መረጃ‼️
በሳዑዲ ዓረቢያ አስተባባሪነት፣ 14 አገራት በቀይ ባሕር፣ ባብኤል መንደብና የኤደን ባሕረ ሠላጤ የንግድና የኢነርጂ አቅርቦት መስመር ደኅንነትን የሚያስጠበቅ ጥምር የመከላከያ ኃይል አቋቋሙ።
ጥምረቱ፣ አባል አገራት መረጃ እንዲለዋወጡ፣ የዘመቻ እቅድ እንዲያወጡና የጋራ የባሕር ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።
ከአፍሪካ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ግብጽ እና ናይጀሪያ የጥምረቱ መስራቾች ኾነዋል።
ከሌሎች መስራቾች መካከል ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና ፓኪስታን ይገኙበታል።
ፍላጎቱ ያላቸው አገራት ጥምረቱን በማንኛውም ጊዜ መቀላቀል ይችላሉ ተብሏል።
ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ እና ኢምሬቶች በጥምረቱ መስራችነት ካልተካተቱ የቀጠናው አገራት መካከል ናቸው።
@Addis_Reporter

🤣11❤10👍2
#USA #Immigration
በአሜሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ያለ ቃለ-መጠይቅ ወደ ፍርድ ቤት የሚላኩበት መመሪያ ጸደቀ።
የትራምፕ አስተዳደር በሀገሪቱ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን የሚመለከት አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
ይህን ተከትሎ በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው ሳይሰማ ቀጥታ ሊባረሩ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
አዲሱ አሰራር ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የተከማቹ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ለማቃለል የታሰበ ነው ተብሏል።
ቀደም ሲል የነበረው አሰራር አመልካቾች መጀመሪያ ጉዳያቸውን ለኢሚግሬሽን ኦፊሰር አቅርበው ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገ ብቻ ወደ ፍርድ ቤት እንዲመሩ የሚያደርግ ነበር።
በአዲሱ መመሪያ በርካታ የጥገኝነት አመልካቾች ከኢሚግሬሽን ኦፊሰሮች ጋር የሚደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ ቃለ-መጠይቅ ሳያደርጉ ጉዳያቸው በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት ሊመራ ይችላል።
444,724 ያህል መዝገቦችን ይነካል የተባለው ይህ ውሳኔ የሕግ ባለሙያዎችና የኢሚግሬሽን ተከራካሪዎች አሰራሩ የስደተኞችን የመሰማትና የፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳና ውሳኔዎችን በማፋጠን ሰዎችን በፍጥነት ለማባረር ያለመ ነው በማለት ተችተውታል።
በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ መንግሥት በሀገሪቱ በሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች ላይ እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ አዲስ ክፍያ ለመጣል ማቀዱ ተሰምቷል።
የታቀደው እርምጃ በተለይ ትምህርታቸውን አጠናቀው በአሜሪካ ለመቆየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
መንግሥት እርምጃው የቪዛ አጠቃቀምን ለማጥበቅና የሀገር ውስጥ የሥራ ገበያን ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ሲገልጽ፣ ተቃዋሚዎች ግን የውጭ ተማሪዎች ለአሜሪካ የትምህርትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን አስተዋፅኦ ሊጎዳ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የትራምፕ አስተዳደር ከስደተኞች ጋር በተያያዝ እጅግ ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተደጋግሞ መገለጹ ይታወሳል።

❤14👍2🤪2
ሰበር ዜና
በኢትዮ ሱዳን ድንበር መጠነ ሰፊ ውጊያ ተከፈተ፡፡
ውጊያ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ከበረኸት እስከ ሸረሪና የከባድ መሳሪያ ድምጽ በስፋት እንደሚሰማ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

