሳኝ ሸረሪና በፌደራል ኃይሎች እና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል የነበረው ግጭት ጋብ ቢልም፣ በራያ አላማጣ ግንባር በኩል ግን ወታደራዊ ዝግጅቱ እና ፍጥጫው ማየሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ፣ የህወሓት ሠራዊት በራያ ግንባር በጨርጨር፣በቢሶበር እና ሌሎች አካባቢዎች ተሰማርተዋል ይላሉ።
«ህወሓት ሠራዊቶች ብዙ አርሚዎች በራያ ግንባር አሰማርተዋል። ለጦርነት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ ወርዶላቸዋል። ዝግጅት ያለው አሁን በጨርጨር በኩልና ቢሶበር ነው። በዛ ቡታ መርፌ አካባቢ አለ። ከዚህ በዋጃ ቆቦ፣ በጃርሮታ ጀምሮ፣ በዳንያ ለኮ፣ ሰሌን ውኃ፣ በላይ በር በባይባዋ፣ ቁሙጋ ላይ ያለውን አካባቢ ሁሉ ነው ዝግጅቱ። የዋጃን መስመር ተከተሎም የራሳቸውን አርሚ አዘጋጅተዋል።»
መካናይዝድ ጦርም በማንቀሳቀስ ቦታ እያሲያዙ ነው ብለዋል።
አሁን ባለው ወታደራዊ ዝግጅት እና እንቅስቃሴ ጦርነቱ በማንኛውም ጊዜ ሊጀምር ይችላል የሚሉት የራያ ወረዳ ነዋሪ፣ ጦርነቱ በተጀመረ ቁጥር ጉዳት የሚደርስበት የራያ ማኅበረሰብ በእጅጉ ነፃነቱን ይሻል ብለዋል።

❤25👍5🤪5👀1
ኤርትራ‼️
ኤርትራ የብሔራዊ የወታደራዊ የአገልግሎት ግዴታቸውን እንዲወጡ የመለመለቻቸውን ወጣቶች ወደ ሳዋ ማሰልጠኛ እየላከች ትገኛለች።
በኤርትራ ማንኛውም ከ18-40 አመት የሞላው ወጣት ግዴታ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ማገልገል እንዳለበት የሀገሪቱ ህግ ይደነግጋል።

❤19👍13🤣7🤯1
የሱማሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኬንያ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ
የሱማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጅብሪል አብዲራሺድ ሀጂ ከጉዞ ሰነዳቸው ጋር በተያያዘ በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ከናይሮቢ አየር ማረፊያ ከተባረሩ ከሳምንታት በኋላ የኬንያ ፓስፖርታቸውን እና የልደት የምስክር ወረቀታቸውን በሞቃዲሾ ለሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ ማስረከባቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ጅብሪል ፓስፖርታቸውን ያስረከቡት በፈቃደኝነት እና “ለሱማሊያ ያላቸውን ታማኝነት” እንዲሁም ቁርጠኝነት ለማሳየት እንደሆነ ተናግረዋል።
ፓስፖርቱ በህጋዊ መንገድ የተገኘ እና ከኬንያ ህግ ጋር በተጣጣመ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውሳኔው በኬንያ ባለስልጣናት በተጠየቀ ጥያቄ ወይም በነበረ አለመግባባት ምክንያት የተደረገ አይደለም ብለዋል።

❤12👍6
ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡
Via : አንዳፍታ ሚዲያ

😢28❤7👍3🤯3
የአነስተኛ ገንዘብ ኖቶች እጥረት‼️
የአነስተኛ የገንዘብ ኖቶች እጥረት የችርቻሮ ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን እየፈተነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ አነስተኛ የገንዘብ ኖቶች በተለይም የ 10 ብር ኖት እጥረት በዕለታዊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው። በርካታ የሱቅ ባለቤቶች መልስ በማጣታቸው ምክንያት ደንበኞችን ለመመለስ ወይም እቃዎችን በዕዳ ለመስጠት ተገደዋል።
የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 13.9% እንዲሁም የምግብ ዋጋ ንረት 15.1% በመድረሱ፣ አነስተኛ ኖቶች በእጅ የመዘዋወር ፍጥነታቸው ጨምሮ በፍጥነት እንዲያልቁና እንዲቀደዱ አድርጓል። እ.ኤ.አ በ 2020 ከተደረገው የብር ቅያሬ ወዲህ አዲስ የ 10 ብር ኖት ያልታተመ በመሆኑም በገበያው ላይ ያለው መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል።
በተጨማሪም ከ 350 ቢሊዮን ብር በላይ ከባንክ ሥርዓት ውጭ በህዝብ እጅ ስለሚገኝ፣ ብሔራዊ ባንክ ያረጁ ኖቶችን ሰብስቦ ለመተካትና ለማስወገድ ተቸግሯል። እስከ እ.ኤ.አ 2030 ሙሉ በሙሉ ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የመሆን ግብ ቢኖርም፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መቆራረጥ እንዲሁም የዲጂታል መሣሪያዎች ውድነት ሽግግሩን እያዘገየው ይገኛል።
"የአነስተኛ ኖቶች እጥረት የዘወትር ራስ ምታት ሆኖብናል። አንዳንድ ጊዜ ደንበኞችን መልሰን እንልካለን፤ ወይም ዕቃዎችን በብድር ለመስጠት እንገደዳለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

