አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
419 videos
22 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
#በኦሮሚያ እና #በሲዳማ አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወት ሲያልፍ፤ ትምህርት ቤት እና የሰብል ምርቶች ወደሙ
√.ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያው ጊርጃ ወረዳ ጉቦ ሄማ ቀበሌ እና በምሥራቅ ሲዳማ ዞን ጭሪ ቀበሌ መካከል ባገረሸው ግጭት የ10 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ቆስለዋል፤ እንዲሁም በበርካታ ቀበሌዎች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ሲሉ በሁለቱም ወገን ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ግጭት በአካባቢው ላይ የነበረውን መረጋጋት በእጅጉ ማደፍረሱን ገልጸዋል።

√.የምሥራቅ ጉጂ ዞን የጊርጃ ወረዳ ነዋሪ፤ በአጠቃላይ በጉጂ በኩል ጊርጃ ወረዳ ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች ሲገደሉ፣ ወደ 40 የሚጠጉ ደግሞ ቆስለው በአዶላ፣ ቦሬ፣ ኩያራ፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ እና አዲስ አበባ በሚገኙ ህክምና ተቋማት በመታከም ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

√. በተጨማሪም በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና የጉቦ ሄማ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወድመሏ ነው የተባለው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🕊63👍3
በርካታ አካባቢዎች መብራት ይቋረጣል‼️
የጥገና ሥራ ምክንያት ነገ በበርካታ አካባቢዎች የመብራት አቅርቦት ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ሥራ ለማከናወን ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰነ ሰዓት እንደሚቋረጥ አስታውቋል።

ከጠዋቱ 4፡00 – 10፡00

• ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ፣ አርበኞች ት/ቤት እና አካባቢያቸው።
• ዕንቁላል ፋብሪካ፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል እና አካባቢያቸው።
• 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ፣ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፣ አትክልት ተራ፣ ጣሊያን ሰፈር፣ ፒያሳ (በከፊል)፣ ማዘጋጃ ቤት፣ አውቶብስ ተራ እና አካባቢያቸው።
• ማርቆስ መጋዘን፣ ቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ፣ ቀጨኔ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ መንገድ፣ ይመር ውኃ፣ መቀጠያ፣ 19 ታቦት ማደሪያ፣ መታፈሪ ሰፈር፣ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ ሽሮ ሜዳ እና አካባቢያቸው።

ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00

• አያት ለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊትለፊት ያሉ ኮንዶሚኒየሞች፣ ክቡርደመና፣ ሰላም ቪሌጅ፣ ጣፎ ገብርኤል፣ ጋሪ ተራ፣ ባጃጅ ተራ እና አካባቢያቸው።

ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡30

• ገላን፣ አራብሳ፣ እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ፕሮጀክት 13 አራብሳ ወታደር ሰፈር፣ ነጋ ቦንገር፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ ቆዳ ፋብሪካ፣ ፓስታና መኮረኒ ፋብሪካ እና አካባቢያቸው።
• አባ ሳሙኤል፣ አቡሴራ፣ ሉግና፣ ዱፍና፣ ደበራ ጢኖ፣ ሻሸመኔ፣ ዱከም፣ በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ካፍ ማደያ እና አካባቢያቸው።

ከጠዋቱ 4፡30 – 11፡00

• መቐለ (ላቺ በከፊል)፣ ሀምዲያ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ቀበሌ 03፣ ባህርዳር (አዲስ ዓለም)፣ ኦቪድ፣ ሰማኤታ፣ ሚሊኒየም ት/ቤት እና አካባቢያቸው።

ከጠዋቱ 1፡00 – 6፡00

• ወልዲያ፣ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቢልባላ፣ ቂርቆስ፣ ሳሬዜና፣ ሶርባ፣ ላሊበላ፣ ገነተ ማርያም፣ ዘሃ፣ ሙቅ ውኃ፣ ተከዜ ገዳሜ፣ ኢርፋ ገለሶቴ እና አካባቢያቸው።
• ቅዱስ አርቢ፣ ዳቦ ከተማ፣ ቡርኮ፣ አይና ሚካኤል፣ ጭሮ፣ ሜኤሶ፣ አሰቦት እና አካባቢያቸው።
በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞች የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ እና የኃይል አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍3🤔1😢1👀1
ኤርትራ የአየር መንገዱን ገንዘብ አልመለሰችም‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የታገደበት ገንዘብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የፖለቲካ ውጥረት እና የነበረው የህግ ሂደት በመቋረጡ ምክንያት ምንም ማድረግ እንዳልተቻለና እስካሁን መፍትሔ ሳያገኝ እንደቀረ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገለጹ።

