ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ ከጠዋቱ 3፡30-11፡04
👉 ስካይላይት ሆቴል፣ ቱርክ ኢምባሲ፣ ቦሌ ት/ቤት፣ ኤድናሞል፣ ቦሌ ቴሌ እና አከባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 5፡40-9፡30
👉 3 ቁጥር ማዞሪያ፣ ሳሚ ካፌ፣ ጎልፍ ክለብ፣ ወይብላ ማርያም፣ አውጉስታ፣ አንፎ፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡30-11፡04
👉ገለን አባ ሳሙኤል፣ አቡ ሴራ፣ ዱፍና፣ ደበራ ጢኖ፣ አርትስቲ፣ ዱከም፣ ቡራዩ ከተማ አስተዳዳር እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡00-10፡00
👉ቃሊቲ ገብርኤል ቤ/ት፣ ሜድሮክ፣ ካዲስኮ፣ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፣ ሸገር ሕንፃ፣ ቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉 ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሲዲሲ፣ ኮሰሮ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ካሰዴ፣ 44 ማዞሪያ፣ ሰንዳፋ ጫፍ እና አካባቢው፣
👉 ጭሮ ከተማ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ሀረማያ፣ ጨላንቆ፣ በሮዳ፣ ሐድስ፣ ቆቦ፣ ከራሚሌ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል።
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
@Addis_Reporter

❤6👍4
ለደብረብርሃን ከተማ ህዝብ እጅግ ልብ ሰባሪ ዜና ነው💔💔🥲
በዛሬው እለት አራት (4) የአንድ ቤተሰብ አባላት ግለሰቦች በመኪና አደጋ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸው እንዳለፈ ተሰምቷል።
የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓልን ታድመው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት አለልቱ ላይ ነው ይህ አሳዛኝ ልብ ሰባሪ አደጋ የደረሰው🥲 ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው፣ ለጎረቤቶቻቸው እንዲሁም ለሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርን🥲
ሸዋ ደብረ ብርሃን

😢58❤12💔10👍4🤯1
በፈረንሳይ እና በስፔን የደረሰዉ ሰደድ እሳት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ
በፈረንሳይ እና በስፔን የሚነደው የሰደድ እሳት ቃጠሎ አሁንም እየቀጠለ ይገኛል፡፡በፈረንሳይ እሳት አሁን ከቦርዶ ከተማ ዳርቻ 15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ብቻ ይገኛል።በጂሮንድ ክልል 220,000 የሚገመቱ ሰዎች አካባቢያቸዉን ለቀዉ ለመዉጣት ተገደዋል፣ 42,000 ሄክታር ያህል መሬት ሲቃጠል 240 ቤቶችም ወድመዋል።
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቦርዶን ከእሳቱ ለማዳን ላከናወኑት ጥረት የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪዎችን አመስግነዋል፣ "መላው ሀገር ከጎናችሁ ነው" ሲሉ መናገራቸዉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መቆጣጠር "ዳዊት ከጎልያድ ጋር የሚያደርገው ትግል" ዓይነት ነው ሲሉ የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ቃል አቀባይ ተናግረዋል።በዚህ ሳምንት በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ የሙቀት መጠኑ 39 ዲግሪ ሴልሺየስ (102 ዲግሪ ፋራናይት) ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ቢያንስ እስከ አርብ ድረስ ዝናብ አይኖርም ተብሎ ተተንብዮአል።
በስፔን ከዋና ከተማዋ ማድሪድ በስተ ምዕራብ 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የእሳት ቃጠሉለፐ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡ ወደ 105,000 የሚጠጉ ሰዎች በሰደድ እሳቱ ተፈናቅለዋል፣ በማድሪድ፣ በአቪላ እና በቶሌዶ ክልሎች በተነሳው የእሳት ቃጠሎ 77,000 ሄክታር አካባቢ ተጎድቷል።እሳቱ በፍጥነት እንዲሰራጭ እና በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቃጠል የሚያስችል ሞቃታማ እና ደረቅ የአየር ሁኔታ እየተፈጠረ ነው ሲሉ የአየር ንብረት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

