አዲስ ሪፖርተር - NEWS
36.2K subscribers
17.1K photos
418 videos
21 files
3.01K links
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !

=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !

🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addisreporter_bot

#ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Download Telegram
ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ‼️
👉በ21ኛው ክ/ዘመን መኪና ሲገፉ/ሲጎትቱ/ ማየት አሳፋሪ ነው።
👉በሶስት አመት ይጠናቀቃል የተባለው መንገድ 8 አመት ሆነው።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማ በር-መለያያ-ሰፌድ ሜዳ -ሞላሌ-ወገሬ የመንገድ ግንባታ ስራ ከተጀመረ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል።

118 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የጣርማ በር-መለያያ-ሰፌድ ሜዳ -ሞላሌ-ወገሬ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በ1.9 ቢሊዮን ብር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ የመንገድ ግንባታ ስራው የተጀመረው ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ነበር።
📌አሁን ላይ የመንገድ ስራው ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፣የስራ አፈፃፀሙም ከ25% አላለፈም።
📌ይህ የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው መንገድ ይሰራል ተብሎ የመሰረተ ድንጋይ ተጥሎ የተጀመረ ሰሞን የነበረው የህዝቡ ደስታ ወደ እርግማን ተቀይሯል፣ህዝቡም ተስፋ ቆርጧል።
📌መንገዱ ያለተለዋጭ መንገድ በየቦታው በመቆፈሩ ለጥገና አስቸጋሪ ሆኗል፣ዝናብ በጣለ ቁጥር መኪና የተባለ ሙሉ መልኩን ቀይሮ፣በጭቃ ዋና ዋኝቶ፣በህዝቡ ተገፍቶ፣ተጎትቶ ነው የሚወጣው።
📌ስራው ሳይጀመር በፊት ወደ ደብረብርሃን 4 ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ስምንት ሰዓት ይፈጅ የነበረው መንገድ አሁን ላይ 118 ኪሎሜትር መንገድ ወደ ደብረብርሃን ለመምጣት 10 ሰዓት ይፈጃል።
📌ለግንባታው የቀረቡ ግብዓቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
ይህ የመንገድ ስራ ከኮንትራክተር ጀምሮ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም የሚመለከተው አካል ከህዝቡ ጋር መክሮ ዘክሮ የህዝቡን እምባ ሊያብስ የሚችል ስራ መስራት ይጠበቅበታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
18🤣6👍4🥰1😢1
ጋምቤላ 💰 ወርቅ

ከጋምቤላ ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሆኗል

በጋምቤላ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 6 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ፣ ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ቢሮ አስታውቋል።

የተመዘገበው ውጤት ከእቅዱ በ1,098 ኪሎ ግራም፣ ከቀዳሚው ዓመት ደግሞ በ1,669 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

በበጀት ዓመቱ በተከናወነ የማዕድን ልማትም ከ6,890 በላይ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ቢሮው መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍5
#OpenAI

በደኅንነት ፍተሻ ወቅት የAI ሞዴል ከሙከራ ገደቡ አምልጦ በሌላ የAI ተቋም ላይ የሳይበር ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።


የChatGPT አምራች የሆነው OpenAI እጅግ የላቁ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎቹ በደኅንነት ፍተሻ ወቅት ያልተጠበቀ ባህሪ በማሳየት ሌላ የAI ተቋም የሳይበር ጥቃት መፈጸማቸውን (ሀክ ማድረጋቸውን) ይፋ አድርጓል።

ኩባንያው እንደገለጸው፣ የሰው ልጅ መመሪያ ከሰጠው በኋላ ብቻውን ሊሠራ የሚችል የAI ሥርዓት ቁጥጥር በሚደረግበት አካባቢ ፍተሻ እየተደረገለት ሳለ ድክመቶችን በማግኘቱ ከሙከራ ገደቦቹ ማምለጥ ችሏል።

ጥቃቱ የደረሰው በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ የሰው ሠራሽ (AI) ሞዴሎች አምራች በሆነው Hugging Face ላይ ሲሆን የኮምፒውተር ሥርዓቱ ውስጥ ዘልቀው መግባት መቻላቸው ተነግሯል።

OpenAI ክስተቱ " ከዚህ በፊት ያልታየ " መሆኑን ገልጾ፣ ከHugging Face ጋር በመተባበር ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል።

