አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
የክፍል አለቃውን የገደለው ታዳጊ በእስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በጅማ ከተማ በሚገኘው ሔርማታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ነው።

የከተማው ፖሊስ እንዳስታወቀው ሙአዝ ቢላል የተባለው ተማሪ የሚማርበትን ክፍል ሲረብሽ ቆይቶ በመስኮት በኩል ከመማሪያ ክፍሉ ዘሎ ወደ ውጭ ይወጣል።

ይህን የተመለከተው የክፍሉ አለቃ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ በማለት ይጠይቀዋል። ድርጊቱም ትክክል እንዳልሆነ ይነግረዋል። በወቅቱ ተማሪውን በመቆጣት የተሰጠውን ሀላፊነት ይወጣል።

በዚህ ምክንያት ሁለቱ ተማሪዎች መካከል ግጭት ይፈጠራል። ልትናገረኝ አይገባም" በማለት የተበሳጨው ተማሪ ሙአዝ ቢላል አስቀድሞ ጩቤ ደብቆ ይዞ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ገብቶ ነበርና የክፍል አለቃ የነበረውን ተማሪ ሙሳብ መሀመድን በያዘው ስለት ወግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋል።

ተከሳሽም በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ተጣርቶበት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሀምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተማሪ ሙአዝ ቢላል ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በ15 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ምንጭ:- የጅማ ከተማ ፖሊስ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26😱23💔10👍3😢2😡2🤯1🙈1
#ፍርድ

" የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል " - የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ 

‎የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ እንዳስታወቀው የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች  ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ የእስራት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

‎የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እና የፖሊስ ኮሚሽነር ላይ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሳሽነት በቀረቡ ክሶች ላይ የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማመሳከር  ተከሳሾቹን ጥፋተኛ ያላቸው፤ ኃላፊዎቹ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ) የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀትና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ ማስተላለፉን ቢሮው አስታውቋል።

‎በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሐምሌ 20/11/2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጹኑ እስራት እና 4000 ሺ ብር እንዲቀጡ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 1 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮው ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍74
ኢሰመጉ፤ በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታወቀ።

ሀገር በቀሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟገች ድርጅት በ37 ገጾች ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂ አካላት ማንነትንና ኃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማልፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል።

በተጨማሪም ከ14,000 በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል።

ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣ በጥቃቶቹ ሳቢያ በየወረዳው የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡

መርቲ ወረዳ፣ 117 ሰዎች፤ ሽርካ ወረዳ፣ 116 ሰዎች፤ ጀጁ ወረዳ፣ 101 ሰዎች ፤ ሮቤ ወረዳ፡ 47 ሰዎች ፤ ጉና ወረዳ፣ 26 ሰዎች ፤ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ 20 ሰዎች ፤ ሙኒሳ ወረዳ፣ 19 ሰዎች ፤ አሰኮ ወረዳ፡ 5 ንጹሃን ዜጎች እና 4 የህዝብ ሚሊሻዎች ፤ አርሲ ሲሬ ወረዳ፣ 3 ሰዎች በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ጉባኤው የሟቾችን ስም ዝርዝር ከነምስላቸው አስደግፎም ነው በሪፖርቱ ይፋ ያደረገው፡፡

ከግድያው ጎን ለጎን በሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ እና ሙኒሳ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ የካሳ ገንዘብ ከፈለው ያስለቀቋቸው ቢኖሩም፤ የበርካቶች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን ሳይታወቅ ቀርቷል። በጥቃቶቹ ወቅት በህጻናትና በአረጋውያን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።

የደህንነት ስጋቱ በዞኑ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ በጀጁ (6,216)፣ በሽርካ (3,746)፣ በአሰኮ (2,133)፣ በሮቤ (1,270)፣ በመርቲ (1,036)፣ በሙኒሳ (29) እና በጉና (21) ወረዳዎች በጠቅላላው ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድቷል። በተጨማሪም ዕድሜ ጠገብ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ መዘረፋቸውንና በስጋት ምክንያት መዘጋታቸውን ይፋ አድርጓል።

ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በህገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶችን የጣሱና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ባህሪያትን የሚያሳይ ነው ብሏል።

በመሆኑም የፌደራልና የክልል መንግስታት ለዜጎች ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ጥሰት ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፈልና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

Via_addis maleda

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16😢115🤯1
የሱዳን ጦር ካርቱምን ከኤል-ኦቤይድ የሚያገናኘውን ዋና መንገድ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ!

