#የውቅያኖስ ወለል ምስጢር፦ የዓለምን ኢንተርኔት የሚያንቀሳቅሱት የባህር ስር መስመሮች❗❗
ብዙዎቻችን በየቀኑ በስልካችን የምንጠቀመው ኢንተርኔት፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ዓለም አቀፍ የመረጃ ፍሰት በሳተላይት በኩል በአየር ላይ የሚጓዝ ቢመስለንም፣ እውነታው ግን ከዚህ እጅግ የራቀ ነው።
የዓለማችን 99 በመቶ የሚያህለው የኢንተርኔት ዳታ የሚጓዘው በጨለማውና በጥቁሩ የውቅያኖሶች ወለል ላይ በተዘረጉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች በኩል ነው። በዓለም ዙሪያ በውቅያኖሶች ስር የተዘረጉት እነዚህ ከ550 በላይ ንቁ ካብሎች ከ1.4 ሚሊዮን ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን፣ በሴኮንድ በመቶ ቴራባይት የሚቆጥር ዳታ የሚያስተላልፉት እነዚህ መስመሮች እንደተጠበቀው ትልቅ ሳይሆኑ የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያ ወይም የጓሮ ቧንቧ ያህል ውፍረት ብቻ ያላቸው ናቸው።
በኬብሉ መሃል የሚገኙት የመረጃ ማስተላለፊያ የብርጭቆ ጫፎች ወይም ቀጫጭን የብርጭቆ ገመዶች የሰው ፀጉር ያህል ቀጫጭን ሲሆኑ፣ መረጃን በብርሃን ፍጥነት ያጓጉዛሉ።እነዚህ መስመሮች ለአደጋ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በየዓመቱ በአማካይ ከ100 በላይ የመቆረጥ አደጋዎች ያጋጥሟቸዋል ተብሏል።
የመርከብ መልሕቆች መሬት ሲቧጥጡ፣ የባህር ስር የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ወይም አልፎ አልፎ የሻርክ አሳዎች ሲነክሷቸው መስመሮቹ የሚበጠሱ ሲሆን፣ አንድ የባህር ስር ኬብል ከተቋረጠ የሙሉ ሀገር ወይም ቀጠና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ወይም ሊዘገይ ይችላል ነው የተባለው።
በአሁኑ ወቅት እንደ Google፣ Meta፣ Microsoft እና Amazon ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የራሳቸውን የባህር ስር ኬብሎች በመዘርጋት የዓለምን የመረጃ መረብ በባለቤትነት እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
@Addis_Reporter

❤22👍5
በወላይታ ሶዶ ከተማ ፌስታል ሲጠቀሙ በተገኙ 130 አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ
በወላይታ ሶዶ ከተማ በህግ የተከለከለውን ፌስታል ሲጠቀሙ በተገኙ 130 ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የከተማው የአካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ጽ/ቤት አስታውቋል።እርምጃው በአብዛኛው በሱቆችና በንግድ ተቋማት ላይ የተወሰደ ሲሆን ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ክትትል የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ለማ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1387/2017ን በመተላለፍ ፌስታል በመያዝ እና ለንግድ አገልግሎት ጥቅም ላይ ሲያውሉ በተገኙ 130 አካላት ላይ በህጉ መሠረት እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።በቅርቡ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንድ ነጋዴ 17 ኩንታል ማዳበሪያ ይዞ በመገኘቱ የተወረሰበት ሲሆን በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ጨምር እንዲቀጣ ተደርጓል።
በመሆኑም ግለሰቦችና ተቋማት ፌስታል መጠቀም በህግ የተከለከለ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ህጉን ሊያከብሩ ይገባል ሲሉ አቶ ጴጥሮስ ለማ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በአዋጁ መሰረት ፌስታል ይዞ የተገኘ ግለሰብ በ2 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል።እንዲሁም በተቋም ደረጃ ፌስታል ያከማቸ፣ የሸጠ ወይም ለንግድ ዓላማ እንደ እቃ መያዣ ያቀረበ ተቋም እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ባለንብረቶችም እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጡ በአዋጁ ተጠቅሷል።

