አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ያለው የክረምት ሁኔታ ከላይ በምስል የተያያዘውን ይመስላል፣ ምንም ዝናብ የለም።
የፓስፍክ ውቂያኖስ ሙቀት ባልተለመደ ሁነታ በመጨመሩ ምክንያት በሰሜን፣ በመካከለኛና  ምስራቅ አከባቢ የዘንድሮው የክረምት ዝናብ አጭር መሆኑና ክረምቱም ቶሎ እንደሚወጣ የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
💔13😢12👍43🙊2
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦

ከጠዋቱ 2፡30-8፡30

👉 ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒየም፣ ዓለም ባንክ 700 ማህበራት ቤቶች፣ ገላን  እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 12፡00 - 4፡00

👉 በመቀሌ ቀበሌ 14፣ 15 ፣ 17 ፣ መቀሌ ተክላይማኖት እና አካባቢው፣

ከጠዋቱ 2፡30-10፡00


👉 አዋሽ መልካሳ እና አከባቢው፣

ከጠዋቱ 3፡00-7፡00

👉 በበህዳር ሪጅን አዲስ ዓለም፣ ኦቪድ ኮኒስትረክሽን፣ ሰማታት፣ ግዮን ት/ቤት፣ ሚሊኒየም ት/ቤት፣ ናይል ቪው ሆቴል እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍2
#USA 🇺🇸 #VISA

አሜሪካ ለቪዛ የምትይዘውን ገንዘብ ወደ 20 ሺህ ዶላር ልታሳድግ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የበርካታ አገራት ዜጎች ቪዛ ሲያመለክቱ ያስይዙት የነበረውን ገንዘብ ከ15 ሺህ ዶላር ወደ 20 ሺህ ዶላር (3.1 ሚሊዮን ብር በላይ) ከፍ በማድረግ ቋሚ ሊያደርግ ነው።

መሥሪያ ቤቱ እንደገለፀው መርሃ ግብሩ የቢዝነስ እና የቱሪስት (ቢ1 እና ቢ2) ቪዛ አመልካቾች ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው።

ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ አሜሪካ ውስጥ ከቆዩ ገንዘቡ ተመላሽ እንዳይሆን የሚያደርገው ይህ አሠራር ተግባራዊ ይሆንባቸዋል ከተባሉ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ከሆኑ 50 አገራት መካከል ፦
- #ኢትዮጵያ
- ጂቡቲ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሴኔጋል፣
- ኡጋንዳ፣
- ታንዛኒያ ይገኙበታል።

ይህ በቀናት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው የተሻሻለው ፕሮግራም፣ ከቪዛ ጊዜያቸው በላይ የሚቆዩ ጎብኝዎችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ መሠረት አመልካቾች እንደ ኤምባሲው ኦፊሰሮች ውሳኔ ለቪዛ እስከ 20 ሺህ ዶላር (ከ3.1 ሚሊዮን ብር በላይ) የሚደርስ ገንዘብ እንዲያስይዙ ሊጠይቁ ይችላሉ።

አሜሪካ ውስጥ ከቪዛ ጊዜያቸው በላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ዜጎች ባሏቸው አገራት እና የአገር ውስጥ ሰነዶች ላይ የላላ ቁጥጥር በሚያደርጉ አገራት የቪዛ ማስያዣ የሙከራ መርሃ ግብር ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ነበር።

መርሃ ግብሩ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የነበረ ሲሆን የተቀመጠለት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው አዲሱ መመሪያ የወጣው።

በቀናት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው ይህ አዲሱ የቪዛ ማስያዣ ገንዘብ ፕሮግራም ቋሚ እንደሚሆንም ተገልጿል።

በተጠናቀቀው የሙከራ መርሃ ግብር መሠረት አመልካቾች ከ5 ሺህ ፣ ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ዶላር ድረስ እንዲያስይዙ ይጠየቁ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ፕሮግራም አነስተኛው 5 ሺህ ዶላር ከዝርዝሩ ወጥቶ፣ ከፍተኛው የማስያዣ ገንዘብ ወደ 20 ሺህ ከፍ ተደርጓል።