❤14👍2😱1😢1
ተጥሎ በረሃብ የሞት አፋፍ ላይ የነበረውን የሁለት ወር ሕፃን ልጅ የፖሊስ አባልዋ የራስዋን ጡት በማጥባት ከሞት ታደገችው
በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ አንዲት እናት ጥላ የጠፋቸውንና በረሃብ የሞተት አፋፍ ላይ የደረሰን የሑለት ወር ሕፃን ልጅ የፖሊስ አባልዋ የራስዋን ጡት በማጥባት ከሞት ታደገችው።
የጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች የተጣለና በምግብ እጦት ከሞት አፋፍ የደረሠን ልጅ አይተው ፖሊስ ጣቢያ ይዘው ይመጣሉ። ይሕ ልጅ በምግብ እጦትና በብርድ በመጎዳቱ የሞት አፋፍ ላይ ደርሷል።
ይህንን የተመለከተችው የጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ፖሊስ አባል ረዳት ሣጅን መስከረም ስምኦን የእናትነት አንጀት አላስችል ብልዋት ጡቷን በማጥባት በሞት አፋፍ የነበረውን ልጅ ከሞት ልትታደገው መቻሏን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።ሕፃኑን ሣየው ሆዴ ስፍስፍ አለ የምትለው ረዳት ሳጅን መስከረም ስምኦን ፖሊስነት ሕይወትን መታደግ ነውና በረሐብና በብርድ የተዳከመውን ልጅ ጡቴን በማጥባት ነብስ እንዲዘራ አድርጊያለሁ በማለት ተናግራለች።
የረዳት ሳጅን መስከረም ስምኦን ተግባር ፖሊስነት ከመስዋዕትነት እስከ ሕይወት አድን ተግባር በመሆኑ ምስጋና የተቸራት ሲሆን ከሞት አፋፍ በረዳት ሣጅን መስከረም ስምኦን ጡት ነብስ የዘራው የሑለት ወር ልጆ በአሑኑ ሠዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንዳለ ተገልጿል።
ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የቀርሣ ወረዳ ፖሊስ የሴቶች ና ሕፃናት ክፍል ኃላፊ ዋና ሣጅን ነይማ ጀማል ተጥሎ የተገኘ ህፃን ልጅ በረሃብ በመኖር እና በሞት መካከል መሆንኑ በመረዳት ወተት ያጋተውን ጡቷን አውጥታ በማጥባት ህይወቱን መታደጓን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሣል።

❤61👍10🥰4🎉4
በጃፓን ኩማሞቶ በሬክተር ስኬል 7.1 የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
በጃፓን ደቡባዊ የኪዩሹ ደሴት በሚገኘው ኩማሞቶ ግዛት ዛሬ የደረሰው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በሰዎች ሕይወት፣ በመሠረተ ልማት እና በኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።
የመጀመሪያ ግምገማዎች መንቀጥቀጡ በ6.8 እስከ 7.1 ማግኒትዩድ መካከል መለካቱን ያሳያሉ፤ ባለሥልጣናት የመጨረሻ ሳይንሳዊ ግምገማ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል።
ከአደጋው በኋላ በካሺማ ከተማ የሚገኘው «ኢዮን ሞል ኩማሞቶ» ውስጥ ከባድ ፍንዳታ ተከስቶ የሕንፃው ክፍል በመፍረሱ በርካታ ሰዎች በፍርስራሹ ስር መቀራቸው ተገልጿል።
እስካሁን ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሰራተኞች የጠፉ ሲሆን፣ የእሳት አደጋ እና የነፍስ አድን ቡድኖች የማዳን ሥራ እያካሄዱ ነው። ፍንዳታው ከጋዝ መፍሰስ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ጥርጣሬ ቢኖርም፣ ባለሥልጣናት መንስኤውን እያጣሩ ነው።
በሌላ በኩል፣ በአካባቢው በሚገኝ የወረቀት ፋብሪካ ውስጥ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች ያሉበት እስካሁን አልታወቀም።
በባቡር መስመሮች፣ በድልድዮች እና በመንገዶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፤ የባቡር አገልግሎት ተቋርጧል፣ አንዳንድ ባቡሮችም ከሐዲድ ወጥተዋል። በአካባቢው የአየር ማረፊያም ለጊዜው ተዘግቷል።
የኃይል አቅርቦት በአስር ሺዎች ቤቶች ተቋርጧል፤ ከ60 በላይ የተከታታይ ንዝረቶች በመመዝገባቸውም ተጨማሪ የመሬት መንሸራተት እና የሕንፃ መውደቅ አደጋ ስለሚኖር ህዝቡ ከተጎዱ ሕንፃዎች እንዲርቅ ጥሪ ቀርቧል።
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ የመከላከያ ኃይሎችን፣ የእሳት አደጋ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የአደጋ ምላሽ ቡድኖችን ወደ ተጎዱ አካባቢዎች መላካቸውን ገልጸዋል።