“አሁን ላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ጤናማ አይደለም፤ በዚህ ምክንያት ምንም ዓይነት ሂደት የለም፣ ጉዳዩ ስታክ እንዳደረገ (ባለበት እንደቆመ) ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በጊዜው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት የነበረ ቢሆንም “ፖለቲካዊ ውሳኔ በመደረጉ ፍርድ ቤቱ መንቀሳቀስ አልቻለም” ብለዋል። በመሆኑም ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ድረስ ለመጠበቅ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ገንዘቡ በኤርትራ ባንክ እንደሚገኝ ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የበረራ መቋረጡም ሆነ የገንዘብ ዝውውሩ መገታት ከፖለቲካዊ ሁኔታዎች ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል። አየር መንገዱ በተለያዩ ሀገራት ገንዘቦቹ እንደተያዙበት ያነሱ ሲሆን፣ በርካታ ገንዘብ በሩሲያ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህንንም ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በኤርትራ ያለለወው ገንዘብ ግን እስካሁን ባለበት እንደተያዘ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13🙊3👍2🤪21
የአበል አፈፃፀም መመሪያ‼️
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ እና በቅዳሜ ቀናት ለሚሰሩ ሠራተኞች የትራንስፖርት አበል አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል።

በመመሪያው መሠረት በቅዳሜ ቀን ለሚሰሩ ሠራተኞች በቀን 200 ብር (በወር 800 ብር) እንዲሁም በምሽት ለሚሰሩ የትራንስፖርት መመለሻ በቀን 100 ብር (በወር 2,200 ብር) ተመድቧል። በዚህም መሠረት አንድ ሠራተኛ በወር እስከ 3,000 ብር የትራንስፖርት አበል ማግኘት ይችላል።

የትራንስፖርት አበል የሚከፈለው ከመደበኛ ሰዓት በኋላ አገልግሎት ለሚሰጡ ሠራተኞች፤ በቅዳሜ ቀናት በተፈቀደ የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት ለሚሰሩ ሠራተኞች ብቻ ነው።

- በረዥም ጊዜ ሥልጠና ወይም ትምህርት ላይ ለሚገኝ ሠራተኛ፤
- በተፈቀደው የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት በሥራ ላይ ላልተገኘ ሠራተኛ፤
- ተቋሙ የጋራ ወይም በተናጥል ትራንስፖርት አገልግሎት ላቀረበለት ሠራተኛ እና በተመሳሳይ ዓላማ ከሌላ ምንጭ የመጓጓዣ ድጋፍ የሚያገኝ ሠራተኛ የዚህ ትራንስፖርት አበል ተጠቃሚ አይሆንም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍2🥰1🤔1👌1
ለሚያገቡ 6 ሚሊዮን ብር ‼️
ደቡብ ኮሪያ የወሊድ ምጣኔን ለማሳደግ ሰዎች ወደ ጋብቻ እንዲገቡ እና እንዲወልዱ ለማበረታታት $38,000 ወይም 6 ሚሊዮን ብር ለማበረታቻ እየሰጠች መሆኑ ተሰምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
29🤣15👍10🥱4🤯1
ዓለማቀፉ የፍልሠት ድርጅት፣ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ እስያ አገራት የበይነ መረብ የማጭበርበሪያ ካምፖች ተጠቂ የመሆናቸው ክስተት በመጨመር ላይ ይገኛል ሲል አስጠነቀቀ።

በበይነ መረብ የማጭበርበር ድርጊቶች ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የውጭ ዜጎች፣ ድብደባና ጾታዊ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸውና ለርሃብ እንደሚጋለጡ ድርጅቱ ገልጧል።

ከአውሮፓዊያኑ 2022 እስከ 2025 ከ3 ሺሕ 500 በላይ የ39 አገራት ዜጎች በደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት በበይነ መረብ የወንጀል ድርጅቶች በግዳጅ ተይዘው ነበር ተብሏል።

አብዛኞቹ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ባንግላዴሽ፣ ስሪላንካ፣ ሕንድ እና ኢንዶኔዥያ ዜጎች እንደኾኑ ድርጅቱ ጠቅሷል።

ድርጅቱ፣ በማጭበርበር ተግባራት ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎችን መንግሥታት እንደ ወንጀለኛ እንዳይቆጥሯቸውና ይልቁንም የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች አድርገው እንዲያዩዋቸው ጠይቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍2😢1
ሐዋሳ በከባድ ዝናብ ተመታች‼️

👉ጎርፍና ኃይለኛ ንፋስ ከዝናብ ጋር በቀጣይ ቀናቶችም ሊቀጥሉ ይችላሉ።

​አሁን ባለው የክረምት ወቅት ሀዋሳን ጨምሮ በዙሪያዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እየጣለ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ባለስልጣን በሰጠው መረጃ መሠረትም የዝናቡ መጠን በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