በአዲሱ መርሃ ግብር ከተካተቱ 50 አገራት መካከል 30ዎቹ የሚገኙት በአፍሪካ ውስጥ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20🤪5😢3👍2
የሼክ መሐመድ አልአሙዲ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ፤ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር 375ኛ ደረጃን ያዙ

የትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ሼክ መሐመድ አልአሙዲ የተጣራ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከትሎ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ በድጋሚ ተካተዋል።

ዛሬ ኦገስት 1፣ 2026 ይፋ በሆነው የብሉምበርግ ዝርዝር መሠረት፣ አልአሙዲ በዓለም 375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በ2026 ብቻ የሀብታቸው መጠን በ1.67 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም በ19.7 በመቶ አድጓል። በቅርብ ጊዜም በአንድ ቀን ብቻ 33.7 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ተመዝግቧል።

የብሉምበርግ ግምገማ እንደሚያሳየው፣ የአልአሙዲ ሀብት መጨመር ከኢነርጂ፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከመሠረተ ልማት እና ከሌሎች የንግድ ንብረቶቻቸው ዋጋ መጨመር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ቀደም ከዋና ንብረቶቻቸው መካከል የነበረው የስዊድኑ ፕሪም (Preem) የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ ግን ለVARO Energy ከተላለፈ በኋላ በአሁኑ ጊዜ VAROPreem በተባለ የተዋሃደ ኩባንያ ስር ይገኛል።

በሌላ በኩል፣ ብሉምበርግ የአልአሙዲን ሀብት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደደረሰ ቢገልጽም፣ በፎርብስ 2026 ዓመታዊ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ግን ስማቸው አልተካተተም። ይህም ሁለቱ ተቋማት የቢሊየነሮችን ሀብት በሚገምቱበት የመረጃ ምንጭና የግምገማ ዘዴ ልዩነት መኖሩን ያሳያል።

በብሉምበርግ የወጣው አዲሱ መረጃ የሚያመለክተው፣ ሼክ መሐመድ አልአሙዲ ከቀደሙት ዓመታት የሀብት መቀነስ በኋላ በድጋሚ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሀብት ደረጃ መመለሳቸውን ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
25👍8🫡1
በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።

ውጤት ለማየት 👇
https://amhara.ministry.et/#/result

አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡

በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot

የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint

VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8😢3👍2
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲዘዋወሩ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ።

በትግራይ በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተወሰኑ ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

በመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ጥያቄያቸውን ለመንግሥት እያቀረቡ ነው።

ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ በሚታየው የጸጥታ ስጋት ምክንያት የቅሬታ ጥያቄ እያስገቡ ሲሆን፤ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የዝውውር ውሳኔም ሆነ የተገባ ቃል አለመኖሩን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሓየሎም ስዩም ገልፀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍6🤔2
የማስታወቂያ ግብዣ

የተከበራችሁ ቤተሰቦች ከ35,000 በላይ ተከታይ ባለው እና በደቂቃዎች ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝ ባለው በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ኪስ በማይጎዳ ዋጋ እንድታስተዋውቁ በአክብሮት ተጋብዛችኋል
Youtube ቻናል …
የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
ሌሎችም የምትሰጧቸውን አገልግሎቶች.....ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ በኩል ኑ 👇
መልዕክት መቀበያ:—@Addis_reporter_bot
👍42
የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ሰራዊት አመራሮችና አባላት በጥቂት የህወሓት ፖለቲከኞች ተገፋፍተው ክልሉን ዳግም ወደ እልቂት ከመክተት እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

አቶ ጌታቸው በኤክስ ገጻቸው የደብረ ጽዮንን ንግግር አያይዘው ባሰራጩት እጅግ ነቀፋ የበዛበት  መልእክት፣ የህወሓት አመራሮች የትግራይን ህዝብ አንድነት በመበተን እንዲሁም በፋኖ፣ በሱዳኑ ጄኔራል አል-ቡርሃን እና በኤርትራ መንግስት (ሻዕቢያ) ላይ ተማምነው ዳግም ጦርነት ለመክፈት የሚያደርጉት ፉከራ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ ገልጸዋል። በዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ በወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) እና በቀድሞው የደህንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሪነት፣ በጉልበት "አራት ኪሎ እንመለሳለን" በማለት የሚያልሙትን "ቅዠት" በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አስጠንቅቀዋል።