የHugging Face ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክሌመንት ዴላንጌም "ይህ ሁሉ በራሱ መከሰቱ በጣም አስደንጋጭ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

በሳይበር ደኅንነት ዘርፍ የሚሰሩ ባለሙያዎች ይህ ክስተት የAI አቅም በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ አሁን ያሉት የደኅንነት መከላከያዎች በቂ ስለመሆናቸው አዲስ ጥያቄዎችን እንዳስነሳ ይገልጻሉ።

የSonicWall ሥራ አስፈጻሚ ስፔንሰር ስታርኪ፣ ድርጅቶች የሳይበር መከላከያቸውን ማጠናከርና ለዚህ ዘርፍ ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ክስተቱ የላቁ የAI ሥርዓቶች እየተሻሻሉ በሚሄዱበት ወቅት የደኅንነት መስፈርቶችንና የቁጥጥር ሥርዓቶችን የበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸው የሚያሳይ አዲስ ውይይት ማስነሳቱን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9🤣7👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ብሄራዊ ግዴታ ተጥሏል‼️
"ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ ጤናውና እድሜው የፈቀደለት ለተሰጠው የህልውና ጥሪ የመሳተፍ ብሔራዊ ግዴታ አለበት"።
የህወሓት አመራር አለቶ አለም ገብረዋህድ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
😢28👍21🤣149🤪2🤔1👀1
አስገራሚ መረጃ‼️
እስራኤል እስር ቤቶቿን በአዞ ለመጠበቅ ጉድጓድ መቆፈር ጀመረች።
👉በሀማስ እና ጋዛ እስረኞች ላይ ተጀምሯል።

የእስራኤል ሚዲያዎች እንደዘገቡት በደቡብ እስራኤል በሚገኘው የሃማስ እና የፓላስቲኒያን እስረኞች በሚገኙበትና ከፍተኛ ጥበቃ ባለው የእስር ቤት ክንፍ ዙሪያ ለአዞዎች መቀመጫ የሚሆን ጉድጓድ እየተቆፈረ ይገኛል።
እነዚህ ጉድጓዶች በኬትዚዮት እስር ቤት ዙሪያ እየተቆፈሩ ሲሆን ወደ 170 ሜትር የሚረዝሙ ይሆናሉ።

እስር ቤቱ የሚገኝበት የራማት ኔጌቭ የክልል ምክር ቤት ባለስልጣን ጉድጓዶቹ በእስር ቤቱ ውስጥ በልዩ ክንፎቹ ዙሪያ እየተቆፈሩ መሆናቸውን እና ከውጭ ማየት እንደማይቻል ተናግረዋል።

"በእርግጥ እዚያ አዞዎች ይኖሩ እንደሆነ ማንም አያውቅም፣ ነገር ግን ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው" ሲሉ ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለስልጣን ተናግረዋል።

የእስራኤል ብሔራዊ የደህንነት ሚኒስቴር ለአዞዎች በተመደቡ ቻናሎች ላይ ሥራ መጀመሩን አረጋግጧል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።

የእስራኤል የእስር ቤት አገልግሎት አዞዎቹን ለመንከባከብ፣ ለመቆጣጠር እና ለማስተናገድ እቅድ አዘጋጅቷል፣ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ደግሞ አዞዎቹን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ስልጠና ወስደዋል፣ ፕሮጀክቱም 21 ሚሊዮን ሰቅል (6.3 ሚሊዮን ዶላር) ተመድቧል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
20👍8😡8😢4🤡4👀1🙉1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ – የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ዜናዎችን በአጭሩ እና በጥልቀት ከኛ ዘንድ ያንብቡ።

🔸 ትኩስ ትኩስ እና የሚፈልጓቸውን መረጃዎችን በፎቶ እና በቪዲዮ ይመልከቱ።

🔸 ለውድ ጊዜዎት ዋጋ እንሰጣለን።እርሶም ዋጋ ከሰጡ ፣ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይቀላለሉ: ያልተነገረውን እንናገራለን፤ያልተሰማውን እናበስራለን።

አሁኑኑ ይቀላቀሉን : https://t.me/+C_9-IRD5_Ws0MDgy

@sputnik_ethiopia
6👍2
ጦርነቱ ወደማይቀርበት ደረጃ ላይ ደርሷል
በትግራይ ድንበር ላይ የሚደረጉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ጦርነት የማይቀርበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።