❤19👍3
በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር ተነገረ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምቹ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።
ከእነዚህም መካከል አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በኤምባሲዎችና በቆንስላዎች በኩል በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጿል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ እንደገለጹት፥ለዲያስፖራው የሚሰጠው አገልግሎት እንዲቀላጠፍ አዲስ ድረ-ገጽ ተዘጋጅቷል።
ይህ ድረ-ገጽ ተገልጋዮች ባሉበት ሀገር ሳይገደቡ የፓስፖርት እድሳትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በቀላሉ እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የቢጫ ካርድ ባለቤቶች ቀደም ሲልም በሀገር ውስጥ ኢንቨስት የማድረግና የመንቀሳቀስ መብት ያላቸው በመሆኑ፤አዲሱ የጎልደን ቪዛ የግድ አስፈላጊ ላይሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
እነዚህ ቅርንጫፎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው፣ ተገልጋዮች ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።
ከፓስፖርት ባለፈም፣ የነዋሪነት ፈቃድና የቪዛ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

❤10👍3
በሳዑዲ 220 ኪሎ ግራም ጫት በኮንትሮባንድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተያዙ
በሳዑዲ አረቢያ የጃዛን ክልል አል-ዳየር ዘርፍ የድንበር ጥበቃ አባላት 220 ኪሎ ግራም ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።
ተጠርጣሪዎቹ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት መመሪያ በመጣስ አደንዛዥ ዕፅ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ሲሆን፣ አስፈላጊው ህጋዊ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከተያዘው እቃ ጋር ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልከዋል ሲል ሳዑዱ ጋዜት ዘግቧል።

😢6❤4👍3
በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ቁጥር 329 ደረሰ አለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 አዳዲስ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
ባለሥልጣኑ ከተሰጡት ፈቃዶች መካከል፦
· ለ14 የበየነ መረብ ወይም ኦንላይን ሚዲያዎች፣
· ለ5 የማህበረሰብ ብሮድካስቶች፣
· ለ19 የሚዲያ ፕሮግራም አዘጋጆች፣
· እንዲሁም ለ9 የማስታወቂያ አዘጋጆች የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ለ5 ቋሚ የውጭ ዜና ወኪሎችና ለአጭር ጊዜ የፊልም ቀረፃና ዘገባ ወደ አገር ውስጥ ለገቡ 78 የውጭ ጋዜጠኞች ፈቃድ ተሰጥቷል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ሁለንተናዊ የሪፎርም፣ የክትትልና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
አክለውም፤ ሚዲያዎች ለአገር ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጉልህ እንዲያሳይ ባለሥልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

❤11👍3
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ስለ ተማሪዎችና መምህራን ዝውውር የተወራውን አስተባበለ!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ተማሪዎቹና መምህራኑ የዝውውር ጥያቄ አቅርበዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ "ከእውነት የራቀ እና ምንም አይነት መነሻ የሌለው ፈጠራ ነው" ሲል አስተባበለ። ተማሪዎችና መምህራን ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳይሸበሩ ያሳሰበው ዩኒቨርሲቲው፣ የተወራው ወሬ መሠረት የሌለው መሆኑን አረጋግጧል።
ሰሞኑን በመቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ አቅርበዋል የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸው አይዘነጋም፡፡

