አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው

‎አሁን ላይ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የኮንዶም ዕጥረት መኖሩም ተነስቷል።

‎ዕድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ሴቶች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል።

‎በአገራችን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሏል።

‎አሁን ላይ 7መቶ ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የተባለ ሲሆን፥ቁጥሩ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰምተናል።

‎ይህን የሰማነው የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ይህን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።

‎ኔፕ ፕላስ በኤችአይቪ ህመም ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፥ ምስረታው ወደ 22 ዓመት እየተጠጋው ነው።

‎በዚህ ኔትወርክ ስር የተቋቋሙ ከ5መቶ በላይ ማህበራትን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ፥ በዋናነት አሁን ላይ በንቃት የሚንቀሳቀሱት እና የግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ ማህበራት ቁጥር 1መቶ29 ነው።

‎የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ፥ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

‎ይህ ጉባዔ እየተዘነጋ ስላለው ነገርግን ዛሬም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው የኤችአይቪ ህመም ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥበት ነው።

‎ድርጅቱ ለሁለት ጊዜ ያህል "Stigma index research" ማሰራቱን ገልጾ፥ ሶስተኛ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍7😢2👀2
6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን ተወለደች

‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።

‎በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።

‎ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7😱3🥰1💯1
"ህወሓት ውጊያ‼️ ከጀመረ ውጊያውን የሚመራው አስመራ ሆኖ እንጂ መቀሌ ሆኖ ውጊያውን መምራት እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጄኔራል ባጨ ደበሌ ለአንድ ሚዲያ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3920👍7🤪6🥰3😡2🙈1
ጅቡቲ፣ በባብኤል መንደብ ሠርጥ ላይ በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች በተናጥል ቀረጥ ለመጣል የሚደረጉ ሙከራዎች በዓለማቀፍ የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ በማለት አስጠነቀቀች።

የባብኤል መንደብ መተላለፊያ ለዓለም የንግድ መርከቦች ሁሉ ክፍት መሆን አለበት በማለት ጅቡቲ አቋሟን ገልጣለች።

አንድ የቀጠናው ኃይል ብቻውን በመርከቦች ላይ የማለፊያ ቀረጥ ከጣለ፣ የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፋ፣ "ተቀባይነት የሌለው" እና የዓለም የንግድና የኢነርጂ ዝውውርን የሚጎዳ ድርጊት ይሆናል ስትል ጅቡቲ አስጠንቅቃለች።

የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነትንና ሉዓላዊ መብቷን ለማስከበር በተናጥልም ይኹን ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር "ዲፕሎማሲያዊ"፣ "ሕጋዊ" እና "የጸጥታ" አማራጮችን እንደምትከተል ያስታወቀችው ጅቡቲ፣ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ባብኤል መንደብ ክፍት ኾኖ መቀጥሉን እንዲያረጋግጥም ጠይቃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95
ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል!

የኢጋድ ሊቀመንበሩ ጉዞ የሱዳኑን አስከፊ ጦርነት በድርደር ለመቋጨት ያለመ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ባሁኑ ወቅት የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እየተለጠጠ እና በኢትዮጵያ ካለው የአገር ውስጥ ግጭት ጋር ተያይዞ እየተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪269👍2😡2
መቐለ ለመግባት ዝግጁ ነን‼️
እራሱን 'የትግራይ የሰላም ሀይል' ብሎ ያደራጀው ታጣቂ ቡድን ትሕነግን ከመቀሌ በማስወጣት ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አጠቃላይ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቡድኑ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ።

በቀድሞ የትሕነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በወዲ አንጥሮ፣ በጀነራል ጉዕሽ ገብረ እና በጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራው ይህ የሰላም ሀይል፣ መቀሌ መሽጎ የትግራይን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የትሕነግ ስብስብ ጠራርጎ በማስወጣት ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማረጋገጥ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አዛዡ አስታውቀዋል።

ወታደራዊ አዛዡ እስካሁን ባለው መረጃ በማንኛውም ሰዓት የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ መወጣት የሚችሉ በርካታ ታጣቂዎች ትሕነግን በመክዳት ወደ ሓራ መሬት በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ የትሕነግን መዋቅር ከውስጥም ከውጭም በቀላሉ በጣጥሶ ለመጣል እና ቡድኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትግራይ ምድር ለማስወገድ ምቹ መደላደል የሚፈጥር መሆኑንም አዛዡ አክለው ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤣19👍8
አሐዱ ራዲዮ እና አርትስ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለቱ ሚዲያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቋል።

አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና አርትስ ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው፣ "ውል የገቡበትን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው" ነው ተብሏል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር "ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች" መፈጸማቸውን በተመለከተ፣ ወይይት ቢደረግም "ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ" ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪10👍4🤔3🤷‍♂2
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!!