የሱዳን ጦር ኃይል ከመዲናዋ ካርቱም ተነስቶ በተቀናቃኙ የፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ከበባ ውስጥ ወደምትገኘው ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚወስደውን ዋና የትራንስፖርት መስመር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ገለጸ።

በእሑድ ዕለት በሱዳን ጦር ኃይል ቁጥጥር ስር የገባው «አል ሳዳራት» የተሰኘው ዋና አውራ ጎዳና  ኃይሉ፤ ወታደሮቹን፣ መሣሪያን፣ የነዳጅ እና የሎጂስቲክስ አቅርቦቶቹን በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የሚረዳው ሲሆን፤ አርኤስኤፍ የሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል-ኦቤይድን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ግስጋሴ የሚያግድ ነው ተብሏል።

በከተማዋ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ዜጎች ተከበው የሚገኙ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ለአርኤስኤፍ የድሮን ጥቃቶች በመጋለጣቸው አሰቃቂ የሰብአዊ ውጥረት ማንዣበቡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስጠነቅቃል።

የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ አውራ ጎዳናውን ተቆጣጥሮት ከነበረው የአርኤስኤፍ ኃይል ጋር ለሁለት ቀናት ያህል ከተካሄደው ከፍተኛ ውጊያ በኋላ፣ በካርቱም እና በኤል-ኦቤይድ መካከል የሚገኙ በርካታ ከተሞችንና መንደሮችን መልሶ መቆጣጠር ተችሏል።

Via_AS

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍2😢1
ግሎባል ባንክ በገንዘብ ተቀማጭ እና የሊኲዲቲ  አያያዝ ላይ የተነሳውን ጥርጣሬ ተክቶ ባካሄደው ምርመራ የባንኩን ፕሬዝዳንት  ተስፋዬ ቦሩን ጨምሮ 18 ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አግዷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኩ  በሚሊዮኖች የሚቆጠር የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወጥቷል በሚል የጀመረውን ማጣራት ተከተሎ፣ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ የራሱን ምርመራ በማካሄድ አቶ ሳህለሚካኤል መኮንንን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ሾሟል።

​ባንኩ እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ ሀብቱን በ42 በመቶ በማሳደግ 34.43 ቢሊዮን ብር ማድረሱ እና ከታክስ በኋላ 756.6 ሚሊዮን ብር አትርፎ የነበረ ቢሆንም፣ የገጠመው የከፍተኛ አመራሮች እግድ እና የቁጥጥር ክፍተት የቀውሱ መንስኤ ሆኗል።

ባለሙያዎች ባንኩ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ገንዘቦች ላይ ከመጠን በላይ መደገፉን በመጥቀስ፣ ጠንካራ የቦርድ ቁጥጥር እና ነፃ የባንክ ባለሙያዎች እንዲካተቱ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍4🤪1
በዚህ ሳምንት የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያ

የበለጠ ሚያሳዝነው ደግሞ በግድያው ቅንብር የቅርብ ጓደኛ መኖሯ ነው

የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሩታ ይርጋለም ታላቅ እህት ቅዱሳን ይርጋለም በአጋቾች ተጠልፋ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ከተጠየቀባት በኋላ በአጋቾቹ በጭካኔ ተገደለች።

የሟች ቅዱሳን ይርጋለም የቀብር ሥነ ሥርዓት ትላንት በቤተል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ አሸናፊዋ እህቷ ሩታ ይርጋለም የሟችን የምረቃ ፎቶግራፍ በማያያዝ፤

«እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ፤ ከጠላቴ እኔ እጠነቀቃለሁ ከወዳጄ አንተ ጠብቀኝ... የኔ ማነው...» በማለት በደረሰባት ጥልቅ ሀዘን የተሰማታን ስሜት ገልጻለች።

ድርጊቱን ፈጽመው ከህግ ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በተካሄደ የተቀናጀ የጋራ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የሟች የቅርብ ጓደኛ እንደነበረችም ለማወቅ ችለናል።

የቀረው የምርመራ ሂደትም በጥብቅ እየተካሄደ እንደሚገኝ የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢2611👍3
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት ሥራ አጥነት ፈታኝ እንደሚሆን የዓለም የሥራ ድርጅት ገለጸ

የዜጎች ማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎት እንዲጨምር ጠይቋል

በትምህርት ያልገፉና የሥራ ልምድ የሌላቸው ወጣቶች በክህሎት ማነስና በራሳቸው ሥራ ለመጀመር በሚገጥማቸው የፋይናንስ ችግር የሥራ ዕድል ዕጦት እንደሚያጋጥማቸው፣ የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) ገለጸ፡፡

የዓለም የሥራ ድርጅት ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከዩናይትድ ኪንግደም ተራድኦ ድርጅት (ዩኤአይድ) እና ከሌሎች ተቋማት በጋራ በመሆን፣ በማኅበራዊ ጥበቃ ላይ ያዘጋጀውን ሪፖርት ይፋ ሲያደርግ ነው ይህንን የገለጸው፡፡በሪፖርቱ መሠረት ቁጥራቸው እያደገ ያለው ሥራ ፈላጊ ወጣቶች፣ በክህሎት ክፍተትና የራስን ቢዝነስ ለመጀመር በሚገጥማቸው የፋይናንስ ዕጦት ከፍተኛ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል፡፡

የሕፃናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ወደ ሥራ ሊገባ የሚገባውን የወጣት ቁጥር የሚያሳድገው በመሆኑ፣ ዕድገቱን ከከተሞች የሥራ ገበያ ዕድል ጋር አጣጥሞና አዋህዶ መሄድ ከፍተኛ ፈተና ይሆናል ብሏል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር 17.6 በመቶ እንደሚደርስ ጠቅሶ፣ አካታችና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ተሳትፎን የሚደግፉ ፖሊሲዎችና መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ለሥራ ብቁ የሆነው የሕዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2015 ከነበረበት 54.7 ሚሊዮን እ.ኤ.አ. በ2025 74.8 ሚሊዮን፣ እ.ኤ.አ. በ2030 ወደ 85.3 እንደሚደርስ ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18😢7👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዋና ከተማ #መቐለ ቀበሌ 17 እናቶች ዋይታና እሪታ እያሰሙ  ወጣቶችን በግዳጅ ታፍሰው ወደ ማሰልጠኛ ተወስደዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢43👍108🤯2🕊1🙊1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
4👍4
አላማጣ አካባቢ አሁናዊ መረጃ ‼️
ዛሬ ሀምሌ 20/2018 ዓ.ም 10፡30 በአላማጣ ገጠራማው ክፍል በሰሌን ውሃ አቅጣጫ በባቡር ሃዲዱ መንገድ የህወሓት ታጣቂዎች በ14 መኪና ተራግፈዋል።
የህወሓት ወታደራዊ አመራር ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነው ጆን መንዲድ ዛሬ ዋጃ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ከዚህ ውጪ የተለየ ነገር የለም።
ህወሃት የፌደራል መንግስቱን ተዋጌቼ እጥላለሁ በሚል በይፋ እንቅስቃሴ መጀመሩን አሳውቋል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊🕊

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍216😢6🎉3🕊2🤯1👌1🤣1👀1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Video
የአሸናፊዎች አሸናፊ ውጊያ ይደረጋል‼️

