አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ራያ‼️
ህወሓት በራያ ጨርጨር የነበረውን ሰራዊት እና መካናይዝድ ጦር ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም ለሊቱን በባቡር መስመሩ ወደ አፋር ድንበር ሲያስጠጋ አድሯል።
ሁሉም የሰራዊት አባላት ስልካቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዋል።
ህዝቡ በመኪና የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች እንዲያቆም አዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍5🤡5🤯3🕊2👀1
ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት ተቀላቀሉ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ስምንት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር አዲስ ተጨማሪ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት አዋቅራለች።

ከእነዚህ ስምንት ሀገራት መካከል አምስቱ ሀገራት ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ናቸው።

የታቀደው ህብረት ሳዑዲ አረቢያን፣ ዮርዳኖስን፣ የመንን እና አምስቱን የአፍሪካ ሀገራት ያካተተ ነው።

የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ጥምረቱ ዓላማው በቀይ ባህር ላይ በሚያዋስኑ ሀገራት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር እና ዓለም አቀፍ የባህር ላይ መስመሮችን፣ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መንገዶችን እንዲሁም የጋራ የባህር ላይ ጥቅሞችን መጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።

ጥምረቱ የተመሰረተው በቀጠናው ውጥረቶች እና በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሱ መስተጓጎሎች እየጨመሩ የመጡበት ወቅት ላይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍97🤪6
#ተራዝሟል‼️
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን፣ ተከታዮቹን መረጃዎች ያስተውሉ፦

➻ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን አሁን ላይ Update ማድረግ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

➻ መስማት ወይም ማየት የማትችሉ አመልካቾች ፕሮፋይል ገፃችሁን Refresh በማድረግ የተደራሽነት ሁኔታችሁን (Accessibility Status) Update ማድረግ ትችላላችሁ።

➻ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ አመልካቾች አሁን ላይ የNGAT ምዝገባቸውን ማድረግ ይችላሉ። Non-Ethiopian applicants can now register for NGAT.

🔔 ለተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የምዝገባ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚላክ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3
በአማራ ክልል ያለዉ የፀጥታ ችግር በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎችን ለማግኘት እክል መሆኑ ተገለፀ

በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ባለመገኘታቸዉ እልባት ያላገኙ መዝገቦች መኖራቸዉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናገረ፡፡ 

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠቅላይ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እልባት ሳያገኙ የቆዩ መዛግብት መኖራቸዉን ተመልክቻለሁ ሲል የበጀት አመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት  ባቀረበበት ወቅት ገልጿል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ አለም አንተአግደዉ እልባት ሳያገኙ በቆዩት መዝገቦች ዙሪያ ጥናት መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎች ለማቅረብ የፀጥታ ችግር እንደ እክል መታየቱን ጥናቱ አሳይቷል።

ከነዚህ መካከል በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎችን ለማቅረብ ማስረጃ የሚሰጡ ተቋማት በፀጥታ ችግር ምክንያት ስራ ላይ ባለመሆናቸዉ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ለመስጠት ምክንያት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ማስረጃ የሚሰጡ ተቋማት ጋር የተጠየቀዉን ማስረጃ ሄዶ ለማጣራት በፀጥታ ችግሩ ምክንያት ያን ማድረግ እንዳልተቻለም በጥናቱ መለየቱን ገልፀዋል።

ባለጉዳዮችም ቢሆኑ የፀጥታ ችግሩን ተንተርሶ ተደጋጋሚ ቀጠሮ መጠየቃቸዉ እንዲሁም በወቅቱ ሊሰጡ የሚገቡ ትዕዛዞች በመዘግየታቸዉ መዝገቦቹ እልባት ሳያገኙ እንዲቆዩ እንዳደረጋቸዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናግሯል።