🔺ዋና ዋና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች፡

📌የሀገር መከላከያ ሰራዊት (ENDF) ከዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ትግራይ ድንበር አካባቢ እየገቡ ይገኛሉ። ድሮኖችም መረጃ ለመሰብሰብ እና ለመከታተል በአካባቢው በተደጋጋሚ እየበረሩ ነው።

📌#ህወሃትም በራያ አካባቢ ከባድ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ሲሆን አዳዲስ ሰልጣኞችን የያዙ ተሽከርካሪዎች እንደ ተጨማሪ ኃይሎች እየገቡ ይገኛሉ።
በሁለቱም ወገኖች በድንበር እና በወታደራዊ ሰፈሮች ላይ ያለው ከፍተኛ ዝግጅት ክልሉ ወደ ሌላ ጦርነት ሊገባ እንደሚችል ያሳያል።
'ትልቁ ጀግንነት ጦርነትን መጀመር ሳይሆን ማስቀረት ነው"(የቻይናዊያን አባባል)።


@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
19💔14👍6🕊5👀5🤣1🤪1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
የራቁታቹን ፎቶ በሶሻል ሚድያ እለቃለሁ በማለት አስፈራርቶ ክብረ ንጽህና የገረሰሳ እና የግብረስጋ ድፍረት በደል ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ በፅኑ እስራት ተቀጣ
 
በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽ ፀጋዬ ሲሳይ ስዩም እንቁላል ፋብሪካ ይገዙ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው መኖሪያ ቤቱ የ14 አመት እድሜ ያላቸውን የግል ተበዳዬችን ‹‹ላስጠናችሁ›› በማለት ለእህቱ ልጅ በማስጠራት በ2018 ዓ.ም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ስለፈጸመባቸው በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
 
ተከሳሽ ግንቦት  30 ቀን 2018 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10፡00 ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው እንቁላል ፋብሪካ ይገዙ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የ14 አመት እድሜ ያላትን የግል ተበዳይ  ‹‹ላስጠናሽ›› ብሎ በማስጠራት እና ከወንጀል ድርጊቱ በፊት ገላዋን ስትታጠብ ያነሳትን ፎቶ ‹‹ፌስቡክ ላይ እለቅብሻለሁ›› በማለት በልጅነት አእምሮዋ አስፈራርቶ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና ክብረ ንጽህናዋ እንዲገረሰስ ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው የግብረ ስጋ  ድፍረት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ከሶታል፡፡
 
በሁለተኛ ክስ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 626/1/ን በመተላለፍ  ሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 11፡00 ሲሆን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው እንቁላል ፋብሪካ ይገዙ ሜዳ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ የ14 ዓመት እድሜ ያላትን የግል ተበዳይ ‹‹ላስጠናሽ›› ብሎ በእህቱ ልጅ በማስጠራት የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና ክብረ ንጽህናዋ እንዲገረሰስ ያደረገ በመሆኑ በግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል፡፡
 
ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ የሰው እና የሰነድ ማሰረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽም በዐቃቤ ህግ የቀረበበትን የሰው እና የሰነድ ማሰረጃ ማሰተባበል ባለመቻሉ ድረጊቱን መፈጸሙ በማስረጃ ተረጋግጦ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበታል  ተከሳሽ ጥፋተኛ የተባለበት ሁለቱም የወንጀል ህጎች ሲሆኑ ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ የተከሰሰው በተደራራቢ ክሶች ስለሆነ   በወ/ህ/አንቀጽ 85 መሰረት ከብዶ እንዲወሰን ያቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ሀምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛው የቀደመ ሪከርድ ስለሌለበት አንድ ማቅለያ በመያዝ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
16💔15😢6🤣5👍2🤯1😱1👀1
መረጃ‼️

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለውጭ ገበያ ካቀረበችው የአበባ፣ የፍራፍሬ እና የአትክልት ምርት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አገኘች።

አገሪቱ በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ ካገኘችው 490 ሚሊዮን ዶላር አጠቃላይ ገቢ ውስጥ፣ የአበባ ምርት 412 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት ከፍተኛውን ድርሻ መያዙን ግብርና ሚንስቴር አስታውቋል።

ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የአትክልት ምርቶች 57 ሚሊዮን ዶላር ሲገኝ፣ ከፍራፍሬ ምርቶች ደሞ 21 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል፡፡

