አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
በግብፅ ወደብ ላይ የአሜሪካ ንብረት በሆነ የጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼️

በግብፅ የሜዲተራኒያን ወደብ በሆነው ዳሚየታ በሚገኝ የአሜሪካ ንብረት በሆነ ፈሳሽ ጋዝ የሚቀይርና የሚያከማች መርከብ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የእሳት መከሰቱንና በኋላም እሳቱ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ መርከብ መሸጋገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

የብሪታኒያው የባህር ላይ ደህንነት ተቋም አምብሬይ የመጀመሪያ ደረጃ ምዘና እና የደህንነትና የንግድ መረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ 'ኤነርጎስ ዊንተር' (Energos Winter) የተባለችው መርከብ የቀኝ ጎኗ በድሮን ጥቃቱ ተመቷል። 

በመቀጠልም እሳቱ በወደቡ ላይ ወደነበረችው 'ጋስሎግ ሳሌም' (Gaslog Salem) ወደተባለች ሌላ የጋዝ መርከብ ተዛምቷል።

በግምት 138,250 ኩቢክ ሜትር የማከማቸት አቅም ያላት 'ኤነርጎስ ዊንተር'፣ መቀመጫው አሜሪካ ለሆነው 'ኤነርጎስ ኢንፍራስትራክቸር' የተባለ ኩባንያ ንብረት ስትሆን፤ የቴክኒክ፣ የደህንነት እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የሚመሩት ደግሞ በ'ቪልሄልምሰን ሺፕ ማኔጅመንት' ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9🤔1
የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪው ከሀድያና ከንባታ ዞኖች ወጣቶችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሳቸው በማታለል ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይቀበል ነበር።

ተጎጂዎችን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በማሻገር፣ በጫካ ውስጥ በድብቅ ያቆያቸው፣ በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ ብቻ ትንሽ ሩዝና ቁራጭ ዳቦ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና ጥም ይዳርጋቸው ነበር። በተጨማሪም በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ ያስገድዳቸው ነበር።

ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ አጉሮ ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስገድዳቸው ነበር። ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ ይደበድባቸው፣ "እዚሁ ትሞታላችሁ" በማለት ያስፈራራቸው እንዲሁም በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃያቸው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።

ከዚያም ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮችና በተሸፈኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ታንዛኒያ በማጓጓዝ በጫካ ውስጥ ጥሎ ይተዋቸው እንደነበር ተገልጿል።

በዚህ ምክንያትም ብዙ ተጎጂዎች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በየመንገዱ በፖሊስ ተይዘው እስር ቤት መግባታቸውንና በኋላም ገንዘብ ከፍለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ፖሊስ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ክትትል በማላዊ ተይዞ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8
ግብጾች የአባይን ውሃ ስለሚጠቀሙ ለኢትዮጵያ ሊከፍሉን ይገባል ዶክተር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ ግብፅ የአባይን ውኃ በነፃ እየተጠቀመች አገሯን እያለማች በመሆኗ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ክፍያ ልትፈጽም እንደሚገባ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በቆይታቸው እንደጠቆሙት፤ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት—በተለይም በግብፅ ላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች።

ሆኖም አገራቱ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ያለምንም ክፍያ በመጠቀም አገራቸውን እያለሙ በመሆናቸው፣ ለሚጠቀሙበት ውኃ ለኢትዮጵያ ክፍያ ሊፈጽሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31🤣19👍10😎3💯2👀1🤪1
የ«ሁሉ ስፖርት» የፈቃድ ስረዛ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሻረ፤ አገልግሎቱ ግን አሁንም ታግዷል

​የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና የገቢዎች ሚኒስቴር በ«ሁሉ ስፖርት» ላይ አስተላልፈውት የነበረውን የንግድ ፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሻረ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው ተቋማቱ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግን ሳይከተሉ እና የተቋሙን የመሰማት መብት ጥሰው ፈቃድ መሰረዛቸውን በመግለፅ ነው።

​መንግሥት ድርጅቶቹ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ሰውረዋል ቢልም፣ ፍርድ ቤቱ ይህ በወንጀል ሕግ የሚታይ እንጂ በደፈናው ለአስተዳደራዊ ፈቃድ ስረዛ ምክንያት ሊሆን አይችልም ብሏል።

​ሆኖም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በውሳኔው ላይ ይግባኝ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አፈጻጸም ከሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት እንዲታገድ ተደርጓል።

በመሆኑም ጉዳዩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ «ሁሉ ስፖርት» ወደ ሥራ አይመለስም።
​ይህ በእንዲህ እንዳለ የሎተሪ አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ምንም ዓይነት የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ድርጅት እንደሌለ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
📱 አንድን አይፎን 17 ፕሮ ገዝቶ ለመያዝ በስዊዘርላንድ 3 የሥራ ቀናት ብቻ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
 
