አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
መረጃ‼️

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የአበባ፣ የፍራፍሬ እና የአትክልት ምርት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አገኘች።

አገሪቱ በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ ካገኘችው 490 ሚሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ውስጥ፣ የአበባ ምርት 412 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ከፍተኛውን ድርሻ መያዙን ግብርና ሚንስቴር አስታውቋል።

ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የአትክልት ምርቶች 57 ሚሊዮን ዶላር ሲገኝ፣ ከፍራፍሬ ምርቶች ደሞ 21 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ኾኖም አገሪቱ ይህን ገቢ ያገኘችው ምን ያህል ቶን ምርቶች ለውጭ ገበያ አቅርባ እንደሆነ ሚንስቴሩ አልጠቀሠም።

ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት 357 ሺሕ 457 ቶን አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ለውጭ ገበያ በማቅረብ፣ 575 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳለች ተብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍2👀1🤪1
የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፎቼን ለመቀጠል 182 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ።

ድርጅቱ፣ በተያዘው አውሮፓዊያን ዓመት ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታዎቹ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጧል።

እስከ ቀጣዩ ነሃሴ ወር በአገሪቱ ውስጥ የስብዓዊ እርዳታውን ለማስቀጠል ለእያንዳንዱ የምግብ እህል ተረጂ ከመደበው መደበኛ ራሽን ላይ 60 በመቶውን ለመቀነስ እንደተገደደም ድርጅቱ ጠቅሷል።

የአገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ የኾነው፣ ግጭት፣ መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ እና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ጫናዎች በተጋላጭ ማኅበረሰቦች ላይ በሚያሳድሩት ጉዳት ሳቢያ ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍5😢21
ለ17 ዓመታት በሕመም ፈቃድ 1 ሚሊዮን ዩሮ የተቀበለችው መምህርት ትምህርት ቤቷን ከሰሰች

በጀርመን የምትገኝ የ62 ዓመት የሙያ ትምህርት ቤት መምህርት ለ17 ዓመታት በሕመም ፈቃድ ላይ ሆና 1 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ደመወዝ ከተከፈላት በኋላ፣ ትምህርት ቤቱ በጡረታ በማሰናበቱ ምክንያት ክስ አቀረበች።

መምህርቷ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት ገብታ የማታውቅ ቢሆንም፣ የሕክምና ማስረጃዎችን እያቀረበች ሙሉ ደመወዟን ስትቀበል ቆይታለች።

አዲሱ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ባደረገው ማጣራት ግን በእነዚህ ሁሉ ዓመታት በአስገዳጅ የመንግስት ሕክምና ምርመራ እንድታልፍ አለመደረጉ ተገልጧል።

​በተጨማሪም መምህርቷ በሕመም ፈቃድ ላይ በነበረችበት ጊዜ የግል የሕክምና ድርጅት ከፍታ ስትሰራ እንደነበር ተጠራጥሮ የዱይስበርግ ግዛት ዐቃቤ ሕግ ምርመራ ጀምሮባታል።

ማጭበርበሯ ከተረጋገጠ የተከፈላትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንድትመልስና በወንጀል እንድትጠየቅ ሊደረግ ይችላል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።

Via fidel

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤪5👍3🤣1🙊1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ኤርትራ ለህወሓት ባለው መሳሪያ ጦርነቱን ጀምሩ ብሏቸዋል -ጌታቸው ረዳ‼️
(ሙሉበሙሉ ከጌታቸው ፖስት ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው .... ሌላ የግል  አስተያየት አልተጨመረበትም )...
--
ሻቢያን በእግራቸው የማይራመዱ ሽማግሌ ወታደሮች ናቸው ያሉት ሲል ዘርጥጧቸዋል።
"....ደብረጽዮን በቅርቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ ኢሳያስ አፈወርቂን ጦርነት ለመጀመር ለእያንዳንዱ ታጣቂ 4 ካርታ የጥይት (120ጥይት) ) እንዲሰጠው ጠይቋል ይላል።
የኢሳያስም አሁን  “ባለህ ነገር ጀምር፤ ከዚያ የሚያስፈልገው  ይላክልሃል  እንዳለው ገልጿል።
በ2014 በምዕራብ ግንባር ስለሚደረግ ውጊያ በተደረገ የኮማንድ ፖስት ስብሰባ
አንድ የጦር ኃላፊ የጥይት እጥረት እንዳለ ገለፀ።፣ የጥይት አቅርቦት የደብረጽዮን ኃላፊነት ስለነበር ደብረጽዮን የሎጂስቲክስ ኃላፊውን አለምሰገድ ሃደራን