❤6👍4🤪2🤔1
በትግራይ ክልል ግጭት በማገርሸቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ያለው ስጋት ዳግም አሳሳቢ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ‼️
በሀገር የመከላከያ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የክልሉ ነዋሪዎች ዳግም ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመጋለጥ ስጋት እንደደገነባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ቲገሬ ቻጉታህ እንደገለጹት ማህበረሰቡ ቀደም ሲል ከደረሱበት አሰቃቂ ጥቃቶች ሳያገግምና ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ አዲስ ግጭት ውስጥ መግባቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።
በትግራይ ክልል ያገረሸው ግጭት ከአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች ጋር ተደማምሮ በሀገሪቱ ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እየደረሰ መሆኑን የገለጸው አምነስቲ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች መርማሪ አካላትን ሥራ በአስቸኳይ መመለስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት፤ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በርካታ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ያስታወሰው ተቋሙ በጥፋተኞች ላይ ምርመራ እና ክስ ያለማቅረብ አካሄድ ልማዳዊ ሊሆን አይገባም ብሏል።
የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ፣ ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም ለነጻ የሰብአዊ መብት ተከታታዮች፣ ለሰብአዊ እርዳታ አቅራቢዎች እና ለገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ፈቃድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

❤7👍2🤣2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
#እንድታውቁት
በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆኖ በሚቆይበት የክረምት ወራት በተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች አሳውቋል።
ፍርድ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳመለከተው፣ አገልግሎቱ የሚሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት ነው።
ይህም መሰረታዊ የመብት ጥሰት እንዳይከሰት እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ መሠረት በክረምቱ የተረኛ ችሎት የሚታዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዝርዝር፦
• አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች እና የልጅ ቀለብ ጥያቄዎች፣
• አካል ነጻ ለማውጣት እና እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀረቡ አቤቱታዎች፣
• የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም ጉዳዮች፣
• ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች፣
• እንዲሁም ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ ጉዳዮች በዳኛው ውሳኔ የሚስተናገዱ ይሆናል።
በወንጀል ጉዳዮች በኩል ደግሞ የሚከተሉት ነጥቦች ተለይተዋል፦
• የዋስትና እና የአምክሮ ጥያቄዎች፣
• እስረኛ ያለባቸው የክስ መዛግብት፣
• የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች (በአራዳ ምድብ ችሎት)፣
• በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ለመሰየም የሚቀርቡ ጥያቄዎች፣
• ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ የወንጀል ጉዳዮች ይስተናገዳሉ።
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሆነባቸው በእነዚህ ሁለት ወራት፣ ለዳኞች ተራ ወጥቶ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፤ የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብም ሆነ ተገልጋዩ ለሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

❤17👍3
የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተናን 81 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም ተባለ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ክልላዊ ፈተና 50 እና ከዚያ በላይ መሆኑን ገልጿል።ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ 48 እና ከዛ በላይ ማለፊያ ነጥብ ተቆርጦለታል።የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመውሰድ የተመዘገቡ ተማሪዎች 86 ሺህ 502 እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን 78 ሺህ 203 የሚሆኑት ፈተናውን ወስደዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ወደ ቀጣይ ክፍል ያለፋት 47 ሺህ 307 ተማሪዎች መሆናቸውን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ የሱፍ አህመድ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በዚህም መሠረት ክልላዊ ውጤት ከመቶ አንፃር ሲታይ 60 ነጥብ 4 መሆኑ ተገልጿል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ ተፈታኞች 126 ሺህ 224 ናቸው። ፈተና የወሰዱት ደግሞ 110 ሺህ 566 ከእነዚህ ደግሞ ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበው ወደ ቀጣይ 7ኛ ክፍል የተዛወሩ 70 ሺህ 584 መሆናቸውን አቶ የሱፍ ነግረውናል።
በዚህም ክልላዊ ውጤት በመቶ ሲገለፅ 63 ነጥብ 8 እንደሆነ ተገልጿል። 540 ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ አሳልፈዋል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ 81 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ አላሳለፉም።
በአጠቃላይ ክልላዊ ውጤቱ ከአምና የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ8ኛ ክፍል በ3 በመቶ ያነሰ አፈፃፀምን አስመዝግቧል ። አምና በነበረው ክልላዊ ውጤት 63 በመቶ የሆነ ውጤት ተመዝግቦበት እንደነበር ተገልጿል።በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል የአምና ክልላዊ ውጤትን በተመለከተ 56 በመቶ አፈፃፀም የታየበት እንደነበር የተነገረ ሲሆን በ2018 በጀት አመት ደግሞ 63 ነጥብ 84 በመቶ መሆኑን አቶ የሱፍ አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤17👍4