መረጃ‼️
የፌደራል ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን፣ ሁሉም የሲቪል ሠርቪስ መስሪያ ቤቶች የሠራተኞቻቸውን ማስረጃዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያረጋግጡ አሳሰበ።
ኮሚሽኑ፣ "የተሳሳቱ" የመንግሥት ሠራተኞች መረጃዎች መንግሥት አስተማማኝ የሠራተኛ መረጃ እንዳይኖረውና ለትክክለኛ ሠራተኞች ብቻ ደሞዝ እንዳይከፍል እንቅፋት ኾኖበታል ሲል ዛሬ በጉዳዩ ዙሪያ በተወያየ መድረክ ላይ ገልጧል።
ኮሚሽኑ ለሁሉም መስሪያ ቤቶች አዲስ በዘረጋው ሥርዓት መሠረት፣ እያንዳንዱ የመንግሥት ሠራተኛ ልዩ የመለያ ቁጥር ይኖረዋል።
የሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሠራተኞቻቸውን መረጃዎችና ማስረጃዎች በዲጂታል ሥርዓት እንዲይዙ አሳስበዋል።
@Addis_Reporter

❤20👍2
ኢትዮጵያ፣ በዓለም ባንክ የካርበን ልቀት ቅነሳ ፕሮግራም ሥር ከልቀት የቀነሠችውን ካርበን ለሽያጭ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አገር ኾነች።
ዓለም ባንክ፣ ኢትዮጵያ "የተረጋገጠ" 14 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን የካርበን ልቀት መቀነሷን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በባንኩ ድጋፍ በሚተገበረው የደን መመናመንን በመግታትና የአካባቢ ጥበቃን በማጠናከር የካርበን ልቀትን የመቀነስ ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር ግምገማ መቀነስ የቻለችው የካርበን ልቀት መጠን፣ ከአገሪቱ ለመግዛት ከታሠበው ካርበን የበለጠ መኾኑን ባንኩ ጠቅሷል።
የባንኩ ማረጋገጫ፣ አገሪቱ ከዓለማቀፍ የካርበን ገበያ ተጨማሪ ገንዘብ እንድታሰባስብ እድል ይፈጥርላታል ተብሏል።
ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ እስከ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ የካርበን ግዥ ስምምነት ከሦስት ዓመት በፊት የተፈራረሙ ሲኾን፣ የስምምነቱ ግብ በኦሮሚያ ክልል ከሚተገብረው ፕሮግራም እስከ አውሮፓዊያኑ 230 ድረስ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀት መቀነስ ነው።

❤10👍4🤪4🤣2🤔1
#ሰበር #ዜና
ኢራን ለኢንግሊዝ ሰጥታ የነበረውን ማስጠንቀቂያ አሁን ተገበረችው።
ቀደም ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኃይል (IRGC) ከኢራን በ4,000 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው የእንግሊዝ ዋና ምድር 'RAF Fairford' ወታደራዊ ጣቢያ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
ሆኖም እንግሊዝ ማስጠንቀቂያውን ችላ በማለቷ የተነሳ ኢራን ስፍራው ላይ በመጠን ያልተገመተ እርምጃ መውሰዷን በቦታው የሚገኙ አንዳንድ የአይን እማኞች እየገለፁ ይገኛሉ ሲል የዘገበው አልአይን ዜና ነው።

❤19👍11😱3🤣3👀1🙈1🤪1🙉1
#ቅዱስገብርኤል
በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ተከበረ።
ከማለዳ ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከሀዋሳና ከአካባቢው የመጡ ምዕመናን በቤተክርስቲያን በመገኘት በዓሉን በቅደሴ፣ በጸሎት፣ በዝማሬ እና በተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።
በስፍራው የኃይማኖት አባቶች፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና ምዕመናን በኦሮቶዶክሳዊ ስርዓት አልባሳት ደመቀው በዓሉን እያከበሩ ሲሆን በቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢና በአካባቢው እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተሰብስቧል።
የከተማው ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የከተማው አመራሮችም በበዓሉ ላይ የተገኝተዋል።
የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል በዓል በሀዋሳ በየዓመቱ በደማቅ መንፈሳዊ ድባብ የሚከበር ሲሆን፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚመጡ ምዕመናንን የሚሰባሰቡበት ታላቅ ኃይማኖታዊ በዓል ነው።
Tikvah