ከፌደራል መንግስቱ ጋር በቅርበት እየሰሩ የሚገኙት አቶ ጌታቸው፣ የትግራይ ሰራዊት ከምንም በላይ የህዝቡን ደህንነት እንዲያስቀድም ጥሪ አቅርበዋል። አቅም እያለ የህዝቡን የህልውና ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ብቻ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ሰራዊቱ በህይወቱና በአካሉ ላይ እየተቆመረበት ያለውን ኃይል 'ይበቃል' ሊለው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም "በሐውልቲ (የህወሓት ጽህፈት ቤት) የመሸገው የብጥብጥ ቡድን" ሲሉ የጠሯቸው እነዚህ አካላት፣ በፉከራና በውጭ ኃይሎች ድጋፍ ላይ በመተማመን የዲፕሎማሲ በሮችን ከዘጉ በኋላ፣ አሁን መሬት ላይ ያለው እውነት ሲከብዳቸው "ዓለም ይድረስልኝ" እያሉ መጮሃቸው ማመዛዘን የጎደለው የፖለቲካ ኪሳራ መሆኑን በአጽንኦት ተችተዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15👍6🤣3🤪3🙊1
በመከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሸረሪና በተባለ ቦታ የተጀመረው ውጊያ መቆሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ማንነታቸው ያልተገለጸ የመረጃ ምንጮች ዋቢ አድርጎ ዘገበ። ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ሸረሪና የተባለ ቦታ ውጊያ የተቀሰቀሰው ትላንት ቅዳሜ ከማለዳው 12 ሰዓት ገደማ እንደሆነ አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የህወሓት አባል መናገራቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

በከባድ የጦር መሣሪያ እና በድሮን ጭምር የተደረገው ውጊያው ከ23 ሰዓታት ገደማ በኋላ እንደቆመ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዋቢ ያደረጋቸው የመረጃ ምንጭ ተናግረዋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ ወይም እንደቆሰሉ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የጸጥታ የመረጃ ምንጭ በእርግጥም ውጊያው እንደቆመ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ይሁንና ከህወሓት በኩል የቀረበው መረጃ ትክክለኛ መሆኑን በገለልተኝነት እንዳላረጋገጠ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በዘገባው ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰረዘው ህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ከማለዳ ጀምሮ በሸረሪና በኩል ውጊያ ጀምሯል በማለት ወንጅሎ ነበር። የፌድራል መንግሥት ግን ስለ ጉዳዩ በይፋ የሰጠው ማብራሪያም ሆነ ምላሽ የለም። ይሁንና የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ባሠፈሩት ጽሁፍ ህወሓትን በሸረሪና በኩል ጦርነት በመክፈት ወንጅለዋል።
በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሐምሌ 25 ቀን 2018 ውጊያ መቀስቀሱ የተሰማው በአዲስ አበባና በመቐለ በሚገኙ ባለሥልጣናት መካከል ያለው ውጥረት በኃይል በተባባሰበት ወቅት ነው።

@Addis_Reporter
28👍5🤯1
AAU ከ500 በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ‼️
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል።

​ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው።

​በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢1918😡8👍5👀3🤔2🤪2🙊2🙉1
የኤርትራ ሰራዊት አቀባበል‼️
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 26 በትግራይ ክልል በጉሎምከዳ ወረዳ ዝባን ሁጻ በተባለ ስፍራ የኤርትራ ሰራዊት እና ወታደራዊ መሪዎች በህወሓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአካባቢው በጋራ ወታደራዊ ቅስቀሳ አካሂደዋል፣የኤርትራ ሰራዊት በይፋ ሲጨፍሩ ታይተዋል።
ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአሁኑ ወቅት በስፍራው የድሮን የስለላ እንቅስቃሴዎችም እየተካሄዱ ይገኛሉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31🤪15👍8😢5👀5🤣1🙈1🙊1
ትርፍ አንጀት ምንድን ነው?