“ስንት ጥይት አለን?” ሲል ጠየቀ።
“11 ሚሊዮን ጥይት ይኖረናል፤ የዲሽቃ ጥይት ግን አነስተኛ  ነው ብሎ መለሰ

ከዚያ ደብረጽዮን፣ “የጠላት ኃይል ስንት ነው?” ብሎ ተወልደ ዕምባብን ጠየቀ።

ተወልደ ዕምባብም

“ፋኖ፣ የኢትዮጵያ መከላከያና የሻዕቢያ ሰራዊትን ጨምሮ 1.1 ሚሊዮን ያህል ይሆናል።”

ከዚያ ደብረጽዮን፣ “የሰራዊታችን ዒላማ የመምታት ውጤት (hit rate) ስንት ነው?” ብሎ ታደሰን ጠየቀ።

ታደሰ (ወዲ ወርደ) እንዲህ ሲል መለሰ፦

“ከ60 እስከ 70 በመቶ ይመታል።”

ከዚያ በኋላ ደብረጽዮን" እንግዲህ ሁሉንም የመጣውን ጠላት ካጠፋን፣ 30% ጥይት ይተርፈናል።” ብሎ ተናገረ
--
እኔም  ሃሳቡን ተቃውሜና ተገርሜ
“ጠላት ተር ብሎ እየመጣ አንድ በአንድ ነው እንዴ የምንመታው?”  ብየ ስጠይቅ

ወዲ ወርደ
“ተወው፤ ያውራ።” ስላለኝ ዝምአልኩ

ከዚያ ስብሰባ በኋላ፣ ደብረጽዮን
“በሰራዊቱ ፊት እኛን በመቃወም ወታደሮቹ እንዲደፍሩንና እንዲያቃልሉን አድርገሃል።” ብሎ  ወቅሶኛል 
--
በጸሎት ወይም በመጠበቅ ብቻ ለውጥ አይመጣም ስለዚህ  የትግራይ ሕዝብ ። እነዚህን ኃይሎች (እነ ደብረፂዮንን) ለማስወገድ  ጊዜው አሁን ነው
--
ደብረፂዮን ማለት በትግራይ ላይ የወረደ እርግማን ነው ይልና...
"..ሕዝባችን ይጥፋ ወይስ ክፉ ተግባር የሚፈጽሙት ይጥፉ?” ብሎ ይደመድማል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
29🤣17👍5🤪3🤔1🤯1🕊1😍1🙊1
ሂውማን ራይትስ ዎች በዌስት_ባንክ የሰፈሩ የእስራኤል ዜጎች የሚያካሂዱት ጥቃት ትልቅ እልቂት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች በዌስት ባንክ አካባቢዎች የሰፈሩ የእስራኤል ዜጎች የሚያካሂዱት ጥቃት እየጨመረ በመምጣቱ ተጨማሪ እልቂቶችን ሊያስከትል እንደሚችል በማስጠንቀቅ የእስራኤል መንግሥት ጥቃቶችን ከመከላከል መቆጠቡን እና ተጠያቂነት ላለመኖር ድርጊቶች መንገድ መክፈቱን ከሰሰ።

ሐምሌ 17 በወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ ናብሉስ አቅራቢያ በሚገኘው የታል የፍልስጤም መንደር ላይ በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች የአራት ፍልስጤማውያን እና የሁለት እስራኤላውያን ሕይወት ማለፉን ገልጿል።

