አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.1K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
#ቅዱስገብርኤል

በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ተከበረ።

ከማለዳ ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከሀዋሳና ከአካባቢው የመጡ ምዕመናን በቤተክርስቲያን በመገኘት በዓሉን በቅደሴ፣ በጸሎት፣ በዝማሬ እና በተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።

በስፍራው የኃይማኖት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ምዕመናን በኦሮቶዶክሳዊ ስርዓት አልባሳት ደመቀው በዓሉን እያከበሩ ሲሆን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢና በአካባቢው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተሰብስቧል።

የከተማው ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የከተማው አመራሮችም በበዓሉ ላይ የተገኝተዋል።

የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል በሀዋሳ በየዓመቱ በደማቅ መንፈሳዊ ድባብ የሚከበር ሲሆን፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡ ምዕመናንን የሚሰባሰቡበት ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል ነው።

Tikvah

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
36👍6🥰2🤔1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | በሕይወትህ ወደ ስኬት ልትደርስ በትኩረት ስትሠራ እንደ ውሻው የሚያናጥብህ "ወዳጅ" አለህ? ላክለት ይታረም 😅

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣209👍4🤪1
የተከለከሉ ፕላስቲኮችን ሲያከፋፍሉ የተገኙ 46 የምርት አከፋፋዮች መዘጋታቸውን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ

ይህ የተገለጸው ባለሥልጣኑ በትናንትናው ዕለት ባስጀመረው 3ኛ ዙር “ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” የከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ነው።
 
በፕላስቲክ ብክለት ቁጥጥር ሥራ 150 ልዩ ልዩ አካላት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የቅጣት ገንዘብ እንደከፈሉ በመድረኩ ተገልጿል።
 
ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚከለክል መመሪያ ከጥር 23፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሚድረጓ የሚታወቅ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3👍3🥱1
ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ‼️
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት)  ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም መረጃ በማጥፋት፣ በከባድ ሙስና፣ በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው ዘሀበሻ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16👍3
በቦምባይ አውሮፕላን መጸዳጃ ቤት ውስጥ 12 ኪሎ ግራም ወርቅ ደብቀዋል የተባሉ  ሶስት ኢትዮጵያውያን መያዛቸው ተሰማ

​በህንድ ሙምባይ የሚገኘው የገቢዎች ደህንነት መመሪያ (DRI) ባለስልጣናት ከአዲስ አበባ በተነሳ አውሮፕላን መጸዳጃ ቤት ውስጥ በግምት 2.1 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ 12 ኪሎ ግራም ወርቅ በድብቅ ይዘው የገቡ ሶስት የኢትዮጵያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።

​ተጠርጣሪዎቹ አህመድ አብዱራህማን ፣ መሐመድ አብዱራህማን እና ጀሚል ኑሪ መሐመድ የተባሉ ሲሆን ባለፈው ሀሙስ ምሽት  አውሮፕላኑ ሙምባይ እንዳረፈ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል።

ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው ባገኙት ጥቆማ መሰረት ፍተሻ ባካሄዱበት ወቅት በተጠርጣሪዎቹ የእጅ ቦርሳ ውስጥ የአውሮፕላኑን ግድግዳዎች መፍቻ መሳሪያዎችን  አግኝተዋል።

​በተደረገባቸው ጥብቅ ምርመራ፣ ወርቁን በአውሮፕላኑ የኋላ መጸዳጃ ቤት ግድግዳዎች ውስጥ ለመደበቅና በኋላም በአየር መንገድ የጽዳት ሰራተኞች አማካይነት ለማስወጣት ማቀዳቸውን አምነዋል።

ፍተሻውን ተከተሎም 6 የወርቅ ባር ብረቶች ተገኝተዋል።

​ተጠርጣሪዎቹ የህንድን ህግ አያውቁም ቢሉም፣ ፍርድ ቤት በቁጥጥር ስር ውለው እንዲቆዩ ብይን አስተላልፎባቸዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19👍2🎉1
የጣና ሀይቅ በወረርሽኝ አደጋ ላይ መውደቁ ተሰማ