❤14😢8👍7🎉2🤪2
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የጥቃቱ መነሻ‼️
👉 የጥቃቱ መነሻና ቦታ፡ አካባቢውን በኃይል ለመቆጣጠር በማሰብ፣ በሱዳን በኩል የተደራጁ የ'ሳምሪ' ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ጠዋት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከፍተዋል። ታጣቂዎቹ ጦርነቱን የጀመሩት በሱዳን ድንበር በኩል በ'ሸረሪና' እና በወልቃይት ጠገዴ ዞን፣ ቃብትያ ሁመራ ወረዳ ስር በምትተዳደረው የበረከት ከተማ አቅጣጫ ድንበር ጥሰው በመግባት ነው።
👉 የሜዳ ላይ ውጊያ ሁኔታ፡ በበረከት ከተማ እና በሸረሪና አቅጣጫ ጥቃቱን የጀመሩት ከሱዳን ሰርጎ የገቡት ታጣቂዎች ('አርሚ 70' ላይ) በቀላል መሳሪያዎች ትንኮሳ የከፈቱ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መጠነ ሰፊ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።
👉 በድሮንና በመድፍ የታገዘ አፀፋ፡ አሁን ላይ ከሁመራ ወደ በረከት ከተማ እና ሸረሪና አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ የመድፍ ድብደባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በሰማይ ላይም የድሮን እንቅስቃሴ በግልፅ እየታየ ነው። የከባድ መሳሪያው (መድፍ) ተኩስ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ርቀት ላይ በምትገኘው ሁመራ ከተማ ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እያነዘረ እንደሚገኝ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።
👉 የመከላከያ ሠራዊት እርምጃ፡ በበረከት እና ሸረሪና አቅጣጫ የተጀመረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረት ያንዣበበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከፈተበትን ይህንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ለመመከት እና ለመደምሰስ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል።
👉በድምፅ አልባ መሳሪያ (መሬት ላይ ሲደርስ ብቻ የሚፈነዳ መሳሪያ) በርካታ የአርሚ 70 ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል።
👉ታጣቂዎቹ ዛሬ ሁመራን ለመያዝ እቅድ እንደሰጣቸው ገልፀዋል።
👉ህወሓት በበኩሉ የፌደራል መንግስቱ ከበባ ሲፈፅም ከርሞ ዛሬ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በምዕራብ ትግራይ ተኩስ ከፍቶብናል ሲል መግለጫ አውጥቷል።

❤32😢9👍5🎉3👀1
የአከራይ ተከራይ ውል እድሳት እስከ ነሐሴ 30 ተራዘመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታውቆት የነበረውን የቤት ኪራይ ውል እድሳት እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 አራዝሟል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል፡፡

❤6🤪5👍4🥰1
ጦርነት ተከፍቶብናል:-ህወሓት‼️
"የትግራይ ህልውና በብልፅግና መቃብር ላይ ይወሰናል" በሚል ስብሰባ ሲያካሂድ የከረመው ህወሓት በምዕራብ ትግራይ ተኩስ ተከፍቶብናል ብሏል።
ሙሉ የመግለጫው ትርጉም👇👇
"የፌደራል መንግሥቱ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ሲያካሂድ የቆየውን ሁለንተናዊ ከበባ እና እገዳ፣ በድሮን እና በተላላኪ ታጣቂዎቹ ሲፈጽም የቆየውን ጥቃት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳው ጀምሮ በምዕራባዊ ትግራይ ዞን በሸረሪ አቅጣጫ ግልጽ ጦርነት ጀምሯል።
የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ በኋላ እንኳ የትግራይን ሕዝብ ለማንበርከክ እና ለመበታተን ካለው ከፍተኛ ፍላጎት ተነሥቶ የተለያዩ ከበባዎችን፣ እገዳዎችን እና ወታደራዊ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቶ፤ ድጋሚ ትግራይን ለመውረር እና ሕዝቡን ለማጥፋት ተነሳሽነት ወስዶ ጦርነት ከፍቶብናል።
ስለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ የትግራይ ሕዝብ፣ ሁላችሁም የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች፣ ብሔራዊ ኃይሎች እና የትግራይ ታጋዮች፣ የትግራይ ሲቪል ማኅበራት፣ የትግራይ ሃይማኖት ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ ብሔራዊ ህልውናችንን ለማረጋገጥ በሚደረገው ፍትሐዊ ትግል "ለብሔራዊ ጥፋት ፈጽሞ አንበረከክም! ብላችሁ ዛሬም እንደ ትናንቱ ተአምራዊ ታሪክ ለመሥራት እንድትዘጋጁ እያቀረብን፤ የተጀመረውን ድጋሚ ወረራ እና ጥፋት የሚመለከቱ የሁኔታዎች እድገት በየጊዜው በሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊው ማብራሪያ እና መግለጫ የሚሰጥበት መሆኑን እናስታውቃለን" ብሏል።