❤24😢14👍3
እዳ ያልከፈሉ እየተከሰሱ ነው‼️
በቴሌብር ዲጂታል ብድር ውዝፍ ዕዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ እና ክስ መጀመሩ ተገለጸ‼️
ዳሸን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር መተግበሪያ አማካኝነት የወሰዱትን የዲጂታል ፋይናንሲንግ ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያልከፈሉ ተበዳሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን እና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ክስ እየመሰረቱ እንደሚገኙ አስታወቁ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ ተበዳሪዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የተደረገውን የቅጣት ክፍያ ምሕረት ተጠቅመው ዕዳቸውን ያልከፈሉ ወገኖች ላይ የህግ አካሄድ መጀመሩን ገልጿል።
በመግለጫው መሠረት፣ አስቀድሞ ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ያልሰጡ ተበዳሪዎች ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ ከዋናው ዕዳ በተጨማሪ ባንኩ ለክስ ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎች እንዲሸፍኑ ውሳኔ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
ዳሸን ባንክ አክሲዮን ማህበር የህዝብ ገንዘብ ለማስመለስ የጀመረውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ እስካሁን የክስ መጥሪያ ያልደረሳቸው ተበዳሪዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት እና ተጨማሪ አላስፈላጊ እንግልት እንዲሁም ወጪ ሳይደርስባቸው ያለባቸውን ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

❤21🤪16🤣5👍2🙏2
የዘመን አቆጣጠራችን ይቀየር ተባለ‼️
በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ የተለያዩ አማራጮች ቀርበዋል።
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ የሂጅራ ወይም የእስላማዊ የዘመን አቆጣጠር ይካተት፣ «ዓመተ ምህረት» የሚለው ይቅርና አሁን ያለው የፈረንጆቹ አቆጣጠር ይቀጥል፣ እንዲሁም ከእስልምናም ሆነ ከክርስትና ሃይማኖቶች ነፃ የሆነ የዘመን አቆጣጠር እንከተል የሚሉ ምክረ ሃሳቦች መቀረባቸው ታውቋል።
በተነሱት አጀንዳዎች ላይ እስካሁን ውሳኔ ደረጃ ላይ አልተደረሰም፣የውሳኔ ሂደቱ ገና መሆኑን ገልፀዋል።

🙉45❤29😡19👍8👀8😢5🙊3🤷♂2🤩2😱1🌚1
#በኦሮሚያ እና #በሲዳማ አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወት ሲያልፍ፤ ትምህርት ቤት እና የሰብል ምርቶች ወደሙ❗❗
√.ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያው ጊርጃ ወረዳ ጉቦ ሄማ ቀበሌ እና በምሥራቅ ሲዳማ ዞን ጭሪ ቀበሌ መካከል ባገረሸው ግጭት የ10 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ቆስለዋል፤ እንዲሁም በበርካታ ቀበሌዎች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ሲሉ በሁለቱም ወገን ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ግጭት በአካባቢው ላይ የነበረውን መረጋጋት በእጅጉ ማደፍረሱን ገልጸዋል።
√.የምሥራቅ ጉጂ ዞን የጊርጃ ወረዳ ነዋሪ፤ በአጠቃላይ በጉጂ በኩል ጊርጃ ወረዳ ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች ሲገደሉ፣ ወደ 40 የሚጠጉ ደግሞ ቆስለው በአዶላ፣ ቦሬ፣ ኩያራ፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ እና አዲስ አበባ በሚገኙ ህክምና ተቋማት በመታከም ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
√. በተጨማሪም በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና የጉቦ ሄማ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወድመሏ ነው የተባለው።