ከዚህ ዉጪ በአንዳንድ ማስረጃ ሰጪ ተቋማት የሚቀረቡ ማስረጃዎች የገለልተኛነት ጥያቄ ሲነሳ ገለልተኛ ነዉ ተብሎ በሚታመንበት ሌላ አካል ማስረጃ እንዲሰጥ ትዕዛዝ መሠጠቱ እንደ ችግር ተነስቷል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለም አንተአግደዉ በሪፖርታቸዉ የዳኞች ስነምግባርን በተመለከተ እንደገለፁት በ80 ዳኞች ላይ የዲሲፕሊን ክሶች ቀርበዋል ብለዋል።

ከዚህ ዉስጥ 51ዱ ዉሳኔ ያገኙ ሲሆን፤ 36 ያህሉ ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ ከገንዘብ እስከ ስራ ስንብት የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸው በሪፖርታቸዉ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
በመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው ታላቋ የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬት እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉን የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።

በተከሰተው በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት፣ እንዲሁም በ2 ሰዎች ላይ መለስተኛ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል። 

የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን መሪር ሐዘን ገልጿል።

አደጋው ከተከሰተበት ቅጽበት ጀምሮ የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በስፍራው በአካል በመገኘት ነፍስ የማዳን ሥራውን በበላይነት ሲያስተባብሩ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ውለዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የሕክምና ባለሙያዎች በቅንጅት በተደረገው ብርቱ ትግል፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቦታው ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3010💔8🤯1😱1
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
4👍2
ይከፈላል ተብሏል‼️
በምርጫ ቦርድ እና በምርጫ አስፈጻሚዎች መካከል ያለው የክፍያ ውዝግብ
​በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የተሳተፉ የመስክ አሠልጣኞች፣ የማስተባበሪያ ኃላፊዎችና የቆጠራ አስተባባሪዎች በገቡት ውል መሠረት ሊከፈላቸው የሚገባው የአገልግሎትና የጉዞ አበል ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ገለጹ።

ባለሙያዎቹ ኃላፊነታቸውን በሰዓቱና በውሉ መሠረት ቢያጠናቅቁም ክፍያው በመዘገየቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የሥነ ልቦና ጫና እንደደረሰባቸው በመግለጽ የቦርዱን ኃላፊዎች ለጥያቄያቸው ግዴለሽነት አሳይተዋል ሲሉ ከሰዋል።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ  በሰጠው ምላሽ፣ ክፍያው ከመፈጸሙ በፊት አሠልጣኞቹ በውላቸው መሠረት ሥራቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን የማጣራትና የማረጋገጥ ሥራ መሠራት እንዳለበት አስታውቋል።

ቦርዱ አክሎም ምርጫው የተካሄደው የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ላይ በመሆኑ የነበረው በጀት በማለቁ ተጨማሪ በጀት እንዲለቀቅለት መጠየቁንና በጀቱ ሲፈቀድ ማጣራቱ ተጠናቆ ክፍያው እንደሚፈጸም አብራርቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18🤪6👍3
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
2👍2
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉ጎጃም በረንዳ ጫፍ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፣ ሰን ሆቴል፣ 3ኛ ፖሊስ ጣቢ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ እና አካባቢው፣

👉 ዳውን ታውን ሆቴል፣ አውራሪስ ሆቴል፣ አዲሱ ስታዲየም፣ ካልዲስ ቡና፣ መድሓኒዓለም ቤ/ክ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡00 - 10፡00

👉 ጉርድ ሾላ፣ ትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት፣ ግብርና ምርምር፣ ጃክሮስ አደባባይ በስተጀርባ እና አካባቢው፣

👉 ላምበረት  መናኸሪያ ፣ ላመበረት፣ እስራኤል ኤምባሲ፣ አቢሲኒያ ሆቴል፣ ሱሉልታ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 4፡00 - 8፡00

👉 ከደንበሯ ሆስፒታል ፣ በግ ተራ፣ ምስራቅ አጠቃላይ፣ ሾላ ገበያ፣ የካ መንፈሻ፣ ዘፍመሽ ሞል፣ እና አካባቢው፣

👉 አትላስ ሆቴል፣ ሻላ መናፈሻ፣ ኤስኦኤስ፣ ደሳለኝ ሆተል ጀርባ፣ ደሳለኝ ሆቴል፣ ፕሬዚደንሺያል ሆቴል፣ሩዋንዳ ኦቨርፓስ እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡00 - 11፡00