ህወሃት የ 1983 ታሪክን እንደግማሁ እያለ ነው።

የሕወሓት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ በአንድ መድረክ ላይ አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሁን ከተጣመርናቸው ኃይሎች ጋር መዋጋታችን አይቀርም ብለዋል፡፡ የሀላፊዋ ንግግር የጽምዶ ኃይሎችን የትብብር መሰረት የሚያናጋ ነው ተብሏል፡፡
ወይዘሮ ፈትለወርቅ ቃል በቃል የተናገሩ፡-

‹‹ዋናው ነገር ብልፅግናን ለመጣል ፍላጎት ያሳይ እንጂ የትኛውም ስብስብ እርስ በራሱ እሳትና ጭድ ቢሆንም እንኳን አብረን እንሰራለን። ብልፅግናን ከጣልን በኃላ ደግሞ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመለየት ሌላ ዙር ፍልሚያ ይኖረናል።

ለዚህም እየተዘጋጀን ነው፤ ይህ በተለያየ መልክ የተጀመረውን ትብብራችንን ስናየው የተለያየ ፍላጎት ያለን ሃይሎች ሆነን ነው ትብብር እየፈጠርን ያለነው። በአላማ፣ በፕሮግም፣ ወደፊት በረዥም ጊዜ እቅድ ምናምን አንድ ነን ማለት አይደለም። ትብብራችን በዛች በምታገናኘን ነገር ብቻ ነው።

እኛ ከፋኖ የምንለይበት የፖለቲካ አቋም አለን። ከሻዕቢያ ይሁን ከሌሎች የተለያዩ ሃይሎች የምንለያይባቸው መዓት ጉዳዮች አሉ። አንድ የሚያደርገን ግን የብልፅግና ስርዓት የሁላችንም ስጋት ነው የሚለው ነው። ይቺ ብቻ ናት የምታገናኘን።

እንደ ተሞክሮ ልንወስደው የሚገባን ነገር ደግሞ እንኳን አሁን በብዙ ጉዳዮች ልዩነት ካለንና በዓላማ ከማንገናኛቸው የተለያዩ ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና ኢህአዴግም እኮ ፈርሷል።

ኢህአዴግ እኮ የኦሮሞ፣የአማራ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ሃይሎች አራት ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነን የፈጠርነውና በፕሮግራም ወይም አላማ አንድ የነበረ ድርጅት ነበር። ግንኙነታችንም ስትራቴጂካዊ ነበር[ታክቲካል አልነበረም] ፣ በተለያየ ቋንቋ የተፃፈች አንዲት ፕሮግራም ነበር የነበረችን።

ግንባር ከመሆናችን ውጭ አንድ ድርጅት ማለት ነበርን፤ በዚህ ደረጃ የነበርን ሰዎች እኮ ተካክደናል[እንኳን ይሄ  በዓላማ ከማይመስሉን ሃይሎች ጋር የምንፈጥረው ትብብር ይቅርና]›› ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
Via :- Andafta

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣3216🤯7👍3👀1🤪1🙊1
🚫

ቬትናም ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች በማህበራዊ ሚዲያ ፖስት ማድረግ፣ አስተያየት መስጠትና ይዘት ማጋራት እንዳይችሉ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አቅርባለች። ልጆች ይዘትን ማየት ብቻ ይችላሉ።

ረቂቅ ሕጉ የህጻናት አካውንት በወላጅ ወይም በአሳዳጊ መረጃ እንዲከፈት ያስገድዳል።

ባለሥልጣናት ይህ ሕግ ህጻናትን ፦
- ከስድብ ፣
- ከኦንላይን ማጭበርበር
- ከሌሎች የኢንተርኔት አደጋዎች ለመጠበቅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ረቂቁ ገና የመጨረሻ ውሳኔ አላገኘም።

ነገር ግን ቲክቶክና ሜታ በዚህ ሀሳብ ተቃውመዋል። ሁለቱ ኩባንያዎች " ልጆች አስተያየት እንዳይሰጡ ወይም ፖስት እንዳያደርጉ መከልከል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣል " ያሉ ሲሆን የህጻናትን ዕድሜ ለመለየትና ለመጠበቅ የሚረዱ መረጃዎችን ያሳጣል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍1913💯1🤷1
ቀይ ባህር አደጋ ላይ ወድቋል‼️
በቀይ ባሕር ላይ የመረከቦች እንቅስቃሴ በእጅጉ ቀነሰ።