አዲሱ አይፎን 17 ፕሮ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሚሸጥበት የገንዘብ መጠን በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ግለሰብ ይህንኑ ስልክ ገዝቶ ለመያዝ የሚያወጣው የሥራ ጊዜና ድካም ግን እጅግ የተራራቁ የኢኮኖሚ እውነታዎችን ያንፀባርቃል ተብሏል።
 
ይህን የገቢና የኢኮኖሚ ልዩነት በግልጽ በሚያሳየው መረጃ መሠረት፣ በስዊዘርላንድ የሚኖር አንድ ሠራተኛ አዲሱን አይፎን 17 ፕሮ ለመግዛት 3 የሥራ ቀናት ብቻ የሚያስፈልጉት ሲሆን፣ በፊሊፒንስ 101 የሥራ ቀናት፣ በሕንድ 160 የሥራ ቀናት፣ እንዲሁም በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ 540 የሥራ ቀናት ሙሉ መሥራት ይጠይቃል ነው የተባለው።
 
አንድ አይነት ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይ የገበያ ዋጋ፤ ነገር ግን እጅግ የተራራቁ የሰዎች የኑሮ እውነታዎች! ይህ ንጽጽር አይፎን በዓለማችን ላይ ያለውን የገቢና የኢኮኖሚ እኩልነት ማጣትን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ መሆኑን እና አንድ ሰው የተወለደበት ወይም የሚኖርበት ሀገር የሚገዛቸውን ዕቃዎች የመወሰን አቅሙ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤣15👍4😢2
ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው

‎አሁን ላይ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የኮንዶም ዕጥረት መኖሩም ተነስቷል።

‎ዕድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ሴቶች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል።

‎በአገራችን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሏል።

‎አሁን ላይ 7መቶ ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የተባለ ሲሆን፥ቁጥሩ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰምተናል።

‎ይህን የሰማነው የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ይህን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።

‎ኔፕ ፕላስ በኤችአይቪ ህመም ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፥ ምስረታው ወደ 22 ዓመት እየተጠጋው ነው።

‎በዚህ ኔትወርክ ስር የተቋቋሙ ከ5መቶ በላይ ማህበራትን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ፥ በዋናነት አሁን ላይ በንቃት የሚንቀሳቀሱት እና የግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ ማህበራት ቁጥር 1መቶ29 ነው።

‎የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ፥ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

‎ይህ ጉባዔ እየተዘነጋ ስላለው ነገርግን ዛሬም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው የኤችአይቪ ህመም ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥበት ነው።

‎ድርጅቱ ለሁለት ጊዜ ያህል "Stigma index research" ማሰራቱን ገልጾ፥ ሶስተኛ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍7😢2👀2
6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን ተወለደች

‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።

‎በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።

‎ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7😱3🥰1💯1
"ህወሓት ውጊያ‼️ ከጀመረ ውጊያውን የሚመራው አስመራ ሆኖ እንጂ መቀሌ ሆኖ ውጊያውን መምራት እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጄኔራል ባጨ ደበሌ ለአንድ ሚዲያ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3920👍7🤪6🥰3😡2🙈1
ጅቡቲ፣ በባብኤል መንደብ ሠርጥ ላይ በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች በተናጥል ቀረጥ ለመጣል የሚደረጉ ሙከራዎች በዓለማቀፍ የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነት ላይ አደጋ ይደቅናሉ በማለት አስጠነቀቀች።

የባብኤል መንደብ መተላለፊያ ለዓለም የንግድ መርከቦች ሁሉ ክፍት መሆን አለበት በማለት ጅቡቲ አቋሟን ገልጣለች።

አንድ የቀጠናው ኃይል ብቻውን በመርከቦች ላይ የማለፊያ ቀረጥ ከጣለ፣ የጎረቤት አገራትን ሉዓላዊነት የሚጋፋ፣ "ተቀባይነት የሌለው" እና የዓለም የንግድና የኢነርጂ ዝውውርን የሚጎዳ ድርጊት ይሆናል ስትል ጅቡቲ አስጠንቅቃለች።

የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነትንና ሉዓላዊ መብቷን ለማስከበር በተናጥልም ይኹን ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር "ዲፕሎማሲያዊ"፣ "ሕጋዊ" እና "የጸጥታ" አማራጮችን እንደምትከተል ያስታወቀችው ጅቡቲ፣ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ባብኤል መንደብ ክፍት ኾኖ መቀጥሉን እንዲያረጋግጥም ጠይቃለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍95
ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል!