​በኦሮሚያ ክልል የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 08 - 09/2018 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

👉 የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

👉 ፈተናውን ከተቀመጡ 517,209 ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ (50% እና ከዚያ በላይ) በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል የተሸጋገሩት 464,839 (89.9%) ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል።

​ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል፡
📍 ወንድ 267,307 ውስጥ 91.2% እና
📍 ሴት 249,902 ውስጥ 88.4% አልፈዋል።

​በዚሁ መሠረት ውጤት ለማየት ከዚህ በታች የቀረበውን ሊንክ በመክፈት፤ የመፈተኛ ቁጥርዎን (Registration Number) ማስገባት፤
ቀጥሎም የመጀመሪያ ስምዎን በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ትችላላችሁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍4
አፈሳና ጦርነት የሰጉ የትግራይ ተማሪዎች አሁንም "ግቢ" ናቸው!

አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን በመስጋት ወደትግራይ ክልል መመለስ ያልቻሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ክረምቱን በግቢው ውስጥ ለማሳለፍ ፍቃድ ማግኘታቸውን ዋዜማ ሰምታለች፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች፣ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ስጋት ምክንያት ወደ ክልላቸው መመለስ ባለመቻላቸው፤ ክረምቱን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንዲያሳልፉ ተፈቅዶላቸዋል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች እንደገለጹት፤ ጥያቄው መጀመሪያ ላይ በዩኒቨርሲቲው በኩል ተቀባይነት አጥቶ ለሳምንታት የቆየ ቢሆንም፤ ከጊዜያት በኋላ ግን በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መፍትሔ ሊያገኝ ችሏል።

Via Wazema

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2610👀1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ በረራ ይጀምራል‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ወደ ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ይጀመራል አለ፡፡

በዚህም መሰረት ዘወትር ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ እንዲሁም ዘወትር ሰኞ ከሁመራ ወደ ጎንደር የበረራ አገልግሎት ይሰጣል።

የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎችን በማስፋት ሕዝብን ለማገልገል እንደሚራ የገለጸው አየር መንገዱ ይህ የበረራ አገልግሎት መጀመር ማኅበራዊ ግንኙነትን ከፍ ያደርጋል ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍108
ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ ታሰረ።

የ"እግረኛው ሚዲያ" መስራችና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የታወቀ ሲሆን፤ ለእስሩ ምክንያት ከመከላከያ ሰራዊት አልባሳት (ዩኒፎርም) ጋር ተያይዞ ከቀረበው ዘገባ ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ጉርሻ page
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2011😱2😢1😍1🙊1
በግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪና የምዝገባ አሰራር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡- የአዲስ አበባ ትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን

በ2019 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን በግል ትምህርት ቤቶች በሚካሄደው የተማሪዎች ምዝገባ፣ የክፍያ ጭማሪና የግብዓት ጥያቄ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ::

ባለፉት ዓመታት የግል ትምህርት ቤቶች በወርሃዊ ክፍያ፣ በምዝገባ፣ በዩኒፎርም እንዲሁም በዓይነት በሚጠይቋቸው እንደ ሳሙና እና ሶፍት ባሉ ቁሳቁሶች ምክንያት በወላጆች ዘንድ ሰፊ ቅሬታ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣85👍3👌2
በ8 ዕዝ ተከበናል:-ሞንጆሪኖ‼️
የህወሓት ስራ አፈፃሚ እና የፅህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር "ባለፉት አራት ዓመታት የህዝባችንን ጉዳዮች በሰላም ለመፍታት ቀን ከሌት እየሞከርን ነበር፣ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያሳወቅን ነበር ነገር ግን እኛን የሚሰማንን ሰው አላገኘንም" ብለዋል።
ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የቻልነውን ሁሉ አድርገናል አሁን ላይ ግን ጉዳዩን በወታደራዊ ሀይል ለመፍታት መደምደሚያ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
የፌደራል መንግስቱም በተለያዩ አቅጣጫዎች በ8 ዕዝ ሰራዊት ከቦናል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪19👍127🤯2🤔1🤣1👀1🙊1
አበባየሁ ደሜ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

“የሀገር መከላከያ ሰራዊት አልባሳት በመጠቀም በየማህበራዊ ሚዲያው አላስፈላጊ መልእክቶችን እንዲሁም የአንድነትና የፍቅር ሀሳብ ከማስተላለፍ ይልቅ የመከፋፈል ንግግሮችን ሲያሰራጭ
ነበረ” የተባለው አበባየሁ ደሜ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

አበባየሁ ደሜ ዛሬ ከሰአት አካባቢ ሜክሲኮ ኬ ኬር ህንፃ ወረድ ብሎ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዱ ተረግጧል።