ሁቲዎች ከሳውዲ ጋር የተገናኙ መርከቦች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃት ማጠናከራቸውን ተከተሎ በቀይ ባሕር ላይ የመረከቦች እንቅስቃሴ በእጅጉ ቀነሰ።

የየመኑ የሁቲ ንቅናቄ በሳውዲ ዓረቢያ የነዳጅ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃቱን በአዲስ መልክ ማጠናከሩን እና ከሳውዲ ጋር ግኑኝነት ባላቸው መርከቦች ላይ የባሕር ላይ ዕገዳ መጣሉን ይታወቃል፡፡

ይህም ክስተት በዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት እና በባሕር ደኅንነት ላይ አዲስ ስጋትን ፈጥሯል።

ሮይተርስ የመርከብ ተከታታይ መረጃዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ትላንት ሐምሌ 20 ቀን በባቢል መንዳብ በኩል ማለፍ የቻሉት 11 የንግድ መርከቦች ብቻ እንደሆኑና ይህም በጥቂት ወራት ውስጥ ዝቅተኛው የዕለታዊ እንቅስቃሴ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሲሆኑ፤ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ያንቡ ወደብ ነዳጅ ለመጫን የሚያመሩ ግዙፍ የክሩድ ነዳጅ ጫኞች ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ አራት መርከቦች ደግሞ የሳውዲ፣ የኤምሬትስ እና የሩሲያ ነዳጅ ጭነው በዋነኝነት ወደ ቻይና እና ፓኪስታን በመጓዝ ላይ የነበሩ ናቸው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
22👍3
🚨በየ5 ደቂቃው ምስል የሚያነሳውና ሰላይ የሆነው የስማርት ፎን ምስጢር ይፋ ሆነ‼️ከሰሜን ኮሪያ በምስጢር ተሰርቆ የወጣ አንድ የስማርት ፎን ስልክ፣ የመንግስቱ አገዛዝ የዜጎቹን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ምን ያህል በአስፈሪ ሁኔታ እንደሚቆጣጠር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርጓል።

ቢቢሲ (BBC) በሴኡል ካለው ዴይሊ ኤንኬ (Daily NK) ከተሰኘው የመገናኛ ብዙሃን ተቀብሎ ባደረገው የቴክኒክ ምርመራ፣ ስልኩ ከተራ መገናኛ መሳሪያነት ይልቅ በኪስ የሚያዝ የወታደራዊ የሰላይ መሳሪያ ሆኖ የተሰራ መሆኑን አረጋግጧል።

ይህ ስልክ ተጠቃሚው የሚያደርገውን ማናቸውንም እንቅስቃሴ በየ5 ደቂቃው በምስጢር ፎቶ (Screenshot) በማንሳት ተጠቃሚው ሊከፍተው ወደማይችለው የተደበቀ ፎልደር ይልካል፤ ይህም መረጃ በመንግስት የደህንነት አካላት ብቻ የሚከፈትና ለቁጥጥር የሚያገለግል ነው።

በተጨማሪም ስልኩ ከማንኛውም የዓለም አቀፍ ኢንተርኔት አውታረ መረብ ጋር በፍፁም እንዳይገናኝ ተደርጎ የተዘጋ በመሆኑ ከውጭ ዓለም የሚመጣ ማናቸውንም መረጃ ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ከዚህም በላይ ተጠቃሚዎች በሚጽፉበት ወቅት ስልኩ በራሱ የቃላት ማረምያ ስልቶችን በመጠቀም ቃላትን ይለውጣል። ለምሳሌ “ኦፓ” (Oppa - በደቡብ ኮሪያ ወንድምን ወይም ፍቅረኛን ለመጠራት የሚያገለግል ቃል) የሚለውን ወደ “ኮምሬድ” (Comrade - ጓድ)፣ እንዲሁም “ደቡብ ኮሪያ” የሚለውን ቃል ወደ “ተላላኪ ሀገር” (Puppet state) በማለት በራሱ ጊዜ አድሶ ይጽፋል።