👉በጭሮ ሪጅን ደደር፣ ሜታ ፣ መልካ በሎ ፣ ጎሮ ጉቱ ወረዳዎች  እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡00 - 11፡00

በበህርዳር ሪጅን ቀበሌ 16 ነጋድራስ በቄ ሰፈር፣ ዶንጎስ መኪና ማሰልጠኛ፣ቤዛ ብዙሃን ት/ቤት እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍4
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከ805 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ተከልኩ አለች

ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ይፋዊ እቅድ በመያዝ "805.3 ሚሊዮን" ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ እቅድ በላቀ ስኬት ማጠናቀቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። 

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በንቃት በተሳተፉበት በዚህ ግዙፍ የንቅናቄ መርሃ ግብር ሀገሪቱ ታላቅ ድምቀት ያለው ድል አስመዝግባለች።

ይህ ታሪካዊ ድል የዕለቱ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የያዘችውን የረጅም ጊዜ እቅድ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣4215👍4🤪2🙊2🤡1👀1
ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማረፊያ የሚሆን መሬት ሰጠች

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የትራንስፖርት ኮሪደር ለማዘመን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ ስምምነት በመተግበር በሞጆ ከተማ የመሬት ርክክብ ፈጸሙ።

ላለፉት 25 ዓመታት ዘግይቶ የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ ለጅቡቲ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ተርሚናል ግንባታ የሚውል መሬት ለጅቡቲ ወገን በመስጠት እውን ሆኗል።

በሞጆ ከተማ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ፣ የጅቡቲ የመሠረተ ልማትና መሳሪያዎች ሚኒስትር ሳይድ ኑህ ሀሰን፣ የሞጆ ከተማ ከንቲባ እና የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

ዓለሙ ስሜ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በጅቡቲ ባለሥልጣናት መካከል በተደረገው ውይይት ውሳኔ ያገኘ ሲሆን፣ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት የበለጠ ያጠናክራል።

ለባህር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ዋነኛ የንግድ መስመር የሆነው የሞጆ-ጅቡቲ ኮሪደር፣ አዲሱ የከባድ መኪኖች ማቆሚያ ተርሚናል ሲገነባበት በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ይባክን የነበረውን ጊዜና ተጨማሪ ወጪ በእጅጉ ይቀንሰዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ጅቡቲን የሚያገናኘውን የባቡር መስመር የጭነት አቅም እስከ እ.ኤ.አ. 2027 ወደ 6.2 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
21🤪12🤔4👍3🤣1
በራያ ውጥረት አለ-ነዋሪዎቹ‼️
ከቀናት በፊት በሱዳን አዋሳኝ ሸረሪና በፌደራል ኃይሎች እና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል የነበረው ግጭት ጋብ ቢልም፣ በራያ አላማጣ ግንባር በኩል ግን ወታደራዊ ዝግጅቱ እና ፍጥጫው ማየሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ፣ የህወሓት ሠራዊት በራያ ግንባር በጨርጨር፣በቢሶበር እና ሌሎች አካባቢዎች ተሰማርተዋል ይላሉ።