የኢትዮጵያ ትልቁ የንጹህ ውሃ ሀይቅ የሆነው የጣና ሀይቅ ከባድ የስነ-ምህዳር አደጋ አንዣቦበታል። የውሃ አረም ወረርሽኝ ወደ 36 ተጨማሪ ቀበሌዎች በመስፋፋቱ ሀይቁ ለመርከብና እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።

ባለሙያዎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ የውሃ መጠኑ ሊቀንስ እና ልዩ የብዝሃ-ህይወቱ ሊጠፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

እነዚህ ባለሞያዎች እንዳሉት፣ ለአረሙ መባባስ ቁጥጥር መዳከም፣ የአካባቢ መበላሸት እና በሀይቁ ዳርቻ ከሚገኙ ሆቴሎች የሚለቀቁ ቆሻሻዎች ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው። ከዚህ ቀደም የተደረጉ የማህበረሰብ ንቅናቄዎች ስኬታማ ቢሆኑም፣ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት የተጀመረው ስራ መቋረጡ አረሙ ዳግም እንዲስፋፋ አድርጓል።

የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊዎች ችግሩ ትልቅ ፈተና እንደሆነበት አምነዋል። ተቋማዊ ማሻሻያዎች ቢደረጉም፣ የሀብት እና የቁሳቁስ እጥረት ስራውን እንዳቀዛቀፈው ተገልጿል። ሪፖርተር እንደዘገበው ሀይቁን ከክፍለ-ዘመኑ አደጋ ለመታደግ ዘላቂ እና የተቀናጀ የመንግስትና የህብረተሰብ ርብርብ ወሳኝ ነዉ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢2417👍5🤣2🤝1
አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ በሚገኙ 6 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆቹ ትምህርታቸውን ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አራት ተከታትለው ያጠናቀቁ ከ3 ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችንም ትናንት አስመርቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍6🤣63🎉1👌1
ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት) ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም

* መረጃ በማጥፋት፣

* በአረብ ሀገር በህጋዊም ጭምር ሄደው የተለያዩ በደል(መከራ) ሞትን ጭምር ከበዳዮችና ከኤጀቶች ጋር በመመሳጠር ችግሮቹ ሲደርስባቸው ፍትህ እዳያገኙ በማጒተት መከራ ሲያደርስ የነበረው

* በተለይ የማዳም ቅመሞች ጠላት በከባድ ሙስና፣
* በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣

በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
13👍9👌3🤣3🎉1
ህወሃት የድሮን ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ስጋት ብሰባዎቹን በድብቅ እያካሄደ ነው።

ከፍተኛ የህወሃት መሪዎች በድሮን የሚሰነዘር ጥቃት ስጋት ምክንያት መደበኛ ስብሰባዎቻቸውን በድብቅ የመሬት ውስጥ ቦታዎች እያደረጉ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

ይህ እርምጃ የአመራሩን ደህንነት ለማረጋገጥ እና ከአየር ላይ የሚሰነዘር ወታደራዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለመ ነው።

📍 የካቢኔ እና የምክር ቤት ስብሰባዎች በከፍተኛ ሚስጥራዊ የመሬት ውስጥ ሰፈሮች ውስጥ እየተካሄዱ ነው።

📍ጂፒኤስ ወይም በአካባቢ ላይ የተመሰረቱ የስልክ ግንኙነቶችን ወደ ውጭው ዓለም ባለማስተላለፍ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ እየሞከሩ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
15🤣15👍4🤪2👀1🙊1
በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ (TPS) እጣ ፈንታ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተገታ

​የአሜሪካው የፌደራል ዳኛ ብራየን መርፊ የትራምፕ አስተዳደር በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ (TPS) የማቋረጥ ውሳኔ በጊዜያዊነት አግደዋል።

​ዳኛው ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝቅተኛ ፍርድ ቤቶች በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ስልጣን የሚገድብ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት ነው።

የመሀል ሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) ህግ አማካሪ ጄምስ ፐርሲቫል የዳኛውን ውሳኔ "በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ላይ የተደረገ አመፅ" ሲሉ አጥብቀው ተችተዋል።

​ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በነበረው የጦርነትና ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት በ2022 እ.ኤ.አ. ይህንን ጥበቃ ያገኙ ሲሆን፣ አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር በታህሳስ ወር 2025 ጥበቃው እንዲያበቃ ወስኖ ነበር።

​ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በግምት 26,700 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከስደትና ከአስገዳጅ ሀገር የማስወጣት ስጋት በጊዜያዊነት ያገደ ቢሆንም፣ የህግ ክርክሩ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
17👍7
የክፍል አለቃውን የገደለው ታዳጊ በእስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በጅማ ከተማ በሚገኘው ሔርማታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ነው።

የከተማው ፖሊስ እንዳስታወቀው ሙአዝ ቢላል የተባለው ተማሪ የሚማርበትን ክፍል ሲረብሽ ቆይቶ በመስኮት በኩል ከመማሪያ ክፍሉ ዘሎ ወደ ውጭ ይወጣል።

ይህን የተመለከተው የክፍሉ አለቃ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ በማለት ይጠይቀዋል። ድርጊቱም ትክክል እንዳልሆነ ይነግረዋል። በወቅቱ ተማሪውን በመቆጣት የተሰጠውን ሀላፊነት ይወጣል።

በዚህ ምክንያት ሁለቱ ተማሪዎች መካከል ግጭት ይፈጠራል። ልትናገረኝ አይገባም" በማለት የተበሳጨው ተማሪ ሙአዝ ቢላል አስቀድሞ ጩቤ ደብቆ ይዞ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ገብቶ ነበርና የክፍል አለቃ የነበረውን ተማሪ ሙሳብ መሀመድን በያዘው ስለት ወግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋል።

ተከሳሽም በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ተጣርቶበት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሀምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተማሪ ሙአዝ ቢላል ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በ15 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ምንጭ:- የጅማ ከተማ ፖሊስ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
26😱23💔10👍3😢2😡2🤯1🙈1
#ፍርድ

" የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል " - የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ 

‎የሲዳማ ክልል ፍትሕ ቢሮ እንዳስታወቀው የቀድሞ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች  ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ የእስራት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

‎የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እና የፖሊስ ኮሚሽነር ላይ በክልሉ ፍትህ ቢሮ ከሳሽነት በቀረቡ ክሶች ላይ የጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማመሳከር  ተከሳሾቹን ጥፋተኛ ያላቸው፤ ኃላፊዎቹ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ) የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀትና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን በማረጋገጥ ውሳኔ ማስተላለፉን ቢሮው አስታውቋል።

‎በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሐምሌ 20/11/2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጹኑ እስራት እና 4000 ሺ ብር እንዲቀጡ እንዲሁም ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 1 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮው ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍74
ኢሰመጉ፤ በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታወቀ።

ሀገር በቀሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟገች ድርጅት በ37 ገጾች ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂ አካላት ማንነትንና ኃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማልፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል።

በተጨማሪም ከ14,000 በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል።

ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣ በጥቃቶቹ ሳቢያ በየወረዳው የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡

መርቲ ወረዳ፣ 117 ሰዎች፤ ሽርካ ወረዳ፣ 116 ሰዎች፤ ጀጁ ወረዳ፣ 101 ሰዎች ፤ ሮቤ ወረዳ፡ 47 ሰዎች ፤ ጉና ወረዳ፣ 26 ሰዎች ፤ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ 20 ሰዎች ፤ ሙኒሳ ወረዳ፣ 19 ሰዎች ፤ አሰኮ ወረዳ፡ 5 ንጹሃን ዜጎች እና 4 የህዝብ ሚሊሻዎች ፤ አርሲ ሲሬ ወረዳ፣ 3 ሰዎች በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ጉባኤው የሟቾችን ስም ዝርዝር ከነምስላቸው አስደግፎም ነው በሪፖርቱ ይፋ ያደረገው፡፡