ይህ መሳሪያ ስልክ ከመሆን ይልቅ የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ዜጎቹ ምን ማንበብ፣ ማወቅ፣ መጻፍ እና መናገር እንዳለባቸው ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የፈጠረው ዘመናዊ የኪስ ውስጥ የክትትልና የቁጥጥር መሳሪያ ነው ተብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍3😡3🤔2😢2
አስደንጋጭ ጥናት‼️፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያ ሴቶች ሚስትን መደብደብን እንደሚያጸድቁ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው አዲስ የዴሞግራፊ እና የጤና ዳሰሳ ጥናት፤ ከግማሽ በላይ (55 በመቶ) የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ አመላክቷል።

ምግብ ማቃጠል፣ መጨቃጨቅ እና ልጆችን ችላ ማለትን ጨምሮ በተዘረዘሩ አምስት ሁኔታዎች ዙሪያ የተደረገው ይህ ጥናት፣ ሚስትን ለመምታት በቂ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ቁጥር 39 በመቶ መሆኑንና ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር በ11 በመቶ መጨመሩን ገልጿል።

በሌላ በኩል፣ ትምህርት እና የቤተሰብ ገቢ ሲጨምር ይህንን አዝማሚያ የመቀበል አመለካከት እየቀነሰ እንደሚሄድ ጥናቱ ያሳያል።

ከሁለተኛ ደረጃ በላይ ትምህርት ካገኙ ሴቶች መካከል እንዲህ የሚያስቡት 29 በመቶው ብቻ ሲሆኑ፤ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ከፍተኛው ቁጥር ሲመዘገብ፣ ሶማሌ ክልል ዝቅተኛውን አሃዝ አስመዝግቧል።

Òየቤት ውስጥ ጥቃትን ተገቢ የሚያደርጉ አመለካከቶችን ለመለወጥ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጠናከር እና የግንዛቤ ሥራዎችን ማስፋፋት እንደ ዋና መፍትሔ ተቀምጧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17🤣13👍4😢3💯2
የገዛ እህቱን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የገዛ እህቱን የአስገድዶ መድፈር  ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሹ በረከት ስዩም የተባለ ሲሆን በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ወካ አራባ ቀበሌ በ"ቡታ" ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በሚገኘው መኖሪያ ቤት የግል ተበዳይ የሆነችውን እህቱን ረድኤት ስዩም ላይ  የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን  ተገልጿል።

ከድርጊቱ በኋላ ለጊምቦ ወረዳ ፖሊስ ጥቆማ በመቅረቡ ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ጉዳዩን አጣርቶ ለጊምቦ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ያስተላልፏል።

ዐቃቤ ሕጉም መዝገቡን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ክሱን ከተመለከተ በኋላ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ መሆኑ ተረጋግጧል።

ፍርድ ቤቱ በቀረበለትን የክስ መዝገብ ተከሳሽን  በ9 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢186👍2
92 ሚሊዮን የሚጠጋ የኢትዮጵያ ሕዝብ "ጤናማ የምግብ ሥርዓት" ለመከተል አቅም እንደሌለው የተመድ የምግብ ዋስትና ሪፖርት አመለከተ።

በኢትዮጵያ ጤናማ የምግብ ሥርዓትን ለማስጠበቅ በነፍስ ወከፍ የሚወጣው ወጪ ከምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛው መኾኑን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ጤናማ የምግብ ወጪ 4 ነጥብ 7 ዶላር እንደነበርና ይህም ከኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛኒያ የበለጠ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ከአውሮፓዊያኑ 2023 እስከ 2025 60 በመቶ ኢትዮጵያዊያን "መካከለኛ" እና "ከፍተኛ" የምግብ ዋስትና እጦት ገጥሟቸው እንደነበርም ሪፖርቱ ጠቅሷል። ሪፖርቱ የትግራይ ክልልን መረጃ አላካተተም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17😢13👍6