«ህወሓት ሠራዊቶች ብዙ አርሚዎች በራያ ግንባር አሰማርተዋል። ለጦርነት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ ወርዶላቸዋል። ዝግጅት ያለው አሁን በጨርጨር በኩልና ቢሶበር ነው። በዛ ቡታ መርፌ አካባቢ አለ። ከዚህ በዋጃ ቆቦ፣ በጃርሮታ ጀምሮ፣ በዳንያ ለኮ፣ ሰሌን ውኃ፣ በላይ በር በባይባዋ፣ ቁሙጋ ላይ ያለውን አካባቢ ሁሉ ነው ዝግጅቱ። የዋጃን መስመር ተከተሎም የራሳቸውን አርሚ አዘጋጅተዋል።»
መካናይዝድ ጦርም በማንቀሳቀስ ቦታ እያሲያዙ ነው ብለዋል።
አሁን ባለው ወታደራዊ ዝግጅት እና እንቅስቃሴ ጦርነቱ በማንኛውም ጊዜ ሊጀምር ይችላል የሚሉት የራያ ወረዳ ነዋሪ፣ ጦርነቱ በተጀመረ ቁጥር ጉዳት የሚደርስበት የራያ ማኅበረሰብ በእጅጉ ነፃነቱን ይሻል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍5🤪5👀1
ኤርትራ‼️
ኤርትራ የብሔራዊ የወታደራዊ የአገልግሎት ግዴታቸውን እንዲወጡ የመለመለቻቸውን ወጣቶች  ወደ ሳዋ ማሰልጠኛ እየላከች ትገኛለች።
በኤርትራ ማንኛውም ከ18-40 አመት የሞላው ወጣት ግዴታ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶ ማገልገል እንዳለበት የሀገሪቱ ህግ ይደነግጋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍13🤣7🤯1
የሱማሊያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኬንያ ፓስፖርታቸውን አስረከቡ

የሱማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጅብሪል አብዲራሺድ ሀጂ ከጉዞ ሰነዳቸው ጋር በተያያዘ በተነሱ ጥያቄዎች ምክንያት ከናይሮቢ አየር ማረፊያ ከተባረሩ ከሳምንታት በኋላ የኬንያ ፓስፖርታቸውን እና የልደት የምስክር ወረቀታቸውን በሞቃዲሾ ለሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ ማስረከባቸውን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጅብሪል ፓስፖርታቸውን ያስረከቡት በፈቃደኝነት እና “ለሱማሊያ ያላቸውን ታማኝነት” እንዲሁም ቁርጠኝነት ለማሳየት እንደሆነ ተናግረዋል።

ፓስፖርቱ በህጋዊ መንገድ የተገኘ እና ከኬንያ ህግ ጋር በተጣጣመ መልኩ ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውሳኔው በኬንያ ባለስልጣናት በተጠየቀ ጥያቄ ወይም በነበረ አለመግባባት ምክንያት የተደረገ አይደለም ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
12👍6
ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

Via : አንዳፍታ ሚዲያ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢287👍3🤯3
የአነስተኛ ገንዘብ ኖቶች እጥረት‼️
የአነስተኛ የገንዘብ ኖቶች እጥረት የችርቻሮ ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን እየፈተነ ይገኛል።
​በኢትዮጵያ የችርቻሮ ንግድ ዘርፍ አነስተኛ የገንዘብ ኖቶች በተለይም የ 10 ብር ኖት እጥረት በዕለታዊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው። በርካታ የሱቅ ባለቤቶች መልስ በማጣታቸው ምክንያት ደንበኞችን ለመመለስ ወይም እቃዎችን በዕዳ ለመስጠት ተገደዋል።

​የአገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ንረት 13.9% እንዲሁም የምግብ ዋጋ ንረት 15.1% በመድረሱ፣ አነስተኛ ኖቶች በእጅ የመዘዋወር ፍጥነታቸው ጨምሮ በፍጥነት እንዲያልቁና እንዲቀደዱ አድርጓል። እ.ኤ.አ በ 2020 ከተደረገው የብር ቅያሬ ወዲህ አዲስ የ 10 ብር ኖት ያልታተመ በመሆኑም በገበያው ላይ ያለው መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መጥቷል።

​በተጨማሪም ከ 350 ቢሊዮን ብር በላይ ከባንክ ሥርዓት ውጭ በህዝብ እጅ ስለሚገኝ፣ ብሔራዊ ባንክ ያረጁ ኖቶችን ሰብስቦ ለመተካትና ለማስወገድ ተቸግሯል። እስከ እ.ኤ.አ 2030 ሙሉ በሙሉ ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የመሆን ግብ ቢኖርም፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መቆራረጥ እንዲሁም የዲጂታል መሣሪያዎች ውድነት ሽግግሩን እያዘገየው ይገኛል።