የመብት ተሟጋች ቡድኑ እንደገለጸው፣ የቅርብ ጊዜው ጥቃት፤ በአካባቢው የሰፈሩ የታጠቁ እስራኤላውያን በፍልስጤም ማህበረሰቦች ላይ ጥቃት የሚያሰነዝሩበትን፣ የእስራኤል ወታደሮች ደግሞ በጥቃቱ የሚሳተፉበትን ወይም ጣልቃ ከመግባት የሚቆጠቡበትን ሰፊ ክስተት ያመላክታል። በጥቃቶቹ ላይ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ከእስራኤል መንግሥት የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የሕግ ድጋፍ እንደሚያገኙ ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3😢2
ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ ያናግሩን 👇
@Addis_reporter_bot
👍21👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መነጋገሪያ የሆነው ቪዲዮ‼️
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው  ወታደራዊ ስልጠና ተከትሎ የተለቀቀው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።
ይህ ከላይ የሚታው ቪዲዮ ወታደራዊ ስልጠና ሲሆን ይህ ስልጠና ከደን ቅጠል ጋር በመመሳሰል (Leafe Mimicry) ከድሮን ጥቃት ለማምለጥ የተደረገ ያለ ስልጠና ነው ተብሏል።
Leafe mimicry በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ተግባራዊ ተደርጎ እንደነበር ይነገራል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍29🤣2512😢8🤔1👀1🙈1
የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ‼️         
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና /National Graduate Admission Test/ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ለመውሰድ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው ከሀምሌ 15 – 25/2018 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ  ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለፈተናውም አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንክ፡-  https://ngat.ethernet.edu.et

#ማሳሰቢያ:-
ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ።

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር (ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) መሆኑን አውቃችሁ በቴሌ ብር በኩል በምዝገባው ወቅት የሚፈጸም       ይሆናል                                                      
ምዝገባው የሚከናወነው በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የፈተና ጣቢያውን በሚመለከት ግን ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ በስታንዳርዱ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9👍2🥰1🙏1
በቢሾፍቱ የኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ዘረፋ የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ‼️
 
በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ውስጥ በኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ዘረፋ የፈጸሙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።የከተማው አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ምርመራ ሂደት እንዳስታወቀው፣ ተከሳሾች ሃሮን ዮሴፍ እና ተገኔ ተሾመ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆኑ የሲሲቲቪ ኬብል ሽቦዎችን ዘርፈው ሊሰወሩ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
 
ወንጀሉ የተፈጸመው በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ኤረር ወረዳ «ጎልደን ሆቴል» ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ላይ መሆኑ ተገልጿል።ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን፣ አቃቤ ሕግም የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 464/2005 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 4ን በመጥቀስ በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ላይ ክስ መስርቶባቸዋል።
 
ጉዳዩን የተመለከተው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ተከሳሾቹ በሕዝብ መሰረተ ልማት ላይ የፈጸሙት የዘረፋ ወንጀል በአቃቤ ሕግ ማስረጃ በበቂ ሁኔታ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤪6👍5🙊3🤣1
ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል

በሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሐምሌ 19 በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓልን ተከትሎ፣ ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶች እንደሚዘጉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ከዛሬ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከአሁን 9:00 ጀምሮ በዓሉ ተጠናቆ እስኪያበቃ ድረስ ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስገቡ መንገዶች ለሁሉም የትራፊክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዝግ ይሆናሉ።

- ከሳውዝ ስታር (መስቀል አደባባይ)፣
- ከሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር፣
- ከትሩፋ በሎጊታ፣
- ከጤና ቢሮ (ማር ሲል)፣
- ከክብሩ ሆስፒታል፣
- ከፒያሳ ዳሽን ባንክ፣
- ከታቦር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) የሚያቀኑ መስመሮች በሙሉ ይዘጋሉ።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች የመንገድ መዘጋቱን አስቀድመው በመገንዘብ አማራጭ መስመሮችን እንዲጠቀሙ፣ ከፀጥታ አካላት ጋርም በመተባበር የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍84
የሳኡዲው ልዑል አብደላህ ቢን ፋህድ
በለንደን ሆቴል ሞቶ ተገኘ