ከግድያው ጎን ለጎን በሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ እና ሙኒሳ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ የካሳ ገንዘብ ከፈለው ያስለቀቋቸው ቢኖሩም፤ የበርካቶች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን ሳይታወቅ ቀርቷል። በጥቃቶቹ ወቅት በህጻናትና በአረጋውያን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።

የደህንነት ስጋቱ በዞኑ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ በጀጁ (6,216)፣ በሽርካ (3,746)፣ በአሰኮ (2,133)፣ በሮቤ (1,270)፣ በመርቲ (1,036)፣ በሙኒሳ (29) እና በጉና (21) ወረዳዎች በጠቅላላው ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድቷል። በተጨማሪም ዕድሜ ጠገብ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ መዘረፋቸውንና በስጋት ምክንያት መዘጋታቸውን ይፋ አድርጓል።

ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በህገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶችን የጣሱና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ባህሪያትን የሚያሳይ ነው ብሏል።

በመሆኑም የፌደራልና የክልል መንግስታት ለዜጎች ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ጥሰት ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፈልና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል።

Via_addis maleda

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍16😢115🤯1
የሱዳን ጦር ካርቱምን ከኤል-ኦቤይድ የሚያገናኘውን ዋና መንገድ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ!

የሱዳን ጦር ኃይል ከመዲናዋ ካርቱም ተነስቶ በተቀናቃኙ የፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ከበባ ውስጥ ወደምትገኘው ኤል-ኦቤይድ ከተማ የሚወስደውን ዋና የትራንስፖርት መስመር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ገለጸ።

በእሑድ ዕለት በሱዳን ጦር ኃይል ቁጥጥር ስር የገባው «አል ሳዳራት» የተሰኘው ዋና አውራ ጎዳና  ኃይሉ፤ ወታደሮቹን፣ መሣሪያን፣ የነዳጅ እና የሎጂስቲክስ አቅርቦቶቹን በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የሚረዳው ሲሆን፤ አርኤስኤፍ የሰሜን ኮርዶፋን ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል-ኦቤይድን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ግስጋሴ የሚያግድ ነው ተብሏል።

በከተማዋ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ዜጎች ተከበው የሚገኙ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ ለአርኤስኤፍ የድሮን ጥቃቶች በመጋለጣቸው አሰቃቂ የሰብአዊ ውጥረት ማንዣበቡን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስጠነቅቃል።

የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ አውራ ጎዳናውን ተቆጣጥሮት ከነበረው የአርኤስኤፍ ኃይል ጋር ለሁለት ቀናት ያህል ከተካሄደው ከፍተኛ ውጊያ በኋላ፣ በካርቱም እና በኤል-ኦቤይድ መካከል የሚገኙ በርካታ ከተሞችንና መንደሮችን መልሶ መቆጣጠር ተችሏል።

Via_AS

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍2😢1
ግሎባል ባንክ በገንዘብ ተቀማጭ እና የሊኲዲቲ  አያያዝ ላይ የተነሳውን ጥርጣሬ ተክቶ ባካሄደው ምርመራ የባንኩን ፕሬዝዳንት  ተስፋዬ ቦሩን ጨምሮ 18 ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አግዷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኩ  በሚሊዮኖች የሚቆጠር የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወጥቷል በሚል የጀመረውን ማጣራት ተከተሎ፣ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ የራሱን ምርመራ በማካሄድ አቶ ሳህለሚካኤል መኮንንን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ሾሟል።

​ባንኩ እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ ሀብቱን በ42 በመቶ በማሳደግ 34.43 ቢሊዮን ብር ማድረሱ እና ከታክስ በኋላ 756.6 ሚሊዮን ብር አትርፎ የነበረ ቢሆንም፣ የገጠመው የከፍተኛ አመራሮች እግድ እና የቁጥጥር ክፍተት የቀውሱ መንስኤ ሆኗል።

ባለሙያዎች ባንኩ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ገንዘቦች ላይ ከመጠን በላይ መደገፉን በመጥቀስ፣ ጠንካራ የቦርድ ቁጥጥር እና ነፃ የባንክ ባለሙያዎች እንዲካተቱ አሳስበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
6👍4🤪1