❤36👍6🥰2🤔1🙏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral | በሕይወትህ ወደ ስኬት ልትደርስ በትኩረት ስትሠራ እንደ ውሻው የሚያናጥብህ "ወዳጅ" አለህ? ላክለት ይታረም 😅
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣20❤9👍4🤪1
የተከለከሉ ፕላስቲኮችን ሲያከፋፍሉ የተገኙ 46 የምርት አከፋፋዮች መዘጋታቸውን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ
ይህ የተገለጸው ባለሥልጣኑ በትናንትናው ዕለት ባስጀመረው 3ኛ ዙር “ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ” የከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ነው።
በፕላስቲክ ብክለት ቁጥጥር ሥራ 150 ልዩ ልዩ አካላት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የቅጣት ገንዘብ እንደከፈሉ በመድረኩ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚከለክል መመሪያ ከጥር 23፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሚድረጓ የሚታወቅ ነው።

❤3👍3🥱1
ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ‼️
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት) ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም መረጃ በማጥፋት፣ በከባድ ሙስና፣ በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው ዘሀበሻ ነው።

❤16👍3
በቦምባይ አውሮፕላን መጸዳጃ ቤት ውስጥ 12 ኪሎ ግራም ወርቅ ደብቀዋል የተባሉ ሶስት ኢትዮጵያውያን መያዛቸው ተሰማ
በህንድ ሙምባይ የሚገኘው የገቢዎች ደህንነት መመሪያ (DRI) ባለስልጣናት ከአዲስ አበባ በተነሳ አውሮፕላን መጸዳጃ ቤት ውስጥ በግምት 2.1 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ 12 ኪሎ ግራም ወርቅ በድብቅ ይዘው የገቡ ሶስት የኢትዮጵያ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ።
ተጠርጣሪዎቹ አህመድ አብዱራህማን ፣ መሐመድ አብዱራህማን እና ጀሚል ኑሪ መሐመድ የተባሉ ሲሆን ባለፈው ሀሙስ ምሽት አውሮፕላኑ ሙምባይ እንዳረፈ ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል።
ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው ባገኙት ጥቆማ መሰረት ፍተሻ ባካሄዱበት ወቅት በተጠርጣሪዎቹ የእጅ ቦርሳ ውስጥ የአውሮፕላኑን ግድግዳዎች መፍቻ መሳሪያዎችን አግኝተዋል።
በተደረገባቸው ጥብቅ ምርመራ፣ ወርቁን በአውሮፕላኑ የኋላ መጸዳጃ ቤት ግድግዳዎች ውስጥ ለመደበቅና በኋላም በአየር መንገድ የጽዳት ሰራተኞች አማካይነት ለማስወጣት ማቀዳቸውን አምነዋል።
ፍተሻውን ተከተሎም 6 የወርቅ ባር ብረቶች ተገኝተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ የህንድን ህግ አያውቁም ቢሉም፣ ፍርድ ቤት በቁጥጥር ስር ውለው እንዲቆዩ ብይን አስተላልፎባቸዋል።

❤19👍2🎉1
የጣና ሀይቅ በወረርሽኝ አደጋ ላይ መውደቁ ተሰማ
የኢትዮጵያ ትልቁ የንጹህ ውሃ ሀይቅ የሆነው የጣና ሀይቅ ከባድ የስነ-ምህዳር አደጋ አንዣቦበታል። የውሃ አረም ወረርሽኝ ወደ 36 ተጨማሪ ቀበሌዎች በመስፋፋቱ ሀይቁ ለመርከብና እንቅስቃሴ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።
ባለሙያዎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ የውሃ መጠኑ ሊቀንስ እና ልዩ የብዝሃ-ህይወቱ ሊጠፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
እነዚህ ባለሞያዎች እንዳሉት፣ ለአረሙ መባባስ ቁጥጥር መዳከም፣ የአካባቢ መበላሸት እና በሀይቁ ዳርቻ ከሚገኙ ሆቴሎች የሚለቀቁ ቆሻሻዎች ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው። ከዚህ ቀደም የተደረጉ የማህበረሰብ ንቅናቄዎች ስኬታማ ቢሆኑም፣ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት የተጀመረው ስራ መቋረጡ አረሙ ዳግም እንዲስፋፋ አድርጓል።
የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊዎች ችግሩ ትልቅ ፈተና እንደሆነበት አምነዋል። ተቋማዊ ማሻሻያዎች ቢደረጉም፣ የሀብት እና የቁሳቁስ እጥረት ስራውን እንዳቀዛቀፈው ተገልጿል። ሪፖርተር እንደዘገበው ሀይቁን ከክፍለ-ዘመኑ አደጋ ለመታደግ ዘላቂ እና የተቀናጀ የመንግስትና የህብረተሰብ ርብርብ ወሳኝ ነዉ።