🤣20❤18👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሳዛኝ ነው‼️
በሸረሪና አቅጣጫ የህወሓት አርሚ 70 በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት በሜካናይዝድ ጦር የአፀፋ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።
አንድ የአርሚ 70 አባል 'ኑ ቁስለኛ እናንሳ' ሲል ይሰማል።
ጦርነት ይብቃ🕊🕊🕊

😢25❤12🕊11🙊4👍2🤪2😱1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
#ቢሾፍቱ‼️
አሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ 12.5 ቢሊዮን ዶላር የቢሾፍቱ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ደጅ እየጠናች ነው።
አሜሪካ በቢሾፍቱ እየተገነባ ባለው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየሰራች መሆኗን የአሜሪካ የንግድ መምሪያ ከፍተኛ ኃላፊ ማርክ ሚቼል ተናግረዋል።
ሚቼል እንዳሉት፣ ዋሽንግተን በፕሮጀክቱ ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲረጋገጥ " በቅርበት እየሰራች " ሲሆን፣ ይህም በአፍሪካ የመሠረተ ልማትና የኢንቨስትመንት ተፅዕኖ ለማሳደግ አሜሪካ ከቻይናና ከሌሎች ኃያላን ሀገራት ጋር እያደረገችው ያለው ፉክክር አካል መሆኑን አመልክተዋል።
እሳቸው ይህን ያሉት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም ወቅት በቪዲዮ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊዎችም ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
ሚቼል የአሜሪካ ኩባንያዎች በፕሮጀክቱ ውስጥ በትክክል ምን ዓይነት ሚና እንደሚኖራቸው በይፋ ባይገልጹም፣ ትብብሩ ወደፊት በGE Aerospace ሞተሮች የሚንቀሳቀሱ ተጨማሪ የቦይንግ አውሮፕላኖች ግዥ ሊያመራ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚያዝያ ወር ተጨማሪ 6 የቦይንግ 787-9 Dreamliner አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት የፈረመ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከታዘዡ 20 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነው።
ከወራት በፊት በቢሾፍቱ የተጀመረው እጅግ ግዙፉ ፕሮጀክት በ2030 ሲጠናቀቅ " የአፍሪካ ዱባይ " እንዲሆን ታቅዷል።
ከአበዳሪዎች አንዱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን ከጠቅላላው ወጪ 8.7 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ማሰባሰብ ሂደትንም እየመራ ነው።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት በፕሮጀክቱ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን መግለጻቸውን ተናግረው ነበር።
በተጨማሪም፥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኢንስቲትዩት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ሚቼል ገልጸው፣ ይህም የአሜሪካ የAI ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ አፍሪካ ገበያ እንዲስፋፋ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

❤24🤪9🙊4👍3😎1
“በብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች ገቢያቸው እጅግ ቀንሷል”ዳቪድ ማልፓስ
የቀድሞው የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዳቪድ ማልፓስ የኢትዮጵያ ብር መዳከም እና የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎች ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማባባሳቸውን በመግለጽ፤ በብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች «ገቢያቸው እጅግ ቀንሷል» ሲሉ ተናግረዋል።
በተቃራኒው ጥቂት ቡድኖች የውጭ ምንዛሬን እና የሀገር ውስጥ ብድርን በልዩ ሁኔታ ማግኘት በመቻላቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ማልፓስ፤ ስታንሊ ፊሸር መታሰቢያ በተሰኘ መድረክ ላይ ባቀረቡት የፖሊሲ ጥናት ላይ ኢትዮጵያን በዋና ምሳሌነት የተጠቀሙ ሲሆን፥ ሀገሪቱ የእርሻ መሬት፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውኃ፣ ተስማሚ የአየር ንብረት እና የሰው ኃይል አቅም ያላት በመሆኗ «ትልቅ የእድገት አቅም» ያላት ሀገር እንደሆነች ገልጸዋል።(AS)