❤16🤪12👍2🤯1
ሰበር መረጃ‼️
የኢትዮጵያን መንግስት ለመጣል ያለመ ስብሰባ በኤርትራ ድንበር ተደረገ፣ስብሰባውን የመሩት አቶ አማኑኤል አሰፋ ናቸው።
ሕወሓት የብልጽግናን መንግስት አስወግዳለሁ እያለ ነው፡፡ ቡድኑ ካለፈው እሁድ አንስቶ 'ህልውናችን የሚረጋገጠው በብልጽግና መቃብር ላይ ነው' በሚል መሪቃል ስብሰባዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ የሕወሓት አመራሮች ‹‹ብልጽግናን ከስልጣን ማስወገድ አለብን›› በማለት በግላጭ እየተናገሩ ነው፡፡
በሚዲያዎቻቸውም የፌደራል መንግስቱን 'ጄንኖሳይዳዊ አገዛዝ' የሚል ስያሜ ሰጥተው በትግራይ ቴሌቪዥን ጭምር ዜና መስራት ጀምረዋል። የፌደራል መንግሥቱ ለህወሓት የጦርነት ጉሰማ በቀጥታ የሰጠው ምላሽ የለም።

👍48🤪17❤9👌4🥰2🕊2👀1
ጄነራል ታደሰ ወረደ ወዴት ተሰወሩ❓
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ በመቀሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መሰወራቸው ተሰማ። እስከ ማክሰኞ ጠዋት ድረስ መኖሪያ ቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅና በጥበቃ ተሽከርካሪዎች የተከበበ የነበረ ቢሆንም፣ ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ ግን አብረዋቸው የነበሩ ጥበቃዎችና ሰራተኞች ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል።
ጄነራሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ከአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር እንዳይገናኙ በትግራይ ጸጥታ ቢሮ ተከልክለው እንደነበርና ቤተሰቦቻቸውም ስለ ደህንነታቸው ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ይታወቃል።
ጄነራል ታደሰ ወረደ በፌደራል መንግሥት ዳግም በተሾሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሕወሓት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው የሚታወስ ነው። ከኃላፊነታቸው ከመነሳታቸው በፊትም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ለመገልበጥ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ክልሉን ወደ አዲስ ጦርነት እንደሚያስገባ አስጠንቅቀው ነበር።
በአሁኑ ወቅት በሕወሓት እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው የፖለቲካ ውጥረት በጨመረበት ሁኔታ፣ የጄነራሉ ከአካባቢው መሰወር በትግራይ ክልል አዲስ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል።

❤15👍3😢1🎉1🤪1
ለምክክር ጉባዔ መጥታ ወንድ ልጅ የተገላገለችው እናት የልጇን ሥም "ኮሚሽን" አለችዉ
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወክላ በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።
ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራዊ ምክክሩ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበረች የጋምቤላ ክልል ተወካይዋ ወ/ሮ ክርኑዶ ኡጁሉ ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላ ስሙም "ምክክር" መባሉ የሚታወስ ነው።
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የመጣችው ሌላኛዋ የምክክሩ ተሳታፊ ወ/ሮ ሀዳ አልማህዲ በተመሳሳይ ወንድ ልጅ በሰላም የተገላገለች ሲሆን፥ ስሙንም "ኮሚሽን" ብላዋለች።
የመውለጃ ጊዜዬ እየደረሰ መሆኑን ባውቅም ለኢትዮጵያዊያን አብሮነትና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ በሚመከርበት በዚህ ጉባኤ መሳተፍ አለብኝ በሚል አቋም ተገኝቻለሁ ብላለች፡፡
በጉባኤው አጀንዳዎች ላይ ለሀገራችን ይበጃል የምትለውን ሀሳብ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፥ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ልጇን በመገላገሏ መደሰቷን ገልጻለች።
ዘገባዉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሚዲያ ነዉ።