ኾኖም አገሪቱ ይህን ገቢ ያገኘችው ምን ያህል ቶን ምርቶች ለውጭ ገበያ አቅርባ እንደሆነ ሚንስቴሩ አልጠቀሠም።

ኢትዮጵያ በ2019 በጀት ዓመት 357 ሺሕ 457 ቶን አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ለውጭ ገበያ በማቅረብ፣ 575 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳለች ተብሏል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
23👍2👀1🤪1
የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ ድጋፎቼን ለመቀጠል 182 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ።

ድርጅቱ፣ በተያዘው አውሮፓዊያን ዓመት ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታዎቹ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንደገጠመው ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት ላይ ገልጧል።

እስከ ቀጣዩ ነሃሴ ወር በአገሪቱ ውስጥ የስብዓዊ እርዳታውን ለማስቀጠል ለእያንዳንዱ የምግብ እህል ተረጂ ከመደበው መደበኛ ራሽን ላይ 60 በመቶውን ለመቀነስ እንደተገደደም ድርጅቱ ጠቅሷል።

የአገሪቱ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ከፍተኛ የኾነው፣ ግጭት፣ መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ እና ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ጫናዎች በተጋላጭ ማኅበረሰቦች ላይ በሚያሳድሩት ጉዳት ሳቢያ ነው ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
7👍5😢21
ለ17 ዓመታት በሕመም ፈቃድ 1 ሚሊዮን ዩሮ የተቀበለችው መምህርት ትምህርት ቤቷን ከሰሰች

በጀርመን የምትገኝ የ62 ዓመት የሙያ ትምህርት ቤት መምህርት ለ17 ዓመታት በሕመም ፈቃድ ላይ ሆና 1 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ደመወዝ ከተከፈላት በኋላ፣ ትምህርት ቤቱ በጡረታ በማሰናበቱ ምክንያት ክስ አቀረበች።

መምህርቷ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት ገብታ የማታውቅ ቢሆንም፣ የሕክምና ማስረጃዎችን እያቀረበች ሙሉ ደመወዟን ስትቀበል ቆይታለች።

አዲሱ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ባደረገው ማጣራት ግን በእነዚህ ሁሉ ዓመታት በአስገዳጅ የመንግስት ሕክምና ምርመራ እንድታልፍ አለመደረጉ ተገልጧል።

​በተጨማሪም መምህርቷ በሕመም ፈቃድ ላይ በነበረችበት ጊዜ የግል የሕክምና ድርጅት ከፍታ ስትሰራ እንደነበር ተጠራጥሮ የዱይስበርግ ግዛት ዐቃቤ ሕግ ምርመራ ጀምሮባታል።

ማጭበርበሯ ከተረጋገጠ የተከፈላትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንድትመልስና በወንጀል እንድትጠየቅ ሊደረግ ይችላል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።

Via fidel

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
24🤪5👍3🤣1🙊1
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
Photo
ኤርትራ ለህወሓት ባለው መሳሪያ ጦርነቱን ጀምሩ ብሏቸዋል -ጌታቸው ረዳ‼️
(ሙሉበሙሉ ከጌታቸው ፖስት ወደ አማርኛ የተተረጎመ ነው .... ሌላ የግል  አስተያየት አልተጨመረበትም )...
--
ሻቢያን በእግራቸው የማይራመዱ ሽማግሌ ወታደሮች ናቸው ያሉት ሲል ዘርጥጧቸዋል።
"....ደብረጽዮን በቅርቡ ወደ ኤርትራ ሄዶ ኢሳያስ አፈወርቂን ጦርነት ለመጀመር ለእያንዳንዱ ታጣቂ 4 ካርታ የጥይት (120ጥይት) ) እንዲሰጠው ጠይቋል ይላል።
የኢሳያስም አሁን  “ባለህ ነገር ጀምር፤ ከዚያ የሚያስፈልገው  ይላክልሃል  እንዳለው ገልጿል።
በ2014 በምዕራብ ግንባር ስለሚደረግ ውጊያ በተደረገ የኮማንድ ፖስት ስብሰባ
አንድ የጦር ኃላፊ የጥይት እጥረት እንዳለ ገለፀ።፣ የጥይት አቅርቦት የደብረጽዮን ኃላፊነት ስለነበር ደብረጽዮን የሎጂስቲክስ ኃላፊውን አለምሰገድ ሃደራን