😢24❤17👍5🤣2🤝1
አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ በሚገኙ 6 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆቹ ትምህርታቸውን ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አራት ተከታትለው ያጠናቀቁ ከ3 ሺህ በላይ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞችንም ትናንት አስመርቋል።

👍6🤣6❤3🎉1👌1
ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ‼
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት) ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም
* መረጃ በማጥፋት፣
* በአረብ ሀገር በህጋዊም ጭምር ሄደው የተለያዩ በደል(መከራ) ሞትን ጭምር ከበዳዮችና ከኤጀቶች ጋር በመመሳጠር ችግሮቹ ሲደርስባቸው ፍትህ እዳያገኙ በማጒተት መከራ ሲያደርስ የነበረው
* በተለይ የማዳም ቅመሞች ጠላት በከባድ ሙስና፣
* በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣
በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ ይገኛል።

❤13👍9👌3🤣3🎉1
ህወሃት የድሮን ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ስጋት ብሰባዎቹን በድብቅ እያካሄደ ነው።
ከፍተኛ የህወሃት መሪዎች በድሮን የሚሰነዘር ጥቃት ስጋት ምክንያት መደበኛ ስብሰባዎቻቸውን በድብቅ የመሬት ውስጥ ቦታዎች እያደረጉ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።
ይህ እርምጃ የአመራሩን ደህንነት ለማረጋገጥ እና ከአየር ላይ የሚሰነዘር ወታደራዊ ጥቃትን ለመከላከል ያለመ ነው።
📍 የካቢኔ እና የምክር ቤት ስብሰባዎች በከፍተኛ ሚስጥራዊ የመሬት ውስጥ ሰፈሮች ውስጥ እየተካሄዱ ነው።
📍ጂፒኤስ ወይም በአካባቢ ላይ የተመሰረቱ የስልክ ግንኙነቶችን ወደ ውጭው ዓለም ባለማስተላለፍ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ እየሞከሩ ነው።

❤15🤣15👍4🤪2👀1🙊1
በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ (TPS) እጣ ፈንታ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተገታ
የአሜሪካው የፌደራል ዳኛ ብራየን መርፊ የትራምፕ አስተዳደር በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ (TPS) የማቋረጥ ውሳኔ በጊዜያዊነት አግደዋል።
ዳኛው ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝቅተኛ ፍርድ ቤቶች በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ስልጣን የሚገድብ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት ነው።
የመሀል ሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) ህግ አማካሪ ጄምስ ፐርሲቫል የዳኛውን ውሳኔ "በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ላይ የተደረገ አመፅ" ሲሉ አጥብቀው ተችተዋል።
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በነበረው የጦርነትና ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት በ2022 እ.ኤ.አ. ይህንን ጥበቃ ያገኙ ሲሆን፣ አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር በታህሳስ ወር 2025 ጥበቃው እንዲያበቃ ወስኖ ነበር።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በግምት 26,700 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከስደትና ከአስገዳጅ ሀገር የማስወጣት ስጋት በጊዜያዊነት ያገደ ቢሆንም፣ የህግ ክርክሩ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥሏል።

❤17👍7
የክፍል አለቃውን የገደለው ታዳጊ በእስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት‼
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በጅማ ከተማ በሚገኘው ሔርማታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ነው።
የከተማው ፖሊስ እንዳስታወቀው ሙአዝ ቢላል የተባለው ተማሪ የሚማርበትን ክፍል ሲረብሽ ቆይቶ በመስኮት በኩል ከመማሪያ ክፍሉ ዘሎ ወደ ውጭ ይወጣል።
ይህን የተመለከተው የክፍሉ አለቃ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ በማለት ይጠይቀዋል። ድርጊቱም ትክክል እንዳልሆነ ይነግረዋል። በወቅቱ ተማሪውን በመቆጣት የተሰጠውን ሀላፊነት ይወጣል።
በዚህ ምክንያት ሁለቱ ተማሪዎች መካከል ግጭት ይፈጠራል። ልትናገረኝ አይገባም" በማለት የተበሳጨው ተማሪ ሙአዝ ቢላል አስቀድሞ ጩቤ ደብቆ ይዞ ወደ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ገብቶ ነበርና የክፍል አለቃ የነበረውን ተማሪ ሙሳብ መሀመድን በያዘው ስለት ወግቶ ህይወቱ እንዲያልፍ ያደርጋል።
ተከሳሽም በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ተጣርቶበት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሀምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተማሪ ሙአዝ ቢላል ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ በ15 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ምንጭ:- የጅማ ከተማ ፖሊስ

❤26😱23💔10👍3😢2😡2🤯1🙈1