ግለሰቡ በሀገር ጥበቃ እና ክብር መገለጫ በሆነው የመከላከያ አልባሳት በየሚዲያው እየቀረበ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታን እና እርስ በእርስ የመከፋፈል ስሜትን ሲፈጥር መቆየቱ ተዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣15👍147👌1🙊1
አሊኮ ዳንጎቴ ከሃብታቸው ሲሶውን ለበጎ አድራጎት ድርጅት ሊያውሉት ነው።

የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ፣ ከሀብታቸው ውስጥ አንድ ሦስተኛውን (35 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ) ኃብታቸውን ለበጎ አድራጎት ሥራዎች ሊለግሱ መሆኑ ተገልጿል።

ልጃቸው ፋጢማ ዳንጎቴ በቅርቡ ከብሉምበርግ ጋር በነበራት ቃለ-መጠይቅ ድጋፉን በስማቸው በተቋቋመው ፋውንዴሽን በኩል ለበጎ አድራጎት ሥራዎች እንደሚያውሉት ይፋ አድርጋለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31👍14👀2🥰1👌1🤝1🙉1
መረጃ‼️

በሳዑዲ ዓረቢያ አስተባባሪነት፣ 14 አገራት በቀይ ባሕር፣ ባብኤል መንደብና የኤደን ባሕረ ሠላጤ የንግድና የኢነርጂ አቅርቦት መስመር ደኅንነትን የሚያስጠበቅ ጥምር የመከላከያ ኃይል አቋቋሙ።

ጥምረቱ፣ አባል አገራት መረጃ እንዲለዋወጡ፣ የዘመቻ እቅድ እንዲያወጡና የጋራ የባሕር ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።

ከአፍሪካ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ግብጽ እና ናይጀሪያ የጥምረቱ መስራቾች ኾነዋል። 

ከሌሎች መስራቾች መካከል ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር፣ ቱርክ እና ፓኪስታን ይገኙበታል።

ፍላጎቱ ያላቸው አገራት ጥምረቱን በማንኛውም ጊዜ መቀላቀል ይችላሉ ተብሏል።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ እና ኢምሬቶች በጥምረቱ መስራችነት ካልተካተቱ የቀጠናው አገራት መካከል ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣1110👍2
#USA #Immigration

በአሜሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎች ያለ ቃለ-መጠይቅ ወደ ፍርድ ቤት የሚላኩበት መመሪያ ጸደቀ።

የትራምፕ አስተዳደር በሀገሪቱ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞችን የሚመለከት አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

ይህን ተከትሎ በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው ሳይሰማ ቀጥታ ሊባረሩ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

አዲሱ አሰራር ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የተከማቹ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ለማቃለል የታሰበ ነው ተብሏል።

ቀደም ሲል የነበረው አሰራር አመልካቾች መጀመሪያ ጉዳያቸውን ለኢሚግሬሽን ኦፊሰር አቅርበው ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገ ብቻ ወደ ፍርድ ቤት እንዲመሩ የሚያደርግ ነበር።

በአዲሱ መመሪያ በርካታ የጥገኝነት አመልካቾች ከኢሚግሬሽን ኦፊሰሮች ጋር የሚደረገውን የመጀመሪያ ደረጃ ቃለ-መጠይቅ ሳያደርጉ ጉዳያቸው በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤት ሊመራ ይችላል።

444,724 ያህል መዝገቦችን ይነካል የተባለው ይህ ውሳኔ የሕግ ባለሙያዎችና የኢሚግሬሽን ተከራካሪዎች አሰራሩ የስደተኞችን የመሰማትና የፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳና ውሳኔዎችን በማፋጠን ሰዎችን በፍጥነት ለማባረር ያለመ ነው በማለት ተችተውታል።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ መንግሥት በሀገሪቱ በሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች ላይ እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ አዲስ ክፍያ ለመጣል ማቀዱ ተሰምቷል።

የታቀደው እርምጃ በተለይ ትምህርታቸውን አጠናቀው በአሜሪካ ለመቆየት ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

መንግሥት እርምጃው የቪዛ አጠቃቀምን ለማጥበቅና የሀገር ውስጥ የሥራ ገበያን ለመጠበቅ ያለመ መሆኑን ሲገልጽ፣ ተቃዋሚዎች ግን የውጭ ተማሪዎች ለአሜሪካ የትምህርትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን አስተዋፅኦ ሊጎዳ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ከስደተኞች ጋር በተያያዝ እጅግ ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተደጋግሞ መገለጹ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14👍2🤪2
ሰበር ዜና

በኢትዮ ሱዳን ድንበር መጠነ ሰፊ ውጊያ ተከፈተ፡፡

ውጊያ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ ከበረኸት እስከ ሸረሪና የከባድ መሳሪያ ድምጽ በስፋት እንደሚሰማ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
14😢8👍7🎉2🤪2