በተለምዶ ትርፍ አንጀት እየተባለ የሚጠራው ችግር  የሚከሰተው አፔንዲክስ (ትርፍ አንጀት) ሚባለው ትንሽ የአንጀት አካል ሲያብጥ ወይም ሲቆጣ ነው። ይህ ችግር በፍጥነት ካልታከሙ ሊፈነዳ እና አደገኛ ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል።

የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ምንድን ነው?

የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ትርፍ አንጀት ለማስወገድ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ሲሆን ለትርፍ አንጀት ችግር በጣም የተለመደው ሕክምና ነው። ቀዶ ሕክምናው በክፍት (open) መንገድ ወይም በላፓሮስኮፒ ሊሰራ ይችላል።

🚨 የትርፍ አንጀት አደገኛ ምልክቶች፡

👉 ከታች በቀኝ በኩል ባለው የሆድ ክፍል ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ህመም ፣
🔹ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ፣
🔹ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት፣
🔹 የምግብ ፍላጎት ማጣት እና
🔹 በእንቅስቃሴ የሚባባስ ህመም ሲኖር በፍጥነት ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል።

የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ለምን ያስፈልጋል?

ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ እና
ከባድ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም
በፍጥነት ለማገገም ይህ ቀዶ ህክምና ያስፈልጋል።

ከቀዶ ጥገናው በኋላ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

🔹 በቀላሉ ሊፈጩ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፣
🔹 ረጋ ያለ እንቅስቃሴ ማድረግ፣
🔹 እረፍት ማድረግ እና
🔹 ውሃ በደንብ መጠጣት ቶሎ ለማገገም ይረዳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍19
ራያ‼️
ህወሓት በራያ ጨርጨር የነበረውን ሰራዊት እና መካናይዝድ ጦር ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም ለሊቱን በባቡር መስመሩ ወደ አፋር ድንበር ሲያስጠጋ አድሯል።
ሁሉም የሰራዊት አባላት ስልካቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዋል።
ህዝቡ በመኪና የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች እንዲያቆም አዟል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍5🤡5🤯3🕊2👀1
ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በሳዑዲ አረቢያ የሚመራውን ስምንት አገራትን ያካተተ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ አዲስ የደህንነት ጥምረት ተቀላቀሉ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ስምንት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚገኙ ሀገራትን በማስተባበር አዲስ ተጨማሪ የባህር ላይ የደህንነት ጥምረት አዋቅራለች።

ከእነዚህ ስምንት ሀገራት መካከል አምስቱ ሀገራት ግብፅ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ ናቸው።

የታቀደው ህብረት ሳዑዲ አረቢያን፣ ዮርዳኖስን፣ የመንን እና አምስቱን የአፍሪካ ሀገራት ያካተተ ነው።

የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ጥምረቱ ዓላማው በቀይ ባህር ላይ በሚያዋስኑ ሀገራት መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር እና ዓለም አቀፍ የባህር ላይ መስመሮችን፣ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መንገዶችን እንዲሁም የጋራ የባህር ላይ ጥቅሞችን መጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።

ጥምረቱ የተመሰረተው በቀጠናው ውጥረቶች እና በንግድ መርከቦች ላይ የሚደርሱ መስተጓጎሎች እየጨመሩ የመጡበት ወቅት ላይ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍97🤪6
#ተራዝሟል‼️
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን፣ ተከታዮቹን መረጃዎች ያስተውሉ፦

➻ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን አሁን ላይ Update ማድረግ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

➻ መስማት ወይም ማየት የማትችሉ አመልካቾች ፕሮፋይል ገፃችሁን Refresh በማድረግ የተደራሽነት ሁኔታችሁን (Accessibility Status) Update ማድረግ ትችላላችሁ።

➻ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ አመልካቾች አሁን ላይ የNGAT ምዝገባቸውን ማድረግ ይችላሉ። Non-Ethiopian applicants can now register for NGAT.