“ስንት ጥይት አለን?” ሲል ጠየቀ።
“11 ሚሊዮን ጥይት ይኖረናል፤ የዲሽቃ ጥይት ግን አነስተኛ  ነው ብሎ መለሰ

ከዚያ ደብረጽዮን፣ “የጠላት ኃይል ስንት ነው?” ብሎ ተወልደ ዕምባብን ጠየቀ።

ተወልደ ዕምባብም

“ፋኖ፣ የኢትዮጵያ መከላከያና የሻዕቢያ ሰራዊትን ጨምሮ 1.1 ሚሊዮን ያህል ይሆናል።”

ከዚያ ደብረጽዮን፣ “የሰራዊታችን ዒላማ የመምታት ውጤት (hit rate) ስንት ነው?” ብሎ ታደሰን ጠየቀ።

ታደሰ (ወዲ ወርደ) እንዲህ ሲል መለሰ፦

“ከ60 እስከ 70 በመቶ ይመታል።”

ከዚያ በኋላ ደብረጽዮን" እንግዲህ ሁሉንም የመጣውን ጠላት ካጠፋን፣ 30% ጥይት ይተርፈናል።” ብሎ ተናገረ
--
እኔም  ሃሳቡን ተቃውሜና ተገርሜ
“ጠላት ተር ብሎ እየመጣ አንድ በአንድ ነው እንዴ የምንመታው?”  ብየ ስጠይቅ

ወዲ ወርደ
“ተወው፤ ያውራ።” ስላለኝ ዝምአልኩ

ከዚያ ስብሰባ በኋላ፣ ደብረጽዮን
“በሰራዊቱ ፊት እኛን በመቃወም ወታደሮቹ እንዲደፍሩንና እንዲያቃልሉን አድርገሃል።” ብሎ  ወቅሶኛል 
--
በጸሎት ወይም በመጠበቅ ብቻ ለውጥ አይመጣም ስለዚህ  የትግራይ ሕዝብ ። እነዚህን ኃይሎች (እነ ደብረፂዮንን) ለማስወገድ  ጊዜው አሁን ነው
--
ደብረፂዮን ማለት በትግራይ ላይ የወረደ እርግማን ነው ይልና...
"..ሕዝባችን ይጥፋ ወይስ ክፉ ተግባር የሚፈጽሙት ይጥፉ?” ብሎ ይደመድማል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
29🤣17👍5🤪3🤔1🤯1🕊1😍1🙊1
ሂውማን ራይትስ ዎች በዌስት_ባንክ የሰፈሩ የእስራኤል ዜጎች የሚያካሂዱት ጥቃት ትልቅ እልቂት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠነቀቀ

የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች በዌስት ባንክ አካባቢዎች የሰፈሩ የእስራኤል ዜጎች የሚያካሂዱት ጥቃት እየጨመረ በመምጣቱ ተጨማሪ እልቂቶችን ሊያስከትል እንደሚችል በማስጠንቀቅ የእስራኤል መንግሥት ጥቃቶችን ከመከላከል መቆጠቡን እና ተጠያቂነት ላለመኖር ድርጊቶች መንገድ መክፈቱን ከሰሰ።

ሐምሌ 17 በወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ ናብሉስ አቅራቢያ በሚገኘው የታል የፍልስጤም መንደር ላይ በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች የአራት ፍልስጤማውያን እና የሁለት እስራኤላውያን ሕይወት ማለፉን ገልጿል።

የመብት ተሟጋች ቡድኑ እንደገለጸው፣ የቅርብ ጊዜው ጥቃት፤ በአካባቢው የሰፈሩ የታጠቁ እስራኤላውያን በፍልስጤም ማህበረሰቦች ላይ ጥቃት የሚያሰነዝሩበትን፣ የእስራኤል ወታደሮች ደግሞ በጥቃቱ የሚሳተፉበትን ወይም ጣልቃ ከመግባት የሚቆጠቡበትን ሰፊ ክስተት ያመላክታል። በጥቃቶቹ ላይ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ከእስራኤል መንግሥት የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የሕግ ድጋፍ እንደሚያገኙ ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
11👍3😢2
ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ ያናግሩን 👇
@Addis_reporter_bot
👍21👌1