🕊6❤3👍3
በርካታ አካባቢዎች መብራት ይቋረጣል‼️
የጥገና ሥራ ምክንያት ነገ በበርካታ አካባቢዎች የመብራት አቅርቦት ይቋረጣል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ሥራ ለማከናወን ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ለተወሰነ ሰዓት እንደሚቋረጥ አስታውቋል።
ከጠዋቱ 4፡00 – 10፡00
• ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ችሎት አደባባይ፣ ዘበኛ ሰፈር፣ ሾላ፣ ሰሜን ሆቴል ጫፍ፣ ቀለመወርቅ ት/ቤት፣ ዶሮ ተራ፣ ራስ ደስታ፣ አርበኞች ት/ቤት እና አካባቢያቸው።
• ዕንቁላል ፋብሪካ፣ ሀግቤስ አራት መንታ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ጅንአድ፣ አበበች ጎበና፣ ቄጤማ ተራ፣ ፓስተር አደባባይ፣ አቤት ሆስፒታል፣ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን፣ ዳትሰን ሰፈር፣ ሰን ሆቴል እና አካባቢያቸው።
• 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ፣ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፣ አትክልት ተራ፣ ጣሊያን ሰፈር፣ ፒያሳ (በከፊል)፣ ማዘጋጃ ቤት፣ አውቶብስ ተራ እና አካባቢያቸው።
• ማርቆስ መጋዘን፣ ቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ፣ ቀጨኔ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ መንገድ፣ ይመር ውኃ፣ መቀጠያ፣ 19 ታቦት ማደሪያ፣ መታፈሪ ሰፈር፣ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ ሽሮ ሜዳ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 2፡00 – 10፡00
• አያት ለገጣፎ ሰብስቴሽን ፊትለፊት ያሉ ኮንዶሚኒየሞች፣ ክቡርደመና፣ ሰላም ቪሌጅ፣ ጣፎ ገብርኤል፣ ጋሪ ተራ፣ ባጃጅ ተራ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 3፡00 – 10፡30
• ገላን፣ አራብሳ፣ እንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ፣ ፕሮጀክት 13 አራብሳ ወታደር ሰፈር፣ ነጋ ቦንገር፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ ቆዳ ፋብሪካ፣ ፓስታና መኮረኒ ፋብሪካ እና አካባቢያቸው።
• አባ ሳሙኤል፣ አቡሴራ፣ ሉግና፣ ዱፍና፣ ደበራ ጢኖ፣ ሻሸመኔ፣ ዱከም፣ በላይነህ ክንዴ፣ በስተቀኝ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ካፍ ማደያ እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 4፡30 – 11፡00
• መቐለ (ላቺ በከፊል)፣ ሀምዲያ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ቀበሌ 03፣ ባህርዳር (አዲስ ዓለም)፣ ኦቪድ፣ ሰማኤታ፣ ሚሊኒየም ት/ቤት እና አካባቢያቸው።
ከጠዋቱ 1፡00 – 6፡00
• ወልዲያ፣ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቢልባላ፣ ቂርቆስ፣ ሳሬዜና፣ ሶርባ፣ ላሊበላ፣ ገነተ ማርያም፣ ዘሃ፣ ሙቅ ውኃ፣ ተከዜ ገዳሜ፣ ኢርፋ ገለሶቴ እና አካባቢያቸው።
• ቅዱስ አርቢ፣ ዳቦ ከተማ፣ ቡርኮ፣ አይና ሚካኤል፣ ጭሮ፣ ሜኤሶ፣ አሰቦት እና አካባቢያቸው።
በመሆኑም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ደንበኞች የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ እና የኃይል አቅርቦቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።

❤13👍3🤔1😢1👀1
ኤርትራ የአየር መንገዱን ገንዘብ አልመለሰችም‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የታገደበት ገንዘብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የፖለቲካ ውጥረት እና የነበረው የህግ ሂደት በመቋረጡ ምክንያት ምንም ማድረግ እንዳልተቻለና እስካሁን መፍትሔ ሳያገኝ እንደቀረ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገለጹ።
“አሁን ላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ጤናማ አይደለም፤ በዚህ ምክንያት ምንም ዓይነት ሂደት የለም፣ ጉዳዩ ስታክ እንዳደረገ (ባለበት እንደቆመ) ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በጊዜው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት የነበረ ቢሆንም “ፖለቲካዊ ውሳኔ በመደረጉ ፍርድ ቤቱ መንቀሳቀስ አልቻለም” ብለዋል። በመሆኑም ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ድረስ ለመጠበቅ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ገንዘቡ በኤርትራ ባንክ እንደሚገኝ ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የበረራ መቋረጡም ሆነ የገንዘብ ዝውውሩ መገታት ከፖለቲካዊ ሁኔታዎች ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል። አየር መንገዱ በተለያዩ ሀገራት ገንዘቦቹ እንደተያዙበት ያነሱ ሲሆን፣ በርካታ ገንዘብ በሩሲያ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህንንም ለማውጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በኤርትራ ያለለወው ገንዘብ ግን እስካሁን ባለበት እንደተያዘ ይገኛል።