🤣70❤11😡6👍3
በሩሲያ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ የመጸዳጃ ቤት ዉሃ የመጠጣት ውድድር ማዘጋጀቱ ዉዝግብ አስነሳ
በሩሲያ ስታቭሮፖል የሚገኝ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ፣ በቅርቡ "Game of Thrones" በሚል ያልተለመደ ውድድር ምክንያት በኢንተርኔት ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊዎች አዲስ ከሆኑ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫዎች ውስጥ፣ ትላልቅ የመምጠጫ ቱቦዎችን በመጠቀም "አልኮል ያልያዘ ጋዝ ያለው መጠጥ" እንዲጠጡ ይጠበቅባቸው ነበር፤ መጠጡን በፍጥነት የጨረሰውም አሸናፊ ተብሎ ተለይቷል።
በስታቭሮፖል ከተማ በሚገኝ የ"ዶሚክስ" መደብር ውስጥ የተካሄደው ይህ ያልተለመደ ውድድር፣ በርካታ ተሳታፊዎች የ100,000 ሩብል (1,276 የአሜሪካ ዶላር) ሽልማት ለማግኘት ሲሉ ከመጸዳጃ ቤት ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ በፍጥነት እንዲጠጡ የሚያስገድድ ነበር። ተወዳዳሪዎቹ በሰባት ሰዎች ቡድን የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ፈጣኑ ጠጪ ወደ ሁለተኛው ዙር ያልፍ ነበር።
በውድድሩ ሁለተኛ ምዕራፍ፣ ከቀዳሚው ዙር ያለፉት ሰባቱ አሸናፊዎች በተዘጋ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ በተቻለ መጠን ረጅም ጊዜ መቀመጥ ነበረባቸው፤ በመጨረሻም መቀመጥ የቻለው ሰው የዚህ ያልተለመደ ዉድድር አሸናፊ ተብሎ ታዉጇል።
በቤዛዊት አራጌ

❤10😡4👍2🥱2
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ዕድገት ያሳየ ነው።መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ለተመዘገበው ዕድገት እንደ አንድ ምክንያት የጠቀሰው የገቢ ምንጮቹ መስፋፋትን ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 16፤ 2018 በሰጡት መግለጫ፤ ከዚህ ቀደም የኩባንያው የገቢ ምንጮች በሞባይል ድምጽ፣ በዳታ እና በኔትወርክ ትስስር (interconnect) ላይ ብቻ የተገደቡ እንደነበሩ አስታውሰዋል።
ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ላገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ ካበረከቱ የአገልግሎት ዓይነቶች መካከል የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ይጠቀሳሉ።ሁለቱ አገልግሎቶች ከተቋሙ ገቢ ያላቸው ድርሻ 31.1 በመቶ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ እንዳገኘው የገለጸው ያልተጣራ ትርፍም፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ51.9 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት ተመዝግቦበታል።
ኩባንያው በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ያልተጣራ ትርፍ 38.7 ቢሊዮን ነው።

😢17❤6👍3🥱2🤪2
በኢትዮጵያ ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ከ500 አይበልጥም ተባለ !
በኢትዮጵያ የሰለጠኑ እና ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም የተመሰከረላቸውን የሂሳብ ባሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ኤችኤስቲ ስኪል አካዳሚ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
በተቋሙ በትምህርት እና ስልጠና ላይ ስትራቴጂክ ቢዝነስ ዩኒት ስኪል አካዳሚ ዳይሬክተር የቦርድ አባል እና የሪስክ እና ኦዲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጎበዜ ደሳለኝ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በኢትዮጵያ በሂሳብ አያያዝ ቴክኒካል ብቃት ብቁ የሆኑ የሒሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ከ500 አይበልጥም።ከዚህ ቀደም ስልጠናውን ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገራት መሄድ አስገዳጅ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጎበዜ ይህንን የሚያስቀር እና ከከፍተኛ ወጪ የሚያድን ስልጠና በሀገር ውስጥ በድረገጽ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል
ከ12ኛ ክፍል ጀምሮ በተለያዩ የስራ ሁኔታዎችም ሆነ የትምህርት ዘርፍ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ላይ ሆኖ ስልጠናውን መውሰድ ይችላል። በማኔጅመንት፣ በኦዲት ፋይናንስ ታክስ፣ እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች በ12 የትምህርት አይነቶች ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን ለመማር ከ12 እስከ 18 ወራት ይወስዳል
ለአንድ የትምህርት ዘርፍ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ክፍያ ብቻ የሚጠየቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጎበዜ አስራ አንድ ድርጅቶች ስልጠናውን ይሰጣሉ ሲሉ አክለዋልከእነዚህም መካከል ሶስቱ የግል ድርጅቶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ስምንቱ ደግሞ የመንግስት ድርጅቶች ናቸው።የዩኒቨርሲቲ ተቋማት በቋሚነት ከሚሰጡት ትምህርት በተለየ መልኩ ስልጠናውን በተግባር እንደሚሰጡ ተነግሯል