👍22❤21😢5🙏1
የጦርነት ውጤት አስከፊ ነው‼️
ዛሬ በሸረሪና የተፈፀመው እልቂት ዘግናኝ ነው።
የህወሓት አርሚ 70 ታጣቂዎች በሸረሪና ግንባር ወደ ሁመራ ለመግባት ጥቃት የፈፀሙት ከታች የተዘረዘሩትን ሎጀስቲክ፣የሰው ሀይል እና መሳሪያ በመያዝ ነው።
- ዙ-23 03 በፓትሮል የተጫነ
- 107 ሮኬት 01
- ኮርኔት 02
- ሞርታር-120 01
- ሞርታር-82 01
- ሞርታር (ልዩ) 02 [በምርመራ ላይ ነው]
- ድሽቃ 09
- የድሽቃ ሆ/እግር 01
- RPG 06
- ብሬን 54
- ስናይፐር 05
- ክላሽ 1347
- ሬድዮ 183
- ኦራል 02
- ፓትሮል 02
- ጄኔሬተር 02
ይህንን ጥቃት ተከትሎ በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት በወሰደው የአፀፋ ጥቃት:-
- የተማረከ 01 ሻለቃ አዛዥ
- የተማረከ 141 ታጣቂ እና የተለያየ የአመራር
- የተገደለ እና የቆሰለ 1000+ መሆናቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች አረጋግጠዋል።
የተለያዩ ትጥቆች፣ የሕክምና ቁሳቁስ፣ ተተኳሾች፣ የደረት ትጥቆች፣ መድኃኒቶች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ነዳጅ ዘይትን ጨምሮ የጥይት ዴፖዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ሸረሪና እና አካባቢው ሙሉ ለሙሉ በመከላከያ ቁጥጥር ስር መሆኑ ተረጋግጧል። ተኩሱ ሙሉ ለሙሉ ቆሟል።
በዚሁ በቃ ይበለን።
Via : አዩዘሀበሻ

❤51💔18👍11🕊6✍3👀2🙈2😢1🙊1
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ያለው የክረምት ሁኔታ ከላይ በምስል የተያያዘውን ይመስላል፣ ምንም ዝናብ የለም።
የፓስፍክ ውቂያኖስ ሙቀት ባልተለመደ ሁነታ በመጨመሩ ምክንያት በሰሜን፣ በመካከለኛና ምስራቅ አከባቢ የዘንድሮው የክረምት ዝናብ አጭር መሆኑና ክረምቱም ቶሎ እንደሚወጣ የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ማስታወቁ አይዘነጋም።

💔13😢12👍4❤3🙊2
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ ከጠዋቱ 2፡30-8፡30
👉 ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒየም፣ ዓለም ባንክ 700 ማህበራት ቤቶች፣ ገላን እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 12፡00 - 4፡00
👉 በመቀሌ ቀበሌ 14፣ 15 ፣ 17 ፣ መቀሌ ተክላይማኖት እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡30-10፡00
👉 አዋሽ መልካሳ እና አከባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-7፡00
👉 በበህዳር ሪጅን አዲስ ዓለም፣ ኦቪድ ኮኒስትረክሽን፣ ሰማታት፣ ግዮን ት/ቤት፣ ሚሊኒየም ት/ቤት፣ ናይል ቪው ሆቴል እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