የኢጋድ ሊቀመንበሩ ጉዞ የሱዳኑን አስከፊ ጦርነት በድርደር ለመቋጨት ያለመ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡ ባሁኑ ወቅት የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እየተለጠጠ እና በኢትዮጵያ ካለው የአገር ውስጥ ግጭት ጋር ተያይዞ እየተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤪269👍2😡2
መቐለ ለመግባት ዝግጁ ነን‼️
እራሱን 'የትግራይ የሰላም ሀይል' ብሎ ያደራጀው ታጣቂ ቡድን ትሕነግን ከመቀሌ በማስወጣት ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን አጠቃላይ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቡድኑ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ።

በቀድሞ የትሕነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በወዲ አንጥሮ፣ በጀነራል ጉዕሽ ገብረ እና በጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራው ይህ የሰላም ሀይል፣ መቀሌ መሽጎ የትግራይን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የትሕነግ ስብስብ ጠራርጎ በማስወጣት ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማረጋገጥ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አዛዡ አስታውቀዋል።

ወታደራዊ አዛዡ እስካሁን ባለው መረጃ በማንኛውም ሰዓት የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ መወጣት የሚችሉ በርካታ ታጣቂዎች ትሕነግን በመክዳት ወደ ሓራ መሬት በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ የትሕነግን መዋቅር ከውስጥም ከውጭም በቀላሉ በጣጥሶ ለመጣል እና ቡድኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትግራይ ምድር ለማስወገድ ምቹ መደላደል የሚፈጥር መሆኑንም አዛዡ አክለው ገልጸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19🤣19👍8
አሐዱ ራዲዮ እና አርትስ ቲቪ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለሁለቱ ሚዲያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስታውቋል።

አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና አርትስ ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው፣ "ውል የገቡበትን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው" ነው ተብሏል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር "ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች" መፈጸማቸውን በተመለከተ፣ ወይይት ቢደረግም "ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ" ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
10🤪10👍4🤔3🤷‍♂2
የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!!

​በኦሮሚያ ክልል የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ሰኔ 08 - 09/2018 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

👉 የማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

👉 ፈተናውን ከተቀመጡ 517,209 ተማሪዎች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ (50% እና ከዚያ በላይ) በማስመዝገብ ወደ ሚቀጥለው ክፍል የተሸጋገሩት 464,839 (89.9%) ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል።

​ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል፡
📍 ወንድ 267,307 ውስጥ 91.2% እና
📍 ሴት 249,902 ውስጥ 88.4% አልፈዋል።

​በዚሁ መሠረት ውጤት ለማየት ከዚህ በታች የቀረበውን ሊንክ በመክፈት፤ የመፈተኛ ቁጥርዎን (Registration Number) ማስገባት፤
ቀጥሎም የመጀመሪያ ስምዎን በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ትችላላችሁ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍4
አፈሳና ጦርነት የሰጉ የትግራይ ተማሪዎች አሁንም "ግቢ" ናቸው!

አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላን በመስጋት ወደትግራይ ክልል መመለስ ያልቻሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ክረምቱን በግቢው ውስጥ ለማሳለፍ ፍቃድ ማግኘታቸውን ዋዜማ ሰምታለች፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች፣ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እና አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ስጋት ምክንያት ወደ ክልላቸው መመለስ ባለመቻላቸው፤ ክረምቱን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንዲያሳልፉ ተፈቅዶላቸዋል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ተማሪዎች እንደገለጹት፤ ጥያቄው መጀመሪያ ላይ በዩኒቨርሲቲው በኩል ተቀባይነት አጥቶ ለሳምንታት የቆየ ቢሆንም፤ ከጊዜያት በኋላ ግን በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ መፍትሔ ሊያገኝ ችሏል።

Via Wazema

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2610👀1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ በረራ ይጀምራል‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ወደ ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ይጀመራል አለ፡፡

በዚህም መሰረት ዘወትር ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ እንዲሁም ዘወትር ሰኞ ከሁመራ ወደ ጎንደር የበረራ አገልግሎት ይሰጣል።

የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎችን በማስፋት ሕዝብን ለማገልገል እንደሚራ የገለጸው አየር መንገዱ ይህ የበረራ አገልግሎት መጀመር ማኅበራዊ ግንኙነትን ከፍ ያደርጋል ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍108
ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ ታሰረ።

የ"እግረኛው ሚዲያ" መስራችና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሆነ የታወቀ ሲሆን፤ ለእስሩ ምክንያት ከመከላከያ ሰራዊት አልባሳት (ዩኒፎርም) ጋር ተያይዞ ከቀረበው ዘገባ ጋር ሳይያያዝ እንዳልቀረ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

ጉርሻ page
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍2011😱2😢1😍1🙊1
በግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ጭማሪና የምዝገባ አሰራር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡- የአዲስ አበባ ትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን

በ2019 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን በግል ትምህርት ቤቶች በሚካሄደው የተማሪዎች ምዝገባ፣ የክፍያ ጭማሪና የግብዓት ጥያቄ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ::

ባለፉት ዓመታት የግል ትምህርት ቤቶች በወርሃዊ ክፍያ፣ በምዝገባ፣ በዩኒፎርም እንዲሁም በዓይነት በሚጠይቋቸው እንደ ሳሙና እና ሶፍት ባሉ ቁሳቁሶች ምክንያት በወላጆች ዘንድ ሰፊ ቅሬታ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣85👍3👌2