❤9👍3🎉1💊1
የአፍሪካ የሰዎችና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተላለፉ ፍርዶችና የሞት ቅጣቶች እንደገና እንዲታዩ "ሁሉንም መንገዶች" እንዲጠቀምና የሞት ፍርድ የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያዊያን ደኅንነት ለማስከበር አስፈላጊ "የዲፕሎማቲክ" እና "የቆንስላ" ርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ።
ኮሚሽኑ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ላይ የተጣለው የሞት ቅጣት በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑ "የሕግ ውክልና" እና የፍርድ ቤት "የትርጉም አገልግሎት" እንዲያገኙና ከቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙ ጥረት እንዲያደርግ፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሠተኞችን መብት "በሁለትዮሽ ግንኙነቶች" እና በጠንካራ "የቆንስላ ድጋፎች" እንዲያስከብርም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

❤9👍7
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ ከተፈቀደው ውጪ በማናቸውም የቨርቹዋል ሀብቶች ግብይት ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።
እገዳው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ክፍያና ኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ በዲጂታል መልኩ የሚተላለፉ መግለጫዎችንም ያካትታል።
በተለይም የሚከተሉት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው ብሏል ባንኩ;
👉በቨርቹዋል ሀብት እና በመደበኛ ገንዘብ መካከል የሚደረግ መመንዘር
👉በቨርቹዋል ሀብቶች መካከል የሚደረግ ልውውጥና ዝውውር
👉የቨርቹዋል ሀብቶችን ማስቀመጥ፣ ማስተዳደር እና የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት
ህብረተሰቡ ከህጋዊ ተጠያቂነት፣ ከማጭበርበር፣ ከሳይበር ጥቃት እና ከከባድ የገንዘብ ኪሳራ ለመጠበቅ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ባንኩ አሳስቧል።

❤10😡7🤪5👍2👌1💔1🤝1
ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ‼️
👉በ21ኛው ክ/ዘመን መኪና ሲገፉ/ሲጎትቱ/ ማየት አሳፋሪ ነው።
👉በሶስት አመት ይጠናቀቃል የተባለው መንገድ 8 አመት ሆነው።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማ በር-መለያያ-ሰፌድ ሜዳ -ሞላሌ-ወገሬ የመንገድ ግንባታ ስራ ከተጀመረ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል።
118 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የጣርማ በር-መለያያ-ሰፌድ ሜዳ -ሞላሌ-ወገሬ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በ1.9 ቢሊዮን ብር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦ የመንገድ ግንባታ ስራው የተጀመረው ታህሳስ 11/2011 ዓ.ም ነበር።
📌አሁን ላይ የመንገድ ስራው ሙሉ ለሙሉ ቆሟል፣የስራ አፈፃፀሙም ከ25% አላለፈም።
📌ይህ የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው መንገድ ይሰራል ተብሎ የመሰረተ ድንጋይ ተጥሎ የተጀመረ ሰሞን የነበረው የህዝቡ ደስታ ወደ እርግማን ተቀይሯል፣ህዝቡም ተስፋ ቆርጧል።
📌መንገዱ ያለተለዋጭ መንገድ በየቦታው በመቆፈሩ ለጥገና አስቸጋሪ ሆኗል፣ዝናብ በጣለ ቁጥር መኪና የተባለ ሙሉ መልኩን ቀይሮ፣በጭቃ ዋና ዋኝቶ፣በህዝቡ ተገፍቶ፣ተጎትቶ ነው የሚወጣው።
📌ስራው ሳይጀመር በፊት ወደ ደብረብርሃን 4 ሰዓት ወደ አዲስ አበባ ስምንት ሰዓት ይፈጅ የነበረው መንገድ አሁን ላይ 118 ኪሎሜትር መንገድ ወደ ደብረብርሃን ለመምጣት 10 ሰዓት ይፈጃል።
📌ለግንባታው የቀረቡ ግብዓቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
ይህ የመንገድ ስራ ከኮንትራክተር ጀምሮ ብዙ ችግሮች ቢኖሩም የሚመለከተው አካል ከህዝቡ ጋር መክሮ ዘክሮ የህዝቡን እምባ ሊያብስ የሚችል ስራ መስራት ይጠበቅበታል።

❤18🤣6👍4🥰1😢1
ጋምቤላ 💰 ወርቅ
ከጋምቤላ ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሆኗል።
በጋምቤላ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 6 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ፣ ከ7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ገቢ መደረጉን የክልሉ ማዕድን ቢሮ አስታውቋል።
የተመዘገበው ውጤት ከእቅዱ በ1,098 ኪሎ ግራም፣ ከቀዳሚው ዓመት ደግሞ በ1,669 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ በተከናወነ የማዕድን ልማትም ከ6,890 በላይ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ቢሮው መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

❤7👍5