❤13🙊3👍2🤪2✍1
የአበል አፈፃፀም መመሪያ‼️
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ እና በቅዳሜ ቀናት ለሚሰሩ ሠራተኞች የትራንስፖርት አበል አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል።
በመመሪያው መሠረት በቅዳሜ ቀን ለሚሰሩ ሠራተኞች በቀን 200 ብር (በወር 800 ብር) እንዲሁም በምሽት ለሚሰሩ የትራንስፖርት መመለሻ በቀን 100 ብር (በወር 2,200 ብር) ተመድቧል። በዚህም መሠረት አንድ ሠራተኛ በወር እስከ 3,000 ብር የትራንስፖርት አበል ማግኘት ይችላል።
የትራንስፖርት አበል የሚከፈለው ከመደበኛ ሰዓት በኋላ አገልግሎት ለሚሰጡ ሠራተኞች፤ በቅዳሜ ቀናት በተፈቀደ የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት ለሚሰሩ ሠራተኞች ብቻ ነው።
- በረዥም ጊዜ ሥልጠና ወይም ትምህርት ላይ ለሚገኝ ሠራተኛ፤
- በተፈቀደው የሥራ መርሐ-ግብር መሠረት በሥራ ላይ ላልተገኘ ሠራተኛ፤
- ተቋሙ የጋራ ወይም በተናጥል ትራንስፖርት አገልግሎት ላቀረበለት ሠራተኛ እና በተመሳሳይ ዓላማ ከሌላ ምንጭ የመጓጓዣ ድጋፍ የሚያገኝ ሠራተኛ የዚህ ትራንስፖርት አበል ተጠቃሚ አይሆንም።

❤19👍2🥰1🤔1👌1
ለሚያገቡ 6 ሚሊዮን ብር ‼️
ደቡብ ኮሪያ የወሊድ ምጣኔን ለማሳደግ ሰዎች ወደ ጋብቻ እንዲገቡ እና እንዲወልዱ ለማበረታታት $38,000 ወይም 6 ሚሊዮን ብር ለማበረታቻ እየሰጠች መሆኑ ተሰምቷል።

❤29🤣15👍10🥱4🤯1
ዓለማቀፉ የፍልሠት ድርጅት፣ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ እስያ አገራት የበይነ መረብ የማጭበርበሪያ ካምፖች ተጠቂ የመሆናቸው ክስተት በመጨመር ላይ ይገኛል ሲል አስጠነቀቀ።
በበይነ መረብ የማጭበርበር ድርጊቶች ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ የውጭ ዜጎች፣ ድብደባና ጾታዊ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸውና ለርሃብ እንደሚጋለጡ ድርጅቱ ገልጧል።
ከአውሮፓዊያኑ 2022 እስከ 2025 ከ3 ሺሕ 500 በላይ የ39 አገራት ዜጎች በደቡብ ምሥራቅ እስያ አገራት በበይነ መረብ የወንጀል ድርጅቶች በግዳጅ ተይዘው ነበር ተብሏል።
አብዛኞቹ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ባንግላዴሽ፣ ስሪላንካ፣ ሕንድ እና ኢንዶኔዥያ ዜጎች እንደኾኑ ድርጅቱ ጠቅሷል።
ድርጅቱ፣ በማጭበርበር ተግባራት ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎችን መንግሥታት እንደ ወንጀለኛ እንዳይቆጥሯቸውና ይልቁንም የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች አድርገው እንዲያዩዋቸው ጠይቋል።