​በከተማዋ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ፣ በረዶና ኃይለኛ ንፋስ በአንዳንድ አካባቢዎች ዛፎችንና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል። በተጨማሪም በመሠረተ ልማት ላይ በደረሰ ውድመት ምክንያት በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል።

​የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ በተጎዱ አካባቢዎች ፈጥኖ በመድረስ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና የማድረስና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራዎችን አስጀምሯል።

​በቀጣይም የክረምቱ ወቅት እስኪያልቅ ድረስ መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ፣ ጉዳቱን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክረው እየተከናወኑ ይገኛሉ።

​በመሆኑም በቀጣዮቹ ቀናት ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስተዳደሩ ያሳስባል።

​በተለይም ዛፎች፣ ያረጁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና አጥሮች ሊወድቁ ስለሚችሉ፣ በዝናብ ወቅት ከእነዚህ አካባቢዎች በመራቅ ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን እንድትጠብቁ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢96👍3
ግብር ሊከፍሉ ነው‼️
በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነዉ።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋስሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል።

ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ፣ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል።

ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ  ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣407🤯6👍2😱2👀1😡1
በግብፅ ወደብ ላይ የአሜሪካ ንብረት በሆነ የጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼️

በግብፅ የሜዲተራኒያን ወደብ በሆነው ዳሚየታ በሚገኝ የአሜሪካ ንብረት በሆነ ፈሳሽ ጋዝ የሚቀይርና የሚያከማች መርከብ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የእሳት መከሰቱንና በኋላም እሳቱ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ መርከብ መሸጋገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

የብሪታኒያው የባህር ላይ ደህንነት ተቋም አምብሬይ የመጀመሪያ ደረጃ ምዘና እና የደህንነትና የንግድ መረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ 'ኤነርጎስ ዊንተር' (Energos Winter) የተባለችው መርከብ የቀኝ ጎኗ በድሮን ጥቃቱ ተመቷል። 

በመቀጠልም እሳቱ በወደቡ ላይ ወደነበረችው 'ጋስሎግ ሳሌም' (Gaslog Salem) ወደተባለች ሌላ የጋዝ መርከብ ተዛምቷል።

በግምት 138,250 ኩቢክ ሜትር የማከማቸት አቅም ያላት 'ኤነርጎስ ዊንተር'፣ መቀመጫው አሜሪካ ለሆነው 'ኤነርጎስ ኢንፍራስትራክቸር' የተባለ ኩባንያ ንብረት ስትሆን፤ የቴክኒክ፣ የደህንነት እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የሚመሩት ደግሞ በ'ቪልሄልምሰን ሺፕ ማኔጅመንት' ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9🤔1
የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪው ከሀድያና ከንባታ ዞኖች ወጣቶችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሳቸው በማታለል ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይቀበል ነበር።

ተጎጂዎችን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በማሻገር፣ በጫካ ውስጥ በድብቅ ያቆያቸው፣ በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ ብቻ ትንሽ ሩዝና ቁራጭ ዳቦ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና ጥም ይዳርጋቸው ነበር። በተጨማሪም በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ ያስገድዳቸው ነበር።

ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ አጉሮ ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስገድዳቸው ነበር። ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ ይደበድባቸው፣ "እዚሁ ትሞታላችሁ" በማለት ያስፈራራቸው እንዲሁም በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃያቸው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።

ከዚያም ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮችና በተሸፈኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ታንዛኒያ በማጓጓዝ በጫካ ውስጥ ጥሎ ይተዋቸው እንደነበር ተገልጿል።

በዚህ ምክንያትም ብዙ ተጎጂዎች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በየመንገዱ በፖሊስ ተይዘው እስር ቤት መግባታቸውንና በኋላም ገንዘብ ከፍለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ፖሊስ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ክትትል በማላዊ ተይዞ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍8
ግብጾች የአባይን ውሃ ስለሚጠቀሙ ለኢትዮጵያ ሊከፍሉን ይገባል ዶክተር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ ግብፅ የአባይን ውኃ በነፃ እየተጠቀመች አገሯን እያለማች በመሆኗ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ክፍያ ልትፈጽም እንደሚገባ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በቆይታቸው እንደጠቆሙት፤ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት—በተለይም በግብፅ ላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች።

ሆኖም አገራቱ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ያለምንም ክፍያ በመጠቀም አገራቸውን እያለሙ በመሆናቸው፣ ለሚጠቀሙበት ውኃ ለኢትዮጵያ ክፍያ ሊፈጽሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
31🤣19👍10😎3💯2👀1🤪1
የ«ሁሉ ስፖርት» የፈቃድ ስረዛ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሻረ፤ አገልግሎቱ ግን አሁንም ታግዷል

​የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና የገቢዎች ሚኒስቴር በ«ሁሉ ስፖርት» ላይ አስተላልፈውት የነበረውን የንግድ ፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ሻረ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው ተቋማቱ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግን ሳይከተሉ እና የተቋሙን የመሰማት መብት ጥሰው ፈቃድ መሰረዛቸውን በመግለፅ ነው።

​መንግሥት ድርጅቶቹ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ሰውረዋል ቢልም፣ ፍርድ ቤቱ ይህ በወንጀል ሕግ የሚታይ እንጂ በደፈናው ለአስተዳደራዊ ፈቃድ ስረዛ ምክንያት ሊሆን አይችልም ብሏል።

​ሆኖም የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በውሳኔው ላይ ይግባኝ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አፈጻጸም ከሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት እንዲታገድ ተደርጓል።

በመሆኑም ጉዳዩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ «ሁሉ ስፖርት» ወደ ሥራ አይመለስም።
​ይህ በእንዲህ እንዳለ የሎተሪ አገልግሎቱ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ምንም ዓይነት የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ድርጅት እንደሌለ አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2
📱 አንድን አይፎን 17 ፕሮ ገዝቶ ለመያዝ በስዊዘርላንድ 3 የሥራ ቀናት ብቻ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
 
አዲሱ አይፎን 17 ፕሮ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የሚሸጥበት የገንዘብ መጠን በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ግለሰብ ይህንኑ ስልክ ገዝቶ ለመያዝ የሚያወጣው የሥራ ጊዜና ድካም ግን እጅግ የተራራቁ የኢኮኖሚ እውነታዎችን ያንፀባርቃል ተብሏል።
 
ይህን የገቢና የኢኮኖሚ ልዩነት በግልጽ በሚያሳየው መረጃ መሠረት፣ በስዊዘርላንድ የሚኖር አንድ ሠራተኛ አዲሱን አይፎን 17 ፕሮ ለመግዛት 3 የሥራ ቀናት ብቻ የሚያስፈልጉት ሲሆን፣ በፊሊፒንስ 101 የሥራ ቀናት፣ በሕንድ 160 የሥራ ቀናት፣ እንዲሁም በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ 540 የሥራ ቀናት ሙሉ መሥራት ይጠይቃል ነው የተባለው።
 
አንድ አይነት ቴክኖሎጂ እና ተመሳሳይ የገበያ ዋጋ፤ ነገር ግን እጅግ የተራራቁ የሰዎች የኑሮ እውነታዎች! ይህ ንጽጽር አይፎን በዓለማችን ላይ ያለውን የገቢና የኢኮኖሚ እኩልነት ማጣትን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ መሆኑን እና አንድ ሰው የተወለደበት ወይም የሚኖርበት ሀገር የሚገዛቸውን ዕቃዎች የመወሰን አቅሙ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ በተግባር ያረጋገጠ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤣15👍4😢2
ኤችአይቪ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው

‎አሁን ላይ በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የኮንዶም ዕጥረት መኖሩም ተነስቷል።

‎ዕድሜያቸው ከ14-24 የሆኑ ሴቶች በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ መሆናቸው ተገልጿል።

‎በአገራችን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል ተብሏል።

‎አሁን ላይ 7መቶ ሺህ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል የተባለ ሲሆን፥ቁጥሩ ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ሰምተናል።

‎ይህን የሰማነው የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ይህን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።

‎ኔፕ ፕላስ በኤችአይቪ ህመም ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን፥ ምስረታው ወደ 22 ዓመት እየተጠጋው ነው።

‎በዚህ ኔትወርክ ስር የተቋቋሙ ከ5መቶ በላይ ማህበራትን የያዘ መሆኑ ሲገለፅ፥ በዋናነት አሁን ላይ በንቃት የሚንቀሳቀሱት እና የግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ ማህበራት ቁጥር 1መቶ29 ነው።

‎የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ(ኔፕ ፕላስ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ፥ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

‎ይህ ጉባዔ እየተዘነጋ ስላለው ነገርግን ዛሬም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው የኤችአይቪ ህመም ሰፊ ግንዛቤ የሚሰጥበት ነው።

‎ድርጅቱ ለሁለት ጊዜ ያህል "Stigma index research" ማሰራቱን ገልጾ፥ ሶስተኛ ዙር ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
8👍7😢2👀2
6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን ተወለደች

‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።

‎በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።

‎ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍7😱3🥰1💯1
"ህወሓት ውጊያ‼️ ከጀመረ ውጊያውን የሚመራው አስመራ ሆኖ እንጂ መቀሌ ሆኖ ውጊያውን መምራት እንደማይችል እርግጠኛ ነኝ" ሲሉ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ጄኔራል ባጨ ደበሌ ለአንድ ሚዲያ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3920👍7🤪6🥰3😡2🙈1