በለንደን ኬንሲንግተን በሚገኘው ማሪዮት ሆቴል የ29 ዓመቱ የሳዑዲ ልዑል አብደላህ ቢን ፋህድ ሕይወት ማለፉን የብሪታንያ የሕክምና ምርመራ ባለሥልጣን  አስታወቀ።

ዋና ዋና ነጥቦች፡

    የሞቱ ምክንያት፡ ታህሳስ 15 ቀን 2025 (እ.አ.አ) በሆቴል መታጠቢያ ቤት ውስጥ ሞቶ  ሆኖ የተገኘው ልዑሉ፣ ሕይወቱ ያለፈው ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል እና የአደንዛዥ ዕፅ  ከአልኮል ጋር በመቀላቀሉ በተከሰተ የልብ ምት መቆም ነው።

    የተገኙ ንጥረ ነገሮች፡ በደም ምርመራው መሰረት ከአልኮል እና ከGHB በተጨማሪ የካናቢስ እና የጭንቀት ማስታገሻ መድሃኒቶች (እንደ Xanax ያሉ) በስርዓተ-ህዋሱ ውስጥ ተገኝተዋል።

    የህክምና ታሪክ፡ ልዑሉ ከዚህ ቀደም ከአልኮልና ከሐኪም ማዘዣ መድሃኒቶች ሱሰኝነት ጋር ይታገል ነበር፤ በለንደን እና በሰሜን ማገገሚያ ማዕከላትም ሕክምናዎችን ተከታትሎ ነበር።

    የባለሥልጣኑ ውሳኔ፡ የሕክምና ባለሙያዎች እሱ ከህክምና ሲወጣ ራሱን የማጥፋት አደጋ ላይ እንዳልነበር ቢናገሩም፣ ረዳት ባለሥልጣኑ ጂን ሀርኪን ክስተቱን እንደ «አደጋ»  ፈርጀውታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24😢8🤩4👍2🤣2🤝2🥰1🎉1
የገጠመን የህልውና አደጋ ነው:- ደብረፂዮን‼️
በፌዴራል መንግሥቱ የተቋቋመውን ጊዚያዊ አስተዳደር አፍርሶ ስልጣን የያዘው የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት ዶክተር ደብረፂዮን ምክር ቤቱን ሰብስበው አወያይተዋል።

በዚህም "የፌደራል መንግስቱ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ የትግራይ ህዝብን ዳግም ለመውረር እየሰራ ይገኛል ብሏል።

የትግራይ ህዝብ አሁን ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመታደግና ያሉትን መሰረታዊ እና ወሳኝ የህዝብ ጥያቄዎች በመመለስ የትግራይ ህዝብ ህልውናን ለማረጋገጥ ለነገ  የማይባል ስራ መሆኑን ተገንዝበን  እነዚህን የህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ መንግስት በቁርጠኝነት ለመስራት እቅድ መያዙንም ዶ/ር ደብረፂዮን ተናግረዋል ፡፡ 

አሁን ላይ ያጋጠመንን የህልውና አደጋ በመመከት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በማረጋገጥ  በኢኮኖሚ እራስዋን የቻለች ትግራይን በመፍጠር የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲፋጠን በትኩረት እንደሚሰራም ለምክርቤቱ አብራርተዋል"።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
🤣2321👍5😢1🎉1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የደቡብ ወሎ ገዳም ጥቃትን በተመለከተ ፓትርያርኩ መግለጫ አወጡ፤ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጠየቁ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ላይ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫቸው፣ በጥቃቱ የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፣ በርካቶች መቁሰላቸውን እና በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ላይ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን መስማታቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይም፣ በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ በመግለጽ ድርጊቱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ፓትርያርኩ እንዳሉት፣ የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ኃላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላትም የሚመለከታቸው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፣ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ እና ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም፣ ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በስብአዊ ድጋፍ እንዲቆሙ አሳስበው፣ ለተበደሉት ፍትሕ፣ ለቆሰሉት ፈውስ፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለሀገሪቱ ፍጹም ሰላም እንዲሰጥ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
44👍13🎉2🙏2👌1