❤8👍2😢1
ሐዋሳ በከባድ ዝናብ ተመታች‼️
👉ጎርፍና ኃይለኛ ንፋስ ከዝናብ ጋር በቀጣይ ቀናቶችም ሊቀጥሉ ይችላሉ።
አሁን ባለው የክረምት ወቅት ሀዋሳን ጨምሮ በዙሪያዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እየጣለ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ባለስልጣን በሰጠው መረጃ መሠረትም የዝናቡ መጠን በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።
በከተማዋ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ፣ በረዶና ኃይለኛ ንፋስ በአንዳንድ አካባቢዎች ዛፎችንና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል። በተጨማሪም በመሠረተ ልማት ላይ በደረሰ ውድመት ምክንያት በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል።
የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ በተጎዱ አካባቢዎች ፈጥኖ በመድረስ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና የማድረስና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራዎችን አስጀምሯል።
በቀጣይም የክረምቱ ወቅት እስኪያልቅ ድረስ መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ፣ ጉዳቱን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክረው እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በመሆኑም በቀጣዮቹ ቀናት ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስተዳደሩ ያሳስባል።
በተለይም ዛፎች፣ ያረጁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና አጥሮች ሊወድቁ ስለሚችሉ፣ በዝናብ ወቅት ከእነዚህ አካባቢዎች በመራቅ ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን እንድትጠብቁ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን

😢9❤6👍3
ግብር ሊከፍሉ ነው‼️
በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነዉ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዋስሁን በላይ ይህ ግብር በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ተሽከርካሪዎቹ በመንግስት በተገነቡ መንገዶች ላይ ስለሚንቀሳቀሱ በየዓመቱ የሚከፈል ይሆናል ብለዋል።
ይህም ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ ወይም ቦሎ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ ነው።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ እንደገለፁት ብዙ ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ፣ አዳዲሶች ደግሞ ዝቅተኛ እንዲከፍሉ ሊደረግ ይችላል ተብሏል።
ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

🤣40❤7🤯6👍2😱2👀1😡1
በግብፅ ወደብ ላይ የአሜሪካ ንብረት በሆነ የጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼️
በግብፅ የሜዲተራኒያን ወደብ በሆነው ዳሚየታ በሚገኝ የአሜሪካ ንብረት በሆነ ፈሳሽ ጋዝ የሚቀይርና የሚያከማች መርከብ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የእሳት መከሰቱንና በኋላም እሳቱ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሌላ መርከብ መሸጋገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።
የብሪታኒያው የባህር ላይ ደህንነት ተቋም አምብሬይ የመጀመሪያ ደረጃ ምዘና እና የደህንነትና የንግድ መረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ 'ኤነርጎስ ዊንተር' (Energos Winter) የተባለችው መርከብ የቀኝ ጎኗ በድሮን ጥቃቱ ተመቷል።
በመቀጠልም እሳቱ በወደቡ ላይ ወደነበረችው 'ጋስሎግ ሳሌም' (Gaslog Salem) ወደተባለች ሌላ የጋዝ መርከብ ተዛምቷል።
በግምት 138,250 ኩቢክ ሜትር የማከማቸት አቅም ያላት 'ኤነርጎስ ዊንተር'፣ መቀመጫው አሜሪካ ለሆነው 'ኤነርጎስ ኢንፍራስትራክቸር' የተባለ ኩባንያ ንብረት ስትሆን፤ የቴክኒክ፣ የደህንነት እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የሚመሩት ደግሞ በ'ቪልሄልምሰን ሺፕ ማኔጅመንት' ነው።

❤13👍9🤔1
የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪው ከሀድያና ከንባታ ዞኖች ወጣቶችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሳቸው በማታለል ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይቀበል ነበር።
ተጎጂዎችን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በማሻገር፣ በጫካ ውስጥ በድብቅ ያቆያቸው፣ በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ ብቻ ትንሽ ሩዝና ቁራጭ ዳቦ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና ጥም ይዳርጋቸው ነበር። በተጨማሪም በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ ያስገድዳቸው ነበር።
ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ አጉሮ ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስገድዳቸው ነበር። ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ ይደበድባቸው፣ "እዚሁ ትሞታላችሁ" በማለት ያስፈራራቸው እንዲሁም በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃያቸው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።
ከዚያም ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮችና በተሸፈኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ታንዛኒያ በማጓጓዝ በጫካ ውስጥ ጥሎ ይተዋቸው እንደነበር ተገልጿል።
በዚህ ምክንያትም ብዙ ተጎጂዎች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በየመንገዱ በፖሊስ ተይዘው እስር ቤት መግባታቸውንና በኋላም ገንዘብ ከፍለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ፖሊስ አመልክቷል።
ተጠርጣሪው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ክትትል በማላዊ ተይዞ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል።

❤9👍8