🔔 ለተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የምዝገባ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚላክ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍3
በአማራ ክልል ያለዉ የፀጥታ ችግር በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎችን ለማግኘት እክል መሆኑ ተገለፀ

በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ባለመገኘታቸዉ እልባት ያላገኙ መዝገቦች መኖራቸዉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናገረ፡፡ 

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጠቅላይ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እልባት ሳያገኙ የቆዩ መዛግብት መኖራቸዉን ተመልክቻለሁ ሲል የበጀት አመቱን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት  ባቀረበበት ወቅት ገልጿል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ አለም አንተአግደዉ እልባት ሳያገኙ በቆዩት መዝገቦች ዙሪያ ጥናት መደረጉን አስረድተዋል።

በዚህም በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎች ለማቅረብ የፀጥታ ችግር እንደ እክል መታየቱን ጥናቱ አሳይቷል።

ከነዚህ መካከል በፍርድ ቤት የተጠየቁ ማስረጃዎችን ለማቅረብ ማስረጃ የሚሰጡ ተቋማት በፀጥታ ችግር ምክንያት ስራ ላይ ባለመሆናቸዉ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ለመስጠት ምክንያት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ማስረጃ የሚሰጡ ተቋማት ጋር የተጠየቀዉን ማስረጃ ሄዶ ለማጣራት በፀጥታ ችግሩ ምክንያት ያን ማድረግ እንዳልተቻለም በጥናቱ መለየቱን ገልፀዋል።

ባለጉዳዮችም ቢሆኑ የፀጥታ ችግሩን ተንተርሶ ተደጋጋሚ ቀጠሮ መጠየቃቸዉ እንዲሁም በወቅቱ ሊሰጡ የሚገቡ ትዕዛዞች በመዘግየታቸዉ መዝገቦቹ እልባት ሳያገኙ እንዲቆዩ እንዳደረጋቸዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናግሯል።

ከዚህ ዉጪ በአንዳንድ ማስረጃ ሰጪ ተቋማት የሚቀረቡ ማስረጃዎች የገለልተኛነት ጥያቄ ሲነሳ ገለልተኛ ነዉ ተብሎ በሚታመንበት ሌላ አካል ማስረጃ እንዲሰጥ ትዕዛዝ መሠጠቱ እንደ ችግር ተነስቷል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አለም አንተአግደዉ በሪፖርታቸዉ የዳኞች ስነምግባርን በተመለከተ እንደገለፁት በ80 ዳኞች ላይ የዲሲፕሊን ክሶች ቀርበዋል ብለዋል።

ከዚህ ዉስጥ 51ዱ ዉሳኔ ያገኙ ሲሆን፤ 36 ያህሉ ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ ከገንዘብ እስከ ስራ ስንብት የደረሰ እርምጃ እንደተወሰደባቸው በሪፖርታቸዉ ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
በመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው ታላቋ የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬት እና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉን የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።

በተከሰተው በዚህ አሰቃቂ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት፣ እንዲሁም በ2 ሰዎች ላይ መለስተኛ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል። 

የሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን መሪር ሐዘን ገልጿል።

አደጋው ከተከሰተበት ቅጽበት ጀምሮ የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት በስፍራው በአካል በመገኘት ነፍስ የማዳን ሥራውን በበላይነት ሲያስተባብሩ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ውለዋል። 

ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የሕክምና ባለሙያዎች በቅንጅት በተደረገው ብርቱ ትግል፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በቦታው ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢3010💔8🤯1😱1
📣ምርት እና አገልግሎቶን በቅናሽ ያስተዋውቁ!!

➠ ሱቆች       ➠ ሆቴሎች እና ሬስቶራንት
➠ ሽያጭ       ➠ ቴሌግራም ቻናል
➠ ድርጅቶች   ➠ የቲቪ ፕሮግራም
➠ ት/ቤቶች    ➠ ስልጠናዎች
➠ ሆስፒታል    ➠ ክሊኒኮች
➠ websites  ➠ Events     
➠ ሆቴሎች      ➠ ፈርኒቸር ቤቶች
➠ ባዛር          ➠ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም

የድርጅታችሁን ወይም የሱቃችሁን ህጋዊነት በማረጋገጥ  ምርትና አገልግሎቶን እንዲያስተዋውቁ እድሉን አመቻችተናል። በቻናላችን በማስተዋወቅ ለብዙዎች ይድረሱ... ትርፋማ እና ተመራጭ ይሁኑ።

ከታች ባሉት ሊንኮች ያነጋግሩን።

👉@Addis_reporter_bot
4👍2