❤15👍2
#USA 🇺🇸 #VISA
አሜሪካ ለቪዛ የምትይዘውን ገንዘብ ወደ 20 ሺህ ዶላር ልታሳድግ ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የበርካታ አገራት ዜጎች ቪዛ ሲያመለክቱ ያስይዙት የነበረውን ገንዘብ ከ15 ሺህ ዶላር ወደ 20 ሺህ ዶላር (3.1 ሚሊዮን ብር በላይ) ከፍ በማድረግ ቋሚ ሊያደርግ ነው።
መሥሪያ ቤቱ እንደገለፀው መርሃ ግብሩ የቢዝነስ እና የቱሪስት (ቢ1 እና ቢ2) ቪዛ አመልካቾች ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው።
ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ አሜሪካ ውስጥ ከቆዩ ገንዘቡ ተመላሽ እንዳይሆን የሚያደርገው ይህ አሠራር ተግባራዊ ይሆንባቸዋል ከተባሉ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ከሆኑ 50 አገራት መካከል ፦
- #ኢትዮጵያ፣
- ጂቡቲ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሴኔጋል፣
- ኡጋንዳ፣
- ታንዛኒያ ይገኙበታል።
ይህ በቀናት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው የተሻሻለው ፕሮግራም፣ ከቪዛ ጊዜያቸው በላይ የሚቆዩ ጎብኝዎችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ መሠረት አመልካቾች እንደ ኤምባሲው ኦፊሰሮች ውሳኔ ለቪዛ እስከ 20 ሺህ ዶላር (ከ3.1 ሚሊዮን ብር በላይ) የሚደርስ ገንዘብ እንዲያስይዙ ሊጠይቁ ይችላሉ።
አሜሪካ ውስጥ ከቪዛ ጊዜያቸው በላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ዜጎች ባሏቸው አገራት እና የአገር ውስጥ ሰነዶች ላይ የላላ ቁጥጥር በሚያደርጉ አገራት የቪዛ ማስያዣ የሙከራ መርሃ ግብር ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ነበር።
መርሃ ግብሩ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የነበረ ሲሆን የተቀመጠለት ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው አዲሱ መመሪያ የወጣው።
በቀናት ውስጥ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለው ይህ አዲሱ የቪዛ ማስያዣ ገንዘብ ፕሮግራም ቋሚ እንደሚሆንም ተገልጿል።
በተጠናቀቀው የሙከራ መርሃ ግብር መሠረት አመልካቾች ከ5 ሺህ ፣ ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ዶላር ድረስ እንዲያስይዙ ይጠየቁ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ፕሮግራም አነስተኛው 5 ሺህ ዶላር ከዝርዝሩ ወጥቶ፣ ከፍተኛው የማስያዣ ገንዘብ ወደ 20 ሺህ ከፍ ተደርጓል።
በአዲሱ መርሃ ግብር ከተካተቱ 50 አገራት መካከል 30ዎቹ የሚገኙት በአፍሪካ ውስጥ ነው።

❤20🤪5😢3👍2
የሼክ መሐመድ አልአሙዲ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ፤ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር 375ኛ ደረጃን ያዙ
የትውልደ ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ሼክ መሐመድ አልአሙዲ የተጣራ ሀብት 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከትሎ በብሉምበርግ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ በድጋሚ ተካተዋል።
ዛሬ ኦገስት 1፣ 2026 ይፋ በሆነው የብሉምበርግ ዝርዝር መሠረት፣ አልአሙዲ በዓለም 375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በ2026 ብቻ የሀብታቸው መጠን በ1.67 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም በ19.7 በመቶ አድጓል። በቅርብ ጊዜም በአንድ ቀን ብቻ 33.7 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ተመዝግቧል።
የብሉምበርግ ግምገማ እንደሚያሳየው፣ የአልአሙዲ ሀብት መጨመር ከኢነርጂ፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከመሠረተ ልማት እና ከሌሎች የንግድ ንብረቶቻቸው ዋጋ መጨመር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ቀደም ከዋና ንብረቶቻቸው መካከል የነበረው የስዊድኑ ፕሪም (Preem) የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ ግን ለVARO Energy ከተላለፈ በኋላ በአሁኑ ጊዜ VAROPreem በተባለ የተዋሃደ ኩባንያ ስር ይገኛል።
በሌላ በኩል፣ ብሉምበርግ የአልአሙዲን ሀብት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደደረሰ ቢገልጽም፣ በፎርብስ 2026 ዓመታዊ የዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ግን ስማቸው አልተካተተም። ይህም ሁለቱ ተቋማት የቢሊየነሮችን ሀብት በሚገምቱበት የመረጃ ምንጭና የግምገማ ዘዴ ልዩነት መኖሩን ያሳያል።
በብሉምበርግ የወጣው አዲሱ መረጃ የሚያመለክተው፣ ሼክ መሐመድ አልአሙዲ ከቀደሙት ዓመታት የሀብት መቀነስ በኋላ በድጋሚ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሀብት ደረጃ መመለሳቸውን ነው።

❤25👍8🫡1
በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል።
ውጤት ለማየት 👇
https://amhara.ministry.et/#/result
አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡
በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇
@emacs_ministry_result_qmt_bot
የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ።
ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint
VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡
በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል።

❤8😢3👍2