​"የአነስተኛ ኖቶች እጥረት የዘወትር ራስ ምታት ሆኖብናል። አንዳንድ ጊዜ ደንበኞችን መልሰን እንልካለን፤ ወይም ዕቃዎችን በብድር ለመስጠት እንገደዳለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍3
በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር ተነገረ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምቹ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን አስታውቋል።

ከእነዚህም መካከል አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት  አገልግሎት በኤምባሲዎችና በቆንስላዎች በኩል በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጿል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ እንደገለጹት፥ለዲያስፖራው የሚሰጠው አገልግሎት እንዲቀላጠፍ አዲስ ድረ-ገጽ ተዘጋጅቷል።

ይህ ድረ-ገጽ ተገልጋዮች ባሉበት ሀገር ሳይገደቡ የፓስፖርት እድሳትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በቀላሉ እንዲያከናውኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የቢጫ ካርድ ባለቤቶች ቀደም ሲልም በሀገር ውስጥ ኢንቨስት የማድረግና የመንቀሳቀስ መብት ያላቸው በመሆኑ፤አዲሱ የጎልደን ቪዛ የግድ አስፈላጊ ላይሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

እነዚህ ቅርንጫፎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው፣ ተገልጋዮች ወደ አዲስ አበባ ሳይመጡ በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

ከፓስፖርት ባለፈም፣ የነዋሪነት ፈቃድና የቪዛ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መንገድ እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10👍3
በሳዑዲ 220 ኪሎ ግራም ጫት በኮንትሮባንድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተያዙ

​በሳዑዲ አረቢያ የጃዛን ክልል አል-ዳየር ዘርፍ የድንበር ጥበቃ አባላት 220 ኪሎ ግራም ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ለማስገባት የሞከሩ 11 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።

ተጠርጣሪዎቹ የሀገሪቱን የድንበር ደህንነት መመሪያ በመጣስ አደንዛዥ ዕፅ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ሲሆን፣ አስፈላጊው ህጋዊ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ከተያዘው እቃ ጋር ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልከዋል ሲል ሳዑዱ ጋዜት ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢64👍3
በኢትዮጵያ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎች ቁጥር 329 ደረሰ አለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
 
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለ52 አዳዲስ የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
 
ባለሥልጣኑ ከተሰጡት ፈቃዶች መካከል፦
 
·         ለ14 የበየነ መረብ ወይም ኦንላይን ሚዲያዎች፣
·         ለ5 የማህበረሰብ ብሮድካስቶች፣
·         ለ19 የሚዲያ ፕሮግራም አዘጋጆች፣
·         እንዲሁም ለ9 የማስታወቂያ አዘጋጆች የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጿል።
 
ከዚህ በተጨማሪም ለ5 ቋሚ የውጭ ዜና ወኪሎችና ለአጭር ጊዜ የፊልም ቀረፃና ዘገባ ወደ አገር ውስጥ ለገቡ 78 የውጭ ጋዜጠኞች ፈቃድ ተሰጥቷል።
 
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፤ በ2019 በጀት ዓመት የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን ዕድገት የሚመጥን ሁለንተናዊ የሪፎርም፣ የክትትልና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
 
አክለውም፤ ሚዲያዎች ለአገር ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጉልህ እንዲያሳይ ባለሥልጣኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ስለ ተማሪዎችና መምህራን ዝውውር የተወራውን አስተባበለ!

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ተማሪዎቹና መምህራኑ የዝውውር ጥያቄ አቅርበዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ "ከእውነት የራቀ እና ምንም አይነት መነሻ የሌለው ፈጠራ ነው" ሲል አስተባበለ። ተማሪዎችና መምህራን ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳይሸበሩ ያሳሰበው ዩኒቨርሲቲው፣ የተወራው ወሬ መሠረት የሌለው መሆኑን አረጋግጧል።

ሰሞኑን በመቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎችና መምህራን በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ አቅርበዋል የሚሉ መረጃዎች መሰራጨታቸው አይዘነጋም፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍4🤪2🤔1